The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ነጻነቱን የተገፈፈ ሕዝብና የሕግ የበላይነት የሌለበት ኅብረተሰብ በእርግጥ መልካም አስተዳደር ሊኖረው ይችላልን? መደመጥ ያለበት ቃለ መጠይቅ

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ከሁሉም የሚያስገርመው ኢሕአዴግ ለሁለት ቀናት (ጥቅምት 22 እና 23) ስብሰባ ካደረገ በኋላ፣ ጥቅምት 23/2015 የሚከተለውን መግለጫ ሠጥቷል

“ኮሚቴው የኢህአዴግ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በመልካም አስተዳደር እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው የ2008 የንቅናቄ እቅድ ላይ በመወያየት ህዝቡን እያማረሩ የሚገኙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተደራጀ የልማት ሃይሎች ንቅናቄ የሚፈቱ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።

በመልካም አስተዳደር መስክ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ስራዎችን በተለያዩ መስኮችና ተቋማት ህዝቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት ጅምር ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም አመልክቷል።”


ከፍተኛ የሕወሃት አስተዳደር ባለሥልጣኖች በተገኙበት የተካሄደውን ይህንን የመልካም አስተዳደር ‘ማሳደድ’ የስም ጥናት ውይይት የሚይሳዩት ቪዲዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል።

የመልከም አስተዳደር ባለሙያ አጥኝዎች ተብየዎቹ ሁለት የሕወሃት ካድሬዎች ሴኮ ቱሬ ጌታቸውና ፍሥሃ ሃብተጽዮን ናቸው፡፡

ውይይታቸው የተንኮል ዓላማቸውን ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደ በመሆኑ፣ በዚህና በዚያ ተወሳስቦ፡ ውስጣቸውን ለማያውቅ ሰው ብዙ አደናጋሪ ስለሚሆን፡ የሚከተለውን ቃለ መጠይቅ በማዳማጥ ሁኔታዎችን መከታተል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
‘በተደራጀ የልማት ሃይሎች ንቅናቄ የሚፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች’? – ‘Good governance and management reforms by campaigns’?

ያቀረቡትን ጥናት ገምግመው መመሪያ የሚሠጡት ደግሞ እነ በረከት ስምዖን፡ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤልና ዐባይ ጸሐዬ ሲሆኑ፡ ኃይለ ማርያም በመጨረሻ የእነርሱ የሶስቱን ሃሣብ ነው ያጠቃለለው – “ማን ያርዳ? የነበረ!” እንደሚባለው” – ኤርምያስ ለገሠ ካለፈው በመነሳት እንደበለተው።

በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈረጠሙን? Whose power to exercise? We see in the video TPLF bosses giving their handiwork the instruction, which he obediently summed up in his conclusion, as Ermias Legesse picked up the cues!

ሕውሃት የፖለቲኮ-ወርታደራዊ-ንግድ ኩባንያ በመሆኑ፣ ነገ የባሰ የዘረፋውን መረብ ዘርግቶ ሲመጣ፡ ማንኛውም ዜጋ በየፊናው ግር ሳይለው ራሱንና ቤተሰቡን እንዲሁም ሃገሩን ለመከላከል ያስችለዋል።

ካለፈው ምርጫ በኋላ ትግራይ ውስጥ የተፈጸመውን ወረዳ ሥራ እንመልከት! አባይ ወልዱ የክልሉ ፕሬዚደንት የእርሱንና የጓዶቹን ዘረፋ ሌላ ሰው እንዳያጋልጥባቸው፡ ሚስቱን ትርፉ ኪዳነማርያምን የጸረ-ሙስና ሃላፊነት ሾሞ ቁጭ አለ!

ይህ እንዴት የመልካም አስተዳደር ምልክት ሆኖ ነው ደፍረው ያላነሱት!

እነዚህ ሰዎች ናቸው ለ25 ዓመታት አንዳችም ዘመናዊ አስተዳደር ለመመሥረት ሳይችሉ፡ አሁን የመልካም አስተዳደር ከበሮ መደለቃቸው ፋይዳ ቢስ ማምታቻ ነው!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቅ የሚገባው፡ በጫንቃህ ላይ የተንሠራፉት ዘረኛ ወራሪዎችና ሃገር ቆራሽና ቸርቻሪዎች፡ ሲዘርፉህ ተመስገን ብለህ እንድትንበረከክ፡ ሲነጥቁህ ቤትህንና መሬትህን ጸጥ ብለህ እንድታስረክብ ይጠብቃሉ! የአሁኑ ቁጣህ መግቢያ መውጫ ስላሳጣናቸው ነው የአሁኑ የመልካም አስተዳደር ዳንስና ዳንኪራ አስፈላጊ የሆነው!

ለነገሩ የሕግ የበላይነት በሌለበት፣ ሕዝቡ በነጻነት ራሱን መግለጽ በማይችልበት እንዴት መልካም አስተዳደርና ችግሮቹ ተነስተው መፍትሄ ለመስጠት ይቻላል?

The Ethiopia Observatory (TEO)

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: