The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ወያኔ አዜብ የወልቃይት ተወላጅ በመሆንዋ እርስዋን ተጠቅሞ የህዝቡን ያለመደፍጠጥ ጥያቄ ለማዳፈን ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀረ

Tigray-after-1991- satenaw News

መላው የአማራ በሙሉ ከወልቃይት ህዝብ ጎን እንድትቆሙ ሲል የወልቃይት አማራዊ ማንነት አራማጅ ኮሚቴ አሳሳበ፡፡ የኮሚቴውን የቪድዮ ምስል ተከታትየዋለሁ፡፡ ለአማራ ክልል መንግስት የቀረበውንም ደብዳቤ ሙሉ ቃል አንብቤ የሚከተለውን ለዛሬ አቅርቤዋለሁ፡፡ ወያኔ ባለፈው ሳምንት ከኮሚቴው ጋር ያደረገው ስብሰባ ያለፍሬ በመጠናቀቁ የመጨረሻ አማራጭ የሆነውን እርምጃ እንደወሰደም የተረጋገጠ መረጃ ደርሶኛል፡፡ እርሱም አዙብ ጎላ መስፍንን ወደጎንደር ልኮ ለአንድ ሳምንት የማሸማገል ሙከራ ስታደርግ ቆይታ የወያኔ ጥረት ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል፡፡ ወያኔ አዜብ የወልቃይት ተወላጅ በመሆንዋ እርስዋን ተጠቅሞ የህዝቡን ያለመደፍጠጥ ጥያቄ ለማዳፈን ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄም ለወያኔ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡
የኮሚቴው ደብዳቤ በከፊል

ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር
ባህርዳር

 

ጉዳዩ ፡- የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ይመለከታል
ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው ፡-

1. ወልቃይት ከ1983 ዓ.ም በፊት በጎንደር ክፍለ ሃገር በወገራ አውራጃ ዳባት ዋና ከተማ ሆኖ ራሱን የቻለ ወረዳ አሰተደዳር የነበረ ሲሆን ይህ አከባቢ በወቅቱ አስተዳደራዊ ክልል በምዕራብ ሱዳን፤ በሰተ ሰሜን ኤርትራና በምስራቅ ትግራይን ያዋሰነ ሠፊ ለም መሬት የያዘ አካባቢ ነው ፡፡ በአጠቃላይ መጠሪያችን ወልቃይት ጠገዴ ሰሜን አርማጭሆ ይባላል፡፡

2. ወልቃይት የአፄ ኃ/ሰላሴ አሰተዳደር ተገርስሶ በምትኩ ጌዚያዊ ወታደሪዊ መንግስት ከተመሠረተበት ጌዜና የደርግ መንግሰት እስከ ተገረሰሰበት ጊዜ ድረስ ደርግን ተቃውሞው ለወጡ ታጋይ ድርጀቶች እንደ ኢድዩ ፣ ኢህአፓና ህወሃት ለትግል እስትራቴጄክ አካባቢ ሆኖ አገልግሏል፡፡

3. የወልቃይት ህዝቡ ከህዝብ እሰከ መሬቱ ይህ ነው የማይባል መስዋዕትነትና ትግል ያካሄደ ሲሆን በተለይ ለህዋሃት ከውጭ አለም ለማገናኘትና ትግሉን ከውጭ ሰፊ ድጋፍ እንዲያገኝ እንደ ባህር በር (ወደብ) ሆኖ አገልግሏል፡፡

5. ህወሃት ይህን አከባቢ በ1972 ዓ.ም ኢህአፓን አስለቅቃ ስትይዘው በቅድሜያ የወልቃይት ህዝብ ህወሃትን ፈልጎ ራሱ መርቶ ያመጣት ሳይሆን በወቅቱ ህወሃት ከውጭ አለም ልትገናኝበት የሞትችል በር ባለመኖሩና በቀላሉ ለጠላት ተጋላጭ ስለነበረች ይህን አከባቢ ስትሪቴጅክ በመሆኑ ምክንያት እንጂ የወልቃይት ህዝብ የብሄር ሆነ የመደብ ጭቆና ኖሮበት ለመፍታት ፈልጋ አስባበት ለወልቃይት ህዝብ ግድ ብሏት አይደለም፡፡

6. ህወሃት ወልቃይት ከገባችበት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ደርግ እስከ ሚደመሰስበት በነበረው የትግል ጊዜ አንድም ቀን በሰላም ከህዝቡ ጋር ተዋህዳ ያሳለፈችበት ጊዜ አልነበረም ፡፡ በወቅቱ የህዋሃት አመጣጥ ሆነ መጠሪያ ስም ያልተመቻችውና ከህዝቡ ፍላጎት ውጭ ይህን አከላለል ወደ ተግራይ ለማካለል መፈለጓን ያዩ ያወቁ የተረዱ የወልቃይት ትላልቅ አባቶችና ወጣቶች በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሃሳባቸውን ቢገልፁም ይህን ሃሳብ ያቀረቡ አባቶችና ወጣቶች ሠው ሣያያቸው በስውር ተወስደው ጠፍተዋል፤ ንብረታችው ተዘርፏል፡፡ በወቅቱ ይህን እርምጃ ድርጅቱ በመውሰዱ ተቃውሞው እየበረታ እየከረረ ሄዶ እሰከ አሁን ድረስ የወልቃይት ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ሆነ በትጥቅ ትግል ተቋውሞውን እየገለፀ ይገኛል፡፡

7. የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ የማንነት ጥያቄ ወይስ የጥላቻ ጥያቄ ነው?

በ 1987 ዓ.ም የሃገራችን ህገ መንግስት ረቅቆ ወደ ተግባር ስከተሸጋገረበተ ጊዜ ድረስ ህዝቦች ያለ ፈቃዳቸው፤ ያለ ፍላጎታቸው ተገደው በሃይል ሆነ በጉልበት ማንነታችው ሊገረሰሰ አይገባም ተብሎ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የወልቃይት ህዝብ ያለ ፍላጉቱ በሃይል ማንነቱን ተነጥቆ ቆይቷል ፡፡ ማንነቱ ተነጥቋል ሲባል ለመሆኑ የህዝቡ ማንነት ማረጋገጫ ምንድን ናቸው? ሊባል ይችላል፡፡ የህዝቡ ማንነት መገለጫው ከሆኑት አንዱ ባህሉ ነው፡፡ ከጥንት ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣ የራሱ የሆነ አማራዊ ባህል አለው፡፡ ለአብነት ህዝቡ ደስታውንና ሃዘኑን የሚገልፅበት የጋብቻ ሥርዓት፣ ጭፈራ፣ ፉከራ፤ እና ሃዘኑን የሚገልፅበት ሙሾና እንጉርጉሮ አለው፡፡ እነዚህ የባህል መገለጫዎቹ በራሱ አንደበት ለዘመናት ሲጠቀምበት ጠብቆ ቆይቷል፡፡ አሁንም እነዚህን አማራዊ እምብርተ-ባህሎቹን ይጠቀምባቸዋል፡፡ በጥቅሉ የወልቃይት ህዝብ ደስታና ሃዘኑን በአማርኛ ይገልፃል ለማለት ነው፡፡ ሆኖም በህገ መንግሰቱ እንደተገለፀው ማንኛውም ህዝህ የራሱን ባህልና ታሪክ የሚገልፅበትን መንገድ ማሣደግ እንደሚችል ቢገለፅም እነዚህ ባህሎቹ የማንነቱ መገለጫዎች እንዲጠፉ እየተደረገ ነው፡፡ አባቶቻችን ያቆዩን ባህል አቅበን ጠብቀን፤ አክብረን ልንይዘው ልንገለገልበት ሲገባ ዘፈናችን፤ ለቅአሶችን በአማርኛ መሆኑ ቀርቶ ወደ ትግረኛ ተገደን እንድንቀይር በልጆቻችንና በልጅልጆቻችን እየተሰራ ያለ ስራ አግባብ የሌለው አንድ የመጨቆናችን መንስኤና ማሳያ ነው፡፡

8. ስነ-ልቦናዊ ባህርያችን እና የጂኦግራፊ አቀማመጣችን ከጥንት ከትውልድ ትውልድ ጀምሮ ምንም እንኳ ትግሪኛ እንደ ቋንቋ በመሳሪያነት እንገልገልበት እንጂ ትግራይ የመሆን ሰነ-ልቦናና ቀልብ በህዝቡ አልነበረም፤ አሁንም አልተፈጠረም፡፡ ይህ ሲባል ህዝቡ ለትግራይ ህዝብ ንቀት ኖሮት አይደለም፡፡ ከጥንት ጀምሮ አስተዳደራዊ መፍትሄ ለማግኘት ሆነ የባህል ትስስሩ ወይም የዘር ሀረጉ የሚመዘዘው ከአማራ ህዝብ ጋር ነው፡፡ ይህ በመሆኑም የአማራ ብሄርተኝነት በሰነ-ልቦናው ተጠብቆ መቆየቱን ያረጋግጣል፡፡ የወልቃይት ህዝብ እስካሁን ድረስ ቢፈልግ አማርኛ ቢፈልግ ትግርኛ ቋንቋ መናገር ይችላል፡፡ መሰረታዊ ጉዳዩ ትግርኛ ተናጋሪ በመሆንና ባለመሆን ሳይሆን በሰነ-ልቦና ረገድ ያለው ትስስር ከማን ጋር ነው የሚለው ገዢ አመለካከት ነው፡፡ ይህ በመሆኑ እድገት ወዳለበት አከባቢ ሄጄ ልኑር፤ ቤት ልስራ ልጆቸን ላስተምር የሚል ሃሳብ ካለው እንኳ ከአካባቢው ወጥቶ የሚኖረው አብዛኛው በአማራ ዞኖችና ወረዳዎች ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጎንደር ከተማ ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ የሚልቀው የወልቃይት ህዝብ ነው ፡፡ ይህም ራሱን የቻለ የህዝቡን የሰነ-ልቦናዊ ፍላጎት መገለጫ አንዱ ማረጋገጫ ነው ፡፡

ሀ. ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት:- የወልቃይት አከባቢ በተለይ ለእርሻ ክፍለ ኢኮኖሚ ሰፊ ጥቅም የሚውል ለም መሬት ያለው በመሆኑ ገና በሃምሳዎቹ አከባቢ ከኋላ ቀር አስተራረስ ወጥቶ ወደ ዘመናዊ መካናይዜሽን ተሸጋግሮ ዘመናዊ እርሻን ለሃገር ያስተማረ፤ ሰፊ ምርት በማምረት ለሃገር ሲጠቅም የቆየ መሆኑን ታሪክ ያስረዳል፡፡ የደርግ መንግስት ሃገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ በኋላ ብዙ ሃብት ያፈሰሰበት የእርሻ መሬቱን የሰራው ቤቱን ጥሎ ለስደት የተዳረገ ህዝብ ነው የሆነው፡፡ ከደርግ ውድቀት በኋላም ያ የነበረው የእርሻ መሬቱ እና ንበረቱ ተወርሶ፤ ከፊሉ ተነጥቆ ለሌሎች ተሰጥቶ መሬት አልባ የሆነና በአካባቢው ተፈጥሮ ሃብት እንዳይጠቀም መብት የተነፈገ የበይ ተመልካች የሆነበት ኢኮኖሚው ከጊዜ ጊዜ አሽቆልቁሎ የሄደበት፤ ወጣቶች እንደልባቸው አርሰው እንዳይጠቀሙ መሬቱ ተነጥቆ ለሰፋሪ የተሰጠበት፤ ፍትህ ያልታየበት አሰራር የነገሰበት፤ ከትግራይ የመጣ ሰፋሪ በሃብት ሲበለፅግ የወልቃይት ወጣት ለድህነት ለልመና እና ለስደት የተዳረገበት ነው፡፡ ስለሆነም ባለው ጭቆና ህዝቡ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዳይሆን አድሎ እየተደረገበት እንዳለ መሬት ላይ ወርዶ መመልከት ይቻላል፡፡

ለ. የዲሞክራሲ መብት ተጠቃሚነት
የወልቃይት ህዝብ እንደሌላው የኢትየጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ ተጠቃሚ ባለመሆኑ በሃገራችን የዲሞክራሲ መብቶች ለማረጋገጥ ታግሏል፡፡ ሆኖም ግን ገና በጠዋቱ በትጥቅ ትግል ወቅት ማንነቱን እንዲረጋገጥለት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቢጠይቅ ለጥያቄው መልስ በአግባቡ ከመስጠት ይልቅ ይህን ጥያቄ ያነሳ ሁሉ በስውር እየታፈነ ደብዛው ሲጠፋ ቆይቷል፡፡ ከደርግ መደምሰስ በኋላም ቢሆን በራሱ ፈቃድ ወደ ሚፈልገው ማንነቱ ሊያረጋግጥበት ወደ ሚችል አማራ “ክልል” እንዲዋሃድ በየ መድረኩ ጥያቄ ቢያነሳ የተሰጠው መልስ በዲሞክራሲ አግባብ መሰጠት ያለበት መልስ መሆን ሲገባው “ብትፈልጉ እናንተ ጥርግ ብላችሁ ወደ ምትፈልጉበት ሄዱ፤ እኛ የምንፈልገው መሬቱንና ሴቱን ብቻ ነው” ተብሎ ነበር፡፡ አሁንም እየተመለሰልን ያለው መልስ ይህ ነው፡፡ ይህን በብዙ አቅጣጫ መመልከት ይቻላል፡፡ እካሁንም ድረስ ማንነቱና ጥያቄው በአግባቡ ሊመለስለት ባለመቻሉ ለብዙ ችግሮች ተጋልጧል፡፡ በሌላ መልኩ ይህንን ጥያቄ ባነሳ ቁጥር አላስፈላጊ ኢሰብአዊ እና ኢዲሞክራሲያዊ የሆኑ እርምጃዎች ስለሚወሰዱበት በመሸማቀቅ አንገቱን ደፈቶ በህገ መንግሰቱ የተቀመጡት ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፋይዳ ሳይሰጡት ተገፍቶና ተሸማቆ ይኖራል፡፡ በዚህ መሠረት መብቱንና ማንነቱን ወደሚያረጋግጥለት፤ የራሱ ማንነት ወደ ሆነው አማራ “ክልል” መቀላቀል ዋና ፍሬ ጥያቄው ሁኗል፡፡ ለዚህም ከአሁን በፊት በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንደታገለው ሁሉ ለወደፊቱም ማንነቱ እሰኪረጋገጥለት ድረስ በሰላማዊ ትግል መብቱን ያረጋግጣል፡፡

ሐ. የወልቃይት ህዝብ ማንነቱን ለማስከበር በሰላማዊ መንገድ ከመታገል ውጪ የማንኛውም ሃይል መሳሪያ ወይም መጠቀሚያ መሆንን አይፈልግም፡፡

መ. እንደ ወልቃይት ህዝብ ፍላጎነትና አሰተሳሰብ የማንነት ጥያቄ የሚፈታው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ እንጂ በሌላ መንገድ እንዳልሆነ ያምናል፡፡ ስለዚህ ብአዴን ለአማራ ህዝብ ማንነትና ጥቅም የሚታገል ሃይል ስለሆነ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ የአማራነት የማንነት ጥያቄ፤ የራሱ ህዝብ ጥያቄ እንጅ የሌላ ሀይል ጥያቄ አለመሆኑን አውቆ አምኖበት ለወልቃይት የማንነት ጥያቄ አጥብቆ ሊከራከርና ሊያስወስን ይገባዋል፡፡ የህዝቡ ጥያቄ የራሱ የሆነ ወግ፤ ታሪክ፤ ባህልና ስነ-ልቦና ያለው ስለሆነ በራሱ ፈቃድ ወደ ሚፈልገው የአማራ ህዝብ ተቀላቅሎ መኖር ስለሚገባው ብአዴን ይህንን የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ በአግባቡ አጥንቶና ጥያቄውን ተረድቶ ከጎኑ ሁኖ ጥያቄው በህገ መንግስቱ በሰፈሩት ህግጋት መሰረት እንዲመለሱለት፤ እገዛም እንዲደረግለት፤ ይህን ለሚጠይቁ ህይሎች የሚሰነዘረው የተለመደው ፀረ ሰብአዊ መብትና ፀረ ዲሞክራሲ በትር እንዳይነሳበት ከለላና ጠበቃ ሊሆንለት እንደሚገባ በመተማመን የጠይቃል፡፡

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ብሄረተኝነት እንቅስቃሴ አስጠባቂ ኮሚቴ፡፡

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: