The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ስለ እቴጌ መነን በጨረፍታ (ከስሜነህ ጌታነህ)

ስለ እቴጌ መነን በጨረፍታ
(ከስሜነህ ጌታነህ)

ግርማዊ እቴጌ መነን መጋቢት 25 ቀን 1883 ዓም በወሎ ጠ/ግዛት በአምባሰል አውራጃ ልዩ ስሙ ዕጎ ከተባለው ቀበሌ ከጃንጥራር አስፋውና ከወ/ሮ ስሀን ሚካኤል ተወለዱ። እቴጌ መነን በልጅነት ዘመናቸው በእናት በእባታው ቤት መምህር ተቀጥሮላቸው አማርኛ ማንበብና መፃፍ ጠንቅቀው አወቁ። በተጏዳኝ ልዩ ልዩ የቤት ባልትና ሙያዎችን ተምረው በማጠናቀቃቸው የቤት ራስ ለመባል በቅተዋል፡፡

በ1892 ማለትም በተወለዱ በአሥረኛ አመታቸው ለመጀመሪያ ባለቤታቸው በህግ ተዳሩ፡፡ ከእኝህ ባለቤታቸው ወ/ሮ በላይነሽ ዓሊንና ጃንጥራር አስፋው ዓሊን ወለዱ፡፡ ከዚያም ሁለተኛ ባለቤታቸውን በማግባት ጃንጥራር ገብረእግዚ አብሄር አመዴንና ወ/ሮ ደስታ አመዴን ወልደዋል፡፡ በ1903 ዓም ወደ መጀመሪያ ራስ ልኡልሰገድ አጥናፍሰገድን አገቡ። በዚሁ ዓመት ወደ መጨረሻም ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋር ተጋቡ። የእቴጌ መነን እና የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋብቻ ፓለቲካዊ ሲሆን የአጎታቸ ውን የልጅ ኢያሱንና የቀዳማዊ ኃይለሥላሤን ጠብ ለማስወገድ ይቻላል በሚል መኳንንቱ ሁሉ በተለይም እነራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው መክረው የፈፀሙት ነበር፡፡

እቴጌ መነን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ያፈሯቸው ልጆች ስድስት ሲሆኑ ዝርዝራቸውም የሚከተለው ነው፤ ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሤ፤ልዑል አልጋወራሽ እስፋወሠን ኃይለሥላሴ፤ ልዕልት ዘነበወርቅ ኃይለሥላሤ ልዕልት ፀሃይ ኃይለሥላሤ፤ልዑል መኮንን ኃይለሥላሤ ልዑል መኮንን ኃይለሥላሤ ናልዑል ሣህለሥላሤ ኃይለሥላሤ
ልዑል ሣህለሥላሤ ኃይለሥላሤ እቴጌ መነን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋር በተጋቡ በሃያ ዓመታቸው ማለትም 1923 ዓ፡ም፡ የእቴጌነት ዘውድ ጫኑ፡፡ በእድሜ ዘመና ቸው በግል ገንዘባቸው በኢትዮጵያና በእየሩሳሌም በርካታ ቤተክር ስቲያናትን አሳንፀዋል፡፡ በጎ አድራጎት ድርጅቶችን አቋቁመዋል፡፡

አንዳንዶችን ለመጥቀስ ያህል መጋቢት 16 ቀን 1910 ዓ፡ም፡ የሐመረ- ኖህ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስቲያንን አሰርተው ታቦቷን በክብር አስገብተዋል፡ በ1915 ኢየሩሳሌምና ግብፅን ጎብኝተዋል፤ በ1923 ዓ፡ም በመስከረም ወር እቴጌ መነን ተማሪ ቤትን አቋቋሙ፤ በ1925 ዓ፡ም፡ በፉሪ ቀበሌ የምትገኘውን የቅድስት ሐናን ቤተከር ስቲያን አሠሩ፤

በመስከረም ወር 1926 ዓ፡ም፡ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ ው በዮርዳኖስ ያሰሩትን የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያንን እርሳቸው በተገኙበት አስመረቁ፤ በ1935 ዓ፡ም፡ ለገሀር የሚገኘውን የእጅ ጥበብ ት/ቤት አቋቋሙ፤ በ1939 ዓ፡ም፡ የካቲት ወር ሰበታ ከተማ የምትገኘውን የጌቴሴማኒን ቤተክርስቲያን በገንዘባቸው አሠሩ፤

በ1943 ዓ፡ም ወደግሸን ማርያም ቤተክርስቲያን የሚወጣውን የሰ ርጥ መንገድ አሠሩ፡፡ በዚሁ ዓመት በጠላት ዘመን ፈርሶ የነበረውን የቦሩ ሥላሴን ብር ወጪ አድርገው አሠሩ፡፡ ግርማዊት እቴጌ መነን ኢየሩሳሌምን ለሁለተኛ ጊዜ ለመሳለምና በዮርዳኖስ ያሠሩትን ቤተክር ስቲያን ለመመረቅ አድካሚ ጉዞ አድርገዋል፡፡ ጉዟቸውም ከአዲስ አበባ ጅቡቲ በባቡር፤ ከጅቡቲ ግብፅ በመርከብ፤ ከግብፅ ወደኢየ ሩላሌም በባቡር ነበር፡ አቡነ ቄርሎስም አዲሱን ቤተክርስቲያን ለማየትና ለመባረክ ከግርማዊት እቴጌ ጋር አብረው መጓዛቸው ተዘግቦ ይገኛል፡፡

የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን እንደሚወር ይፋ በሆነበት ጊዜ ግርማዊት እቴጌ መነን መስከረም 1 ፤ ቀን 1928 ዓ፡ም፡ የዘመን መለወጫ ዕለት ለዓለም ሁሉ ሴቶች የትግል ጥሪ አድርገው ነበር፡፡ በንግግራቸውም “በዓለም ያላችሁ ሴቶች ሁሉ በዓለም ላይ እውነተኛ ፍርድና ሰላም እንዲነግስ የመንግሥት ሰዎ ች ሁሉ በሚሠሩት ሥራ በእግዚአብሔር መንፈስ እንዲመሩ በምና ደርገው ፀሎት ተባባሪዎች እንድትሆኑ እንለምናለን” የሚል ነው።

እቴጌ መነን በ1928 ዓ፡ም፡ ግርማዊ ባለቤታቸው ጦር ሜዳ ሄደው ከጠላት ጋራ ስላገራቸው ሲዋጉ በከተማው ያሉ ወይዛዝርትን እ ሰበሰቡ ለቁስለኞች እና ለሠራዊቱ የሚሆን ስንቅ፣ ትጥቅና የህክምና ቁሳቁስ እያዘጋጁ ይልኩ ነበር፡፡ የከተማውም ፀጥታ እንዲጠበቅ ከከተማው የዘበኛ ኃላፊዎች ጋር በመመካከር በትጋትና በብርታት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

በጦር ሜዳ ካሉት ለባለቤታቸው እና በዚያው ከሚገኙ የመረጃ ሰዎች የጣሊያን አውሮፕላኖች በአዲስ አበባ በሚኖረው በሰላማዊ ህዝብ ላይ የቦንብ ጥቃት ለማድረስና ህፃን፣ ሽማግሌና ሴት ሳይለይ በአንድነት ለመደምስስ እየመጡ እንደሆነ በስልክ በተላለፈ ጊዜ ግርማዊት እቴጌ መነን በአውቶቢል ሆነው በድፍረት በከተማው እየዞሩ በየመንገዱና በየገበያው ያለው ህዝብ በአንድነት እጅብ ብሎ መቆሙን ትቶ እንዲበተንና አደጋውን ወደሚከላከልበት ቦታ እንዲደበቅ በማድረጋቸው ብዙ ህዝብ ሊድን ችሏል፡፡

እቴጌ መነን በፓለቲካዊ አስተሳሰብ የተነሳ የእና ታቸው የወሮ ስህን ወገኖች በተለይም አያታቸው ንጉሥ ሚካኤልና አጎታቸው ልጅ ኢያሱ ከባለቤታቸው ከቀዳማዊ ኃይለሥላ ሴ ጋር በፈጠሩት ፓለቲካዊ ቅራኔ ሰበብ በተካሄደው የሰገሌ ጦርነት ከግራ ከቀኝ ተሰልፈው የተዋጉ ወገኖቻቸው ያለቁባቸው ቢሆ ንም በየጊዜው ሁለቱንም ወገኖች እያስማሙ በአንድነት እንዲኖሩ አስችለዋል፡፡ ይህንን የእቴጌ መነን አስፋውን ብርታት በማስታወስ አርብ የካቲት 9 ቀን 1954

የአፄ ኃይለሥላሴ ታሪክ በተባለውና በሌሎችም መፅሃፍት እንደተረጋገጠው እቴጌ መነን አስፋው የአፄ ፋሲል ተወ ላጅ ናቸው፡፡ በዚሁ መፅሃፍ እንደተብራራው ከአፄ ፋሲል ጄምሮ የዘር ሃረጋቸው ሲመዘዝ አያታቸው ንጉሥ ሚካኤል ስምንተኛ ትው ልድ ናቸው፡፡ እናታቸው ወ/ሮ ስሀን ዘጠነኛ እራሣቸው ግር ማዊት እቴጌ መነን አስፋው ደግሞ እስረኛ ትውልድ ናቸው፡፡ በአፄ ፋሲል በኩል እቴጌ መነን እስፋውና ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዝምድና እላቸወ፡፡ዝምድናቸው ግን ጋብቻ የማይከለክል ሲሆን አሥራ ሁለተኛ ትውልዳቸው ላይ የሚገጥም መሆኑን የታሪክ መፅ ሃፍት ያረጋግጣለ፡፡

ግርማዊት እቴጌ መነን አስፋው የካቲት 9 ቀን 1954 ዓ፡ም፡ በተቀበሩበት ዕለት ከተሰሙት የሃዘን እንጉርጉሮ ዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፡፡
የመኮንን እናት ምነው ምን ነካዎ፣
ብቸኛ ጓዶዎን ጥለው መሄድዎ፡፡
እረ ምን ይወራል ምን ትንፋሽ አላና፣
መነን ስታቋርጥ የሞትን ጉዳና፡፡
መኮንን ገሥግሦ ሥላሴ መግባቱ፣
ቤት ሊሠራ ኖሯል ለወላጅ እናቱ።

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: