The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ኢሳት ቴሌቪዥን፣ OMN ቴሌቪዥን፣ የአሜሪካ ራድዮ ድምጽ፣ ዘሐበሻ ድረ ገጽ፤ በወያኔ መንግስት በቢሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ በኢትዮጵያ እንዳይታዩ ከፍተኛ የሆነ አፈና እየተደረገባቸው ነው። – ከተማ ዋቅጅራ

media

ፌድራል ፖሊስ እንደ ሸለምጥማት ጣራ ለጣራ በመንጠላጠል ዲሽ ሲነቅል ማየታችን ስርአቱ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳለ የሚያሳይ ነው። ዛሬ ዲሻችንን እንደነቀላችሁ ነገ እናንተ ትነቀላላችሁ ዛሬ መብታችንን እንደረገጣችሁ ነገ የእናንተ  እጣ የከፋ እንደሚሆን አትዘንጉ።

አፈናን ዋና አላማው አድርጎ  እየተንቀሳቀሰ ያለው ወያኔ በአገር ቤት ሆነ በመላው አለም በከፍተኛ ሁኔታ አድማጭ እና ተከታዮችን እያፈሩ ያሉትን ነጻ የህዝብ ሚዲያ  አካሎችን የአገሪቱ ንብረት እየዘረፈ በቢሊዮንስ ዶላይ በማውጣት ወንጀል ከመስራት አልፎ ህዝቡ እውነተኛ መረጃን እንዳያገኝ የማፈን ስራዎችን በመስራት ለይ ይገኛል። ወያኔ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ያላቸውን አቅም ሁሉ ለአፈናቸው ተግባር በማሰማራት በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሚዲያ አውታሮች እንዳይሰራጭ ከፍተኛ መፍጨርጨር እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ  መስማት የሚፈልገው እውነትን ስለሆነ ዛሬ በይፋ ለማፈን የሚንቀሳቀሱባቸው የሚዲያ አውታሮችን ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በሚባል መልኩ የነጻ ሚዲያ አድማጭ ሆኗል። ህዝቡም  እውነተኛ መረጃዎችን የሚያገኝባቸው በዋነኛነት ኢሳት፣ OMN፣ የአሜሪካ ራዲዮ፣ የጀርመን ራሪዮ፣ ዘ-ሐበሻ፣ ECADF፣ ሳተናው፣ Gadaa.com፤ ከመሳሰሉት የህዝብ ሚዲያዎች ሲሆን ከነዚህ ነጻና  ትክክለኛ ዘገባዎችን በመዘገባቸው የተነሳ ለህዝቡ ከፍተኛ ግንዛቤ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ምን እየተሰራ እንዳለ በስልጣን ላይ ያለው አካል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን አይነት ጥፋትና በደል በመቀየስ አደገኛ አካሄድ እየሄደ እንዳለ ለህዝቡ በግልጽ በነዚህ የሚዲያ አውታሮች  ሲለሚነገራቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የነዚህ ሚዲያዎች ተከታዮች እና አድማጮች ሆነዋል።

ኢሳት ከጅምሩ ጀምሮ በወያኔዎች  አፈናዎች እየተደረገበት በኢትዮጵያ ውስጥ መሰማት የለበትም ብለው ቢንቀሳቀሱም ኢሳት ግን ከፍተኛ ርብርቦሽ በማድረግ ዜናዎችን ወደ ህዝቡ እንዲደርስ እያደረገ ነው። ኢሳት ለኢትዮጵያ  ህዝብ  ሲተረጎም ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን የሚለውን ትርጉም ሲይዝ ለወያኔዎች እና ለሆድ አደር ካድሬዎች ደግሞ እሳት የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል።  ምክንያቱም አይስማማቸውም ይፈጃቸዋል በጓራቸው የሰሩትን ደባ በአደባባይ ይበትነዋል በምሲጢር ያወሩትን ተንኮል በህዝብ ፊት ያጋልጣቸዋል የህዝብን ችግር እና ሃሳብ በነጻነት ወደ ህዝብ ያደርሳሉ።  በዚህ አጋጣሚ ለኢሳት ጋዜጠኖች በሙሉ ከፍተኛ ክብር ያለኝ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለው።በተለይ ለሲያይ አጌና፣ ለመሳይ መኮንን፣ለፋሲል የኔአለም፣ እንዲሁም ለሌሎቹ ከፍተኛ አድናቆት እና ክብር አለኝ  የእናንተ ክብራችሁ እውነታችሁ፣ ክብራችሁ ኢትዮጵያ አገራችሁ፣ ክብራችሁ ህዝባቹ ነውና በርቱልን እንላለን።

OMN በኤትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰማ ብዙ  ተከታይ እያገኛ ነው። ወደ መጀመሪያው አካባቢ ላይ በወያኔ መንግስት ምንም ተቃውሞ  ያላጋጠመው ነበረ ወደ በኋላ ላይ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ መሰማት የለባቸውም ከሚባሉት ነጻ ሚዲያ ውስጥ ተካቷል። ይህ የሆነበት ደግሞ  የOMN ዋና ዳሬክተር የሆነው አቶ ጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ስልት የገባው በመሆኑ ወያኔን ለመጣል ወያኔ በዘረጋው መንገድ ሄዶ ሳይሆን በተቃራኒው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ሲታገል ብቻ ነው በማለቱ ከወያኔዎች ሃሳብ ጋር በመጋጨቱ በወያኔዎች ጥርስ ውስጥ ሊገባ ችሏል። የወያኔን ዛቻ የማይበግረው ጀዋር ለህዝቡ የሚያስብ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውንም አዋቂ ስለሆነ ስልቱን ወደ ጋራ በመለወጥ ወያኔ የሚፈጽመውን ነገር  የኢትዮጵያ ህዝብ ማሸነፊያው መንገድ አንድነት ብቻ እንደሆነ ስለተገነዘበ ሁላችን የጋራ ጠላታችን ወያኔ ነው በአንድነት እንታገል በማለቱ  ወያኔዎች ስለደነገጡ የመከፋፈል ስራ ለመስራት  ውስጥ ውስጡን በመግባት አማራን እና ኦሮሞን የማጣላት ስራን ሊሰሩ ስለሚችሉ ህዝቡ በንቃት እንዲከታተላቸው እና ይሄንንም ድርጊት የሚሰሩትን  ለፍርድ እንዲቀርቡአቸው በማለት  ሁለቱ ህዝቦች በጋራ መስራት አለባቸው ብሎ  በሳልና የኢትዮጵያ ህዝብ በቀላሉ ነጻነቱን ሊያመጣበት የሚችለውን መንገድ በመያዙ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ በጀዋር ላይ የስም ማጠልሸት ፕሮፓጋንዳ  ቢነዙም ቅሉ አቶ  ጀዋር ግን ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል እናድርግ በማለቱ ፖለቲካው ወደ አሸናፊነት እንዴት እንደሚመጣ የተረዳ ሰው ነው።በOMN ላይ የኦሮሞ  ህዝብ እና የአማራ  ህዝብ ብሎም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የማይነጣጠሉ መሆናቸው እየተዘገበ  በመሆኑ በኢትዮጵያ  ውስጥ እንዳይታይ ወያኔዎች አፈና አድርገውበታል በዚህ አጋጣሚ ለOMN  ጋዜጠኞች አድናቆቴን ለመግለጽ እፈልጋለው በተለይ አብዲ ፊጤ፣ በፍቃዱ ሞረዳ እና ሌሎችንም ሳላደንቅ አላልፍም።  ፍቃዱ ሞረዳ ከመድረኩየእናንተ ክብራችሁ እውነታችሁ፣ ክብራችሁ ኢትዮጵያ አገራችሁ፣ ክብራችሁ ህዝባቹ ነውና በርቱልን እንላለን።

ዘ-ሐበሻን ድረ ገጽ ወያኖዎች የሚፈሩት እና ብዝም ግዜ ከዌብ ፔጃቸው ላይ ለማጥፋት ሲሯሯጡ የነበሩት የሚቀርበውን እውነተኛ መረጃ እና ዘገባ በመፍራት ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነጻነት የሚስተናገዱበት የኢትዮጵያ አለኛታ እውነተኛ ነጻ የህዝብ ሚዲያ ድረ ገጽ በመሆኑ ነው። ዘ-ሐበሻ  ወያኔዎች ካስታጠቃቸው አጋዚ ጦር በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ እውነታነትን በማስታጠቅ ትታወቃለች። ወያኔ ካሰማራቸው አድማ በታኝ የበለጠ ዘ-ሐበሻ  የወያኔዎችን በህዝብ መሃል የቋጠሩትን ተንኮል ቀድማ በመድረስ ትበትናለች በዘሐበሻ ድረ ገጽ ሁሉም ነገር ይስተናገዳል ዜናዎች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ውይይቶች፣ የህዝብ ድምጾች፣ የሙሁራን አስታያየቶች፣ ወቅታዊና ጽሁፎች፣ አገራዊ፣ ፐለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ይነበባሉ። በዘሐበሻ  ድረ ገጽ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነጻነት ለሚዲያው በሚመጥን መልኩ የተጻፉ ስነ ጽሁፎችም ሆኑ እውነተኛ መረጃዎች ያለአድሎ ይስተናገዳሉ። ይህ ደግሞ ለወያኔዎች ትልቅ እራስ ምታት ነው።

ኢትዮጵያዊው ውሸት የግሌ የሚሏት ቴሌቭዝን(ETV) የወያኔዎችን የውሸት ወሬ እንዲሰማላቸው ቢፈልጉም ህዝቡ ግን መልሶ መላልሶ  ነግሯቸዋል። ኢቲቪን ማመን ዘግቶ  ነው፣ ኢቲቪ ውሸት አይሰለቸውም፣ ኢቲቪ ሌባ በማለት ህዝቡ ቢነግሯቸውም ህዝቡን በመስማት እና ወደ እውነተኛ መረጃ ወደ ማስተላለፉ ከመምጣት  ይልቅ የበለጠ ውሸትን ይገልጹበት ጀመረ ሌላው ቀርቶ በኢትቪ መስኮት ብቅ ብለው አንድ አንድ ወያኔዎች የምናየውን እና የምናነበውን ብሎም የምናስበውን መርጠውልን እነሱ የሚሉት ብቻ እንድንከውን  ይፈልጋሉ። ሌላው ቀርቶ  ሼርም ላይክም ማለት እንዴሌለብን ይነግሩናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል የወያኔ ውሸት ካንገሸገሸው በጣም ቆዩቷል ሁሉም በሚያስብል መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚተላለፉት ዜናዎች እና ወቅታዊ ፕሮግራሞች የሚገኝ አንዳችም እውነት የለም። የምንሰማቸው እውነተኛ መረጃ እና ከስሜቱ  አልያም በተመስጦ እየተከታተለ ያለው በዘሐበሻ ላይ እና በሌሎች ነጻ ሚዲያዎች በሚወጡት ዜናዎች ነው። ስለዚህ የዘሐበሻ አዘጋጆችን ላደንቃቸው እፈልጋለው ለኢትዮጵያ ህዝብ በማሰብ ለህብረተሰቡ መረጃን በማቅረብ እና የሚፈለገውን ሁሉ በማስተናገድ ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ የሚያደርሰውን ጭቆና እና አፈና እንዲታወቅ እንዲሁም ታሪካዊ  እና አስተማራዊ ነገሮችን በማቅረብ ለህዝብ ትልቅ ግንዛቤ እያስጨበጣችሁ ስለሆነ እናንተም ላገራችሁ ኢትዮጵያ ማድረግ ያለባችሁን ነገር እያደረጋችሁ ስለሆነ  አድናቆቴን መግለጽ እፈልጋለው።

በመጨረሻም ማፈን የማይሰለቻቸው ወያኔ ህዝቡ ስለ መብቱ ሲናገር ማፈን፣ የሃይማኖት ሰዎች ስለ ሃይማኖታቸው መብት ሲናገሩ ማፈን፣ የፖለቲካ ሰዎች ስለ ፖለቲካ ሲናገሩ ማፈን፣ ነጻ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ እንዳይታዩ  ማፈን፣ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴን ማፈን፣ መብትን ማፈን፣ እንደዚህ ሁሉኑም ነገሮች አፍኖ ምን ያህል ግዜ መቀጠል እንደሚችል አናውቅም ማፈን መልስ አይደለም፣ ማፈን ስልጣንን ማራዘሚያ መንገድ አይደለም፣ ዛሬ ሚዲያዎች ያፈናችሁ ቢመስላችሁ ዛሬ ህዝባ ችንን ያፈናችሁ ቢመስላቹ ዛሬ ነጻነታችንን ያፈናችሁ ቢመስላችሁ ነገ አፋኞቹ ታፍነው ለፍርድ እንደሚቀርቡ አንዳችም ጥርጥር የለኝም። ሁሌም ህዝብ እና እውነት አሸናፊ ናቸው።

 

ከተማ ዋቅጅራ

23.12.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: