The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ልጆች በጥይት አይቀጡም። የትኛው መንግስት ዛሬ ተማሪዎችን በጥይት ይደበድባል? (ቢላል አበጋዝ)

ቢላል አበጋዝ / ዋሽግተን ዲ ሲ ዓርብ ፣ ዲሴምበር 4 ቀን 2015   ዛሬ የዓለም መሪዎች በፓሪ ፈረንሳይ ስለ ዓለማችን ያየር ንብረት ችግሮች እየመከሩ ነው።ችግሩ ደግሞ ቀድሞ ሰለባ ያደረገው ደሃ አገሮችን መሆኑ ግልጽ ነው።ኢትዮጵያም አንድዋ ናት።ከኢትዮጵያ ህዝብ አስራ አምስት ሚሊዮን ለራብ መጋለጡ መደበቅ የማይቻል እውነት ነው።ወያኔ ሃላፊነት ያለው መንግስት ቢሆን እዲህ ጊዜ የማይሰጥ ችግር ላይ ያተኩር ነበር።የአስራ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ለራብ መጋለጡን የአውሮፓ ህብረት ጉዳዬ ብሎ ሲመክርበት ህወሃት ይህን ችግር ከፖለቲካ ተቃውሞ መለየት ተስኖት ከውይይቱ እንኳን ለመሳተፍ አልመረጠም።ካአየር ንብረት ችግሩ እጅግ የከፋው የአስተዳደር ጉድለቱ የሚፈጸመው ግፍ ነው በኢትዮጵያችን።ኢትዮጵያ መንግስትዋ ሽብርተኛ ያየር ንብረት ችግሯ በጣም ፈታኝ የሆነበት ዘመን ዛሬ ነው።ያየር ንብረት ችግር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ልጆችዋን እየገበረች ነው።ልጆች በጥይት ይቀጣሉ።የህወሃት ግፍ ይህ ነው።   ህወሃት የዛሬውን አይበለውና የትግራይ ህዝብን አታግልለታለሁ ሲል “ሃረሽታይ ሸቃላይ” ወይም አርሶአደር ላብአደር ይል ነበር። ለህዝብ እንደቆመ ሁሉ።ዛሬ “መሬት ላራሹ”ን ተረተረት አድርጎ የኢትዮጵያን አርሶ አደር መሬት ንብረቱን ቀምቶ እያራቆተው ይገኛል። ከአርሶ አደሩ አብራክ የወጡትን ልጆቹን ለአርሶ አደሩ በደል ቢነሱ በጥይት ይደበድባቸዋል። የዓለም ዜና ይህን ባያተኩርበትም ዛሬ የኢትዮጵያ ሁኔታ በከፋ መጠን እየተናጋ መሆኑን ማንም ሊክድው አይችልም።በዓለም ተበትነን ያለነው ዜጎች በየሰዓቱ የምንከታተለው ይህንኑ ነው።   ማንም ህብረተሰብ ቀጣዮን ትውልድ ያስተምራል።ፈደል ተቆጥሮ፤ሂሳብ ተምሮ፤ ቋንቋ ሰዋስው አጥንቶ፤ሳይንስን ተቃምሶ የህብረተሰብ ጥናት ታሪክንም ለካክፎ ወደከፍተኛ ትምህርት ማምራት አለ።ከፍተኛ ትምህርት አንድ ህብረተሰብ ለወጣት ዜጋው የሚያቀርበው ትልቁ የውቀት ገበታ ነው።አላፊነት የሚሰማው አገሩን የሚወድ ትውልድ የሚዘጋጅበት፤ራስንም ዓለምን ለማወቅ የሚሞከርበት የድሜ ዘመን የሚልፍበት ነው ማለት ስተት አይሆንም።በከፍተኛ ትምህርት ቅጥር ውስጥ እማይጠየቅ የለም።እማይፈተን የለም። ሁሉም በነጻነት ይፈተሻል።ይሞከራል።ጉልበት፤ ስልጣን አለው ተብሎ የሚፈራ የለም።በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሁሉም ይተቻል።ይጠናል።ይተነተናል።የበደለም ይኮነናል።ለውነት ለፍትህም ቆምን ይባላል።ዛሬ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተቃውሞ ቢወጡ ለአገር ለወገን ብለው ነው።ተቃወሞ ወግ ነው።ልጆች ስለተቃወሙ በጥይት አይቀጡም።የትኛው መንግስት ዛሬ ተማሪዎችን በጥይት ይደበድባል ? ፈሪው ህወሃት ብቻ!ጨካኙ ህወሃት ብቻ!ከፖለቲካ ድርጅትነት ዘቅጦ የእጽ ሻጭ ካርቴል የነብሰገዳይ ጥርቅም ዓይነት የሆነው ህወሃት ብቻ!   ህወሃት መሩ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ቅጥር ግቢን የሞት አውድማ ያደረገው ገና ድሮ ነው።የመለስ ዜናዊም “ሌጋሲ” “ትሩፋት” አንዱ ይህ ነው።ሰሞኑን በሀረር ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሆነው ዘግናኝ ነው። በሌሎቹም ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁ። የህወሃት አገዛዝ ከጅምር አካሄዱ ይሄው ጥፋት ነበር።በዘውዱ ስርዓት ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ቅጥር ሲገባ እጅግ ይኮነን ነበር።ወታደራዊ ደርግም ወጣቱን በቀይ ሽብር ቢጨፈጭፍም እዲህ እንደ ህወያት መሩ መንግሰት ዩንቨርሲቲውን የጦር ቀጠና አላደረገውም ነበር።ህወያት መሩ መንግሰት ቁንጮ ላይ ያሉት ጥራዝ ነጠቅ የዛሬ ተራ ቀማኞች “መሬት ላራሹ” ካለው ትውድ እንደመር ይሉ ይሆን ?ያትውልድ ህወያት የሚባል ጉድ ትቶ አለፏል።ግን የኢትዮጵያ ተማሪዎችን አኩሪ የትግል ታሪክን ህወሃት አይሽረውም።እዚህ ቀጣይ የሞት ሂደት ውስጥ የከተተው የቀማኛ ቡድንን አስወግዶ የዜግነት ክብር የነገሰባትን፤እኩልነት የሰፈነባትን ነጻ ኢትዮጵያ ከህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ጋር በመሆን ይመሰርታል።እልሙ ኢትዮጵያ! ናት።ድል የሚገኘው በህብረት ትግል እንደሆነ ይገነዘባል።   የኢትዮጵያ ተማሪዎች ቀድሞ ሲነሱ ኢትዮጵያ! ነው ያሉት።”መሬት ላራሹ” የተባለው ለትግራዩ፤ለኦሮሞው፤አማራው፡ለአፋሩ፤ለሱማሌው ለደቡቡ ለሁሉም ነው፤የህወሃት የአዲሱ አገዛዝ አናት ላይ መሆን እንጂ ”መሬት ላራሹ” ዛሬም ፍቺ ያላገኘ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው።የምናየውን እልቂትን የሚገፋው ምክንያት ይሄው ነው።”አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ?” ቴዲ አፍሮ ጨርሶታል። እኩይ ንጉስ ነው የመጣ!   በኦሮሚያ ክልሎች የሆነው ከላይ ያልኩት ነው። የከፍተኛ የትምህርት ገበታን የሞት አውድማ ማድረግ ነው ።ተማሪዎች ልክ ድሮ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንደታገሉት ሁሉ “መሬት ላራሹ” ብለው ዛሬም እየታገሉ ነው።የወገንን መሬት “ኢንጉርጉረምቱ!” አይሸጥም ! ነው ያሉት።ጥያቄው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ሁሉ ጥያቄ ነው።በተለይ የኦሮሚያ ክልል ብቻ ብሎ የሚፈረጅ አይደለም።የአፋሩ፤የጋምቤላው በደል ከአማራውና ከኦሮሞው የሚለይ አይደለም።   የገጠመንን ችግር የከልል ማድረግ የኢትዮጵያን ሁኔታ ጠንቅቆ አለመረዳት ነው።የልጆቻችን ተስፋም እመረቃለሁ፤ ለማዕረግ እበቃለሁ እንጂ እሞታለሁ መሆን አይገባውም። የልጆቻችን ሞት የኢትዮጵያዊ ወገናችንም ሁሉ ሞት ሊያገሸግሸን ይገባል።ኢትዮጵያ ተበደለች። ልጆችዋን ገበረች።ተምሬ ወግ ማእረግ አይባታለሁ የምትባለዋን ኢትዮጵያን የምናይበት ጊዜው እሩቅ አይሆንም።የሚጠይቀው ህብረታችንን ብቻ ነው። ህወሃት መሩን መንግስት ተባብረን እንሸኝ።ከዚህ ወዲያ ድርድር የለም።   የኦሮሚያ ክልልን መዝረፍና ማስዘረፍ የአማራውን ክልል የሞት፤የቃጠሎ የእስራት ቀዬ ማድረግ በሁለቱም የኢትዮጵያ አካሎች ላይ የዘር ማጥፋት ወጀልን ወደ መፈጸም የሚቀርብ ክፋት ነው።የጎንደር ህዝብ በደል የኢትዮጵያ በደል ነው።በተለይ አጠገቡ ለሆኑት የትግራይና የወሎ ህዝቦች በደል ነው።ጎንደርን መሸንሸን እንደምን ይሆናል ? የኢትዮጵያ አንድነት ምንጭ መሰረቱን ?! የወልቃት አልበቃ ብሎ ቅማንትን! ከወንድም እቶቹ ማጋጨት ?ወሰን ድንበር ለባዕድ ለመለገስ ሸር ጉድ? አዲሳባን እናስፋ በማለት ዝርፊያ አሁን ይቁም! ራብም እየፈጀን ልጆቻችንም እየሞቱ እየተቃጠልን እየደማን እስከ መቼ? ወገኖቼ።ዘረፋው እስከመቼ? ምን እንጠብቃለን።   ለደሃው የኢትዮጵያ አርሶ አደር አለኝቶቹ ዛሬ በዳያስፖራ የምንገኝ ነን! በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህወሃት ገዳዮች የሚፈጽሙትን በህብረት እናውግዝ ኢትዮጵያን ከክፉ መከራ አላህ የሰውራት! ሁላችንም እየጸለይን እንታገል! – See more at: http://www.zehabesha.com/

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: