The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

አቶ ሬድዋን እወቀው (ሄኖክ የሺጥላ)

September 26, 2015

ሄኖክ የሺጥላ

ሶስት ነገሮች በጣም ሰልችተውኛል ። የአቶ ሬድዋን ሁሴን ዛቻ ፣ የሃይለማርያም ደሳለኝ ደደብነት እና የሰን-ፍራይስ እንጀራ ። ሁሉም መደምደሚያቸው ፈስ ስለሆነ ። የማያባራ ፈስ።

በቀደም አቶ ሃይለማርያም ፣ <<ቁንጮ ሁነህ አንተ ምራን ብለውኛል ብሎ>> ያለ ፕሮግራሜ ሲያስቀኝ ነበር ። ማለቴ መለስን << መላጣ ሁነህ አንተ ምራን >> ብለውት ነበር እንዴ ። ታዲያ በቶፓዝ ምላጭ መቆንጨት ነዋ ፣ ምን ማሳወቅ ያስፈልጋል ። ደሞ ቅጫም ለወረረው ጭንቅላት ቁንጮ መድሃኒት ነው።Redwan Hussein, head of Ethiopia's communication affairs office

ደሞ በቀደም ይሄ ሬዲዋን የተባለ አሽከር ሊያስፈራራን ሞከረ ። << ከአሜሪካ መንግስት ጋ አንድ ላይ ሁነን በመስራት ላይ ነን ፣ ይህ በአሜሪካን ሀገር የሚኖር አሸባሪው የግንቦት ሰባት ቡድን ፣ የአሜሪካ ዜግነቱን ይነጠቃል >> እና ወዘተ ። ላንቺ ቁም ነገርሽ በሶ ብላ ወጥሽ አሉ ። ቆይ ግን ሰውየው ግን እንዴት ነው የሚያስበው ? ለሱ ብርቅ የሆነበት ነገር ሁሉ ለኛም ብርቅ ይመስለዋል ማለት ነው ። ሬድዋን ሆይ ፣ወያኔን የምንታገለው የአሜሪካ ዜግነታችንን ለማስጠበቅ አስመሰልከው እኮ ። እንደው በሞቴ ፣ እኛ የባንዳ ልጆች ስላለመሆናችን ፣ እናም ከኢትዮጵያዊነት ሌላ ፣ ሌላው ብንለብሰውም እንደማይሞቀን እና እንደማያደምቀን አሁን ማን ይሙት ሳይገባህ ቀርቶ ነው በሰው ሀገር ዜግነት መነጠቅ እና መሰጠት እኛን ልታስፈራራ ስትል ትንሽ አታፍርም ? እንደው ትንሽ አይሰቀጥጥህም ። ለነገሩ ለምን ይሰቀጥጥሃል።

ያን ሰሞን የአዲሲ ግብረሃይል ባንዱ ልብስ መሸጫ አግኝቶ ፣ በጠራ አርፍተ ነገር ስለ ማንነትህ ሲነግሩህ አይቼ ነበር ። ታዲያ ያኔ እኔን የሳበኝ ልጆቹ አንተን ያገኙህ ቦታ ። ትዝ ይልሃል ጨርቅ ልትገዛ ስትል ። ታዲያ ከአንድ ጨርቃም ከዚህ በላይ መጠበቅ ራሱ እዚህ አማሪካ በወንጀል ያስቀጣል።

በነገርህ ላይ ፣ የአማሪካ መንግስት ፣ እንደ አንተ መንግስት በመደዳ ባንድ ሌሊት ቤት እየሰበረ ሰው የሚያስር ስላለመሆኑ ታውቅ ይሆን ? እዚህ ሀገር ሕግ አለ ። ፍርድ ቤት አለ ። ዳኝነትም አለ ። እነዚህ ሶስቱ ነገሮች እስካሉ ድረስ እኛ የወያኔ ተቃዋም ሆነን እንቀጥላለን ። እኔ በግሌ << እንዳንተ ከሆነ ፣ ያው ዜግነቴን ይውሰዱት በቃ >> ፣ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራውን የትጥቅ ትግል እደግፋለሁ ። ምን መደገፍ ብቻ ገና እቀላቀላለሁ ። ይቺን አሁን ያልኳትን ለመረጃነት አስቀምጣት ። <<ዜግነቱን ያኔ ላንተ በፌዴክስ ወይም በዲ ዔች ኤል እልክልሕና አንተ ታደርስልኛለህ ፣ በዚያውም ሸሚዝ እና ፓንት ገዝተህ ትመለሳለህ >> ምን ይልሃል?

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አዳፍኔ በተሰኘው ድንቅ መጽሐፋቸው በገጽ 19 ላይ እንዲህ ይላሉ

“አንድ የውጭ ሀገር ጸሐፊ በኢትዮጵያ ውስጥ የታሪክ ማስረጃ የሚባል ነገር ሁሉ ጠፍቶ ፣ በጣም ጠጣር በሆነው ድንጋይ ላይ የተጻፈው ብቻ ቀርቷል …ስለዚህ ድንጋይ ለድንጋይ አይናበብም ወይም አይነጋገርም ነው እንጂ መረጃው በእጃቸው ነው”

አዎ ድንጋይ ስለሆናችሁ አይገባችሁም እንጂ ፣ እኛ ኢትዮጵያውያኖች ነን ። መረጃውም በእጃችሁ ነው ። እኛን የሚገልጸን ወይም የምገስጸን ኢትዮጵያዊነታችን እንጂ እንደ ‘ናንተ ቃራሚ ተቀጽላችን አይደለም ። “ዛሬም በድንቁርናችሁ መተማመናቹን ቀጥላችሁበታል” ፣ ስለዚህ ሌላው ሰው የናንተን ዛቻ እና ገላባ ፍከራ እንጂ ሌላ ነገር የማያውቅ በድን አድርጋችሁ ታስባላችሁ ። የኢትዮጵያን ሕዝብ አሸማቃችሁ በያዛችሁበት የስነ -ልቦና ሰለባ እና አምካኝ ስብእና ፣ ደሞ ባህር ተሻግራችሁ ልታስፈራሩ ትሞክራላችሁ ፣ ምክንያቱም ድንጋይ ስለሆናችሁ ። ስለ እኛ ከአሜሪካ መንግስት የተሻለ እናንተ ታውቃላችሁ ፣ ከናንተ ጋ አብረን አድገናል ፣ ኑረናል ፣ ግን በእጃችሁ ያለውን ማንነታችንን ፣ በልባችን ላይ የተቀረጸውን ኢትዮጵያዊነታችን አውጥታችሁ ጥላችሁ ፣ በሌላ ማንነት ነጠቃ ለማስፈራራት ትሞክራላችሁ ። አይሳካም እንጂ።

አሁንም ፕሮፌሰር መስፍን እንዲህ ይላሉ

“አዳፍኔ ነጻነትን አከሸፈ ፣ እኩልነትን አከሸፈ ፣ ትምህርትና እውቀትን ከማህበረሰባዊ አላማ ወደ ግለሰባዊ አላማ ለወጠ ፣ ወይም ግለሰቡን ከማህበረሰቡ አሰወጣው ፣ ማህበረሰቡ ባዶ ቀፎ ሆነ ፣ የንቦች ንግስት አዳፍኔ ሆነች ፣ ኢትዮጵያ የአገዛዙ ሹማምንት ቤት ሆናለች ፣ ኢትዮጵያ ከቤታቸው የተባረሩ ፣ ቤታቸውን በመልቀቅ ላይ ያሉ ፣ የዘጠና ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እሾህ ሆናለች ።” ይላሉ ። በናታችሁ ከየትም ቢሆን ይህንን መጥሀፍ ፈልጋችሁ አንብቡት።

እና ጋሽ ሬድዋን አዳፍኔ ፣ እኔን በአሜሪካዊ ዜግነቴ ልታስፈራራ ስታስብ ፣ እኔ አንተ የወሰድክብኝን ኢትዮጵያውነት ላስመልስ በርሃ እንደወረድኩ ስለመፍራትህ እየተናገርክ እንደሆነ ነው የሚገባኝ ። አዎ ለነጻነቴ የምሰዋ ፣ ለክብሬ የምሞት ፣ የማንንም ባንዳ ሆዳም ቅጥረኛ የማልፈራ ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ይህ ማንነቴ ከምንም ይቀድማል። እወቀው!

ECADF

posted by Gheremew Araghaw

 

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: