The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ወያኔው ግርማ ካሳ ሆይ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

b23ae_Amsalu

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ዘመኑ ምን ቢሸፋፈኑ የማይታወቁበት ዘመን ላይ አይደለም ያለነው፡፡ ይሄንን የማያስተውሉ ሰዉ ሁሉ እንደነሱ ቂል የሚመስላቸው እንደ ግርማ ካሳ ያሉ ቂላቂሎች በርካቶች ናቸው፡፡ “አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል” ይባላል፡፡ አፍ ሲከፈት ጭንቅላት የሚያስበው መነበቡ ነው እንግዲህ ሰውን የቱን ያህል ቢሸፋፈን መደበቅ መሸሸግ እንዳይችል የሚያደርው፡፡ አንዳንድ ጠንቃቆች ደግሞ አሉ አፋቸውን ሲከፍቱ ጭንቅላታቸው እንዳይታይ እንዳይነበብ ለማድረግ ተጠንቅቀው የሚከፍቱ፡፡ አቶ ግርማ ግን አልተሳካላቸውም አልቻሉበትም፡፡

ትላንት ማታ አንድ ግርማ ካሳ የተባለ ወያኔ “መሪዎችን በጭፍን መከተል መቆም አለበት!” በሚል ርእስ የጻፈውን ጽሑፍ በዚሁ ድረገጽ ተለጥፎ ዓይቸ ነበር፡፡ ሰውየው ወያኔ ነው፡፡ ወያኔ ነው ያልኩት የወያኔ አባል መሆኑን አውቄ አይደለም፡፡ በሐሳቡ ለድሀ ልጅ ያዘነ በመምሰል የወያኔን ጥቅም ለማስጠበጥ ስለሞከረ እንጅ፡፡

ሰውየው ዶክተር ብርሃኑን የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ እስከነበረበት ጊዜ ድረስ ቀንደኛ ደጋፊው እንደነበር የትጥቅ ትግሉን ሲመርጥ ግን ድጋፉን እንዳቋረጠ እንዲህ ባለ መንገድ ነበር የገለጸው፡-

““አንድ ጊዜ ትዝ ይለኛል ዶር ብርሃኑ የተናገረው ነገ “እነርሱ ጠመንጃ አላቸው። ይገድሉናል። እኛ የራሳችን ጠመንጃ አለን። የራሳችን ኮልት አለን። ፍቅር የሚባል። በዚያ እናሸንፋቸዋለን” ያለውን አልረሳዉም። ሌላ ጊዜ ደግሞ “ወያኔ በጠመንጃ ካልሆነ በሰላም አይወርድም!” ብሎ አንድ ሲዊድን በተደረገ ስብስበ ሲጠየቅ ዶር ብርሃኑ የመለሰው መልስ አስደናቂ መልስ ነበር “ማንነው የሚዋጋው? የድሃው ልጅ ሄዶ እንዲዋጋ ነው ወይ የምትፈልገው? ያንተ ልጅ ሄዶ ይዋጋል ወይ? ” የሚል መልስ ነበር በመመለሰ ዉጭ ሆኖ ዘራፍ የሚሉትን አፋቸዉን ለጉሞት የነበረው። ሌሎች፣ ሌሎች ፣ በግሌ፣ ደስ ያሰኙኝ አባባሎችን ነበር ዶር ብርሃኑ ይናገር የነበረው። እሥር ቤት ሆኖ የጻፈው መጽሐፍማ አስደናቂ መጽሐፍ ነው። በቺካጎ እኔ ነበርኩ መጽሐፉን ሳሻሽጥለት የነበረው። እና እዉነት ነው የዶር ብርሃኑ አድናቂ ነበርኩ። ዶር ብርሃኑ ግንቦት ሰባትን አቋቁሞ ሲወጣ ግን፣ ልዩነት ተፈጠረ። እንዳደንቀዉ ያደረገኝን ነገሮች በሙሉ የሚቃረንና የሚያፈርስ ሆነብኝ። ልደገፈው አልቻልኩም። በፖለቲካ ተለያየን። ሳልፈራ የእርሱንም ፖለቲካ መቃወም ጀመርኩኝ። ነገ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጥሩ ነገር ከሠራ፣ በሚገባ እደግፈዋለሁ። ለምሳሌ በመጪው የግንቦት ሰባት የዲሲ ስብስበ ጥሩ ነገር ከሰማሁና ከተመቸኝ፣ ደግፌ የማልጽፍበት ምክንያት አይኖርም”” በማለት ነበር አቶ ግርማ ካሳ የተናገረው፡፡

አስመሳዩ ሆይ! ለመሆኑ እነ ዶ/ር ብርሃኑ የሰላማዊ ትግል አማራጭ በሀገራችን የሚሠራ ሆኖ እያለ ነው ወይ የትጥቅ ትግልን የመረጡት? መቸስ ነው በዘመነ ወያኔ ሕዝቡ ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ የአድማ (boycott) አማራጮችን ተጠቅሞ በሰላማዊ ትግል ሰላማዊ ሽግግር ወይም ለውጥ ለማምጣት ተፈቅዶለት የሚያውቀውና ተፈቅዶለት ሊጠቀምበትስ ያልቻለው? ሕዝቡ እንኳን ተፈቅዶለትና ሳይፈቀድለትም እንኳን እነኝህን የሰላማዊ ትግል አማራጮችን ተጠቅሞ ለውጥ ማምጣት የሚችልበት ነባራዊ ሁኔታ በሀገራችን አለ ወይ? ይሄንን ሁኔታ መፍጠር የሚቻልበትስ ዕድል አለ ወይ? ሰላማዊ ትግል በሚሠራበት ሀገር መቸና የትስ ነው የትጥቅ ትግል አማራጭ ተመራጭ ሆኖ የታየው?

ነው ወይስ እያሉን ያሉት ወያኔ እስከፈለገ ጊዜ ድረስ እስከ የልጅ ልጁ በሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅሞችና ሉዓላዊነት ላይ እየቆመረ፣ ሕዝብን በገዛ ሀገሩ ባይተዋር አድርጎ እንደባሪያ እየረገጠና የበይ ተመልካች አድርጎ እየቀጠቀጠ በግፍ እየገዛ እንዲኖር እንፍቀድለት ነው እያሉ ያሉት?

ነው ወይስ ሕዝቡ ባዶ እጅን እያውለበለበ ለተቃውሞ አደባባይ ላይ በመውጣት፣ አድማ ብሎ አድማዎችን በማድረግ በወያኔ እየተለቀመ ተፈጅቶ ይለቅ፣ ነፍሱን በከንቱ ያሳልፋት እንጅ መሣሪያ ማንሣት የለበትም ነው እያሉ ያሉት?

የድሀ ልጅ እኮ አሁንም ከማለቅ አልዳነም፡፡ አልሰሙም እንዴ ስንት ወገናችንን ባሕርና በረሀ እንደበላውና እየበላው እንደሆነ? ሞቱ ስቃዩ ችጋሩ ካልቀረለት ዶ/ር ብርሃኑ አሉ ብለው ያሏቸው የሀብታም ልጆች ተቀላቀሉም አልተቀላቀሉ ወጡም አልወጡ የድሀ ልጆች ለዚህ ድህነት የዳረጋቸውንና ከዚህ ድህነት እንዳይወጡ ያደረጋቸውን ከምንም በላይ ደግሞ ሀገራቸውን እያመሰቃቀለ ወደ ማጥ ውስጥ እያሰጠመ ያለውን አንባገነን አገዛዝ ታግለው እንዳይጥሉ ማን ነው ከልካያቸው?

እርስዎ ምንም ስላልጎደለብዎትና እንደነ ዶ/ር ብርሃኑ የወገንዎን ችግር የራስዎ አድርገው ስለማያዩ ወገናችን ያለበት ችግር ምን ያህል ጊዜ የማይሰጥና አጣዳፊ ችግር እንደሆነ አልተሰማዎትም፡፡ የሚገርመው ደግሞ ሌላውም እንዲሰማው አለመፈለግዎ ነው፡፡ በአገዛዙ ሕይዎቱና ሀገሩ የተመሰቃቀለችበት ዜጋ ሁሉ በሀገራችን ሰላማዊ የትግል አማራጭ ካልሠራና እንዲሠራም ካልተፈቀደ የተተወለትን ቀሪ የትጥቅ ትግል አማራጭ ተጠቅሞ ሕይዎቱንና ሀገሩን የተስተካከለ ሁኔታ ላይ ለማስቀመጥ የመታገል የሞራል (የቅስም) ግዴታስ የለበትም ወይ? ይህ የዜግነት ግዴታ የማይሰማቸውና አብረው የማይታገሉ አሉና ተብሎ የሚሰማቸው መታገል የለባቸውም ይባላል ወይ? ቀድሞስ ቢሆን የሚታገለውና የሚሸፍተው የከፋው የጎደለበት የተገፋው የሀገር የወገኑ ነገር የሚያብሰለስለው እረፍት የነሳው ነው እንጅ እንደ እርስዎ የሞላለትና ያልጎደለበት የሀገርና የወገን ነገር የማይሰማው የማይገደው ሆኖ ያውቃል ወይ? ሁሌም የትም ቢሆን በእንዲህ ዓይነት ትግል ላይ ከአጠቃላይ ሕዝቡ አንጻር ሲታዩ ጥቂቶች የሚባሉ ቆራጥ ወገኖች ጥረት እንጅ የመላ ሕዝቡ ተሳትፎ አይደለም በእንዲህ ዓይነት ትግል ላይ ወሳኝ ሆኖ ለውጥ ሲያመጣ የሚታየው፡፡

ወያኔ ሆነው ካልሆነ ይሄንን ያሉት እንዲህ እንጭጭ እንዲሆኑ ያደረገወት ሀገራችንና ሕዝባችን በወያኔ ምክንያት ለምን ዓይነት ከባባድ አደጋ እንደተጋፈጠች ባለማወቅዎ ወይም ለማወቅ ባለመፈለግዎ ነው፡፡ ይሄንን የሚረዳ ሰው እንቅልፍ የለውም፡፡ ሌት ተቀን የተገኘውን አማራጭ ሁሉ ተጠቅሞ ሀገርንና ሕዝቧን ወያኔ ካጋፈጣቸው አደጋ ለመታደግ ይባትላል እንጅ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው  amsalugkidan@gmail.com

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: