The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ሩሲያ በISIS ላይ በወሰደችው እርምጃ በአውሮፓ እና በአፍሪካ ያመጣው አንድምታ በጨረፍታ

ከተማ ዋቅጅራ

ከተማ ዋቅጅራ

ISIS የሚለው ስያሜ ይዘው ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በመጀመሪያ የአለም አሸባሪ ሆኖ  ይታወቅ የነበረው በኦሳማ ቢላደን የሚመራው አልቃይዳ ነበር።አልቃይዳ ከ2000 አመት ጀምሮ በአለም መንግስታት በአሸባሪነት ተፈርጆ በአሜሪካ መራሹ ኃይል ይታደን ጀመረ። የሚገርመው እና ውስብስብ የሚያረገው ጉዳይ ግን ኦሳማ ቢላደን በሲአኤ የስለላ ቡድን ውስጥ በአሜሪካን ወታደራዊ ትምህርትም  ድብቁን የስለላ ስልቶችን  የሰለጠነ መሆኑ ይነገራል። አሜሪካኖች ይጠቅመናል ብለው ወታደራዊ የስለላ ስልጠናዎችን ቢያሰለጥኑትም ቅሉ ተመልሶ ለአሜሪካኖች ስጋት በመሆኑ በመቀጠል 2001 የአሜሪካ መንትዬ ህንጻዎች ላይ ጥቃት የፈጸመው አልቃይዳ እንደሆነ እና በኦሳማ ቢላደን የተቀነባበረ እንደሆነ የአሜሪካ መረጃ ኃይሎች ይጠቁማሉ በዚህም የተነሳ ለአሜሪካን ስጋት እንዲሁም የአለም ስጋት በመሆኑ  ቢላደንን የሚጠቁም ወይም ይዞ አሳልፎ  የሚሰጣት ከፍተኛ ዶላሮችን እንደምትከፍል በማሳወቅ እና የራሷን ወታደራዊ ሃይሎቿን በደ አረብ አገራት በመላክ አሰሳዎችን የተደረገበት በወቅቱ የአልቃይዳ መሪ የሆነ ነበረ። 2011 ላይ ፓኪስታን ውስጥ ተገደለ ተብሎ እስከሚነገርበት ግዜ ድረስ የአለማችን አነጋጋሪው ሰውና ትላልቅ የሚዲያ ሽፋን ያገኘ ሆኖ ቀጥሎ ነበረ ከ20011 በኃላ የመገደሉ ዜና ከተነገረ በኃላ የአልቃይዳ አቅጣጫ ወደ ሌላ ስልት ዞሯል። በአንድ አንድ የዜና አውታሮች የቢላደን አለመሞት ቢነገርም በፊት የሚሰጠውን ትኩረት ማግኘት አልቻለም። በአሁኑ ሰአት ስሙን ከአልቃይዳ ወደ ISIS (Islamic State of Iraq and Syria) ከዛም ISIL (Islamic State of Iraq and the Levant) በማደግ አድማሱን እያሰፋ ያለውን አሸባሪ ኃይል ነው። በዚህም እንደ አቡበከር አልባግዳዲን የመሰሉ ጨካኝ መሪዎችን ፈጥሯል።

ISIS/ISIL ማን ነው?

ISIS/ISIL ማን ነው ለሚለው በአረብ አገራት የሚንቀሳቀስ የሰውን ዘር በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የአለምን ትኩረት ለማግኘት ዘግናኝ ቪዲዮችን በመልቀቅ እራሱን የሚያስተዋውቅ የአለማችን አሸባሪ ቡድን ነው።

ISIS ማለት ሴቶችን በማፈን የዝሙት ባሪያ አድርጎ የሚያሰቃይ አፋኝ ቡድን ነው።

ISIS/ISIL ማለት ህጻናትን ለጥፋት ተግባሩ በማሰልጠን የህጻናትን አእምሮ የሚመርዝ መርዘኛ ቡድን ነው።

ISIS/ISIL ማለት ክርስቲያኖችን፣ እስላሞችን፣ እንዲሁም ሌሎች የእምነት ክፍሎችን ያለርህራሄ በዘግናኝ ሁኔታ ያለምንም በደላቸው የዚህ ጨካኝ ቡድን አላማ አልተቀበላችሁም ወይም ተከታይ አልሆናችሁም በማለት ሰይጣናዊ ስራን የሚያራምድ ቡድን ነው።

ISIS/ISIL ማለት የእስልምናን ስም ይዞ  የሚንቀሳቀስ ተከታዮቹም እንደሱ ጽንፈኛ ሆነው እንዲጓዙ የሚመኝ  እና አላማውን የሚከተሉ ብቻ በግዛቱ እንዲኖር የሚፈልግ ጨካኝ እና ዘግናኝ ድርጊቶችን የሚከውን ቡድን ነው።

ታዲያ እንደዚ የሰይጣን ስራን የሚያራምድ እና በግፍ በንጹኃን የሰው ደም የታጠበ ISIS በሚንቀሳቀስበት አካባቢ ሁላ ሰዎች በሰላም መኖር እንዳይችሉ የሚከለክል ከማንም ህብረተሰብ ጋር የማይስማማ አረመኔአዊ ክንውኖችን የሚከውን ሆኖ ሳለ ለምን በአጭር ማጥፋት አልተቻለም? አሜሪካን እና አውሮፓን የሚያክሉ አገራትን በጦርነት ስልቱ በልጦአቸው ነውን? ወይስ በታጠቀው መሳሪያ  ገዝፎባቸው?  ለሚለው ጥያቄ መልሱ አይደለም ነው። ታዲያ ካልሆነ ለምን ማጥፋት አልቻሉም ለሚለው በሌላ ግዜ እመለስበታለው አሁን ግን በርእሴ ወዳነሳሁት ነጥቤ ልመለስ።

ISIS/ISIL በአሁኑ ሰዓት በሩሲያው መራሹ ኃይል በከባድ ሁኔታ እየተደበደበ ነው። ሶሪያን ያለምንም እገዛ ሩሲያ ብቻዋን ISISን መድረሻ እያሳጣችው ትገኛለች። አሜሪካ እንዲሁም ኔቶ ISISን ማጥቃቷን ቢቃወሟትም ሩሲያ ግን የነሱን ማስጠንቀቂያ ወደጎን በመተው ጭራሽኑ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በሶሪያ አየር ክልል ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ ጭምር በመስጠት ISISን የማጥፋቱን ስራ ተያይዘዋለች። የISISን የጦር ካንፖችን፣ የመሳሪያ ማከማቻዎችን፣ ድብቅ ምሽጎችን፣ ከአየር በምታዘንበው ቦንቦች እንዳልነበሩ ሆነዋል። ሰው አይደርስበትም ምሽጋችንም አይደፈርም ብለው በመንቀሳቀስ ሶሪያን እና አካባቢዋን ሲያውኩ የነበሩት የሽብር ቡድን የሩሲያ ጦር ኃይል ከተደበቁበት ቆፍሮ አውጥቶ  ወደ ሰማይ በሚበትነው ቦንቦቿ በተነቻቸው። ታዲያ ይሄ የሩሲያ ጥቃት ለሶሪያ ፕሬዝዳንት  እና ለሶሪያ ህዝብ እፎይታን የሚያስገኝ ሲሆን ለአውሮፓ እና ለአፍሪካዊያን የሚያመጣውን ጉዳት እና ጥቅሙን በጥቂቱ እንይ።

አውሮፓን ስንመለከት ከፍተኛ ውጥረት እና ስጋት ላይ ናቸው። ምክንያቱም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሶሪያ፣ የኢራቅ እና የአፍጋኒስታን ስደተኞች ወደ አውሮፓ በመሰደድ ላይ ናቸው። በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በስደተኛ እንድትጥለቀለቅ ምክንያት ሆኗል ዋናው ቁም ነገሩ አውሮፓ በስደተኛ መጥለቅለቋ ብቻ ሳይሆን ከተሰዳጆቹ ጋር ጥቂት የማይባሉ የISIS አባላት እና ደጋፊዎች ወደ አውሮፓ መግባታቸው በአውሮፓ ለሚኖረው ዜጋው እና ስደተኛው ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠር የአውሮፓ መንግስታትን እያወያየ ያለ ጉዳይ ነው። በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በአውሮፓ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ከፍተኛ እንደሚሆን አንድ አንድ የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነው። በዚህም የተነሳ አውሮፓዊያኖች ስጋት ውስጥ እንደገቡ ይናገራሉ።

አፍሪካን ስንመለከት በጥቂቱም ቢሆን ሩሲያ በወሰደችው በISIS ላይ የማጥፋት ዘመቻ ተጠቃሚ ናት። ምክንያቱም የሱማሌው አልሸባብ የናይጀሪያው ቦኮሃራ እንዲሁም በሊቢያ፣ በማሊ፣በግብጽ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ መሳሪያዎችን በመስጠት ገንዘቦችን በመርዳት ትልቁን ድጋፍ የሚያገኙት በነዚው ISIS መሪዎች ከሚገኙባት ግንባር ቀደም አገር ውስጥ ነው። የISIS ቡድን መሳሪያና ገንዘብ ከመርዳት በተጨማሪ የሽብር ስራዎችን የሚሰሩበትን ስልጠናዎችንም ይሰጣሉ። ለዚህም ማስረጃ  የአረብ ዜግነት ያላቸው ከሱማሌው አልሸባብ ጋር አብረው የሽብር ተግባርን ሲሰሩና ሲያሰሩ መያዛቸው ነው። ታዲያ ISIS  በሩሲያ ጦር አከሪካሪው  መመታቱ በዙሪያው ተሰብስበው እናብባለን ያሉት ቅርንጫፎች ሁሉ ያደርቃቸዋል የተዘረጉትን መረቦች ይበጣጥሳቸዋል። ሩሲያ ISIS ላይ በምታደርሰው ጥቃት አፍሪካ ውስጥ ከዚህ አሸባሪ ቡድን ጋር በድብቅም በግልጽም ግንኙነት ያላቸውን ቡድኖች  ድንጋጠን ፈጥሯባቸዋል። ሩሲያ መራሽ ኃይሉ የISISን አከርካሪውን ሰብራ ከጣለችው ISISን ተስፋ አድርገው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ቡድኖች ሁሉ በአፍሪካ መድረቅ ይጀምራሉ። ፍጻሜው ግን ገና ነው። ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው ጉዳይ ነው።

ከተማ ዋቅጅራ

10.10.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: