The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ፓትርያሪክ አቡነ ማቲያስ “እስከምሞት እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ” ሲሉ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዛቱ

የሐራ ተዋሕዶ ዘገባ እንደወረደ

holy-synod-tik07-on-protestant-reformation

ቅዱስ ሲኖዶስ፡-

 • በምልመላ፥ የደቀ መዛሙርቱ የሃይማኖት ጥንካሬ እንዲታይ አህጉረ ስብከትን አስጠንቅቋል
 • በቅበላና በትምህርት ዝግጅትም፥ ጥራቱና የመምህራኑ ሃይማኖት እንዲፈተሽ ኮሌጆቹን አሳስቧል
 • አህጉረ ስብከቱ ጤናማ ተማሪ ቢልኩም፣ ተመርቀው ሲወጡ “ሌላ ሰው ኾነውና መስለው ነው”
 • በጤና የተላኩ ልጆች መናፍቃን ኾነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል
 • እነማን እንደሚማሩባቸው፣ መምህራኑ እነማን እንደኾኑና መጻሕፍታቸው ሊመረመሩ ይገባል

*          *           *

ማኅበረ ቅዱሳን፡-

 • በየኮሌጆቹ፥ የተሐድሶ ኑፋቄን አስከፊ ደረጃ የሚያትቱ ጽሑፎችን በሚዲያዎቹ አስነብቧል
 • ከተማሪ ምልመላ ጀምሮ የአመራር፣ የክትትልና አያያዝ ድክመቶች በመንሥኤነት ተጠቅሰዋል
 • የኑፋቄው ተጽዕኖ ስለማየሉ የቀረቡት ገለጻዎች፣ በበቂ ማስረጃ መደገፋቸው ተገልጧል
 • ማስረጃዎቹ፥ በ1991 እና በ2004 በቅ/ሲኖዶስ በተላለፉ ውግዘቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል
 • በመተዳደርያ ደንቡ፣ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ትውፊትን የማስጠበቅ ተልእኮ ተሰጥቶታል

*          *           *


ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፡-

 • ማኅበሩን በፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴው ከሚከሡ የኮሌጆቹ ተቃዋሚዎቹጋ ትላንት ተወያይተዋል
 • ማኅበሩ እያስቸገረን ነው፤ በሚል “ከመንግሥት ጋር ተረዳድተን መጣል አለብን” ሲሉ አሳሰበዋል
 • በአሜሪካ ጉብኝታቸው፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊረከብ ትንሽ እንደቀረው መረዳታቸውን ገልጸዋል
 • “ወይ ማኅበሩ ይረከበናል፤ ወይ እኛ እንወርሳቸዋለን” ሲሉ የኮሌጅ ተቃዋሚዎቹን አበረታተዋል
 • ማኅበሩን፣ ደንብ አልባ እንዳደረጉት ጠቅሰው በቀጣይም፣ “የሚኾነውን እናደርጋለን” ብለዋል
 • ቅ/ሲኖዶሱን ለተጋፉ የኮሌጆቹ አካላት፣ አባቶችን በአድመኝነት በማማት እገዛ እጠይቀዋል

*          *           *

በኮሌጆቹ ስም የሚንቀሳቀሱት ሓላፊዎች እና ደቀ መዛሙርት፡-

 • ማኅበሩን፥ በፖሊቲከኛነት፣ በአሸባሪነት፣ በዘረኝነት፣ በደም አፍሳሽነት እና በኑፋቄም ከሠዋል
 • በቅ/ሲኖዶስ የተሰጠው ዕውቅና ተነስቶት በአሸባሪነትና በስም አጥፊነት እንዲከሠሥ ጠይቀዋል
 • የማኅበሩን፥ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስኮላርሽፕ“ኮሌጆቹን ለማዘጋት ያቀደበት ነው፤” ብለዋል
 • ያስመረቃቸውም ደቀ መዛሙርት፥ “ሙስሊሞች ይኹኑ አሸባሪዎች አይታወቁም” ሲሉ አፊዘዋል

Birhane Gebra tsadikan

ብዙዎች፥ በአካዳሚያዊ አቅሙና በማስተማር ክሂሉ “የኮሌጁ ኀፍረት” ነው፤ ይሉታል፡፡ በሓላፊነት ከተቀመጡ ሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋርፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑን እያደራጀ፣ በቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል – በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የማታ መርሐ ግብር ሓላፊውብርሃኔ ገብረ ፃድቃን

በተለይ፣ አስተምረበታለኹ የሚለውን ማስታወሻ ጭምር በተማሪዎቹ እገዛ የሚያዘጋጀው አቅመ ቢሱ እና ቀንደኛ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑ አስተባባሪ ብርሃኔ ገብረ ፃድቃን፡-

 • “ከማኅበሩ ይከፈላቸዋል፤ ሙዝ ይገባላቸዋል” እያለ ብፁዓን አባቶችን ሲዘልፍ አምሽቷል

በጽሑፍ ባዘጋጀው መግለጫው፥ በአንድ በኩል ማኅበረ ቅዱሳንዕውቅናው ይነሳው እያለ በሌላ በኩል ደግሞ ማኅበሩንበፖሊቲከኛነት እየከሠሠ ለአባላቱ እና ለመንግሥት መልእክት ሲያስተላልፍ የነበረው የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ ዲኑ ተስፋይ ሃደራ፡-

 • “ቅዱስነትዎ፥ በሲኖዶስ ስብሰባዎች አጋዥ እያጡ ነው፤ እኔ 150 ተማሪ ይዤ መምጣት እችላለኹ፤” ብሏል፡፡

*           *           *

abune-matyas

የኮሌጆቹ ታዛቢ ሓላፊዎች እና ብዙኃን ደቀ መዛሙርት፡-

 • ካልፈረማችኹና ካልተሰልፋችኹ በሚል በግዴታ ወደ ፓትርያርኩ ቢሮ እንዲገቡ ተደርገዋል፤
 • ለምሩቃን የደመወዝ ጭማሪ እንጠይቅ በሚል የፈረሙበት አቤቱታ ተለውጦ ለሌላ ቀርብዋል፤
 • ፓትርያርኩ ከከሣሾቹ ይልቅ፥ “የዐቅሜን ታግየዋለኹ፤ የሚሰማኝ አጣኹ” ሲሉ አቤቱተኛ ነበሩ፤
 • “በቅ/ሲኖዶስ የወሰኑበትን የተሐድሶ ኑፋቄን አሳሰቢነትና የደመወዙን ጉዳይ እንኳ አልጠየቁም፤”
 • “ሌሎችም አሉ፤ እነርሱንም ላነጋግራቸው አላሉም፤ ውይይት ሳይደረግ በአንድ ጊዜ ዳኛ ኾኑ፤”
 • ማኅበረ ቅዱሳን፥ ለቤተ ክርስቲያን እንደማያስፈልግ፣ ያለጥናት እንደተመሠረተና ዕውቅናም እንደሌለው ተናገሩ፤
 • ሊቃነ ጳጳሳቱንም፥ “በያንዳንዱ ይሔዱበታል፤ ያስጠኗቸዋል፤ አንድ ኹነው አድመው ይመጣሉ፤ እዚኽ አንድ አጀንዳ ሳነሣ ይንጫጫሉ፤ ራሴ ላይ ይወጡብኛል፤” በማለት አምተዋቸዋል፤
 • “አቋም ካላችኹ፣ ቆርጣችኹ ከተነሣችኹ እኔ ማኅበሩን እስከ ሞት ድረስ ነው የምታገለው፤ እስከምሞት ድረስ እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ፤” ሲሉ እነብርሃኔ አስጨበጨቡ፤
 • ትግሉም ከፍተኛ መሥዋዕትነት እንደሚጠይቅና ከፍተኛ ጦርነትም እንደሚከፈት አስገነዘቡ፤
 • “ወሳኝ አካላት ናችኹ፤ የሌላችኹበት አገር የለም” ብለው ከሣሾችን በማበረታታት በቀጣዩ የሲኖዶስ ስብሰባ፣ “ልታስረዱን ትችላላችኹ፤ ከመንግሥት ጋር ተረዳድተን መጣል አለብን፤” ሲሉ አሳሰቡ፤
 • የትግሉ ውጤት እና ፍጻሜም፥ “ወይ እነርሱ ይወርሱናል፤ ወይ እኛ እንወርሳቸዋለን፤ ወይ እርሱ ተረክቦ እንዲመራ ይደረጋል፤ ወይ እኛ እንመራለን፤” መኾኑን አስታወቁ፤
 • ‘ታጥቃችኹ ውጡ፤ እንጋደላለን’ እያሏቸው እኮ ነው፤ ጭፍን ጥላቻ ነው ያላቸው፤ በእውነቱ ለእርሳቸው ይታዘንላቸዋል፤ እኛም ሐሳብ ልንሰጥ ተነጋግረን እንዴት ብለን እንስጥ!
 • ደጋጎች በተቀመጡበት መንበር እንዲኽ ያሉ የወረዱ አባት ስናይ እርሳቸውን ነው፤ ምንም አይጠይቁም፤ አቋም የላቸውም፤ አስቀድሞ የተነገራቸውን ብቻ ነው መልሰው የሚያስተጋቡት፤ ተራ ንግግራቸው መልሶ የሚያስንቃቸው ራሳቸውን ነው፤ ቤተ ክርስቲያኗ ምን ዕዳ ነው የጣለባት??? በጣም አዝነንና ንቀናቸው ነው የወጣነው!!!
 • posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: