The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

“ኦሮሞ” ነን የሚሉ አክራሪዎች የኦሮሞን ባህል ያዉቁ ይሁን ? – ግርማ ካሳ

12019927_10207669814654153_6449382028045128258_n

በኦሮሞዉና በአማርኛ ተናገሪው መካከል ጥላቻ እንዲሰርጽ ተብሎ አንድ የተጻፈ መርዛማ መጽሐፍ አለ። የቡርቃ ዝምታ የሚባል መጽሃፍ። የዚህ መጽሀፍ ደራሱ አቶ ተስፋዬ ገበረ አብ ይባላሉ። የሕወሃት/ኢሓአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ ጊዜ የጻፉት መጽሀፍ ነው። “በሞጋሳ ኦሮሞ ሆኛለሁ” ሲሉ ይሰማሉ። ምን ያህል የሞጋሳ ሚስጠር እንደገባቸው ግን አላውቅም።
ከአራት መቶ አመታት በፊት፣ የኦሮሞ ጦረኞች አንድ አካባቢን በሚቆጣጠሩና በሚማርኩ ጊዜ፣ አንድ የሚያደርጉት ሥርዓት ነበር። የጎሳው ሽማግሌዎች ከተማዋ ሲገቡ ከዚያ ጊዜ ጀመሮ ያቺ ክከተማ ኦሮሞ ትሆናለች። በከተማዋም የሚኖረው ህዝብ፣ በሽማግሌዎቹ ፊት ያልፋል። በዘሩ ከሌላ ወገን ቢሆንም፣ በአለቃዉ ያለፈ ሰው ሁሉ ኦሮሞ ይሆናል። ይህ ስርአት ሞጋሳ ይባላል። ኦሮሞነት ከዘር ጋር ግንኙንት እንደሌለው የሚያስተምር የኦሮሞ ባህል !

ሞጋሳ የሚያሰባስብ ነው። አንድ የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ኦሮሞነት አንድነት ነው። ኦሮሞነት ሌላውን እንደ እራስ አድርጎ ማቀፍ ነው። ኦሮሞነት ሌላውን ማሳነሳ፣ ሌላውን ማባረር፣ ሌላውን መጥላት አይደለም።

እርግጥ ነው አንዳንድ አክራሪ የኦሮሞ ብሄረተኞች፣ በኦሮሞነት ስም ሌሎችን የመጥላት ፖለቲካ ያራምዳሉ። ከሌሎች የመለየት፣ ሌሎችን የማግለል፣ የመከፋፈል፣ የጥላቻ ፖለቲካ ያራግባሉ። ዘረኝነት በተባለ በሽታ የተለከፉ ናቸው። ሁሉንም ነገር የሚያሰሉት ከዘር ጋር በማገናኘት ነው። የኦሮሞ ባህል ግን ፣ የሞጋሳ ባህል ነው። አንድ የሚያደርግ ባህል ነው። ኦሮሞው ከማንም በላይ ከሶማሌው፣ ከወሎዬው፣ ከጎጃሜው፣ ከጎንደሬው፣ ከጉራጌው ..ጋር ተዋልዷል፣ ተዛምዷል። የኦሮሞ ባህል እነዚህ አክራሪዎች ከሚናገሩትና ከሚረጩት መርዝ ጋር ግንኙነት የለውም።
ሌላው በአማርኛም ሳይቀር የምንጠቀማት ቃል አለች። ጉዲፈቻ። ጉዲፈቻ ማለት የሌላውን ሰው ልጅ እንደ ራስ አድርጎ ማሳደግ ማለት ነው። ጉዲፋቻ የሚለውን ቃል በአማርኛ መጠቀማችን በራሱ የሚያሳየው፣ የሌላውን ልጅ እንደራስ አድርጎ የማቀፍ ባህል፣ በኦሮሞው ማህበረሰብ ዉስጥ ምንም ያህል ስር የሰደደ ባህል እንደሆነ ነው። የኦሮሞው ማህበረሰብ፣ ትግሬ ይሁኑ አማራ፣ ጉራጌ ይሁኑ ከፊቾ ፣ ከሌላ ዘር የሆኑትን እንደራሱ አድርጉ የሚያሳድግ ማህበረስብ ነው። ደግሜ አሰምርበታለሁ፣ ከሌላው ጋር የተዛመደ፣ የተዋለደ፣ የዘረኝነት ነገር የሌለበት ማህበረሰብ ነው።
ላለፉት 23 አመታት ግን በሽታ ገባ። የኦሮሞ ማህበረሰብን ከሌላው ለማጣላት ብዙ ተሞከረ። የባለስልጣናቱ ካድሬዎች ሆን ብለው በኦሮማኛ ተናጋሪውና እና ኦሮምኛ በማይነገረው ማህበረሰብ መካከል ልዩነቶች እንዲፈጠሩ ቀን እና ሌሊት መስራት ጀመሩ። ቂም በቀል እንዲያደርግ፣ ክሊኒኮችና ት/ ቤቶችን ሊያስገነባ የሚችል በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለአኖሌና ጨለንቆ የጥላቻ ሃዉልት ማሰሪያ ዋለ።

ለአማርኛ ተናጋሪዎች “ ኦሮሞዎቹ ዘረኞች ናቸው። አማርኛን ይጠላሉ። ይጨርሷቹሃል። ያርዱዋቹኋል” የሚል እድምታ ያለው መልእክት በጎን ያስተላልፋሉ። ለኦሮምኛ ተናጋሪዎች ደግሞ ” እነርሱ ነፍጠኞች ናቸው። በቋንቋህ እንዳትናገር ሊያደርጉህ ነው። ሊያጠፉህ ነው። የድሮው የአማራ የበላይነትን ሊያመጡብህ ነው። አሃዳዊ ስርዓት ሊጭኑብህ ነው” ይሉታል። አማርኛ ተናጋሪዎች በአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ላይ ፣ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ደግሞ በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ጥርጥሬ እንዲያድርባቸውና እና እንዳይግባቡ እያደርጓቸው ነው። ኦሮሞዎች አማርኛ እንዳይማሩ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች ደግሞ አማርኛ ብቻ እንዲናገሩ ተደርጎ፣ የአንድ አገር ልጆች ሆነው እንዳይግባቡ ተደርገዋል።

መንቃት ይኖርብናል። እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በኛ ላይ የሽረቡትን ወጥመድ ማፈራረስ አለብን። የኦሮሞ ባህል፣ የኦህደድ ካድሬዎች ወይንም ዉጭ ያሉ አንዳንድ ለኦሮሞ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ግን በጥላቻ የተሞሉ አክራሪዎች እንደሚነግሩን አይደለም። ኦሮሞነት ዘረኝነት አይደለም። ኦሮሞነት አንድነት ነው። ኦሮሞነት ሌሎች እንደ ራሱ አድርጎ መቆጠር ነው። ኦሮሞነት የሚለያይ ሳይሆን የሚያሰባስብ ነው። የኦሮሞነት ፖለቲካ የጉዲፈቻና የሞጋሳ ፖለቲካ ነው። ኦሮሞነት ኢትዮጵያዊነት ነው።

ኢትዮጵያዊነትን የሚያሳንስና የሚያጥላላ ኦሮሞነት ኦነጎችና መሰል ዘረኞች የፈጠሩት የዉሸት ኦሮሞነት ነው። ትክክለኛው ኦሮሞነት የኢትዮጵያዊነት ካባ የደረበ የነ ባልቻ አባ ነፍሶ፣ የነ ቡራዪ፣ የነ አብዲሳ አጋ ፣ የነ ጀኔራል ደምሴ ቡልቶ ኦሮሞነት ነው።

የኦሮሞ ማህበረሰብ ከምንም በላይ ፣ በባሃሉ የሚመቸውና የሚቀበለው የአንድነትን እና የፍቅርን ፖለቲክ ነው። “እገሌ ከዚህ ዘር ስለሆነ፣ ወይንም ይሄ ቋንቋ ስለሚናገር ከአገራችን ይዉጣ። ይሄ ምድር የኦሮሞ ብቻ ነው ….ወዘተረፈ” የሚባለው አክራሪዎችና ካድሬዎች የሚረጩት እንጂ, ከሕዝቡ የሚመጣ አይደለም። የኦሮሞ ማህበረሰብ በባህሉ ሌላውን የሚቀበል፣ እንደራሱ አድርጎ የሚያኖርና የሚያሳድግ ነው።

አፋን ኦሮሞ የማናውቅ ካለን፣ እንማር። አማርኛ የማናውቅ ካለን፣ አማርኛ እንማር፡ ብዙ ቋንቋ ማወቅ በረከት ነው። ሌላ ቋንቋ መማር አያሳንሰንም። እንደ ወንድማማቾች፣ ለመግባባት፣ ለመነጋገር፣ አብረን አገራችንን ለማሳደግ ቋንቋ አለማወቃችን እንቃፋት ሊሆንብን አይገባም። ጠላቶቻችን እና ዘረኞች ይፈሩ፤ አማርኛንም፣ አፋን ኦሮሞንም የኛው እናደርጋቸዋለን። የሃረር ሰው ያስደስተኛል። ቢሻው ኮቱኛ (አፋን ኦሮሞ) ፣ ቢሻው አማርኛ እየደበለቀ ያወራል። በቃ ቋንቋ ከሆነ ሁሉንም እንማራለን። ሁለንም ማስተናገድ እንችላለን። የሚያስፈልገው ከጥላቻ፣ ከጸረ-ኢትዮጵያዊነት የጠራ ጤናማ አስተሳሰብና ፍቅር ማዳበሩ ላይ ነው።

ከዚህ በታች ያሉት ከኦሮሞ ጀግና ኢትዮጵያዉይን መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፤ ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል ጉዲሳ (የሃረር ገዢ የነበሩ) እቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ጀነራል ደምሴ ቡልቶ (የሶስተኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበሩ )

satenaw

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: