The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

አሁንም ( ሄኖክ የሺጥላ )

henock-yeshitla

አጃኢብ ነው ! ይሉ ነበር የሰፈራችን አረቦች ! አጃኢብ ነው! በኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን ሕዝብ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚሻበት ወቅት ላይ ነን ያለነው፣ በየቀኑ ሰዎች እየሞቱ ነው ፣ እናት የልጇን የቀብር ጉድጓድ እና የኛን ጉድ እያለቀሰች ስታሳይ አይተናል ። ከኛ አልፎ ምስጢሩ ትናንት መንግስታችንን ለ G-8 ስብሰባ በምግብ ራስን በመቻል ብለው ሲያጩት እና ሲያሳጩት የነበሩ ሃገራት ሳይቀር መለመላችንን የቀረን ፣ አንዳች የሚላስ የሚቀመስ የሌለው 15 ሚሊዮን ነብስ ዋይ ዋይ እያለ እንደሆነ መስክረዋል ፣ የምንታጭ ሳይሆን የጫጨን እና የቀጨጭን መሆናችን ደሞ እየተረኩ ነው ። ያም ሆኖ <ረሃብ ጊዜ አይሰጥም> የሚለው አባባል ግን ዋጋ ያገኘ አይመስልም ። እነ ወያኔ ጸጥ ብለዋል ፣ ወያኔን የወለደው ሕዝብም ፣ መንግሥቴ ከሚጋለጥ እና ተጋልጦ ከሚገለበጥ እኔ ገላ ላይ አፈር ይገልበጥ ያሉ ይመስላሉ ። በራብም ቢሆን ሞተው እሱን ለማጽናት ፣ ስርዓቱን ለማቆየት የቆረጡ ይመስላሉ ። ለመሞት መወሰን መብታቸው ነው ፣ በኛ ሕይወት ግን አይቀልዱ !

አዎ ጸጥታው ከላይ በወረደ ቀጭን ትእዛዝ የሚተገበር አንድ የዝምታ መዋቅር ነው የሚመስለው ። አባይ ይገደባል ፣ እያሉ ሲፎክሩ የነበሩ አርቲስቶች ፣ ሽርጥ አንገታቸው ላይ ለብሰው ሲፎክሩ እንዳልከረሙ ፣ ዛሬ የአባይ ዳር ልጆች ሲራቡ የት ገቡ ? ምነው ጸጥ አሉ ? ባለ ራእይ ፣ አባይን የደፈረ ፣ ታላቁ መሪ እና ወዘተ እያለ እብቅ እብቅ እየተነፈሰ መርዶውን የነገረን የኢቲቪ ጋዜጠኛ ወዳጃችን ተመስገን የት ሄደ ? አማረ ማሞ አዲስ ባያሰፋ እንኳ ለመለስ ቀብር የለበሰውን ጥቁር ልብስ ምነው ለ 15 ሚሊዮን ረሃብተኛ መልበስ አቃተው ? የሰይፉ ፋንታሁንን ሰርግ የደገሰው ፣ የ 6 ሚሊዮን ብር የጋብቻ ቀለበት የገዛው ባለ ሀብት ምነው ስለ ድርቁ አንዳች ነገር አልተነፍስ አለ ? ወይስ በድርቅ ከተጠቁት ውስጥ አንድ ሁለት ልጃገረድ እራሳቸውን እስኪሰዉለት ድረስ የሚሞተው ይሙት ? አረ ዲያቆኖቹ የት ገቡ ? ያኔ ጀማል አይደልም ኤፍሬም ነው እያሉ ሕዝብ ሲያንከላውሱ የነበሩት ፣ ነገር ሲቆምሩ የከረሙት ፣ እንደ ክርስቲያን ፣ እንደ አንድ ኢትዮጵታዊ ይህን ያህል ሕዝብ ሲራብ ምን ጻፉ ? ምን ተናገሩ ? ምን መሰከሩ ? ወይስ የብርቱካን ልጅ አብዱ እስላም ስለሆነ አይመለከተንም ብለው ይሆን ? ማን ያውቃል !

እነ ሰይፉ ፋንታሁን የት ገቡ ? ለመቅዶንያ ምናምን ታህል ብር ከሰርግ መደገሻቸው ላይ አንስተው እንዳልሰጡ ፣ ዛሬ ምነው ጭጭ አሉ ? ማለቴ ደግ ከነበሩ ፣ የተቸገረ ካሳሰባቸው ? የህዝብ ራብ ሰላም ከነሳቸው ለምንድን ነው አንድ ነገር ሲሉ የማንሰማቸው ? ወይስ እነሱም እንደ ቴዎድሮስ አድሃኖም ድርቅ እንጂ ራብ የለም ብለው ስለሚያምኑ ነው ? የሞተ ከብት እንጂ የሞተ ሰው የለም ብለው ስለሚያምኑ ነው ።

በነገራችን ላይ ቴዎድሮስ አድሃኖም < የሞተ ከብት እንጂ የሞተ ሰው የለም ሲሉ > አንድ ነገር ወደ ጭንቅላቴ መጣ ። ጓድ ቴዎድሮስ አባባሎት ፍጹም ውሸት ወይም ስህተት ነው ለማለት አልደፍርም ፣ ግን ሀሳቦትን ወይም አስተያየቶትን በክልል ይክፈሉልን ። እርግጥ በአንዳንድ ክልል ያሉ ሰዎች ዘንድሮ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ እንስሳ እንደሚያስቡ ደርስንበታል ፣ ስለዚህ ፍሬ ነገሮ ለሱ ጥሩ ትንበያ ይመስላል !

ወያኔን እቃወማለሁ የሚሉት እነ ምናምን ሚዲያ የት ገቡ ? ክንፈ ገ/መድህን በድርቅ ከሞቱት 15 ሚሊዮን ህዝቦች አንዱ ሆነ እንዴ ? የኛ ነገር !
ባሩድ የተሞላ በርሜል ላይ የምደንሰው ባእዴን እና ባሩድ ላይ የሚያስደንሰው ወያኔ ትግሬ ፣ እዬዬም ሲዳላ ነው የሚለውን ተረት ምነው ፈጽሞ ዘነጉትሳ ?
በፈረንሳይ ሀገር በደረሰው የአሸባሪዎች ቅጣት ልባቸው የተነካ የትግራይ ተወላጆች የፈረንሳይ ባንዲራን የፌስ ቡክ ገጸ-ምስል በማድረግ ሃዘናቸውን ሲገልጹ አይቼ

1ኛ ለማያውቅሽ ታጠኝ አልኩ
2ኛ የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች የሚለውም አብሮ ትዝ አለኝ
3ኛ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ከበሮ በሰው እጅ ያምር ሲይዙት ያደናግር የሚለውም ትዝ አለኝ !
ለማንኛውም የ 15 ሚሊዮን ሕዝብ ስቃይ ያልታያቸው የፈረንሳይ የአሸባሪዎች ጥቃት ልባቸውን ያደማቸው የትግሬ -ወያኔዎች አንድ ቀን የምንለው በደንብ የገባችሗል ።
ትንሽ ቀልድ ልጨምር
አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ( የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ልጅ ወይም የ አቶ ታደለ ይድነቃቸው አባት ) አንድ አብሮ አደግ ወዳጅ ነበራቸው ። ታዲያ ይህ አብሮ አደግ ወዳጃቸውን ባንድ ወቅት መንገድ ላይ ያገኙትና
” ጃል እንደው ስንት ዓመት ሆነህ ?” ይሉታል ። ወዳጃቸውም ” 29 ” ሲል ይመልሳል ። በል ልጆችን ባለቤትህን ሰላም በልልኝ ብለው ይሰናበቱታል።
ከ 10 ዓመት በሗላ አቶ ይድነቃቸው ይህንኑ ወዳጃቸውን መንገድ ላይ ያገኙታል
” እንዴት ነህ ጃል ? ”
ወዳጅ ይመልሳል ” ክብሩ ይስፋ ለመድሃኒያለም !”
አቶ ይድነቃቸው ” እንደው ብዙ ጊዜ ሆነን ሳንገናኝ ፣ መቼም ልጆችህ አድገዋል ፣ ባያቸውም ላውቃቸው !”
ወዳጅ ” አዎ ማን ያለበት ቆሞ ይቀራል ብለው ነው !”
አቶ ይድነቃቸው ” እሱስ እውነት ብለሃል ፣ እንደው ስንት ዓመት ሆነህ ?”
ወዳጅ ” 29 ”
አቶ ይድነቃቸው ” አሁንም ?”
ወዳጅ ቆጣ ይልና ” ምኑ ?”
ነገሩ የገባቸው አቶ ይድነቃቸው እንዲህ ሲሉ ይመልሱለታል ” እርግጠኛ ነኝ አንድ ቀን 30 ትገባለህ !”
ታዲያ እኔም የትግሬ ወያኔን ነገር ሳስብ ፣ ዛሬም ስለ እድገት ፣ ስለ ብልጽግና ፣ ስለ ግድብ ፣ ስለ ፋብሪካ ሲያወሩ ስሰማ ” አሁንም ?” ማለት አማረኝ። በሞቴ አሁንም ስለሱ ታወራላችሁ ?
ቸር ይግጠመን !

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: