The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የማለዳ ወግ…የባለስልጣኖቻችን ጉብኝትና የእኛ ኑሮ…. ! (ነቢዩ ሲራክ)

neb4

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ በጅዳ ሳውዲ አረቢያ

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በምንገኝበት በሳውዲ አረቢያ በአለማችን በመንግስት ባለስልጣናት ከሚጎበኙት ቀዳሚ መሆኑ አሊ አይባልም። ከጠቅላይ ሚኒስትር ከፍተኛ ባለስልጣል ጀምሮ በሚኒስቴር ፣ በሚኒስቴር ዴታና በዳይሬክቶሬት ኃላፊነት ያሉ ከፍተኛ ሹሞቻችን እያሰለሱ ጎብኝተውናል ። ምንም እንኳን ኃላፊዎች ሲመጡ ተራው ነዋሪን ለማነጋገር ባይችሉም በአደረጃቸት የታቀፉትን የገዥው ፖርቲ አባላት ፣ ማህበራትንና ኮሚኒቲውን በተደጋጋሚ ሰብስበው አነጋግረው ያውቃሉ።  ለመንግስት አስተዳደር በታቀፉት ድርጅት በኩል ቀረቤታ ካላቸው ካደሬዎች ፣ በልማት ማህበር ተብየዎችና በኮሚኒቲው ኃላፊዎች የተሸራረፈም ቢሆን ነዋሪው ስላለበት ችግር ፣ በቆንስልና በኢንባሲ ተወካዮች ስላለው የመብት ማስጠበቅ ህጸጽ ሳይናገሩ የቀሩበት ጊዜ የለም ።

ዳሩ ግና የሚመጡት ባለስልጣናት ሁሉ ብሶት መከራው ን ሰምተው ” እርማት ይደረግበታል !” ብለው ቃል ከገቡት የሚጨበጥ ለመጥፋቱ ብዙዎችን ለነዋሪው ሳይሆን ለድርጅት ታማኝ አገልጋይ የሆኑ ካድሬዎች ሳይቀር  ተስፋ አስቆርጧቸዋል ፣ አስከፍቷቸዋል  ! እውነቱ ይህ ሆነና ሀገሪቱን ከፍተኛ የአስተዳደር ከፍ ያለ መቀመጫ ያላቸው ባለስልጣናት የህዝብና ሀገር ገንዘብ ተደርጎ የሚያደርጉት ጉብኝት ” ባለስልጣናቱ የሚመጡት በስራ ስም  ለገብያ ነው! ” ወደ ሚል መደምደሚያ እንዳደረሳቸው ” መረጃው በእኔና ባንተ ይቅር! ” ያሉኝ አንዳንዴ ከፖለቲካው ሰብዕናው እያጠቃቸው አሾልከው መረጃ የሚያቀብሉኝ ከፍተኛ የኢህአዴግ ድርጅት ኃላፊዎች ሹክ ብለውኛል …

ከወራት በፊት ወደ ጅዳ መጥተው በአካል ያገኘኋቸ ው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ ጋር ባረፉበት ሆቴል ተገኝቸ ብዙ በማህበራዊ ህይዎቱ ዙሪያ ስለሚታዩ የመብት ጥሰትና ተዛማጅ ጉዳዮችን ከነመረጃ ማስረጃው አቀብያቸውም ነበር ።  በተለይ በተለይ  ካረፉበት ሆቴል የአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ካለው የዶር ፈቂ ሆስፒታል ስለተኛው ስለ ብላቴናው መሀመድን እና በቤተሰቡ ላይ ያረፈውን የመከራ ቀንበርና በብሪማን እስር ቤት ለወራት በታሰርኩበት አጋጣሚ በአካል ያየሁትን ወንድም የከፋ በደል በተጨባጭ ማስረጃ አጫውቻቸው በጥልቅ አዝነውና እንባ ተራጭተናል …

በወቅቱ እጅጉን የከፋው በደል  የከብትና ግመል እረኛ ሳለ ” ከብት አጥፍተሃል ” ተብሎ የታሰረው ” እረኛ “ወንድም በህግ ከለላ በእስር ላይ እያለ በአንድ አዕምሮ እስረኛ የባለቤቱን ነፍስ አጥፍቶ በታሰረ ያገር በደረሰበት ድብደባ አካሉን የረገፈው ጎልማሳ አሳዛኝ ህይዎት አሻውቻቸዋለሁ። ይህ ወንድም  ፍትህ ርትዕ ማግኘቱ ቀርቶ በቂ ህክምና ሳይደረግለት በግፍ ከሳውዲ መሸኘቱን አግባነት የሌለው ስራ መሆኑን ለዶር ደስታ ከፎቶ ማስረጃ ው አሳይቻቸዋለሁ አብረን ተላቅሰናል ። ጉዳዩ እንዲጣራ  ያደርጉ ዘንድ ያ ግፉኡ ወንድም የረባ ህክምና ሳያገኝ ለምን ተሸኘ ?  አካሉ ረግፎ ሀገር እንዲገባ ከጅዳ ቆንስላ የመጓጓዣ ሰነድ ሊሴ ፖሴ ማን ሰጠው  ? መጓጓዣ ከመሰጠቱ በፊት  በህግ ከለላ ያለ ሰው ህግ በአስከባ ሪዎች እንዝህላልነት በደል ሲደርስ በት ለተፈጸመበት ወንጀል ተጠያቂዎች ለምን ለፍርድ እንዲቀርቡ  አልተደረገም ? ቁስሉ ሳይሽር አዋክቦ ለመሸኘት ተፈለገ ?  ለምን ተበዳይ ለተበደለው ካሳ አግኝቶ ይሂድ ተብሎ  አልተጠየቀም  ? ለሚለው ጥያቄ መልስ እንደ ሚያስፈልገው ከዶር ደስታ ወ/ ዮሃንስ ጋር ተስማምተን ፣ ባለስልጣኗ ይህንን ለማጣራት ቃል ገብተውልኝ ተለያየን ። ያ ከሆነ ቀናት ሳምንታትን ፣ ሳምንታት ወራትን እየወለዱ  ጊዜው ነጉዶ ዛሬ ላይ ስንደርስ  ” አዲስ አበባ የገባውን ወንድም እከታተላለሁ ፣ በመንግስት ሆስፒታል እንዲታከም አደርጋለሁ ፣ ጉዳዩን አጣርቸ ተጠያቂዎችን አጣራለሁ! ” ብለው ቃል ከገቡልኝ እመቤት  ከዶር ደስታ ጠብ የሚል መልስ  አላገኝ አልኩ ..  ያ የፈረደበት ምስኪን መከረኛ ” እረኛ ” ወንድምም  ህክምና ሳያገኝ ከነቁስሉ ተሸኝቷልና የድሃ ቤተሰቦቹ ሸክም ሆኖ ቀረ ፣ የዶር ደስታ ቃል እንደ ሀምሌ ጉም በኖ ጠፋ  … ” ቄሱም ዝም ፣ መጽሐፉም ዝም! ” እንዲሉ ዶር ደስታ  ቃል የገቡትን ሳይፈጽሙ እነሆ ግራ ያጋባ ለሁለተኛ ጊዜ የጅዳ ጉብኝታቸውን ከዋውነው ትናንት ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል ! የባለስልጣኗ ጉብኝት ምን ይመስል ነበር ?  ካላችሁ ደግሞ ወደዚያው እናቅና …

neb3

የዶር ደስታ የንጉስ ፋአድ ሆስፒታል ጉብኝት …
=============================
በአዲሷ የሴቶች ሊቀ መንበር ወሮ ሙሉካ ሁሴን አጋፋሪነት በንጉስ ፉአድ ሆስፒታል የተኙትንና ሶስት ታህል ታማሚዎች የጎበኙት ዶር ደስታ  ምንም እንኳን የጉብኝታቸው መቋጫ ውሉ ባይገባኝም ሶስት ታማሚዎችን መጎብኘታቸውን በቦታው ከነበሩት ሰምቻለሁ ።  በንጉስ ፉአድን ሆስፒታል ከተጎብኙት  ታማሚዎች መካከል ባንድ ወቅት የጅዳ ቆንስል ከአፍንጫው ስር ለአመታት በሰመመን ውስጥ ስላለችው እህት ይጎብኝ ብየ መረጃ በማቀበሌ እኔና የመረጃ አቀባየ በቆንስሉ አንድ ዲፕሎማት የተወረፍንባት ማንነቷ ሳይታወቅ በንጉስ ፉአድ ለአመታት የተኛችው እህት ትገኝበታለች። ግራ ቢገባኝ ዶር ደስታ  የዚህች እህት ማንነትና ይታወቅና  ቤተሰቦቿ ይፈለጉ ዘንድ ትዕዛዝ በሉት መመሪያ አለመስጠታቸውን ስሰማ አዝኛለሁ  ! የሴቶች ዳይሬክቶሬት ከሆስፒታሉ ኃላፊዎችም ሆነ ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር ግንኙነት ፈጥረው የጎበኟቸው እህቶች ህክምናቸው ይሻሻል ስለማለታቸውም ሆነ አድራሻቸው የማይታወቀውን ለማጣራት ስላደረጉት ጥረትም ውጤት አልተነገረምና ፣  አልሰማሁም … ታላቋ ባለስልጣን መጎብኘታቸውን ብቻ ሰምተናል  !
ክፍል አንድ በዚህ አከተመ …

የቀጣይ ወጎች ቅምሻ …
================
በዶር ደስታ ክፍል 2 …ዳሰሳየ
ሀሙሱ ፣ ሰኞ ፣ የሽሜሲ እስር ጉብኝት ውይይት  …
===============================
በሳውዲ መንግስት በኩል ” ህገ ወጥ”  ተብለው በሌሊት ቤት ሰበራና አፈሳ የታሰሩ ዜጎች የሚገኙበትን የሽሜሲ እስር ቤት ዶር ደስታ ሀሙስ ታሳሪዎችን ፣ ሰኞ የሳውዲውን ባለስልጣን   ጎብኝተዋል …ህጋዊ መኖሪያ ፍቃድ እያላቸው ያለ አግባብ ለተያዙት ”  መብታችን ተጥሶ  ወደ ሀገር ለመግባት ፎርም አንሞላም!” ያሉትን በርካታ ኢትዮጵየ ያን እንዳገኙና እንዳወያዩዋቸው የጨነቀ የጠበባቸው ሁሌም እያለቀሱ ብሶት ምሬታቸውን የሚነግሩኝ ታሳሪዎች ያቀበሉኝ መረጃ ያስረዳል …

በዶር ደስታ ክፍል 3 4  … ዳሰሳየ
እያልኩ  በማቀርበው ዳሰሳየ የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ የሴቶች ስብሰባን ይሆናል… ለቅምሻ ስቀጥል :)
=================================
የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ ጉብኝት አስመልክቶ ጉብኝቱን ስዳስስ ይህም አይቀር ላንሳው ብየ እንጅ ውይይት ምክክሩ የረባ እንዳልነበር ተነግሮኛል። ዲፕሎማቶች በሞሉበት የሴቶች ስብሰባ የሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሶስተኛ ሙት አመት በሻማ ማብራት ታስቧል ። ከዚህ ቀደም አዳራሹን የሚያደምቁት የድርጅት ማህበር አባላት ፣ የጅዳ ቆንስል ” ነጭ በሬ”  ሴቶች ወይዛዝርት በዚህ የሴቶች ስብሰባ አልተሳተፉም።  በጣት የሚቆጠሩ እህቶች በታደሙበት የቀዘቀዘ ውይይት ተደርጎም የብዙሃኑ ነዋሪ እህቶች ብሶት በስብሰባ ውይይቱ አልተንጸባረቀም  …
****************
እልና በሴቶች ስብሰባ ስላልተወሳው በርካታ የሴቶች ጉዳይ ብላቴናው መሀመድ በባለስልጣኗ እንዳይጎበኝ ግፊት አለመደረጉን  አነሳለሁ …
****************
..ቢረሳ ቢረሳ መዲና ለሁለት አመታት ያለ ጠያቂ በአንድ ሆስፒታል ተጥላ ያለችውን እህት ጉዳይ እንኳ ማንሳት ለምን አልተቻለም?  ከአሰሪያቸው ተፈናቅለው ፣ ተባረውና ተጥለው በመጠለያው ስለሚገኙ እህቶች  ፣ በኩንትራት መጥተው ስለሚሰቃዩ ፣ ስላበዱ ፣ ስለተደፈሩ መናገር አለመቻሉ ፣ በዘገየው ፖስፖርት መኖሪያ ፈቃዳቸው ስለወደቀባቸው ሴቶች እና ሌላም ሌላም መወያየት  መረጃ ጠፍቶ ሳይሆን” ያገባኛል !” ባይ ለነፍሱ ያደረ ደፋር ጠፍቶ በስብሰባው ጥልቅ ውይይት ሳይደረግበት ተዘሏል  ! ….

የሴቶች ዋና ዳይሬክቶሬት በተገኙበት ስብሰባ የመሀመድን ጉዳይ ለምን ማንሳትና መወያየት እንዳልቻሉ አልገባኝም ! ” ነግ በኔ !”  ነውና ቢያንስ ማህበሩ የመሀመድን እናት በቤት ኪራይ ፣ በትራንስፖርት በመሳሰሉት  እንደግፍ ብሎ መም ከር ያልቻለበት ምክንያት ምን እንደሆነ የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው !

neb4
 ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ በጅዳ የሽሜሲ እስር  ቤት ጉብኝትና ውይይት !
=============================
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ ጅዳ ለሁለተኛ ጊዜ ሲጎበኙ አውቃለሁ። አምና ተገናኝተን በሆነውና ከሰሞኑም ለቀናት ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ተከታታይ መረጃ ማቅረብ ጀምሬያለሁ ።  በክፍል አንድ ዳሰሳየ ዶር ደስታ በጅዳ ንጉስ ፉአድ ሆስፒታል ያደረጉትን ጉብኝት ማነሳሳቴ አይዘነጋም ። ዛሬ ደግሞ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታስረው በሚገኙበት ከመካ የቅርብ ርቀት በሚገኘው የሽሜሲ እስር ቤት ታዳሪዎችን ስለጎበኙበትና ከሳውዲ ኃላፊዎች ጋር ስለተቀመጡበት ውይይት ከፍል ሁለት ዳሰሳየን እንዲህ እቀጥላለሁ! የፈቀዳችሁ ተከተሉኝ …በሽሜሲ እስር ቤት ዶር ደስታ  ከታሳሪዎች ጋር ..
==============================
በሳውዲ መንግስት በኩል ” ህገ ወጥ”  ተብለው በሌሊት ቤት ሰበራና አፈሳ የታሰሩ ዜጎች የሚገኙበትን የሽሜሲ እስር ቤትን ጅዳን ለቀናት የጎበኙት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ ሀሙስ  ፣ ነሀሴ 14 ቀን 2007 ዓም  ጎብኝተዋል።  በዚሁ ጉብኝት  ”  መብታችን ተጥሶ  ወደ ሀገር ለመግባት ፎርም አንሞላም!” በሚል ከእስር ቤት ወደ ሀገር ለመሄድ ፈቃደኛነት ያላሳዩ  ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እያላቸው ያለ አግባብ የተያዙትን ፣  ከአሰሪያቸው ጋር ተጣልተው ጉዳያቸው በፍ/ቤት ተይዞ እያለ “ህጋዊ አይደላችሁም!” ተብለው የታሰሩትን  ፣ ሌሊት ቤት እየተሰበረ እርቃናቸውን የተያዙትን ፣ በሌሊት አሰሳ ፍተሻው ከነ ልጆቻቸው የተጋዙ አባዎራዎችን ፣ ሁሉንም ባይሆን በመቶዎች የሚቆጠሩትን ዶር ደስታ በጉብኝታቸው በአካል አግኝተው የተበደልን ተገፋን ሮሮ ፣ አቤቱታ ምሬታቸውን አድምጠዋል ፣ ታሳሪዎች በተለይም ወደ ሀገር ይሸኙ እንኳ ቢባል በሳውዲ ለአመታት ሲኖሩ ያፈሩትን ሀብት ንብረት ፣ የሰሩበትን የላብ ዋጋ በአሰሪ አረቦች የተቀሙትና የበተኑትን ሀብት ንብረት እንዲመለስላቸውም ሆነ እንዲሰበስቡባ ወደ ሀገር እንዲልኩ ያደርጉ ዘንድ ባለስልጣኗን ሲማጸኑ ” በዋስትና እንኳ እንድንፈታ መንገድ ይፈልጉልን ” እንዳሏቸው ታሳሪዎች አጫውተውኛል ። ጨነቀ የጠበባቸው ሁሌም እያለቀሱ ብሶት ምሬታቸውን አሾልከው በሚያገኟት አጋጣሚ በስልክ የሚነግሩኝ እኒሁ ታሳሪዎች ከዶር ደስታ ጋር ሲወያዩ ዶሯ  በውይይቱ በሰሙት መረጃ ማዘን መቆጨታቸውን ጠቁመውኛል .. .ዶር ደስታ ሁሉንም ሰምተው ፣ በሆነው አዝነው ፣ በእስር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካይ ከሆኑት ከዶር መሀመድ ኑሪጋ ጋር በቀረበው የታሳሪዎች ብሶት ፣ ምሬትና አቤቱታ ዙሪያ ለመምከር ለሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓም  በቀጠሮ ተለያዩ …በሽሜሲ እስር ቤት፣ዶር ደስታና የኃላፊው ውይይት!
===============================
የአረብ ቀጠሮ ሆነና የሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓም ቀጠሮ ወደ ማክሰኞ 18 ቀን 2007 ተላለፈ …ከሀሙስ እስከ ማክሰኞ ባሉት ቀናት ፍተሻ አሰሳው ጦፎ ፣  ከሌሊት ሰበራው ለመሸሸት ከሚኖርበት ፎቅ ደመ ነፍሱን በመስኮት የዘለለ የሁለት ልጆች አባወራ ከሞት ላደረሰ አደጋ መጋለጡን ሰማን …የዶር ደስታና የሳውዲው ኃላፊ ቀጠሮ ማክሰኞ 18 ቀን 2007 ደረሰ ።  ዶር ደስታ ፣ የቆንስሉ ኃላፊዎችና የጅዳ ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር በተገኙበት በሳውዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሽሜሲ እስር ቤት ተወካይ ከሆኑ ከዶር መሀመድ ኑጋሪ ጋር ውይይቱ  እኩለ ቀን ተጀመረ  !ዶር ደስታ በውይይታቸው ሀሙስ ታሳሪ ኢትዮጵያውያንን ሲጎበኙ ያዳመጡትን በዜጎች የቀረበውን አቤቱታ በዝርዝር አቀረቡ። ሳውዲው ኃላፊ ዶር መሀመድ ዶር ደስታ ስላቀረቡት በሌሊት ቤት ሰበራ ፣ ማዋከብ ፣ ሀይማኖቱ በማይፈቅደው መልኩ እርቃናቸውንና የረባ ልብስ ሳይለብሱና ጫማ ሳይጫሙ የመሳሰለውን አይነት ግፍ በታሰሩ ዜጎች ላይ ተፈጽሟል ስላሉት ቅሬታ የቆንስሉ በኩል ከዚህ ቀደም ምንም አይነት ቅሬታም ሆነ አቤቱታ እንዳልቀረበና በዚህ ረገድ ከቆንስል ኃላፊዎች በኩል ክትትል መጉደሉን ሳውዲው ኃላፊ እንቀጩን ተናግረዋል።  ዶር መሀመድ በዚሁ ውይይት የመብት ገፈፋን ለመከላከል አሰሳው በጥናትና ከተለያዩ የመንግስት አካላት በተውጣጡ ኮሚቴዎች  የሚካሄድ በመሆኑ የመብት ጥሰት አለ ብለው እንደማያምኑ በመጠቆም ጉዳዩ ተፈጽሞ ከሆነ እንደሚያጣሩት ቃል ገብተዋል። በማከልም የሳውዲ መንግስት ከህገ ወጦች አስጠግተው ወይም ተጠግተው የተያዙትን መያዙ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ቆንስል መስሪያ ቤቱ ይህንን ለመተግበር ትብብር እንዲያደርግ መጠየቃቸው ተጠቁሟል ። ባለስልጣኑ ይህን ቢሉም ዶር ደስታ ከታሳሪ ኢትዮጵያውያን በኩል የቀረበላቸውን አቤቱታና ተማጽኖ በማውሳት ለአመታት ሲኖሩ ያፈሩትን ሀብት ንብረት የመሰብሰብ  ፣ የሰሩበትን የላብ ዋጋ በአሰሪ አረቦች የተቀሙትና የበተኑትን ሀብት ንብረት እንዲመለስላቸውም ሆነ እንዲሰበስቡ ዋስትና አግኝተው እንዲፈቱ እንዲደረግ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ጥያቄው በሳውዲው የውጭ ጉዳይ ተወካይ ለዶር መሀመድ በኩል ተቀባይነት አላገኘም።

ለአመታት ጠያቂ ያጣው የዜጎች ንብረት እንደቀልድ !
================================
በዚሁ ውይይት የተነሳው ሌላው ጉዳይ እአአ 2013 ሳውዲ በአዋጅ ህገ ወጦች ስታስወጣ “እናንተ ሂዱ ፣ እቃችሁ ይላካል! ” ተብሎ ቃል የተገባላቸውና የሰልተፈጸመው በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተነላሾች የሻንጣና የተንቀሳቃሽ ስልክ ጉዳይ ነው።

(ከአመታት በፊት ዜጎች ወደ ሀገር ሲሸኙ ጥለውት የሄዱት በመቶዎች የሚቆጠር ሻንጣና ወደ 7 ሽህ ጉዳይ እኔም በጅዳ የወገን ለወገን አስተባባሪ ኮሚቴ እያለው የማውቀው ጉዳይ ሲሆን ለአመታት እልባት በቆንስል መስሪያ ቤቱ እንዝህላልነት በሉት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እህት ወንድሞቻችን በላባቸው ያፈሩት ንብረት ጠያቂ አጥቶ ጉዳዩ ያለባለቤት ሲንከላወስ መኖሩን አውቃለሁ)

ወደ ውይይቱ ስንመለስ ዶር መሀመድ ከላይ በጠቀስኩት ወቅት በሽሜሲ የተሸኙ ዜጎቻችን ሻንጣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ንብረት እንዳለ አስረግጠው ፣   የጅዳ ቆንስል መ/ቤት ንብረቱን ተረክቦ ወደ ሀገር እንዲልክ ደብዳቤ ሳይቀር መጻፉን ለዶር ደስታ አስረድተዋል። በማከልም  አሁንም በሽሜሲ እስር ቤቱ ያለውን የኢትዮጵያውያን ንብረት የጅዳ ቆንስል እንዲረከባቸው ለዶር ደስታ አስረድተዋል ሲሉ በስብሰባው ዙሪያ ያገኘሁት የመረጃ ምንጭ ያስረዳል !

ከወራት በፊት የታገደው ለታሳሪዎች ሻንጣ ማቀበል ይከፈት ዘንድ በዶር ደስታ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም ሻንጣ ማቀበሉ ስራ በውስጣዊ ችግር ምክንያት በቅርቡ እንደማይከፈት ሳውዲው ኃላፊ በማያሻማ ቋንቋ አሳውቀዋቸዋል ። …

“ዜጎቻችሁ ህግና ስርዓት ይያዙ  “የውይይቱ መቋጫ ….
==================================
በዚሁ ውይይት የሳውዲው ኃላፊ በአጽንኦት ባስተላለፉት መልዕክት  ” ዜጎቻችሁ ህግና ስርዓት ካልያዙ ፣ ከህገ ወጥ ጋር ከተገኙና ከተያዙ ታስረው ወደ ሃገራቸው መላኩ በህግና መመሪያ የወጣበት ጉዳይ ነውና ፣ ተጠናክሮ ቀጣይ እንጅ የሚቆም አይደለም! ” ሲሉ የሳውዲው ባለስልጣን ለዶር ደስታ ገልጸውላቸዋል !

በጉብኝቱ የዜጎችን ብሶት ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ መናገራቸው እውነት ነው ፣ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነና ” የታሰሩት አይፈቱም ፣ በዋስም አይወጡም ፣ ህግ ነውና ይተገበራል ፣ ቀሪውም ህገ ወጥ ያልታሰረ ዜጋችሁ በቀጣዩ ዘመቻ እንዳይታፈስ ህጋዊው ለህገ ወጦች ወጦች ሽፋን እንዳይሆን ምክሩት ፣ በዚህ ላይ ምህረት የለም  !” የሚለውን መልዕክት ብልጡ የሳውዲ ባለስልጣን ለእኛዎቹ ባለስልጣናት አስተላልፈዋል …

በጉብኝት ውይይቱ የተገኘ ውጤትና ፋይዳ ይህው ነው … ታሳሪዎች ብሶትና ሮሮ በዶር ደስታም ሆነ በጅዳ ቆንስል ሺሞቻችን መልስ አላገኘም  ! ፎርም አንሞላም ብለው በእስር ቤት የሚገኙ ሀቁን ተገንዝበው የራሳቸውን ውሳኔ ሊወስዱ ይገባል  !  …  ጠቅለል ብሎ ሲቀርብ ከታማኝ ምንጮቸ ያሰባሰብኩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች  ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ የሽሜሲ ውሎ ሲብራራ ከዚህ ያለፈ አይደለም …

የሴቶች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዶር ደስታና በጅዳ የሴቶች ስብሰባ
==========================
እነሆ አንድ ሁለት ብየ የሴቶች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስን ባደረጉት ሰሞነኛ የሳውዲ ጅዳ ጉብኝት አስመልክቶ ከጀመርኩት ሶስተኛ ክፍል ዳሰሳ ደርሻለሁ።  ይህም አይቀር ላንሳው ብየ እንጅ ውይይት ምክክሩ የረባ እንዳልነበር ተነግሮኛል ። ባሳለፍነው ቅዳሜ ነሀሴ 16 ቀን 2007 በጅዳ ኮሚኒቲ አዳራሽ በተካሄደው የሴቶች ስብሰባ በርከት ያሉ ወንድ የቆንስል ፣  ኮሚኒቲ ፣ ሰራተኞችና ዲፕሎማቶች ተገኝተው የሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሶስተኛ ሙት አመት በሻማ ማብራት ታስቧል ። ከዚህ ቀደም አዳራሹን የሚያደምቁት የድርጅት ፣ ማህበር አባላት ፣ የጅዳ ቆንስል ” ነጭ በሬ”  ሴት ወይዛዝርት እንደቀድሞው በዚህ ስብሰባ አልተሳተፉም። የኢህአዴግ ድርጅቶችና ማህበራት ድግስ ደግሰው የማያለቅ ልደትና የተለያዩ በአላትን ሲያከብሩ ቄጠማ ነስንሰው አምባሻ ደፍተውና ቡናና አበባ ቆሎ ቆልተው የሚያቀርቡ የሚያስተባብሩት እማማ አደይ በስብሰባው የተገኙት በሽምግልናና ጉትጎታ መገኘታቸው ተጠቁሟል ። ያም ሆኖ በእነ እማማ አደይ ዘንድ ግብብ የሌላቸው በጣት የሚቆጠሩ የአዲሧ የሴቶች ሊቀመንበር የወሮ ሙሉካ ሁሴን ባልንጀሮችና ወዳጆችነ ጨምሮ ጥቂት ነባር አባላት በታደሙበት የቀዘቀዘ ስብሰባ ውይይት ተደርጎ ነበር ። መረጃውን ያቀበሉኝ ወዳጆቸ ውይይቱ የብዙሃኑ ነዋሪ እህቶች ብሶት አልተንጸባረቀም ሲሉ አንቶ ፈንቶ  በማለት የጅዳ ቆንስልን የውስጥ አሰራር የተገመገመበት እዚህ ግባ የማይባል ውይይት ነበር ሲሉ አጣጥለውታል ።

እኔ ከሁሉም ያዘንኩት ከጀዳ ቆንስል ኃላፊዎች ጋር ጥብቅ ግንኙነት መመስረት የማይታክታቸው ፣ ከዚህ ቀደም በሰብአዊ ድጋፍና በዜጎች ተቆርቋሪነታቸው ፤ጠንካራ ሰራተኝነታቸው የማውቃቸው አዲሷ የጅዳ ሴቶች ማህበር ሊቀ መንበር ወሮ ሙሉካ ሁሴን በከባቢው ሴቶች በደል ዙሪያ የጠለቀ መረጃ እያላቸው ፣ ለስብሰባው ግብአት አለማድረጋቸው ገርሞኛል ።  ብርቱና ታታሪዋ ሰርቶ አደር እህትወ/ሮ ሙሉካ  የሴቶች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዶር ደስታን ከሽሜሲ እስከ የደመቁ የጀዳ ዘመናዊ አልባሳትና ቁሳቁስ ገበያዎች ሲያጋፍሩ ሲሰነብቱ በእጃቸው ያሉ መረጃዎችን ማቀበል ለምን እንዳቃታቸው ሳስበው አዝናለሁ ። ወሮ ሙሉካ የሴቶችን አስረጅ ደፋር አባል ቢያጡና ቢጠፋ ፤ ሰርክ እንደኔ መረጃ በሚለቅሙበት ሰልካቸው ያለውን አንድ ሁለት በተቃረብ ጊዜ መረጃ ስበው በስብሰባው ወቅት ማወያያ ማድረግ እንዴት እንደገደዳቸው የሚያውቀው ፈጣሪ ነው ! ቢረሳ ቢረሳ መዲና ለሁለት አመታት ገደማ ማንነቷ አልታዎቀም ተብላ ያለ ጠያቂ በአንድ ሆስፒታል ተጥላ ያለችውን እህት ጉዳይ እንኳ ማንሳት ለምን አልተቻለም ?  ከአሰሪያቸው ተፈናቅለው ፣ ከስራ ተባረውና ፣ተደፍረው ፣ ተደብድበው ፣ በፈላ ውሃ ተቃጥለውና ተጥለው ፣ በመጠለያው ሰላለፉና ስለሚገኙ እህቶች መደረግ ሰላለበትና ወደፊት መሰራት ሰላለበት ለመምከር ለምን አልተሞከረም ?  በሴቶች ስብሰባ በኮንትራት መጥተው በየቤቱ መድረሻ አጥተው ስለሚሰቃዩ ፣ ”ድረሱልን“ ስለሚሉ ደራሽ ግን ስላጡት ፤ ስላበዱ ፣ ተደፈረው አርግዘውና ወልደው አበሳ ስቅየት ስላዩትና ስለሚያዩት ፣ የድሃ ቤተሰብ ሸክም ስለሚሆኑት ምንዱባን እህቶች መናገር እንዴት አልተቻለም ? በዘገየው ፖስፖርት መኖሪያ ፈቃዳቸው የወደቀባቸው ሴቶች የሉም ?ይህ ሁሉ ተረስቶ ነው ? ወይስ ተዘሎ ?  ይህ ሁሉ የስደተኛ አበሳ ያልተዳሰሰው ለሊቀመነበሯና ለቀሩት ተሰብሳቢዎች እንግዳ ነገር ሆኖ ወይስ መረጃ ጠፍቶ  ?  ለእኔ መረጃ የመረጃ እጥረት ሳይሆን ለእውነት የቆመ ሰው ችግር እያንገላታን እንደሆነ ይሰማኛል።  ” ያገባኛል !” ባይ ተቆርቋሪ አጥተናል ፤ ለነፍሱ ያደረ ደፋር ጠፍቶ የሴቶች ጉዳይ በሴቶች ጥልቅ ውይይት ሳይደረግበት ተዘሏል ብየ ስበሰባውን እኔም በበቃኝ ልዝለለው !

ዶር ደሰታ ሹም ስንፈግ መጡ ፣ ባስፈላጊው ቦታ ሳይገኙ ቀሩ  …
===================================
የስብሰባው ተውሸክሽኮ መከዎን እና በስብሰባው ይነሳል ብየ የጠበቅኩት የብላቴናው መሀመድና የእናቱ ጉዳይ ሳይነሳ የመቅረቱ አንደምታ አንድ የቅርብ ቀን ትዝታን አስታዎሰኝ ።  ሰኔ ሲጠባ የብላቴናው መሀመድን የ9 አመት ሰቃይና አቤቱታ ይዥ እንድቀርብ እናት ሀሊማ “ የበደል ድምጼን ለአለም አሰማልኝ !” ብላ ጠይቃኝ በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ አቀረብኩ ፣ ይህን ባቀረብኩ ማግስት የጅዳ ቆንስል አንድ ሃላፊ “ ከዚ በፊት የነበሩ የቆንስል ሃላፊዎች ባይሰሩትም ፤ አሁን ያለነው እኛ ጉዳዩን ይዘን እየተከታተልን እያለ ለምን ለነቢዩ ሲራክ መረጃ ታቀበላለች ” ከሚል ቅንነት በጎደለው እሳቤ ቅር መሰኘታቸው መረጃ ደረሰኝ ፣ ቀጠለና ባልንጀራቸው አዲሷ የሴቶች ሹም ወሮ ሙልካ ጓዶቻቸውን ይዘው ብላቴናውን መሀመድን እናት ለመጠየቅ ሄዱ፣ ችኩሏ እህት ወሮ ሙልካ የባልንጀራቸ ቅሬታ አሟቸው ብቻ ምኑንም ሳይረዱ  ” ለምን ለነቢዩ ሲራክ ቆንስል ኢንባሲ 9 ዓመት አልደገፈኝም አልሽ ? ” በማለት ብርቱዋን የብላቴላው መሀመድ እናት ሀሊማን ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ጠይቀው ያሰራጩትን መረጃ “ተብየ” ተመልክቻለሁ ።  ታዲያ የያኔው የአዲስ ተሿሚና የሴቶች ማህበር አመራሮች ጉብኝት ከተቆርቋሪነት ስሜት የመነጨ ከነበር የሴቶች ዋና ዳይሬክቶሬት በተገኙበት ስብሰባ የመሀመድን ጉዳይ ለምን ማንሳትና መወያየት እንዳልቻሉ አልገባኝም !

” ነግ በኔ !”  ነውና ቢያንስ ማህበሩ የመሀመድን እናት በቤት ኪራይ ፣ በትራንስፖርት በመሳሰሉት  እንደግፍ ብሎ ከመምከር ያልቻሉበት ምክንያት ምን እንደሆነ የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው !  አንደበተ ርቱዕ የሆኑት የቀድሞ ወዳጀ የጅዳ ሴቶች ሊቀ መንበር ወሮ ሙሉካ ሌላው ቢቀር በየደቂቃዋ መረጃ በሚመለከቱባት በእኔው ፊስ ቡክ መረጃ መረብ ለክቡር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ የላኩላቸውን ተከታይ አጭር መልዕክት አልተመለከቱትም አልልም ! መልዕክቴም አጭርና ግልጽ ነበር

“ይድረስ ለክቡር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ …
ብላቴናው መሀመድን ይጎብኙ ፡ ብላቴናው መሀመድ እርስዎ ካረፉበት ሆቴል የአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ካለው የዶር ፈቂ ሆስፒታል ተጋድሞ ይገኛል ፣ አስጎብኝዎ የሴቶች ማህበር ተብየዎችም ሆኑ የቆንስል ሰዎች ለምን ብላቴናው መሀመድን እንዲጎበኙ እንዳላደረጉ አልገባኝም …  በተለይ እንደ ልጅ እናትነትዎ የታዳጊውን አበሳ ፣ እንደ ሴትና እንደ ሴቶች ተወካይ ዳይሬክቶሬትነትዎ ሰብዕናዋን ለንዋይ ፍቅር ያልሸጠችውን እናት ሃሊማን ማግኘት በራሱ ለእርስዎ መታደል ነው … በሆስፒታል ሄደው ብላቴናው መሀመድንና የመሀመድን እናት ይጎብኙ ፣  በአልጋ ላይ ተንጋሎ ባደገው ህጻን የግፉን ልክ ፣ ከመሀመድ እናት ከሀሊማ ደግሞ ጽናትና  የእምነት ጥንካሬን ይማራሉ ! የእናት የልጅና የቤተሰቡን የ9 ዓመት የመከራ ጉዞም ይረዱታል …  ! እናም ብላቴናውን ይጎብኙት  ! …ሳውዲ ለምንም ይሁን ለምን ከመጡ አይቀር መሀመድን ጎብኝተው በነካ እጅዎ ስለበደሉ ለሳውዲ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃላፊዎች አቤት ይበሉልን  !  ለፍትህ አካላትና ለሚመለከታቸው የሳውዲ ባለስልጣናት በብላቴናው መሀመድ  አብድልአዚዝ የተፈጸመውን ተዳፍኖ የከረመ በደል ያቅርቡልን ፣ ”  ፍትህ ለመሀመድ !” ብለው ይጠይቁን ዘንድ በባንዴራው ብቻ ሳይሆን በልጆችዎ እንማጸንዎታለን ! … ” ብየ መጠቆሜን ወሮ ሙሉካ አስታውሰው በስብሰባው ላይ ጉዳዩ እንዲነሳ ባለማድረጋቸው ባለስልጣኗን ዶር ፈቂ ሆስፒታል 9 አመት ፍትህ ተነፍጎ የተኛውን ብላቴናው መሀመድና እናቱን ማስጎብኘት አልቻሉና እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎች አዝነናል ።
አረቦች ብረትና “ምንቴስን” “ሲግል ነው መቀጥቀጥ !” እንዲሉ የብላቴናው መሀመድ ጉዳይ  ከሳውዲ አልፎ የአረብ ሀገራትና የአለም መነጋገሪያ እየሆነ ባለበት በዚህ ወሳኝ አጋጣሚ በጅዳ ሴቶች ስብሰባ ላይ ዶር ደስታ ከሳውዲ ባለስልጣናትና የፍትህ አካላት ጋር ተገናኝተው እንዲመክሩ አለመጠየቁና ግፊት አለመደረጉ አዙሮ ላየው የሴቶች ማህበር ወዴት ነህ ? ያስብላል…
በደፈናው ዶር ደሰታ ሹም ስንፈግ መጡ ፣ ባስፈላጊው ቦታ ሳይገኙ ቀሩ  … በላቴናው መሀመድንና በርቱዋን እናት ላይ ግን ጨከኑ…

ማጠቃለያ …
=========
ከዚህ በላይ ለመጠቃቀስ እንደሞከርኩት በሴቶች ማህበር ስብሰባ አንኳር አንኳር የአካባቢያችን ሴቶች ጥያቄ የሆነው የኮንትራት ሰራተኞች አበሳ ጨምሮ የብላቴናው መሀመድን እና የእናቱን ጉዳይ በጥልቅ ውይይት እንዲደረግበት አልተደረገም ።  ዛሬም “ ስብሰባው የእውነት ፡ የሴቶች ማህበር ከተገፉ ሴቶች ወኪል ነው!” እንድንል በተጨባጭ ያየነው እውነት የለምና በሴቶች ማህበር ስም የሚሰራው ሁሉ ያሳስበናል! ትናንትናም ሆነ ዛሬ የምናውቀው የማንቀበለው እውነት አለ ፡ እሱም ስም ይዘው በተደራጁ ማህበራት ብዛት ችግራችን አይፈታም ፡ ችግራችን የሚገፈተው ፡ የሚገፋው ድፍን አንድ አመት ሙሉ እየተቀያየሩ እየሄዱ በሚመለሱት ጉምቱ ባለስልጣናት ሳይሆን በእኛ በችግር ቀማሽ ስደተኞች ትብብር መሆኑን ልብ ይሏል !
ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ነሃሴ 2015 ዓም

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: