በረሃቡ ዙሪያ ሪፖርተር እንደዘገበው – የሚሊዮኖች ድምጽ

ሪፖርተር ጋዜጣ ከዚህ በፊት በአፋርና በሶማሌ ክልል እንዳደረገው፣ በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር፣ በረሃቡ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ጠቃሚ ዘገባ ለአንባቢያኑ አቅርቧል። በዘገባው የቀረበው በጣም አስፈሪና አስደንጋጭ ነው። አስችቸኳይ ርብርቦሽ ካልተደረገ እጅግ በጣም አስከፊ ሁኔታ ነው የሚፈጠረው። በትግራይ የሚኖረው ሕዝብ ወደ 6 ሚሊዮን የሚደርስ ነው። ከ38 ወረዳዎች በሃያው ፣ እክስድስትት ሚሊዮን ክአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ እንደ ሪፖርተር አባባል “የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል።
ሪፖርተር በዘገባ ካጠቀሳቸው ወረድአዎች መካከል የአጽቢ ወረዳ ነው። ይሄ ወረዳ የጦማሪ አብርሃ ደስታ ወረዳ ሲሆን፣ በፓርላማም የዚህ ወረዳ ተወካይ የተከበሩ ዶር ቴዎድሮስ አዳኖም ናቸው። ዶር ቴዎድሮስ እንኳን በፓርላማ የወከላቸው የአጽቢ ሕዝብ ስቃይ ሊሰማቸውና በወረዳዉም ሄደው ህዝቡን ሊጎበኙ ቀርቶ፣ በአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ እንደተናገሩት፣ “አንድ ሰው የሞተ የለም፤ ስምንት ሚሊዮን ሕዝብ ለረሃብ ቢጋለጥም 88 ሚሊዮን ህዝብ አልተራበም” በሚል ችግሩን በማቃለልለ የአደባባይ ዉሽት ተያይዘዋል።
የፓርላማ ተወካይ ዶር ቴድሮስ “ሰው አልሞተም” ቢሉ ‹‹የድርቁ ሽፋን እየጨመረ በአብዛኛዎቹ ዞኖች በግልጽ ከመታየቱም አልፎ፣ ብዙዎች ለከፋ ረሃብና የውኃ እጥረት ተዳርገዋል፡፡ እኔ በበኩሌ ከመቐለ ወጣ ብሎ በእንደርታና በአካባቢው ያለውን ችግር ለማስተዋል ሞክሬያለሁ፡፡ አምዶራታ በሚባል አካባቢ እንኳን ሦስት ሰዎች መሞታቸውን ከነዋሪዎቹ ተነግሮኛል፡፡ በቅርቡ ደግሞ እንዲሁ አንዲት ሴት በሴፍቲኔት አማካይነት የሚደርሳት ዕርዳታ በመቋረጡ ለሞት ተዳርጋለች” ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ አትቶ አምዶም ገብረስላሴን ጠቅሶ ዘግቧል::
ሪፖርተር ጋዜጣ በተከታታይ የረሃቡን ጉዳይ ለሕዝብ እየተከታተለ እንደሚያደርስ ያለንን ተስፋ እየገለጽን፣ እስከ አሁን ለተደረገዉም ምስጋናችንን እናቀርባለን።
posted by Gheremew Araghaw