The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

አዲሱ በረከት – ጌታቸው ረዳ

Getachew Reda
በሱፍቃድ ደረጄ

ብቻ የዚህች አገር ጉዳይ እጅግ ተሰፋ አስቆራጭ ከሆነ ውሎ አድሯል፤ አንድ ፓርቲ እጅግ በአገር መቀለድ ከጀመረ ያለ ጥርጥር የዚያ ፓርቲ ግበአተ መሬት እየተፋጠነ እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል፤ የቀና በሞላበት አገር ጎባጣ ሲመለመል ብሎም ለሹመት ሲታጭ መመልከት እንደ ሀገር ያሳዝናል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእለተ ማክሰኞ ካቢኒያቸውን አቅርበው ጸድቋል፤ እንደተጠበቀውም ለይስሙላ ስብጥር ያለው ቢመስልም የበላይነቱን እነ እንትና ወስደውታል፤

ከሁሉ ከሁሉ እጅግ ግርም ያለኝ የአቶ ጌታቸው ረዳ አቶ ሬድዋንን መተካት ነው፤ በርግጥ የቀድሞ የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር የነበሩት ደራሲ ኤርምያስ ለገሰ በዚህ ጉዳይ አስቀድመው አቶ ሬድዋን ተግባር በጌታቸው ረዳ እንደተያዘ ተናግረው ነበር፤ አሁን ደግሞ በይፋ የመንግስት አቋም ተናጋሪ ሚንስትር ሆነዋል፤ በርግጥ በዘመነ ኢህአዴግ አንድ ሰው በችሎታውና በችሎታው ሹመት እንደማይሰጠው አገር ያወቀው ሀቅ ነው፤ ቢሆንም ቢሆንም በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸውን፣ አማካይ የሆነ የስነ ምግባር ሬከርድ የሌላቸውን ሰዎች ማማው ላይ በማውጣት ሚኒስቴር ማድረግ አገር ላይ ማላገጥ እንደሚሆን አገረ ገዢዎቻችን ሳያጡት ባይቀሩም ሆነ ብለው ማድረጋቸውና ከህዝብ ጋር እልህ መጋባታቸው አሳዛኝ ነው፤

ጌታቸው ረዳ እስከ ዛሬ የተጓዘበትን መንገድ በአንክሮ ለተከታተለ ሰውየው እንኳን ሚኒስቴር ሊሆን ይቅርና የአንድ ቤተሰብ አስተዳዳሪ ለመሆን የማይችል አቅምና ብቃት፣ ስነ ምግባር የሚጎድለው ግለሰብ ነው፤ ስራውን ሀ ብሎ በጀመረበት መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሚታወቅባቸው ባህሪያት መለገም፣ ከልክ በላይ መጠጥ መጎንጨት፣ በተከታታይ ከማስተማር ስራው መቅረት፣

ከአንድ መምህር የማይጠበቅ አስነዋሪ ቃላትን በእንግሊዝኛም በፈረንጅ አፍም መናገር፣ ስብሰባ ላይ ከተተቸ ተሳድቦ ስብሰባውን ማቋረጥ፣ ለአለቆቹ ተገቢውን ክብር መንፈግ፣ ባጠቃላይ ጊዜውን የሚያሳልፈው በእንቶ ፈንቶና በቧልት እንደነበረ የጊቢው ማህበረሰብ የሚያውቀው ነው፤ በመጨረሻም እነዚህ አስነዋሪ ድርጊቶቹ ሞልተው ስለፈሰሱ ከግቢው ሊባረር ችሏል፤

በመቀጠልም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚዘጋጅ አንድ ጋዜጣ መሳይ ነገር ባልደረባ ሆነ፤ ጥቅት ቆይቶም የአዲስ ነገር ጋዜጣ ተከፈተች የጋዜጣው አምደኛ ሆኖ ብቅ አለ፤ የሚጽፋቸው መጣጥፎች ግን የበለጠ ገልቱነቱን የሚያሳዩ የነጻነት ታጋዮችን ክብርና መስዋእትነት ዋጋ የሚያሳጣ ነበር፤ እነ ቴዲ አፍሮና ብርቱካን ሚደቅሳ የመሳሰሉትን እንቁዎቻችንን በግልጽ ቋንቋ በመሳደብ ሚሊየኖች ያከበራቸውን በርሱ ጉልድፍድፍ ብእር ይዋረዱ ይመስል በየሳምንቱ የስድብ ናዳ ሲያወርድባቸው ነበር፤ ከዚህ ባለፈም በወቅቱ ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን መድረክ የተሰኘውን የታዋቂ ግለሰቦችና ፓርቲዎች ስብስብ ሲኮረኩም ሲያጣጥል በግለሰብ ደረጃም በውስጡ የተጠለሉትን ፓለቲከኞችን በመዝለፍ የወያኔ አፍ ሆኖ አገልግሏል፤ ይህ ቢሆንም ቅሉ ልዩ ምልክቱ በሆነው ስንፍና ምክንያት አምደኝነቱን ለተከታታይ ጊዜ ያቋርጥና ከትናንቱ የቀጠለ ስድብ ይዞ ብቅ ይል ነበር፤ ያለማጋነን እርሱ በዚህ ሳምንት ከጻፈ ሁለት ሶስት ሳምንታት በተከታታይ የርሱን ግራ የሆነ ጽሁፍ የሚቃወሙ ቀለሞችን ጋዜጣው ለማስተናድ ይገደድ ነበር፤ ስንፍና፣ስካር፣ልግመኝነት፣ ገንዘቡ የሆነ ሰውየ ሚኒስቴር ሆነ ብትሉን መስሚያ የለንም፤
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: