The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ኢህአዴግ እህቴ የሚለው የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ አባላቱን ከዝሙትና ጎልፍ ከመጫወት አግዷል – ኢህአዴግ አዲሱን ደንብ ለመኮረጅ ይደፍር ይሆን?

china

Share0  192  1

ከዳዊት ሰለሞን

የቻይናው ገዢ ኮሚኒስት ፓርቲ 88 ሚልዩን የሚደርሱ አባላቱን ጎልፍ ከመጫወት፣ከትዳራቸው ውጪ ከመቅበጥ፣ ተስገብግቦ ከመብላትና ከመጠጣት ማገዱን የአገሪቱ መንግስታዊ የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡


በያዝነው ወር ይፋ የተደረገው አዲሱ የኮሚኒስት ፓርቲ ደንብ ፕሬዘዳንቱ ዢ ጂንፒንግ የሚመሩት የጸረ ሙስና ትግል አንድ አካል ነው ብሏል የቻይናው ዤንዋ በዘገባው፡፡ደንቡ ሁሉም የፓርቲው አባላት ሊታዘዙት የሚገባ የስነ ምግባር መመሪያ ስለመሆኑም አክሏል፡፡


‹‹የጂም ካርዶችን መያዝ፣ የጎልፍ ክለብ አባል መሆን፣ ሌሎች ሸማቾች የሚጠቀሙባቸውን የግዢ ካርዶችን መጠቀምና በግለሰቦች ወደሚተዳደሩ የምሽት ክለቦች መግባት ››በአዲሱ ደንብ በጥብቅ የተከለከሉ ናቸው፡፡እንደ ኤፍፒ ዘገባም ከሆነ የቻይና ባለስልጣናት በ2004 ተጀምሮ የነበረን አዲስ የጎልፍ ክለብ ግንባታን አስቁመዋል፡፡ነገር ግን ከአመታት በኋላ ግንባታው ቢጀምርም እስካሁን ድረስ አለመጠናቀቁን የዜና አውታሩ አስታውሷል፡፡  


ጎልፍ መጫወት፣ ለታይታ መብላትና መጠጣት ለመጀመሪያ ግዜ በቻይና እንደ ህገ ወጥ ድርጊት መቆጠሩን የጠቀሰው ዤንዋ የፓርቲው አባላት ቀደም ብለው ባለትዳርን ከማፍቀርና ከትዳር ውጪ ከመማገጥ ተከልክለው ቆይተዋል ብሏል ፡፡አዲሱ ደንብ ከሌሎች ጋር ኢ መደበኛ የሆነን የግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግን በጥብቅ ይከለክላል፡፡ 


እንደ አልጀዚራ ዘገባ ከሆነም ፓርቲው አባላቴ የሚላቸውን 88 ሚልዩን ቻይናዊያንን ከቡድነኝነትና ከአድልኦ የሚያቅብ ተጨማሪ ደንብ አጽድቋል፡፡ፕሬዘዳንቱ በ2012 ወንበራቸውን እንዳገኙ በፓርቲው ውስጥ ሙሰኝነትን ለመዋጋት አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን መጀመራቸው ቢታወቅም ባለፉት ጥቂት አመታት በዛ ያሉ የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት መሳቡ ይታወቃል፡፡
በሰኔ ወር የቀድሞው የአገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ ዙ ዮንግካንግ በቀረበባቸው የሙስና ክስ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የእድሜ ልክ እስራት እንደተበየነባቸው ዋሽንግተን ፖስት ዘግቦ ነበር፡፡ባለስልጣኑ 21 ሚልዮን ዶላር በሙስና መቀበላቸው በክሳቸው ተጠቅሶም ነበር፡፡
ዤንዋ ስለ አዲሱ ደንብ ከመዘገብ ውጪ ደንቡን መጣስ በኮሚኒስት ፓርቲው አባላት ላይ ምን አይነት ቅጣት እንደሚያስከትልባቸው የገለጸው ነገር የለም፡፡ነገር ግን የፓርቲው ደንብ በአገሪቱ ከሚገኙ ህጎች ሁሉ ጠንካራውና አባላቱ ሊታዘዙት የሚገባ መሆኑን አስታውሷል፡፡አዲሱን ደንብ የሚተቹ አካላት በበኩላቸው ፕሬዘዳንቱ በፓርቲው ውስጥ የማይፈልጓቸውንና በተጻራሪነት ይቆማሉ በማለት የሚያስቧቸውን ለመምቻነት ለመጠቀም እንዳዘጋጁት ያወሳሉ፡፡
በ2014 ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለ ተቋም ባወጣው የአገራት የሙሰኝነት ደረጃ ቻይና ከ175 አገራት በ100ኛ ደረጃ መቀመጧን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡
የምስራቅ አፍሪካው ኮሚኒስት ፓርቲ ኢህአዴግስ ከዚህ ምን ይማር ይሆን?
ኢህአዴግ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጋር በፍቅር መውደቁን ለማስታወስ በየግዜው ልምድ ለመቅሰም ወደ አዲስ አበባና ቤይጂንግ የሚደረጉ የየድርጅቶቹ አመራሮች ምልልስን ማስታወስ ብቻ ይበቃል፡፡ኢህአዴግና ኮሚኒስት ፓርቲው ‹‹እህት ››ፓርቲዎች እየተባባሉ መጠራራት መጀመራቸውም ተጨማሪ ማሳያ ይሆናል፡፡ቻይና በኢትዮጵያ እያደረገች የምትገኘው መጠነ ሰፊ ተሳትፎም ከንግድ ሽርክና ብቻ የተገኘ ነው ብሎ ማሰብም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡የሆነስ ሆነና ኮሚኒስት ፓርቲው አባላቶቹን ከላይ በተመለከትነው አዲስ ደንብ አማካኝነት ለመቆጣጠር እየሞከረ እንደሚገኝ አሳይቶናል፡፡የኢትዮጵያው እህት ፓርቲው ያንን መንገድ ቢከተል ምን የሚፈጠር ይመስልዎታል?
የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውሎና አዳራቸው ጦር ኃይሎች አካባቢ በሚገኘው ጎልፍ ክለብ ነበር ከጥቂት አመታት በፊት አሁን ሁሉም በመኖሪያ ቤቱ የጎልፍ መጫወቻ በማስገንባቱ ከአባ ዱላ በስተቀር ጦር ኃይሎችን የሚያዘወትር እምባዛም አይገኝም፣በትጥቅ ትግሉ ዘመን ወንድና ሴት እንዳይገናኙ እግድ የነበረ ቢሆንም ይህች ትዕዛዝ አመራሩን የምትመለከት አልነበረችም፡፡
የድርጅቱ አባላት አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ግን ታስራ እንደተፈታች ጊደር እዚህም እዚያም መዝለሉን ፣በየምሽት ክለቦቹ ማዘውተርንና በአውሮፓ፣በአሜሪካና ዱባይ መዝናናትን የግላቸው አደረጉት፡፡ብዙዎቹም በጫካ የመሰረቱት ትዳርን እያፈረሱ ከተሜዎቹ ላይ በጉልበት ጭምር ዘመቱ፡፡
የቀድሞዎቹ ባለጎማ ጫማዎች በአሁኑ ወቀት አዲስ አበባን ጨምሮ በዘመድ አዝማድ ስም የቆሞ የታላላቅ ህንጻ ባለቤቶች ሆነዋል፡፡በአሜሪካና በሆላንድ የሚበዙት የሚከራዩ አፓርታማዎች አሏቸው፡፡የቤተሰቦቻቸውን አባላት አስመጪና ላኪ በማድረግም በእጅ አዙር አገሪቱን የጥገት ላም ያደረጉ እንደ ጉድ ናቸው፡፡
ኢህአዴግ የኮሚኒስት ፓርቲውን ደንብ ሊኮርጅ አይችልም ማለት የሚያስኬድ ይመስላል

satenaw

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: