The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የሳኡዲን ንጉስ ሰልማንን ልክ እንደ ግብፁ ሙርሲ ከስልጣን ለማሶገድ ምዕራባውያን እና ጀሌዎቻቸውን እያሴሩ ነው

የሳኡዲን ንጉስ ሰልማንን ልክ እንደ ግብፁ ሙርሲ ከስልጣን ለማሶገድ ምዕራባውያን እና ጀሌዎቻቸውን እያሴሩ ነው  Muslim Wedaje

ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳይ ኢነዲፔንደንት የተሰኘው የእግሊዙ ጋዜጣ ንጉስ ሰልማን ከስልጣን እንዲወገዱ መፈንቅለ ስልጣን ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን መዘገቡን ተከትሎ ነው፡፡

ጋዜጣው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የንጉሳዊው ቤተሰብ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ ብሎ በዘገበው መሰረት ንጉስ ሰልማን በጥሩ አቋም ላይ እንደማይገኙ እና ሃገሩቷን እየመራት የሚገኘው ልጃቸው መሃመድ ሰልማን እንጂ ንጉስ ሰልማን አለመሆኑን መግለፃችን ጋዜጣው አስፍሯል፡፡ ሳኡዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ መውደቅ፣በየመን ጦርነት ውስጥ መግባቷ እና በመካ በሃጅ ወቅት ሁለት ከፍተኛ አደጋ መድረሱ ንጉስ ሰልማን ሃገሪቷን መምራት አለመቻሉን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ አያየዘውም የነዳጅ ዋጋ መውደቁ የሳኡዲአረቢያ ኢኮኖሚ በነዳጅ ላይ ጥገኛ በመሆኑ የበጀት ጉድለት እንደሚያመጣ እና ኢኮኖሚዋ እያሽቆለቆለ መሆኑን በመግለፅ ንጉስ ሰልማን ከስልጣኑ እንዲወገድ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከንጉስ ሰልማን የወንድም ልጆች መካከል ከሆኑት እኙህ መፈንቅለ ስልጣን ለማካሄድ የሚያሴሩት ከፍተኛ ባለስልጣን በቅርቡ ንጉስ ሰልማን ከስልጣኑ የሚወገድበት እና ሌላ መሪ በሚሾምበት ሁኔታ ላይ አጎቶቹ እንደሚወያዩ ገልፆል፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይም ንጉስ ሰልማን ከስልጣኑ እንዲወገዱ የሚጠይቅ 2 ደብዳቤ በኦንላይን ተለቆ በሚሊዬን የሚቆጠር የሳኡዲ ህዝብ ደብቤውን እንዳነበበው ገልፆል፡፡ ንጉስ ሰልማን ከስልጣኑ እንዲወገድ የሚፈልገው ይህ አሚር ብቻ ሳይሆን ብዙሃኑ የንጉሳዊው ቤተሰቦች እና የሃገሪቱ የጎሳ መሪዎች ጭምር መሆኑን አንዱን የሳኡዲ የንጉሳዊ ቤተሰብ መፈንቅላ ስልጣን አራማጅ ባለስልጣን ጠቅሶ ጋዜጠው ዘግቧል፡

ጋዜጣው እንደዘገበው ከሆነ በሳኡዲ አረቢያ አሁን ባለው ሁኔታ መፈንቅለ ዙፋን መካሄዱ የማይቀር መሆኑን የገለጸ ሲሆን በሃገሪቷ መፈንቅለ ስልጣን ያልተለመደ እና ከዚህ ቀደመም በታሪክ በ1964 በንጉስ ፋይሰል ላይ መፈንቅለ ስልጣን መደረጉን ዘግቧል፡፡

ንጉስ ሰልማንን ለምን ከስልጣን እንዲወገድ ተፈለገ???

የሳኡዲ ንጉስ ሰልማን ከበፊተኞቹ ንጉሶች አቋሙ በጣም የተለየ በመሆኑ በምዕራባውያንም ሆነ በፀረ ሙስሊም አቋም ባላቸው ወገኖች ዘንድ አልተወደደም፡፡ ንጉስ ሰልማን ወደ ስልጣን ከወጣ ቡኃላ ልክ የግብፁ የመጀመሪያው በዲሞክራሲያዊ መንገድ በተመረጠው ፕሬዝደንት ሙሪሲ ላይ ምዕራባውያን እና ከኳተር ውጪ ያሉት ሳኡዲ አረቢያን ጨምሮ የገልፍ ሃገሮች ሴራዎችን በመሸረብ ከስልጣን እንዲወገድ አንዳደረጉት ሁሉ የሳኡዲ ንጉስ ሰልማንንም ከስልጣኑ ለማሶገድ በውስጣዊ መርዘኞች ሴራ እየተጠነሰሰበት መሆኑ በተደጋጋሚ እየተከሰቱ ያሉ ሁኔታዎች ያመላክታሉ፡፡

የግብፁ ፕሬዝደንት የነበረው ሙርሲ በህዝብ ተመርጦ ስልጣን ላይ ሲወጣ ከምዕራባውያን ጋርም ሆነ ከእስራኤል ጋር ጠንከር ያለ አቋም የነበረው በመሆኑ በተመረጠ በአንድ አመቱ ህዝቡ በሙርሲ ላይ እንዲማረር የሚያደርጉ ተግባራትን በግብፅ በውስጣዊ ጀሌዎች አማካኝነት ስራ ተሰርቶ ህዝቡ በሙርሲ ላይ እንዲያምፅ በማድረግ ከስልጣን እንዲወገድ አድርገውታል፡፡ በተመሳሳይም ንጉስ ሰልማንንም ከስልጣን ለማሶገድ በውስጥ አርበኞች የሳኡዲን ህዝቡን እና የሙስሊም ሃገራትን የሚያማርር ተግባራት እየተፈፀመ እንደሆነ እየታየ ነው፡፡

በተመሳሳይም ሙርሲን ካሶገዱ በኋላ ለሙስሊሙ ኡማ ቀኝ እጅ በመሆን እያገለገለ የሚገኘው የቱርኩ ፕሬዝደንት ኤርዶጋንንም ከስልጣን ለማሶገድ በተደጋጋሚ ምዕራባውያን አመፅ በሃገሩቱ ሲያነሳሱ እና ሲቀሰቅሱ ቆይተውበታል፡፡ በሃገሩቱ ህዝብ ዘንድም እንዲጠላ አፋኝ ነው፣አምባገነን ነው በሚል ህዝቡ እንዲማረርበት ሲቀሰቅሱ ቆይተውበታል፡፡ በአላህ ፈቃድ ሆኖ በተደጋጋሚ ያስነሱት አመፅ ሊከሽባቸው ችሏል፡ ሆኖም በምርጫ ግን ከግማሽ በላይ ህዝብ ድምፅ ለኤርዶጋን ፓርቲ ነፍጎታል፡፡ ቱርክም ስትሸሸው ወደ ነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ገፍተው በመክተት በአሁኑ ወቅት ከኩርድ አማፂያን እና ከISIS ጋር ከባድ የጦር ውጊያ ላይ ትገኛለች፡፡ የአንድ ሃገር መንግስት ጦርነት ውስጥ ሲገባ ኢኮኖሚው ይላዥቃል፣በሃገሪቱ እየተፈፀመ በሚገነው የሽብር ጥቃትም ቱርክ ዜጓቿን እያጣች ነው፡፡ በዚህዝም ህዝቡ ሰላም አማራጮችን ስለሚፈለግ በኦርዶጋን መንግስት ላይ ቅሬታውን ማሰማቱ አይቀሬ ነው፡፡ ቀጣይ የነኤርደጋን እጣ ፋንታም ምን ይሆን የሚለውን ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡

ወደ ሳኡዲ አረቢያ ስንመለስ ከምዕራባውያን እና ከጸረ ኢስላም ወገኖች ዘንድ ጥብቅ ወዳጅት የነበረው ንጉስ አብደላህ (አላህ ይዘንለት) መሞትን ተከትሎ የሳኡዲ አረቢያ ንጉስ መሆን የቻለው ንጉስ ሰልማን ቁርአን ሃፊዝ የነበረ ሲሆን በዲኑ ከሌሎች የሳኡዲ ንጉሶች ጠንከር ያለ አቋም ያለው በመሆኑ ለምዕራባውያንም ሆነ ለሌሎች አካላት እንደበፊተኞቹ ንጉሶች ምቹ አልሆነላቸውም፡፡

ንጉስ ሰልማን ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት የሪያድ ከተማ አሚር በነበረበት ወቅት በሚሊዬን የሚቆጠር ዶላር ለአፍጋኒስታን እና ለቺቺኒያ የነፃነት ታጋይ ሙጃሂዲኖች የገንዘብ ድጋፍ ያደርግ ነበር፡፡እንዲሁም ከ1998 እስከ 2003 ለፍልሥጤም የነፃነት ታጋይ ሙጃሂዲኖች ገንዘብ የሚያሰባስብ ኮሚቴ በማቋቋም የኮሚቴው ሰብሳቢ በመሆን 53ሚሊዬን ዩሮ ለፍልሥጤም የነፃነት ታጋይ ሙጃሂዲኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ንጉስ ሰልማን የታላቅ ወንድሙን ሞት ተከትሎ ወደ ስልጣን መውጣቱ ይፋ ከተደረገ ወቅት ጀምሮ የምዕራባውያን ሚዲያዎች እና ድህረገፆች ንጉስ ሰልማንን አሸባሪዎችን በገንዘቡ ሲረዳ የነበረ ሰው ነው በማለት ለሙጃሂዲኖች ሲያደርግ የነበረውን የገንዘብ ድጋፍ በመጥቀስ ችግር ፈጣሪ መሪ ይሆናል በማለት ሲያንቋሽሹት ነበር፡፡

ንጉስ ሰልማን የአሜሪካው ፕሬዝደንት የንጉስ አብደላን ለቅሶ ለመድረስ ወደ ሳኡዲ አረቢያ በተጓበት ወቅት አስር ሰላት አዛን ሲል ከአውሮፕላን ኦባማ እንደወረደ ተቀብሎት እዛው ኤርፖርት ጥሎት ወደ ሰላቱ መሄዱ ብዙሃኑን አስገርሞ ነበር፡፡ በሁለተኛ አልጋ ወራሽነትም ወጣቱን ልጁን ሲሾም በቀናት ውስጥ ልጁ በሂጃብ ጉዳይ ተጨማሪ ኢስላማዊ ህጎችን ደንግጎ ነበር፡፡

በሳኡዲ አረቢያ ንጉሶች ታሪክ ንጉስ ፋይሰል እጅግ በጣም ጠንካራው እና ምዕራባውያንን በገሃድ የታገለ ንጉስ ነበር፡፡ በፍልስጤም መስጂደል አቅሳንም ነፃ ለማውጣት ለጀሃድ ጥሪ ሲያደርግ እና በጀሃድ ላይ መሞት ምኞቱ እንደሆነም ሲገልፅ ቆይቶ ነበር፡፡ንጉስ ፋይሰል የያዘው ጠንካራ አቋም በምዕራባውያን ዘንድ ጥርስ እንዲነከስበት ምክንያት ሆኖበታል፡፡ ይህ ጠንካራ አቋሙም ብዙ እንዲያዛልቀው አልቻለም፡፡ አላህ የውሳኔ ሆኖ በአጎቱ ልጅ እንዲገደል ተደረጎ ከስልጣኑ በሞት ተወገደ፡፡

ንጉስ ሰልማንም ከታላቅ ወንድሙ ከንጉስ ፋይሰል(አላህ ይርሃመው) ጋር ተመሳሳይ አቋም ያለው ሲሆን ወደ ስልጣን በወጣበት ጊዜ የመጀመሪያ ህዝባዊ ንግግር ሲያደርግ በቀዳሚነት ከሚሰራባቸው ጉዳዬች መካከል የፍልስጤምን ነፃነት ማስመለስ መሆኑን ተናግሮ ነበር፡፡ በተደጋጋሚም እስከዛሬ ድረስ እስራኤል በመስጂደል አቅሳ እና በፍልስጤም እየወሰደች ያለውን ህገ ወጥ የሃይል እርምጃ በጥብቅ እያወገዘ እና ለተባበሩት መንግስታት እና ለአለም ሃያላን ሃገር መሪዎች እስራኤል አደብ ትይዝ ዘንድ ሲያስጠነቅቅ ቆይቷል፡፡በቅርቡም በ እስራኤል በመስጂደል አቅሳ እየፈፀመች የሚገኘውን ህገ ወጥ ድርጊት ካላቆመች ሃይማኖታዊ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ንጉስ ሰልማን ማስጠንቀቁን የእስራኤል ሚዲያዎች ሲዘግቡ ነበር፡፡

በንጉስ አብደላህ ዘመን የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ እና በቀጥታም ባይሆን ሃማስን በአሸባሪነት ተፈርጆ የነበረ ሲሆን የሱን መሞት ተከትሎ ንጉስ ሰልማን ወደ ስልጣን ሲመጣ ብዙም ቀናት ሳይቆጠር በቅርቡ የሞቱት የንጉስ ፋይሰል ልጅ የነበሩት የሳኡዲው ውጪ ጉዳይ ሚነስተር ከሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ጋር ስር የሰደደ ምንም አይነት ፀብ እንደሌላቸው ይፋ አድርገው ነበር፡፡

የፍልስጤም የነፃነት ታጋዬችም ለመጀመሪያ ጊዜ ብዙ በደል ሲያደርስባቸው የነበረው የሳኡዲ አስተዳደር በንጉስ ሰልማን በመተካቱ ከኢራን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመተው ከሳኡዲ አረቢያ ጋር መወገናቸውን ተያይዘውታል፡፡ የሃማስ መሪዎችም ከብዙ አመታት ቡሃላ በሳኡዲ አረቢያ በረመዳን ወር በመገኘት ከንጉስ ሰልማን ጋር በጋራ ጉዳያቸው በአካል ተገኝተው በንጉስ ሰልማን ቤተመንግስት ተወያይተዋል፡፡ ይህን ክስተት ለምዕራባውያንም ሆነ ለአይሁዷ እስራኤል የሚወጥ ጉዳይ አልነበረም፡፡የፍልስጤም የነፃነት ትግል በሃብቷ ቀዳሚ በሆነችው ሳኡዲ አረቢያ በይፋ መደገፉ ሳያንስ በገንዘብ እና በማቴሪያል ሃማስ መደገፉ ትልቅ እራስ ምታት እንደሚሆንባቸው ግልፅ ሆኗል፡፡

ንጉስ ሰልማን ወደ ስልጣን ከወጣ ቡኋላ ከተቀዳሚ አላማዎቹ መካከል በአለም ላይ የሚገኙ ሙስሊም ሃገራትን ማሰባሰብ እና አንድ ጠንካራ ሃይል እንዲኖራቸው እና ተመሳሳይ አቋም እንዲይዙ ማድረግ የነበረ ሲሆን በየመን ጉዳይ ላይም ተመሳሳይ አቋም እንዲይዙ በማስቻል በከፊልም ቢሆንም አላማውን አሳክቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙስሊም ሃገራት አንድ አቋም በመያዝ በአንድነት ሃይላቸውን ማሰባሰብ የቻሉት በንጉስ ሰልማን ጊዜ ነው፡፡ ይህን በማድረጉም አለም አቀፍ ዱዓቶች ሳይቀር ሲያወድሱት ቆይተዋል፡፡ ይህን ማድረጉ ለምዕራባውያንም ሆነ ለጸረ ሙስሊም አቋም ላላቸው ሃይሎች ሙስሊሙን ሃገራት በሙስሊም ሃገር እና በሙስሊሞች በመጠቀም በማፈራረስ በተጠመዱበት ሰአት አንድነት ማምጣታቸው እንደስጋት የሚቆጠር በመሆኑ ለንጉስ ሰልማን ጥርስ አስነክሶበታል፡፡

ከንጉስ ሰልማን በፊት በነበሩ ሳኡዲ ንጉሶች በተለይም በንጉስ አብደላ ወቅት በርካታ ኡለሞች እና ዱዓቶች ወደ ወህኒ ተወርውረዋል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዬን የሚቆጠር ተከታታይ ያላቸው ዱዓቶችም ሳይቀር ንጉሳዊያኑ በሙስሊሙ ላይ ለሚፈፅሙጽ ደባ በየጁምአ ኹጥባቸው ሲያወግዙ እና ሲቃወሙ ነበር፡፡ በዚህም ለእንግልት እና ለእስር ሲዳረጉ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ንጉስ ሰልማን ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ንጉስ ሰልማንን ወደ ማወደስ እና ዱዓ ወደ ማድረግ ገብተዋል፡፡ የንጉሳውያኑን አስተዳደር በመቃወም የሚታወቁት አለም አቀፍ ዱዓት ከሆኑት መካከል ሼህ ሰልማን አውዳ፣ሼኽ መሐመድ አረፊ እና ሌሎችም ንጉስ ሰልማን የያዘውን ጠንካራ አቋም በማወደስ ሲደግፉት ተስተውሏል፡፡ በሚሊዬን የሚቆጠር ተከታይ ባላቸው የቲውተር አካውንታቸውም ላይ ሳይቀር ለንጉስ ሰልማን በግጥም ሲያሞግሱት እና ዱዓ ሲያደርጉለት ነበር፡፡በየመን ሺአዎች ላይ እየወሰደው ባለው እርምጃ ሁሉም በአንድ ድምፅ ደግፈውታል፡፡ በየመስጂድ ኹጥባቸው ደግፈው አሞግሰውታል፡፡ ንጉስ ሰልማን በእስር ላይ የነበሩ ዱኣቶችንም በመፍታት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ለዲን ቀናኤነት ማሳየቱ ግን ለምዕራባውያን እና በሙስሊሙ ደም ነግሰው መኖር ለሚፈለጉት የምዕራባውያን ጀሌ አሚሮች የሚዋጥ አልሆነላቸውም፡፡

በተመሳሳይም ንጉስ ሰልማን እንዲዘጋጅ ባደረገው ታላቅ ኢስላማዊ ጉባኤ ላይ በተባበሩት አረብ ኢምሬት የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አንዱ ክንፍ ነው በሚል በአሸባሪነት የተፈረጀው እና በዶ/ር ዩሱፍ አልቃርዳዊ የሚመራው የአለም ኡለማዎች ህብረትም በንጉስ ሰልማን ከተጋበዙት መካከል አንዱ ሲሆን የአለም ኡለማዎች ህብረትም የንጉስ ሰልማን ጥሪውን አክብረው የህብረቱን ዋና ጸሃፊያቸውን ፕሮፌሰር አሊ ሙህዲንን በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ ወደ ሳኡዲ አረቢያ በመላክ እንዲሳተፉ አድረገዋል፡፡ ይህ ማድረጉ ከኳታር ውጪ ያሉ የገልፍ ሃገሮችን የሚያስደስት አልነበረም፡፡

ንጉስ ሰልማን የስልጣን ተተኪውን ሲመርጥም ከወንድሙ ልጅ መሃመድ ቢን ናይፍ ቀጥሎ የሰልማንን አቋም በሚገባ ያራምዳል ብሎ የሚያምንበትን የመጀመሪያውን በሳኡዲ ታሪክ የ34 አመቱን ወጣት ልጁን ተተኪ አልጋ ወራሽ ማድረጉ ለንጉሳውያን ቤተሰቦች ብዙም አላስደሰታቸውም፡፡

ለዚህም ይመስላል ንጉስ ሰልማን ወደ ስልጣን ከወጣ 1 አመት ባልሞላ ጉዜ ውስጥ ሳኡዲ አረቢያ እያሳየች የሚገኘውን የአቋም ለውጥ ያላስደሰታቸው ምዕራባውያን እና ጀሌዎቻቸውን ሴራ እየጠነሰሱባቸው መሆኑ እየተሰማ ያለው፡፡

ከሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ እና ከሃማስ ጋር ሳኡዲ አረቢያ የነበራት የጠላትንን እይታ በንጉስ ሰልማን ዘመን በመቀየሩ ብዙሃኑን አላስደሰተም፡፡ በተለይም ከኳታር ውጪ ያሉ የገልፍ ሃገራት እና ምእራባውያን እንዲሁም እስራኤልን እያስደሰተ አይደለም፡፡

በዚህም የተነሳ የአረቡ አለም መሪ በመሆን የምትታወቀውን ሳኡዲ አረቢያ መሪዋን ንጉስ ሰልማንን ማሶገድ ወይም በኢኮኖሚ እና ተቀባይነቷን ማድቀቅ ምእራባውያን አማራጭ አድረገው ሳይወስዱት አይቀርም፡፡

ይህንንም ተፈፃሚ ለማድረግ በግብፁ ፕሬዝደንት በነበረው ሙርሲ ላይ ሲፈፅሙት የነበረውን ውስጣዊ ደባ እየፈፀሙ ይመስላል፡፡ ለዚህ ማሳያ

1. ንጉስ ሰልማን ስልጣን ላይ ከወጣ ወዲህ የነዳጅ ዋጋ እጅግ አሽቆልቁሏል፡፡ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በመውደቁ የሳኡዲ አረቢያ ገቢ እጅጉኑ ቀንሷል፡፡ አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በፊት ከሚሸጥበት ዋጋ በግማሽ በታች እንዲወርድ ተደርጓል፡፡

2. የሳኡዲ አረቢያ እና የገልፍ ሃገሮች የነዳጅ ዋጋ መውደቁን ተከትሎ ገቢያቸው ከቀዘቀዘ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ በኢራቅ እና በሶርያ ከፍተኛ ግዛቶችን እየተቆጣጠረ የሚገኘውን የ ISIS ሃይል ለመደምሰስ በሚል አሜሪካ የገልፍ ሃገሮችን በመስተባር በኢራቅ እና በሶሪያ ጦርነት ውስጥ እንዲሳተፉ አድረጋቸዋለች፡፡ በቀን ውስጥ በሚሊዬን የሚቆጠር ዶላር የአረብ ሃገራቱ ለአየር ድብደባ እየከሰከሱ ይገኛሉ፡፡

3. ሳኡዲ እና የገልፍ ሃገራት በኢራቅ እና በሶሪያ ጦርነት ውስጥ እንዲገቡ በተደረገበት ወቅትም ከሳኡዲ አረቢያ ጎረቤት በሆነችው የመን በኢራን የሚደገፉት አናሳዎቹ የሁሲ አማፂያን የሱኒ መንግስት የሆነውን የሃዲ መንግስትን በመገልበጥ ዋና ከተማዋን ሰንዓን በመቆጣጠር ለሳኡዲ አረቢያ ከፍተኛ አደጋ እንዲደቅኑ ምክንያት ሆነዋል፡፡ በዚህም ሳኡዲ አረቢያ አረብ ሃገራትን አስተባብራ ጦርነት ውስጥ እንድትገባ ተደረጓል፡፡እስካሁን በየመን ጦርነት ሳኡዲ አረቢያ በቢሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ እያደረገች ሲሆነ በአለም አቀፍ ባንኮች ስር ተቀማጭ አድርጋው ከነበረ ካፒታሏም ላይ የሃገሪቱን ወጪን ለመሸፈን ከ 70% በላይ ከባንኮቹ ወጪ አድረጋለች፡፡ በዚህም ሳኡዲ አረቢያ በጦርነት ውስጥ በመግባቷ በኢኮኖሚዋ እንድትደቅ እየተደረገ ነው፡፡በኢኮኖሚ እየደቀቀች መገኘቷ የንጉሳዊያን ቤተሰቦችንም ሆነ በነሱ ስር ያሉ ምዕራባውያን ጀሌዎች በንጉስ ሰልማን ላይ እንዲነሳሱ እያገዛቸው ነው፡፡

4. የገልፍ ሃገሮች በጦርነት ውስጥ እንዲገቡ ተደርጎ፣ የነዳጅ ዋጋ ቀዝቅዞ ባለበት ሁኔታ ከኢራን ጋር ምዕራባውያን የነበራቸው የኒኩሌር እሰጣ ገባ ቆሞ ስምምነት ተደርሶ በኢራን ላይ ተጥሎ የነበረው ኢኮኖሚ ማዕቀብ ተነስቶላታል፡፡ በዚህም ኢራን እየተሽመደመደ የነበረውን ኢኮኖሚዋን በአጭር ጊዜ ውስጥ እየገነባች ትገኛለች፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ላይም የነበረት ሚና እና የበላይነትም እየጨመረ እንዲሄድ በምዕራባውያን ስልታዊ በሆነ ሁኔታ እየተደረገ ነው፡፡ይህም በአረቡ አለም መሪ በነበረችው በሳኡዲ አረቢያ መዳከም ምክንያት በመሆኑ የገልፍ ሃገራትም በንጉስ ሰልማን ላይ ያላቸው ቅራኔ እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

5. በሳኡዲ አረቢያ የውሃ እና የመብራት መቆራረጥ በፊት ብዙም ያልነበረ ቢሆንም አዲስ በሆነ ሁኔታ እየተከሰተ መሆኑ የሳኡዲን ህዝብ እያነጋገረ ነው

6. በሃጅ ወቅትም በመካ ለግንባታ ቆሞ የነበረ ግዙፍ ክሬን ወድቆ የ 111 ሃጃጆች ሂወት መቅጠፉ የአለም ሙስሊሞችን ያሳዘነ ክስተት ነበር፡፡ ይህ አሳዛኝ ክስተት ተሰምቶ ሳያባራ በመካ ከተማ ሃጃጆች ካረፉበት ሆቴሎች መካከል እሳት ቃጠሎ ተነስቶ በሁጃጆች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ አሁንም በተከሰተው አደጋ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ሙሰሊም ማህበረሰብ ከድንጋጤው ሳያባራ በሃጅ ወቅት በሚና ከተማ ጭንቅንቅ ተፈጥሮ ከ 769-1100 የሚደርሱ ሁጃጆች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተሰማ፡፡ ይህ አደጋ ከረጅም አመት ቡሃላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃጃጅ ሲሞት የመጀመሪያ በመሆኑ ጉዳዩን አገነነው፡፡ በርካቶች በሳኡዲ አረቢያ ላይ ቅሬታቸውን እንዲያቀርቡ ምክንያት ሆነ፡፡ ይህ አሳዛኝ አደጋ በአላህ ውሳኔ ከተከሰተም ቡኋላ ሌላ አደጋ መከሰቱን አላቆመም፡፡ በሚና በሃጃጆች ጊዜያዊ ማደሪያ ላይ የግብፃውያን ካረፉበት ማረፊያ እሳት አደጋ ተነስቶ ሃጃጆች ላይ ጉዳት ባያደርስም እሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ተቆጣጥረውታል፡፡ የአለም ሙስሊሞችን ትኩረት በሚስበው የሃጅ ስነስርአት ላይ የዚህ መሰሉ ተደጋጋሚ አደጋ መድረስ እንዲሁም እስካሁን ድረስ በደረሰው አደጋ ሃጃጆች የደረሱበት መጥፋቱ ሙስሊሙን ማህበረሰብ አሳዝኗል፡፡

ይህ ሁሉ ተደራራቢ ችግር በንጉስ ሰልማን ላይ መፈንቅል ለማድረግ ያሰቡት ሃይሎች ያቀነባበሩት ስለመሆኑ እንድንጠረጥር ምክንያት ሆኗል፡፡ እነዚህ ሃይሎች የሙስሊሙን አለም እርስ በእርስ በማፋጀት የጦር አውድማ በማድረግ እነሱ ከዳር ቆመው እሳት እየሞቁ ይገኛሉ፡፡ ምዕራባውያን አንዱን የሙስሊም ሃገር በሌላኛው ላይ በማነሳሳት ለስልጣናቻው ስጋት እንደሚሆንባቸው በማሳመን እርስ በእርስ ሴራ እንዲጠነስሱ እና እንዲፋጁ እያደረጓቸው ይገኛል፡፡

ከላይ በሳኡዲ አረበያ እየሆነ ያለው ችግር በግብፅም በፕሬዝደን ሙርሲ ላይ በተመሳሳይ መሰል ሴራዎች ሲጠነሰሱ ቆይተዋል፡፡ ህዝቡ በሙርሲ ላይ እንዲማረር የማብራት እና የውሃ መቆራረጥ፣የዋጋ ንረት፣ከኑሮ ሁኔታ እየዘቀጠ መምጣት፣በአብዬቱ ምክንያት የደቀቀው የግብፅ ኢኮኖሚ እንዳይንሰራራ በማድረግ ህዝቡ በሙርሲ ላይ እንዲያምፅ በማድረግ በወታደራዊ መፈንቅለ ስልጣን እንዲወገድ አድረገዋል፡፡ ይህን ሴራም ከምዕራባዊያን ጋር በመሆን በቀዳሚነት ንጉስ አብደላህ ይመራት የነበረችው ሳኡዲ አረቢያ እና የገልፍ ሃገሮች ዋነኞቹ ነበሩ፡፡

አሁንም በተመሳሳይ ንጉስ ሰልማንን ለሙስሊሙ አለም ከሌሎቹ በተሻለ ሁኔታ ስልጣን ላይ ከወጣ አንድ አመት ባይሞላውም የተወሰኑ የአቋም ለውጦችን በማሳየቱ ምዕራባውያን እና የምእራባውያን ጀሌሎች እሱን ከስልጣን በማሶገድ ልክ እንደ ቀድሞ ሳኡዲ ንጉሶች የምእራባውያን ባሪያ የሆነ መሪ ለማምጣት እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡

በመጨረሻም ስለንጉስ ሰልማን የተወሰነ ለማለት ያህል ንጉስ ሰልማን በሳኡዲ አረቢያ ካለፉት 85 አመታት ታሪክ ውስጥ የሃጃጆችን ሁኔታ እና መስተንግዶ እራሱ ህዝቡ ጋር ታች ወርዶ የተከታተለ የመጀመሪያው የሳኡዲ ንጉስ ሲሆን በመስጂደል ሀራም ክሬን ወድቆ አደጋ በተከሰተ ወቅትም የተጎዱትን በየሆስፒታሉ በመሄድ ሁሉም ክፍል እየዞረ የተጎዱትን በመጨበጥ ዱዓ ሲያደርግላቸው ነበር፡፡ በአደጋው ጥፋተኛ የተበለው የቢላዲን ግሩፕ ቢሆንም “የአላህ እንግዶች እኔ በማስተዳድረው ሃገር መጥተው በመሞታቸው እና በመጎዳታቸው አዝኛለው” በማለት ለሞቱት እና አካል ጉዳተኛ በአደጋው ለሆኑት ለእያንዳዳቸው የ 1ሚሊዬን ሪያል ካሳ እንዲሁም በአደጋው ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው ደግሞ የ 500.000 ሪያል ካሳ ከፍሏቸዋል፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃም በአደጋው ሂወታቸውን ላጡት በሚቀጥለው አመት ከቤተሰባቸው አባላት መካከል 2 ሰዎች የንጉሱ እንግዳ ሆነው በንጉስ ሰልማን ወጪ ሃጅ እንዲያደርጉ ወስኖላቸዋል፡፡

ንጉስ ሰልማን በተለያዩ ስብሰባዎች እና አጋጣሚዎች አሚሮቹ ሰላም ሲሉት በክብር ተናንሰው እጁን ሊስሙት ሲሞክሩ በፍፁም እንዳይስሙት እጁን ይነጥቃቸው ነበር፡፡ እራሱን ያስተናነሰ ንጉስ ነው፡፡ ስልጣኑን ከተረከ በኋላ ለሳኡዲ ህዝብም ባስተላለፈው መልዕክት “ማንም ሰው በፍትህ ስርአቱ መበደል እንደሌለበት፣ የተበደለ አካልም ካለም ቀጥታ እኔ ሰልማን ጋር መጥቶ መክሰስ ይችላል” በማለት መናገሩ ብዙሃኑን አስገርሞ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይህ ንግግሩ ሽፋን አግኝቶ ነበር፡፡

ሳኡዲ አረቢያን በመፈንቅለ ስልጣን ሰበብ በማተራመስ እንደጎረቤት ሀጋሮች ሰላሟን በማደፍረስ የጦር አውድማ ለማድረግ እየተደገሰ የሚገኘውን ሰይጣናዊ ሴራ አላህ እንዲያከሽባቸው ዱዓ ልናደርግ ይገባል፡፡ ከማንም እና ከምንም በላይ የሁለቱ ቅዱስ መስጂዶች መናሀሪያ የሆነችው ሳኡዲ አረቢያ ሰላም ያሳስበናል፡፡ በግብፅ የተፈጠረው አይነት እልቂት በሳኡዲ አረቢያም እንዲከሰት አንሻም፡፡

ንጉስ ሰልማን በትክክል እና በሃቅ ኡማውን የሚያገልግል ሙስሊም መሪ ያድርገው፡፡

ያሰቡበትን ሴራ እና ተንኮልም አላህ ያክሽፍባቸው፡፡

አሚን

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: