The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

አቶ አንዳርጋቸውን ለፍርድ ለማቅረብ ፍርድ ቤቱ ተችገረ – የሚሊዮኖች ድምጽ

12027563_513050365537865_5618218307343537825_n

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፣ በአሁኑ ወቅት የሚገኙት በኢትዮጵያ ዉስጥ ነው።፡የ እንግሊዝ አምብሳደር አራት ጊዜ እንደጎበኟቸው በስፋት ተዘግቧል፡ ከአቶ አንዳርጋቸው መመሪያ ተቀብላቹሃል፣ ከግንቦት ሰባት ጋር ትሰራላችሁ በመባል በርካታ ሰላማዊ ታጋዮች በዉሸት ክስ በወህኒ እየተሰቃዩ ነው።፡

እስረኞቹ ጥፋተኛ እንዳልሆኑ በማረጋገጥ አቶ አንዳርጋቸውን በመስክርነት ለማቅረብ የጠየቁ ቢሆንም አቶ አንዳርጋቸው ግን ለምስክርነት እዲቀርቡ የሕወሃት/ኢሕአዴግ የደህንነት አካል ግን ፍቃደኛ አልሆነም።፡የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት አቶ አንዳርጋቸውን ማቅረብ አልተቻለም። በዚህ ጉዳይ ላይ ዳኛው አንድ ነገር እንዲያደረጉ የተጠየቁት ዳኛ ግራ ከመጋባታቸው የተነሳ ” እኛ ምንም ማድረግ እንችላለን ? ” እስከማለት የደረሱበት ሁኔታ ነው የታየው።

በኢትዮጵያ ያለው የሕግ ስርዓት፣ ዳኞች ተብዬዎች ጥርስ የሌላቸው ዉሾች የሆኑበትና አብዛኞቹ መረጃዎችን አመዛዝነው የሚፈርዱ ሳይሆን፣ የተሰጣቸዉን መመርያ የሚያነቡበት፣ ዉሳኔ ሲያሳልፉና ትእዛዝ ሲሰጡ ትእዛዛቸው እንደ ሽንት ቤትው ወረቀት ተቀዳዶ የሚጣልበት፣ የሕግ ስርዓት ነው ያለው። ዳኞች የደህንነት አካላትን ከመፍራታቸው የተነሳ “እኛ ምንም ማድረግ እንችላለን ብለው” የሚጨነቁበት ሁኔታ ነው ያለው።

ዛሬ በዘመነ ምህረት መዝገብ የተከሰሱ እስረኞች የፍርድ ዉሎ ለገሰ ወልደሃና እንደሚከተለው አቅርቢታል።

የፍርድ ቤት ውሎ – (ለገሰ ወ/ሃና )
እነ ዘመነ ምህረት ለህዳር 3/2008 ዓም ተቀጠሩ
ዛሬ ጥቅምት 12/2008 ዓም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) አመራር እና አባላት በተለያየ መዝገብ ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። እነ ዘመነ ምህረት የእምነት ክህደት ቃል ሰጥተዋል። በዘመነ ምህረት የክስ መዝገብ ስር ጌትነት ደርሶ ይገኝበታል።
ዘመነ ምህረት እና ጌትነት ደርሶ ለተከሰሱበት የሽብር ክስ፣ ክሱ እንዲነበብላቸው ይፈልጉ እንደሆነ ከዳኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ክሱ ላይ የተለወጠ ነገር ከሌለ ማንበብ አያስፈልግም፣ የምናውቀው ነው ብለዋል። በክሱ ላይ ግን ሀሣብ እንዳላቸው ጥያቄ አቅርበው ተፈቅዶላቸዋል የሚከተለውን ብለዋል
ዘመነ ምህረት በተከሰሰበት ክስ እንዲህ ብሏል
” እኔ ጎንደር ተወልጄ በጎንደር ባህል እና እምነት ተኮትኩቼ ያደግሁ ክርስቲያን ነኝ ። የቀረበብኝ ክስ “በጥምቀት በዓል ላይ ቦንብ ሊያፈነዳ ሲል” የሚል ክስ አለበት ። ይህ ፈፅሞ ሀሠት ነው። እኔ ይህንን እንዳደርግ እምነቴም እድገቴም አይፈቅድም። ይህንን እንኳን እኔ ክርስቲያኑ፣ ግራኝ መሃመድ እና ደርቡሾችም አላደረጉም። እኔ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) አመራር እና የፕሮፌሰር ዓስራት ወልደየስ አላማ እንዲፈፀም የምደክም ሠላማዊ ታጋይ ነኝ። ፕሮፌሰር ዓስራት ደግሞ የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ ጉዳዩን በግልፅ የተቃወሙት ነው ። እንዴት እኔ የሻዕቢያ ተላላኪ ልሆን እችላለሁ ? ሌላው በእስር ቤት እየተፈፀመብኝ ያለው ግፍ መግለጽ እፈልጋለሁ ብዙ ጊዜ ድብደባ ተፈፀሞብኛል በዘመድ ፣ በጓደኛ እንዳልጠየቅ ተደርጊያለሁ የምተኛበት ቦታ ሸንት ቤት ላይ ነው ወዘተ ። ፍ/ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ ። ዛሬም ይህንን በመናገሬ የሚደርስብኝን አውቃለሁ።”
ፍ/ቤቱም ተከሳሽ ባቀረበው አቤቱታ ላይ በዘመድ እና በጓደኛ የመጠየቅ መብቱ መገፈፍ እንደሌለበት ማረሚያ ቤቱ እንዲያስተካክል ትዕዛዝ ሰጥቷል
ጌትነት ደርሶ ደግሞ ” የተከሰስኩበት ክስ በሽብር ነው ። እኔ ግን ሠላማዊ ታጋይ ነኝ። ” እኔን ለ3ወር በጨለማ ቤት አስሮ፣ ከህግ ውጭ እየደበደበ፣ በደል ያደረሰብኝ፣ አሸባሪው ወያኔ ነው ..ወዘተ ” ብሏል
ምስክር ለመስማት ፍርድ ቤቱ ለህዳር 23/2008 ቀጠሮ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን፣ ተከሳሾች ቀጠሮው እረዘመ በማለት ባቀረቡት ቅሬት፣ ለህዳር 3/2008 ዓም ተለውጧል።
መለሰ መንገሻ ቀደም ሲል በክሱ ላይ ባቀረበው የክስ መቃወሚያ ላይ፣ ” የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በአሸባሪነት ያልተፈረጀ ድርጅት በመሆኑ በአሸባሪነት ልከሰስ አይገባም” ብሎ ክሱን መቃወሙ ይታወቃል። በዚህ መሠረት ከነ ዘመነ ምህረት የክስ መዝገብ ተነጥሎ ለብቻው እንዲታይ ተወስኗል
በነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ስር ከተከሰሱት የመኢአድ አባላት ዉስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡
አሸናፊ አካሉ
አብርሃም ሞገስ
አወቀ ሞኝሆዴ
ቢሆነኝ አለነ
ደህናሁን ቤዛ
ምንዳየ ጥላሁን
አንሙት የኔዋስ ወዘተ
እነዚህ ተከሳሾች አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን የመከላከያ ምስክር ማድረጋቸው ይታወቃል። አቶ አንዳርጋቸውን ያሰረው አካል ምክንያት እየደረደሩ ሊያቀርቡት አልቻሉም። ቀደም ሲል የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በአድራሻየ አልተፃፈልኝም በማለት አቶ አንዳርጋቸው ሳያቀርብ ቀረ። በመቀጠል “እድሜ ልክ ወይም ሞት የተፈረደበት መከላከያ ምስክር መሆን አይችልም” አሉ፡
በዛሬው ችሎት ደግሞ “አንዳርጋቸው ፅጌ የሚባል ታራሚ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የለም” ብለዋል።
“አንዳርጋቸው ፅጌ የት ቦታ እንዳለ የኢትዮጵያ ህዝብ ያወቃል። ማንኛውም ሠው በመንግሥት ቁጥጥር ስር መሆኑን ያውቃል። ይህ ሁሉ የሚደረገው እኛን ለማጉላላት ነው። የመከላከያ ምስክርነቱን አንስተናል” ሲሉ ምንዳየ ጥላሁን ግን ” ከአንዳርጋቸው ፅጌ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መቅረብ አለበት፤ ለኔ ይጠቅመኛል፣ ይቅረብልኝ” ብሏል ።
ዳኛው “እኛ ምን እናድርግ ?” በማለት ለታሳሪዎቹ ጥያቄ አቅርቧል። ተከሳሾቹ “በኛ ላይ የሚቀርብ ማስረጃ ቢሆን ኖሮ በሰአታት ተፈብርኮም ቢሆን ይቀርብብን ነበር። እኛ እስረኞች ነን ፣ የት እንዳለ እንድንጠቁማችሁ ነው እኛን የምትጠይቁት ? እንዲህ ከሆነ ቀልድ ነው ። ከምታጉላሉን አጭር ቀጠሮ ይሰጥና የመሠላችሁን ወስኑብን” በማለት ብሶታቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ማረሚያ ቤቱ የሚያቀርበው ምግብ በተመለከተ ሁሉም አማረዋል። በተለይ አሸናፊ አካሉ ምግቡ ለሠው ልጅ ቀርቶ ለእንስሳትም መቅረብ አይገባውም ብሏል ።
ዳኛውም ለህዳር 3 /2008 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጥቷል ፡፡

satenaw

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: