The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

መልካም አዲስ ዓመት እንላችሁአለን -2008 የነፃነት ዘመን እንዲሆን እንመኛለን (ግርማ ሰይፉ)

 

happy New Year

ውድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም መሰከረም አንድን በሀይማኖታዊ ትሁፊቱ አብራችሁን የምታከብሩ ከእኛ በባሰ ባርነት ስር የምትገኙ ኤርትራዊያን (ተገዳችሁ ከዚህ አቆጣጠር መውጣታችሁን ስለማስብ) እንኳን ለ2008 ዓ.ም አደረሳችሁ የሚል መልዕክት ሳስተላልፍላችሁ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል፡፡ በቋንቋ ብዛሃነታችን እንድንኮራበት ከሚነግሩን ጋራ ምንም ልዮነት የሌለኝ ቢሆንም የሃሳብ ብዝሃነትን እያፈኑ አንድን ጉዳይ ብቻ በተለያየ ቋንቋ እንድንናገር ለሚፈልጉ ሰዎች አዲስ ዓመት ልቦና የሚገዙበት እንዲሆን ምኞቴ ነው፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ጠንካራ አማራጭ ማቅረብ የሚችል ስብስብ መፍጠር የማይችል የሚያስመስሉ የድንክ ድርጅት መሪዎችና አስመሳዮች ሰልፍ የማስተካከል እድል አላቸው ብዬ ባላምንም በለሁሳስ ከጫወታ ቢወጡ የፃፉትን ጥቁር ታሪክ ሊያጠይሙት ይችላሉ የሚል ሃሳብ ስለአለኝ ይህ ምኞቴ ነው፡፡ ይህ መልዕክት ከቅንጅት መፍረስ – እሰከ ቅርቡ አንድነት ድረስ ያሉትን የኢትዮጵያ የታሪክ ጥቀርሻዎችን ይመለከታል፡፡ ሌላው ዋነኛ የአዲስ ዓመት መልዕክቴ ደግሞ የተቃዋሚ መሪ ነን በማለት ላለፉት 20 ዓመታት በላይ ሙከራ ያደረጉ አንጋፋ መሪዎች እስከ ዛሬ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋናችን የላቀ ቢሆንም፤ የሄዳችሁበት መንገድ ኢህአዴግ ከሚሰራው ሴራና ተንኮል ጋር የሚመጥን ባለመሆኑ ይልቁንም የትርፍ ጊዜ ፖለቲካ ያደረጋችሁት በመሆኑ አሁንም በክብር ሃላፊነታቸውን እንዲለቁ ወይም ተተኪ ካላቸው እንዲያስረክቡ ጥሬዬን አቀርባለሁ፡፡

ለኢህአዴግዊያን በሙሉ በጉባዔያችሁ ያነሳችሁት የውስጠ ዲሞክራሲ ጉዳይ የህውነት እንዲሆን እና የድርጅቶች የቋንቋ ብዝሃነት ብቻ ሳይሆን የሃሳብ ብዝሃነት የሚታይበት እንዲሆን መልካም ምኞቴ ነው፡፡ የሃሳብ ብዝሃነት የጎደለው ስብስብ ምን ሊፈይድ አይችለም፡፡ ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን የሚመጣው የሃሰብ ፍንዳት የሚፈጥረው ጎርፍ ጠራርጎ እንደሚወስዳችሁ ስጋቴም ነው፡፡ አቶ ሀይማሪያም ደሳለኝ አሁንም ትልቅ ታሪካዊ ዕድል በእጃቸው አስቀምጦላቸዋል፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን በእርሳቸው ዘመን አደጋ ላይ ብትወድቅ የሚሰጡት ምንም ዓይነት ሰበብ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ይህ እንዳይሆን በኃላፊነት ሰሜት ተግባራዊ የማሻሻያ እርምጃ እንዲወስዱ እጠይቃለሁ፡፡ አሁንም አንድነት ፓርቲ የፈረሰበትን የደህንነት ሴራ አጣርተው (የውስጥ ችግር ነው የሚሉትን ትተው) ለኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ዝርጋታ የሚበጅ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስዱ እጠይቃለሁ፡፡ በእርግጠኝነት የማውቀው አንድነት የፈረሰበትን ሴራ ኢህአዴግ የ2007 ምርጫን ለማሸነፍ በደህንነት የተሰራ መሆነን ስለማውቅ ነው፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ ያለምንም ጥፋት በእስር የሚማቅቁ የህሊና እስረኞችን በመፍታት ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስዱ እጠይቃለሁ፡፡ የህሊና እስረኞችን ይዞ ወንጀለኞችን መፍታት አንድም የሞራል ልዕልና የሚስጥ አይደለም፡፡ ውድ ኢትዮጵያዊያን ነፃነት በነፃ አይገኝም፤ ነፃነታችንን በሰፈር ላሉ ካድሬዎችና የስርዓቱ ተላላኪዎች አሳልፈን ላለመስጠት የምናደርገው ትግል ድምር ውጤት ሁላችንንም የነፃነት ባለቤት ያደርገናል፡፡ ማንም ነፃ ሊያወጣን እንደማይችል ተረድተን ነፃነታችን በእጃችን መሆኑን ተረድተን ነፃነታችንን የምናስከብርበት ዓመት እንዲሆን በተግባር መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡

የዛሬ አራት ዓመት አንዱዓለም ልጁን ትምህርት ቤት አድርሶ ሲመለስ ሳያየው አራት ዓመት ሊሞላው የአንድ ጣት እጅ የማይሞላ ቀኖች ይቀሩታል፡፡ አንዱዓለም እና ጓደኞቹ አሁንም በእስር ላይ በጥንካሬ እንዳሉ ይስማኛል፡፡ ይህ ለነፃነት የተከፈለ እና እየተከፈለ ያለ ዋጋ ነው፡፡ በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥም በውጭም ለምትኖሩ ሁሉ እመኛለሁ፡፡

satenaw

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: