The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የዞን 9 ጦማሪው ዘላለም ክብረት ከሃገር እንዳይወጣ ታገደ

zelalem Kibret

(ዘ-ሐበሻ) የባራክ ኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት ተከትሎ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ከተከሰሰበት የሽብር ክስ በነፃ የተሰናበተው የዞን 9 ጦማሪው ዘላለም ክብረት ከሃገር እንዳይወጣ በደህንነቶች ፓስፖርቱን ተቀምቶ መመለሱ ተሰማ::

ዘገባዎች እንደሚሉት ጦማሪው ዘላለም ክብረት ድንበር የለሽ የዘጋቢዎች ተቋም (Reporters Without Borders) በፈረንሳይ ሃገር ሊሸልመው የጠራው ቢሆንም ወደዚያው ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ቢደርስም ፓስፖርቱን ተቀመቶ እንዲመለስ ተደርጓል::

የዞን ዘጠኝ ጦማሪው ዘላለም ክብረት ፓስፖርቱን ቀምተው ወደ ውጭ እንዳይወጣ የከለከሉት የደህነነት አባሎች ምክንያታቸውን ያልገለጹለት ሲሆን በፍርድ ቤትም ክሱ ተቋርጦ እንደወጣ ምንም ዓይነት ከሃገር እንዳይወጣ እግድም ሆነ ገደብ እንዳልተሰጠው የዘ-ሐበሻ ምንጮች ለማወቅ ችለዋል::

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካለፍርድ ቤት ት ዕዛዝ የትኛው የመንግስት አካል እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ ስውሩ መንግስት የሚፈልጋቸውን ሰዎች ከሃገር እንዳይወጡ በማሰቃየት እንዲሁም በማህበራዊ ሕይወቶቻቸው ውስጥ ጣልቃ በመግባት እንደሚያሰቃይዋቸው ይታወሳል:: ከነዚህም መካከል አንዱ ድምፃዊው ቴዲ አፍሮ ነው:: ቴዲ አፍሮ ከዚህ ቀደም ፓስፖርቱን ተቀምቶ ከአንድ ጊዜ በላይ የውጭ ሃገር ኮንሰርቶቹን ለመሰረዝ መገደዱ ይታወሳል::

Zehabesh.com

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a comment