The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

አቶ ሬድዋን ሁሴን ከመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትርነት በመነሳታቸው በጣም ደስ ብሎኛል (በኤልያስ ገብሩ)

Redwanad reda

አቶ ሬድዋን ሁሴን ከመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትርነት በመነሳታቸው በጣም ደስ ብሎኛል፤ ተግባሩን ለተከታታለ፣ ለዚህ ትልቅ ቦታ የሚመጥን ሰው አልነበረምና፡፡ ሬድዋን ሥልጣኑን የብሽዘሽቅ ፖለቲካ ማራመጃ አድርጎት ነበር – ያውም በወሳኝ ህዝባዊ ጉዳዮች ላይ!!! አሸባሪው ISIS ውድ የሀገር ልጆችን አንገት በአደባባይ ሲቀላና አናታቸውን በጥይት ብሎ ሲደፋ፤ ‹‹ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ገና አልተረጋጋጠም›› ብሎ በዜና ያስነገረ ሰው ነበር ሬድዋን! በህወሃቶች በል ተብሎና ታዝዞም ቢሆን እንኳ፣ ‹‹እምቢ›› የማለት ወኔው የለውም ማለት ነው፡፡ ሬድዋን በሚሰጣቸው መግለጫዎቹ፣ በ‹‹ምርጫ ክርክር›› ወቅትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚጣረስ ነገር ሲገልጽ እንደነበረ በስፋት ዘርዝሮ መግለጽ ቢቻልም ወቅቱ አይደለምና ልለፈው፡፡ የሬድዋንን ቦታ የተካው አቶ ጌታቸው ረዳም ቢሆን በአደባባይ ሲዋሽ እናውቀዋለን፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በበየመን የፀጥታ ሀይሎች ተይዞ ለኢትዮጵያ መንግሥት መሰጠቱን ተከትሎ ከሀገር ውጪ ከሚገኝ አንድ የሚዲያ ተቋም ጉዳዩን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ መረጃው እንደሌለውና ጉዳዩንም እንደማንኛውም ሰው በማኅበራዊ ድረ-ገጽ መስማቱን ነበር በወቅቱ የገለጸው፡፡

በሌሎች ጉዳዮች ላይም፣ የተለያዩ ዓለምአቀፍ ስብሰባዎች ሲኖሩ፣ አውሮፕላን ውስጥ ቆጭ ብሎ ከውስጡ ጋር በግልጽ ያልተዋሃደ መልስ ለአገዛዙ ጋዜጠኞች ሲሰጥ በግሌ አስተውያለሁ፡፡ በባለፈው ዓመት ‹‹የምርጫ ክርክር›› ወቅትም ከዶ/ር ቴዎድሮስ ጎን ሆኖ፣ ለተቃዋሚዎች ብሽሽቅ የሚመስል መልስ ሲሰጥ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ …ብቻ በግሌ፣ አቶ ጌታቸው ለምቾቱ ቅድሚያ የሚሰጡ አይነት ሰው አድርጌ ነው የተረዳሁት፡፡ ቦታው ደግሞ ምቾት የሚቀድምበት አለመሆኑን እነበረከት ስምኦን ጠፍቷቸው አይሆንም፤ ‹‹የብሽሽቅ ፖለቲካውን ያስቀጥለው›› ካላሉ በስተቀር!!! እውነት እንነጋገር ከተባለ፣ ፖለቲካ ማናደድ እና ብሽሽቅ – ተኮር ከሆነ መዘዙ ከማንም በላይ ለባለቤቱ ነው፡፡

ጊዜያዊ ስልጣንን ምርኩዝ በማድረግ በማንአለብኝነት ዜጎችን በንግግር ማናደድ እና ተቀናቃኝ የፖለቲካ ሃይላትን ማብሸቅ ለቀድሞ ሟች ጠቅላይም አልበጀም፡፡ …ለማንኛውም ሬድዋንም ሄደ ጌታቸው ተተካ ለህሊና፣ ለእውነትና ለመርህ መኖር፣ ብሎም ሕዝብን ማገልገል እስካልተጀመረ ድረስ አዲስ ሚኒስትር እንጂ ለውጥ አይመጣም!!! ዳሩ፣ በሀሰት ውስጥ ሀሰት ሆነው ለቆሙት እነ‹‹መገርቱ ረጋሳ››ም በአደባባይ መግለጫ የሚሰጡበት ቀን ወጣላቸው እንበል እንዴ? (ረዥም ሳቅ ጨምሬበታለሁ) … ከሳቁ ስመለስ፣ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚቀልድባት ሳይሆን ለእውነት የሚሰራላት ሰው ነው የምትሻው!!! መቀለዱ እና ቀልድን መለማመዱ ቆዩ ከበቁን!!!.

satenaw

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a comment