The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የህዝብ ድል ጭልፊቶች

East Hararge 3

 

ከአንተነህ መርዕድ

የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቆናን በመቃወም ትግል ከጀመረ ቆይቷል። ዋናዎችን የ 1966፣ 1983 እና 1997 ዓ ም የህዝብ ድሎች የተነጠቁት ራሳቸውን በህዝብ ትከሻ ላይ ለመጫን በተዘጋጁ ጭልፊቶች ነው። መንግስቱና ጓደኞቹን ቀጥ ብለው ወደ ጨፍጫፊ ፋሺስትነት ይለወጣሉ ብሎ የዋሁ ኢትዮጵያዊ አልጠበቀም። ያደረሱንት መአት መዘርዘር አያሻም። ጫካ ውስጥ ጓደኞቻቸውን እያረዱና ተቀናቃኞቻቸውን እያጠፉ የመጡት ወያኔዎች ይህን ያህል ዘረኛ ሆነው አገር ለማፍረስ ያሴራሉ ብሎ ብዙሃኑ አልጠረጠረም። በ1997 ዓም ምርጫም ወያኔዎች ገሃድ የወጣ ፋሺስታዊ እርምጃ ወስደው የህዝቡን ልጆች በመጨፋት ብቻቸውን ለዘለዓለሙ ለማንገሥ ይህንን ሁሉ ጥፋት ያደርሳሉ፣ እዚህም ይደርሳሉ ብሎ ባለማሰብ አብዛኛው ህዝብ ተዘናግቷል።

East Hararge 3

ወያኔና ደርግ ብቻ ሳይሆኑ የህዝቡን ድል ለመንጠቅ ያሰፈሰፉ በርካታ ጭልፊቶች ነበሩ። በተቃውሞ ጎራ አለን የሚሉ በደርግ ጊዜ የነበሩ ድርጅቶች ሆኑ ያሁኖቹ ነጣቂ ጭልፊት እንዳይሆኑ ምን ዋስትና አለ? የልደቱን ገናናነትና እውነተኛ ማንነት ተመልከቱ? ኸረ ብዙ ስም አይጠሬዎች አሉ? ዛሬ ህዝባዊ አመፅ ሲቀጣጠል ራሱን የተቀጠቀጠ እባብ አፈር ልሶ እንደሚነሳው ሁሉ ብዙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ከእንቅልፋቸው (ሃይቨርኔሽን) ነቅተው አሮጌ ማንነታቸው ላይ አዳዲስ ቀለም እየቀቡ ብቅ ማለት ጀምረዋል። በዚያ ሁሉ ጊዜ ህዝቡ ተታለለ ብልም ፍርሃታቸውን የገለፁ፤ተጠንቀቁ ባዮች ( ፈረንጆች ዊስል ብሎወርስ ይሏቸዋል) ኢትዮጵያውያን ጥቂት ቢገኙም ሰሚ አላገኙም። ባለመስማታችን፣ በድንቁርናችን ብለው ይሻላል፤ አሁን አለንበት አዘቅት ውስጥ እንገኛለን።

 

ጨለምተኛ አትበሉኝ። አይደርስም ከማለት ይደርሳልን ማሰብ ጥሩ ነው። በተለይ እንደኛ ላለ ደጋግሞ ለወደቀ። በተቀጣጠለው ህዝባዊ ትግል መስዋዕት ከፋዩ ምስኪኑ ዜጋ ነው። ወያኔ ገና ከዚህ የመረረ መስዋዕት ሊያስከፍል ቆርጦ የተነሳ አረመኔ ድርጅት ቢሆንም፤ ህዝቡም ኑሮው ከሞት ያልተለየ በመሆኑ ወደፊት ሄዶ ጠላቶችን አደባይቶ የራሱን እድል ለመወሰን ከመግፋት የተሻ የሚያፈገፍግበት ብሩህ ተስፋ የለውም። ወያኔዎች እንደሚወድቁ ለማወቅ ነብይነት አያስፈልግም። በተለይም አሁን። ታድያ ትግሉን ህዝቡ ተያይዞታል። አምባገነን ስርዓትን በብዙ መስዋዕት መጣል ለኢትዮጵያ ህዝብ ማስተማር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል።  ከጎኑ ሆኖ ማገዝ የቅን ዜጎች ተግባር ቢሆንም  ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ተቆርቋሪ የህዝብ ልጆች ትልቁ ትኩረት የድል አጥቢያ አርበኛ ሆነው የሚመጡ ጭልፊቶችን መጠበቁ ላይ ቢሆን ይበጃል። ኢትዮጵያ ከደቡብ ጫፍ እስከሰሜን፣ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ ያሉትን ዜጎች ታካትታለች። የነዚህን ሁሉ የጋራ ፍላጎትና ጥቅም የያዘ ውጤት ለማምጣትና ያንንም ለማስከበር በንቃት የሁሉንም ተሳትፎ መጨመርን ይጠይቃል።

 

አገር ውስጥ ሆነ ውጭ አለን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ትግሉን ለመምራት ህዝብ መካከል መገኘትና መስዋዕቱንም በመጋራት ካልተዋሃዱ በድል ጊዜ እጅ ታጥቦ መቅረብ የትም አያደርስም። መግለጫ በመስጠት ስም ማስመዝገብም ፋይዳ አይኖረውም። በምድር ላይ ያለን ትግል ወርዶ መምራት የሚጠይቅበት ጊዜ ነው። በተለይ ሰሞኑን ሁሉም የአንደንት፣ የትብብር፣ የመስዋዕትነት አቀንቃኝ ሆኗል። ጥሩ ነው። ከሁሉም በላይ የሚጨበጥ የተግባር አንድነት አሁኑኑ ያስፈልጋል። አዎ ይህንን ጨለማ እጅ ለእጅ ካልተያያዝን የምንወጣው አይደለም። ግን ይህንን ማወቅ ብቻ ፋይዳ የለውም። ግዙፉን የኦሮሞና የአማራ ጥቅም እናራምዳለን የምትሉም ሆነ ሌሎች የህዝቡን ያህል ልበ ሰፊ፣ ታጋሽና ለሌሎች አሳቢ ሆናችሁ ካልተገኛችሁ ሲነጎድበት በቆየው ስሜታዊ አካሄድ የትም አትደርሱም። መከራውን በጋራ የተካፈለ ይህ ህዝብ ድሉንም በጋራ ሲያገኝ ነው ዋስትናው የሚጠበቅለት። ህወሃት የትግሬን ጥቅም እንዳላስጠበቀ ሁሉ እናንተም የዞጋችሁን ጥቅም እንደማታስጠብቁ በቂ ተመክሮ አለ። የሌላውን ኢትዮጵያዊ መበደል ለማየት የተጨፈነ ዐይን አለሁልህ የሚለውን ህዝብም ሊያይ አለመቻሉን ከህወሃት ተማሩ። አብርሃ ደስታ የት ነው ያለው? ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እኩል ማየት ይቅርና ትግሬውን እንኳ እኩል የማየት ብቃት የላችሁም በማለቱ ትግሬነቱ ከህወሃት በትር አላዳነውም። በየዞጋችን ተኩላዎች አሉ። ሌላውን ለመንከስ ሲዘጋጁ ካየን ውስጣቸው አራዊትነት አለና እንጠብቃቸው።

ጭልፊቶችን እንጠብቅ

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: