The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

በዲሲ ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለተፈጠረው ብጥብጥና የፍርድ ቤት ውሎ የተጠናቀረ ዘገባ

ጥቅምት 8 ቀን 2008  ዓ.ም.

አንደኛ፤ የፍርድ ቤት ውሎ

የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን (ር/አ/ደ/ሰ/ቅ/ማ/ቤ/ክ) በዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ መሪነት፣ በአቶ አዲሱ አበበ አስተባባሪነት፣ በመምህር ተስፋዬ መቆያ ቀስቃሽነት የሚንቀሳቀሰው ቡድን የቤተክርስቲያኗን ህልውና የሚፈታተኑ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ ፈጽሟል። ይህ ቡድን የቤተክርስቲያኗ የመተዳደሪያ ደንቡን ሽሮ፣ አባል ምዕመናን የመረጡት የባለአደራዎች ቦርድ ገልብጦ፣ ቁልፍ ሰብሮ ቤተክርስቲያኗን ጥቅምት 8 ቀን 2008  ዓ.ም.  (September 27, 2015) እንደምሽግ በየተራ ተቆጣጥሮ ቆይቷል። ስለሆነም ቤተክርስቲያኗ ሕጋዊ መብቷን ለማስከበር በመሰረተችው ክስ ምክንያት አጥፊዎች ፍርድቤት እንዲቀርቡ ተገደዋል።

ችሎቱ የዋለው ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. (OCTOBER 13, 2015)  ከቀኑ 2:00 PM ገደማ ነበር። የዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ ቡድን በተስፋዬ መቆያ የተጀነጀኑት ተከታዮቹ አብዛኛዎቹ ነጫጭ ልብሶቹ ለብሰው ወደ ፍርድቤቱ ይጎርፋሉ፤  ነጭ ልብስ ያለበሰውን ከነሱ ያልሆነውን ከቦርዱ ነው ብለው የሚገምቱትን ይገላምጣሉ፣ በማጉረምረም ይሳደባሉ እንዲሁም ለማሳፈርና ለማስደንገጥ የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ። ኮሪደሩ እየሞላ ሲመጣ የፍርድቤቱ የጸጥታ ጠባቂዎች ስጋት እየጨመረ በምጣቱ ቦታውን እንዲለቁ ተጠየቁ። በጥያቄው መሠረት ወደ ተዘጋጀላቸው ክፍል ወደ ምድር ቤት መውረድ ጀመሩ።

የሁለቱ ወገን ጠበቆቹ መጡ፤ በሁለቱም በኩል  ጉዳዩን ለመከታተል የመጡት ሰዎችም ብድግ ብድግ በማለት ጉዳይ የተያዘበት ክፍል ቢሮ ቁጥር 4220 ሁሉም ከበበ። የዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ ቡድንና በተስፋዬ መቆያ የደነዘዙት ስድባቸው ቀጥሏል። ጉዳዩ ከተያዘበት ወደ ሁለተኛ ፎቅ ተቀይሮ ክፍል  ቁጥር 219 ሆነ። ሁሉም ጠበቆችን ተከታትለው ወረዱ። የዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ ቡድን ጠበቃ የር/አ/ደ/ሰ/ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጠበቃን እንደራደር ብሎ ጠየቀው። እዚህ ላይ አቶ ቢልልኝ ማንደፍሮ በቦታው ተገኝቷል። የሕግ ባለሙያ በመሆኑ የድርድሩን ሀሳብ ያመጣው እሱ መሆኑ በቦታው ለነበረ ሰው ማስረጃ አያስፈልግም።

ለአንድ ሰዓት የሚሆን ድርድሩ ቀጥሎ በየክፍላቸው ሆነው ጠበቆቹ እየወጡ ሲያደራድሩ ቆዩ። በመጨረሻ ዳኛዋ እየመጡ ነው ተብሎ ፍርድ ወደሚሰጥበት ክፍል እንድትገቡ ተብሎ በየቦታቸው እንዲቀመጡ በጸጥታ አስከባሪዎቹ ተነገረ። ሁሉም ቦታውን ከያዘ በኃላ ክፍሉ ስለጠበበ አዳማጩ ህዝብ ከክፍሉ ተርፎ በሩ ክፍት ሆኖ ህዝቡ በዉጭ ቆሞ ለማዳመጥ ተዘጋጀ።

የፍርድ ቤቱ ጸሀፊዎችና ሁለት አስተርጓሚዎች ቦታ ቦታቸውን ያዙ። የተወሰነ ደቂቃ መጠበቅ በኃላ ዳኛዋ ወይዘሮ መጡ። “እንደምን ዋላችሁ አሉ?”፤  አጸፋውን መልስ ሁሉም ሰጠ። “ተቀመጡ አሉ”።ጠበቆቹ እራሳቸውን አስተዋወቁ፤ የቅድስት ማርያም ጠበቃ “ክቡር ዳኛ እኔና የተከሳሽ ጠበቃ የተስማማንበት የመደራደሪያ ሀሳብ አለን ሲፈቅዱልን ማንበብ እንችላለን” በማለት ተናገረ። ክቡር ዳኛዋም “ከማንበባቸሁ በፊት ለእኔ እንድታስረዱኝ እፈልጋለሁ”። በማለት ወደ ሌላ ክፍል ይዘዋቸው ሄዱ። 45 ደቂቃ ያህል ቆይተው መጡ።

ክቡር ዳኛዋ “የተደረሰበትን የድርድር ጽሑፍ ጠበቆች ከማንበባቸው በፊት እኔ መናገር የምፈልገውን መልዕክት አስተላልፋለሁ” ካሉ በኃላ “ጉዳዩን  አንብቤዋለሁ፤ ተመልክቼዋለሁ፤ አሳዝኖኛል፤ ከአንድ ህፃን በስተቀር ሁላችሁም እዚህ ያላችሁት እራሳችሁን የቻላችሁ ሙሉ ሰዎች ናችሁ። ስለዚህ አሁን የምናገረውን መረዳት የምትችሉ በመሆናችሁ በጥሞና እንድታዳምጡኝና እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ። ያየሁትና ያነበብኩት በፍጹም የቤተክርስቲያን ባህሪ ያልታየበት፣ ጨዋነት የጎደለው፣ ስልጣኔ ያልታየበት፣ በአመጽ የተሞላ፣ መከባበርና ፍቅር የሌለበት፣ ድፍረት የሞላበት፣ አሳፋሪና ክርስቲያናዊ ባህሪ የጎደለው በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ህገወጥ የሆነ ድርጊት መሆኑን ተመልክቻለሁ።የሀሳብ ልዩነት ሊኖር ይችላል ነገርግን ጓደኝነታችንን የሚያበላሽና የሚያጠፋ  መሆን የለበትም። ተነጋግሮ በሀሳብ ልዩነት መኖር ተማምኖ መመልከት ያለብን የእኔ ሀሳብ ካልሆነ የሚለውን ሳይሆን ትልቁን ዓላማና የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት ነው። አሁን መጀመሪያ የምናደርገው ህጋዊ ሥርዓት ወደ ነበረበት መመለስ ነው። ከመለስን በኋላ ቤተክርስቲያኗ ወደ ቀድሞ አግልግሎቷ ተመልሳ ለአማኞቿ ክፍት ትሆናለች።” በሚሉበት ጊዜ ጭብጨባ ቀለጠ። “ምን የሚያስጨበጭብ ነገር ነው የተናገርኩት”? አሉና ንግግራቸውን ቀጠሉ።

“ቤተ ክርስቲያኗ ክፍት በምትሆንበት ሰዓት አስተዳዳሪው ወደ ቢሮቸው ይገባሉ። የቀን ተቀን ሥራቸውን ይጀምራሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ባለፈው ሳምንታት እንዳየሁት የተደረገውን እንደተመለከትኩት ሳይሆን፣ ተከባብሮ፣ መሰዳደብ ሳይኖር አማኞቹን ሳይሳቀቁ በነጻነት አምልኳቸውን እንዲፈጽሙ ምንም አይነት ሁከት መኖር የለበትም። ይህን ትዕዛዝ የሚጥስ ለፖሊስ ሪፖርት ይደረጋል። የምትሰሙትና የምትፈራረሙት ስምምነት የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ነውና መከበርና  ተግባራዊ መሆን አለበት ብለው ጠበቆቹ ትዕዛዙን እንዲያነቡ ፈቀዱ።  ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. (OCTOBER 13, 2015) በዋለው ችሎት መሰረት የሁለቱም ወገን ጠበቆች በተስማሙበት መሰረት ዳኛዋ ፊት ለመፈራረም ተስማምተዋል። ያንን የተስማሙበትን ተፅፎ እንዳለቀ ዳኛዋ ፊት ሄደው እንደሚፈራሩም ይጠበቃል። ጉዳዩ ሲደርሰን እናቀርባለን።

ሁለተኛ፤ የፍርድ ቤት ቀጠሮን ለማደናቀፍና ህዝብን ለማወናበድ የተደረጉ ሙከራዎች

የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያ የባለአደራዎች ቦርድ ቤተክርስቲኗን በጉልበት ቁልፍ ሰብረው የተቆጣጠሯትን በፍርድ ቤት ለመክስስና እነዚህ ሕግን የማያከብሩትን ከችግር ፈጣሪነት ለመግታት ሲባል ለ October 13, 2015 ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል።  ይህን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተሰርዟል  የሚል የሐሰት ፕሮፓጋንዳ አስራጭተው ነበር። ከነዚህ አንዱ፣ የፍርድበቱን የቀጠሮ ማስታወቂያ ገጽ 3 ላይ በቢጫ ቀለም ተመልክቷል። ይህንን ያንብቡ።

Fake Cancellation of DC Court Hearing distributed  by Tesfaye Meqoya Group on 10-7-15 via viber

ከላይ ያያችሁትን የሐሰት ዘመቻ ለአንድ ቀን ሲያሰራጩ ቆይተው ሊያልፉት የማይቻላቸውን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ ተከታዮቻቸውን ነጭ ልብስ ለብሰው እንዲቀርቡላቸው የተማጽንዖ  መልክት በቫይበር አስራጭተዋል።  እንዲህ ያለ የማወናበጃ መልክት ሀይማኖተኛ  ነኝ ከሚል ወገን ሲተላለፍ መስማቱ እምነትን የሚፈትን እንደሚሆን ያነጋገርናቸው ምዕመናን ይጋራሉ።  በተገላቢጦሽ  የይድረሱልን መልክት ለማየት ቀጥሎ ያለውን ይመልከቱ። Contradicting the Fake Cancellation message distributed on 10-6-15

ሶስተኛ፤ በፍርድ ቤት ውሳኔ ተስማምተው ከፍተኛ የሐሰት ዘመቻ መቀጠላቸው  

የነ ዶክተር አክሊሉ ቡድን በፍርድ ቤት የተስማሙበትን ሁሉ የሚቃረን ሐሰት መንዛት አበክረው ቀጥለዋል። ይህ ዓይነት ምስቅልቅሉ የወጣ የሐሰት አባዜ እንዴት እየተለመደ ሊመጣ ቻለ ብለን የተለያዩ ምዕመናን አነጋግረን  ነበር። አንድ የተስማሙበት ነጥብ ቢኖር የወያኔዎች ‘ነብይ’ የሆነው መለስ ዜናዊ ያስተማራቸው ዐመል ነው የሚል ነበር።  ምን ማለታችሁ ነው ብለን ስንጠይቃቸው የሚያቀርቡት ምክንያቶች ሁለት ናቸው።

  1. “በነጋታው ለሚታወቅ እውነታ ለአንድ ቀንም ቢሆን ዋሽተህ ህዝብን አደናግር፣ አምታታ” የሚለው መርሆ በተግባር የታየው ባድመ ድንበር ውሳኔ የተሰጠ ዕለት ወያኔ “ባድመ ለኢትዮጵያ ተፈረደ” በሚል የአዲስ አበባን ሕዝብ አደባባይ አስጨፍረው በማግስቱ ዉሸት እንደሆነ ታወቀ።
  2. የምርጫ 97 ተከትሎ  መለስ ዜናዊ “ከሰማይ በታች የማንደራደርበት ነገር የለም” በሚል ማታለያ ዘዴ የተቃዋሚውን ጎራ በዶ/ር በየነ ጴጥሮስ በኩል እንዲፈርም ከተደረገ በኋላ ወያኔ መተንፈሻ ጊዜ አግኝቶ እስከ አሁን በኢትዮጵያ ሕዝብ ጭንቅላት ላይ ለመፈንጨት ችሏል።

አሁን በዲሲ ማርያም የሚታየው የማምታታትና የማታለል ዘመቻ የወያኔ ልዩ ባሕሪ የተጎናጸፈ ይመስላል። በዶክተር አክሊሉ ሐብቴ ቡድን ውስጥ አንዳንድ የቀድሞ የደርግ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩና አሁን አሜሪካ ውስጥ በስደት የሚኖሩ መገኘታቸው ብቻ ወያኔ የለበትም ለማለት ፈጽሞ የማያስችልና ታላቅ ስህተት ላይ የሚጥል ድምዳሜ ላይ ያደርሳል የሚሉ የፖለቲካ በሳሎች ብዙ ናቸው። ባለፈው 20 ዓመታት ዉስጥ ካህናትና መነኮሳት ነን እያሉ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው፣ የገንዘብና የስልጣን ስግብግብነት ያደረባቸው ግለሰቦች ለዚህ ዓይነቱ አቀንቃኝ ሆነው ብናገኛቸው አይደንቀንም።

እስቲ እስከ አሁን የዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ፣ አቶ አዲሱ አበበ፣ መምህር ተስፋዬ መቆያ ቡድን ያደረገውን እንመልከት። ሰሞኑን በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ ባደረግነው  ጠለቅ ያለ ክትትል ቤተክርስቲያኗ ያለችበትንና  የነገሩ አብይ ተዋንያን  የሆኑትን የዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ፣ አቶ አዲሱ አበበና መምህር ተስፋዬ መቆያ መሆናቸው ተረጋግጧል።  ሆኖም ከዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ በስተቀር፣ አቶ አዲሱ አበበና መምህር ተስፋዬ መቆያ በቀጥታ ከአባ መላኩ ጋር በመመካከር እንደሚሰሩ ከተለያዩ መረጃዎች ማረጋገጥ ተችሏል።

መምህር ተስፋዬ መቆያና አቶ አዲሱ አበበ የየራሳቸው ፍላጎትና አብረዋቸው የሚሰሩ ተከታዮች አሏቸው። መምህር ተስፋዬ መቆያ ትልቁ ፍላጎታቸው ገንዘብ መሰብሰብ ብቻ እንደሆነ በተለያየ ጊዜ የነገሯቸው ሰዎችና የሚያያደርጉት ተግባር በግልጽ ይጠቁማል። ለምሳሌ በሊቢያ የተሰዉትን መማዕታት ወገኖቻችንን ለማሰብ May 10, 2015  የተደረገውን ሕዝባዊ የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ ያልተገኙበትን ምክንያትን ሲጠየቁ  እርስ በርሱ የሚጣረስ መሆኑ ነው።አሁን ማጣፊያው ሲያጥር የተለያየ የማወናበድ ስራ እንደሚሰሩ ነው ያረጋገጥነው።

  1. “ባልና ሚስት ተጣልተው የማርያም ቤተክርስቲያን የመኪና ማቆሚያ ላይ ስለጠበቁኝ ነው የቀረሁት”
  2. “ብዙ ተከራርክሬ  የዝግጅቱ አቅጣጫ በመሳቱ  ተናግሬ ወጣሁ”
  3. “ባልመጣም መብቴ ነው” የሚሉ ንዴትና መረታትን የሚያረጋግጡ ምክንያቶች ይገኙበታል

ሌላው መምህር ተስፍዬ መቆያ ሁለት ጊዜ አቡነ ፋኑኤል የሰጧ ቸውን ስልጣን “እኔ ሳልፈቅድ ነው ወይም እዚህ አልነበርኩም”፣ የመሳሰሉት ምክንያቶች ያቀርባሉ። ነገር ግን የተሰጡትን ስልጣን አለመቀበላቸውን የሚያሳረዳ መረጃ፣ ወይም አቡነ ፋኑኤል ስልጣኑን ማንሳታቸውን የሚገልፅ አንድም ማስረጃ አላየንም። ( ምናልባት አሁን ሊያዘጋጁት ይሞክሩ ካልሆነ በስተቀር)። ይህ ዓይነት ክህደት አዲስ አለመሆኑንን የሚናገሩት አንዳንድ ምዕመናን ከዚህ በፊትም የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መምህር ዘበነ ለማ በሰርጋቸው ላይ አቡነ ጳውሎስ በመገኝታቸው ምክንያት በደረሰባቸው ተቃውሞ “ፓትርያርኩን ሳልጠራቸው መጡ” በማለት ፓትርያርኩን ቀላዋጭ አስመስለው ማቅረባቸው ከወያኔ ደጋፊዎችም ሆነ ከተቃዋሚዎቹ ወገን በአታላይነት መተቸታቸው ይታወሳል።

በዲሲ ማርያም ስለተከሰተው ሁኔታ አንዳንድ ያነጋገርናቸው ስለ ቤተክርስቲያን ጉዳይ አበክረው የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚሉት በተዘዋዋሪ መልኩ በዲሲ ማርያም እየተካሄደ ያለው በመላው ዓለም እየተፈጸመ እንዳለ  ይታያል። ታዲያ ከዚህ ችግር  ተጠቃሚ የሚሆነው ማነው የሚለውን ሲያብራሩ ቤተክርስቲያኗን ለማጥፋት በማንፌስቶ መርሃ ግብር ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ ያለው ወያኔ ብቻ ነው ተጠቃሚ የሚሆነው። “አማራንና  ኦርቶዶክስ አከርካሪውን ሰብረነዋል” እያለ የሚመጻደቀው የስርዓቱ  ቁንጮ የሆነው ስብሐት ነጋ የተናገረውም ይህንኑ ነው። ቤተክርስቲያኗን መበጥበና በማናከስና በሚፈጠረው ክፍተት ሾልኮ በመግባት ሁኔታዎችን መቆጣጠርና መተማመን እንዳይኖር ማድረግ፣ አንዱን ካንዱ ማጋጨት ትልቁ መሳሪያቸው መሆኑን እስከ አሁን በለንደን፣ በሚኖሶታ፣ በቦስተን፣ በዳላስ፣ በናሽቪል፣ በአትላንታና በሌሎችም  አካባቢዎች ከታየው መገንዘብ ይቻላል።

በአንዳንድ ካህናት አካባቢ የሚታየውን በገንዘብ ላይ ያተኮረ ፍላጎት እንዴት ነው ፖሊቲካ ዉስጥ ሊገቡ የሚያስችለው ብለን ላቀርብንላቸው ጥያቄዎች ያገኘነው ምላሽ የሚከተለው ነው። ሁለት አደገኛ ባህርያት በሕዝባችን  ጭንቅላት ላይ ወያኔ ለ25 ዓመታት ተክሏል። እነዚህ ሁለት መርዘኛ ባህሬያት የገንዘብ ፍላጎት የተጸናወታቸው አንዳንድ ካህናትና ወደ ገንዘብ የሚጠጉ አንዳንድ ሰዎች ላይ ሲደርስ ይታያል።  ይህም “በገንዘብ የማይገዛ ጭንቅላቱ  የታመመ ነው” ይላል ወያኔ።  ፍቅረ ንዋይና ስርዓተ አልበኛነትን በተመለከተ የባለደራ  ቦርዱ የሰጠውን ቃል ምልልስ ያዳምጡ።

ደ/ሰ/ቅ/ማ/ የባለአደራ ቦርድ ተወካዮህች ጋር ቃለ ምልልስ-ነፃነት  ለኢትዮጵያ  ሬድዮ -መስከረም  23 ቀን 2008 ዓ . ም.

የወያኔ ሆድ አደር ካድሬ የሆነው ንጉሴ ወልደማርያም  ለአባ ፋኑኤል (አባ መላኩ) አገልግሉትን ለመስጠት ብሎ በየሳምኑት ስለ ዲሲ ማርያም መርሃ ግብር በማቅረብ ላይ ነው። ባለፉት ሳምንታት ካቀረባቸው ሁለቱን የሬድዮ መርሐግብሮች፣  የሚቀጥሉትን ሰንሰለቶች በመጫን ያድምጡ።

Hager Fikr Radio Nigussie Weldemariam October 3- 2015

Hager Fikr Radio Nigussie Weldemariam October 17- 2015

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: