The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የሰሞኑ ህወሃት ሕዝቡን አቅጣጫ የሚያስቀይስበት ዘዴ ከሽፏል ወይስ አልከሸፈም? – ከአንተነህ ገብርየ

ከሞላ ጎደል በዚህ ዓመት ህወሃት የሚያደርገውን ማምታታት አቅጣጫ የማስቀየስ ስልት ሕዝቡ የነቃበትና ርምጃውን በጥንቃቄ ያካሄደበት ስለሆነ በኃይል ከሚወሰድ የጉልበትና የግድያ ድርጊት በስተቀር ዓላማው ከሽፏል የሚል እምነት ስለአለኝ ይህችን መጣጥፌ ለንባብ አቅርቤያለሁ›

ህወሃት የሚመራው አገር አጥፊ ቡድን አንዱን ከሌላው ጋር በማናከስ፤በሃይማኖት፤በጎሳ እርስ በእርሳቸው እምነት እንዲያጡና በጥርጣሬ እንዲተያዩ ማድረግ የተቋሙ ዋና ፕሮግራም ሆኖ እየተሰራበት የመጣ ቢሆንም ከምርጫ 1997(2005)በኋላ በስውር ይካሄድ የነበረው ግድያ(silent killing methods) ተቀይሮ ወጣት ሽማግሌ ሴት ሕጻን የማይለይ ሕገ-አራዊት የሆነ መርህ በመከተል በኃይል አንበርክኮ ለመግዛት ከተጀመረ እነሆ አሥር አመታት አለፉት።

ከእውነት ጋር በፍጹም ላይገናኙ ወይም እውነትን ላለመናገር ጨክነው ቃል የገቡት የህወሃት መሪዎችና ግብረ-በላዎች ጧት የተናገሩትን በምሳ ሰአት ሲንዱት በምሳ ሰአት የተናገሩትን በእራት ሰአት እየካዱ የመገናኛ ብዙሃንን በቁጥጥር ስር አድርገው ዝባዝንኬ የበዛበትን የቅጥፈት ላዛናቸውን ሲያላዝኑ ተመልክተናቸዋል።ይህ መዋቅር ከላይ እስከ ታች ድረስ በነፍሰ ገዳዮች የሚመራ ሲሆን በሰላም ቀን ከሕዝብ ጋር አብሮ ለመኖር እንደማይችሉ ስለሚያውቁት በትንሹም በትልቁም አጋጣሚ ሁሉ ቀዳሚው መፍትሄያቸው መግደል ነው። የድርጅቱ አወቃቀር የኮሚኒስት ርዕዮት ዓለም ይከተሉት የነበረው አይነት ልክ እንደ (Joseph Stalin red terror system) ሲሆን የምእራቡ አለም አገራትም በህወሃት ተጭበርብረው ድጋፋቸውን እየቸሩ ዘልቀዋል። አያውቁትም ማለቴ አይደለም እያወቁ ግን ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅ እስከተገኘ ድረስ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያ ህዝብ እስራት ሞት ስደት ርሃብ አጠቃላይ የዲሞክራሲያው ስርአት መጨለሙ ምናቸው አይደለም።

ከርእሱ እንዳልወጣ ጥቂት ነገሮችን ማከል ስለአለብኝ  ይቅርታ፦ባለፈው በአንድ ጹሑፍ ላይ ብቅ አድርጌ የተውኳት ነገር ነበረች እንደሚታወቀው በዓለማችን ሙስና ተስፋፍቷል(corruption is spreaded in the world )  በተለይ ደግሞ በአፍሪቃ አንድ እንኳን ከዚህ ግባ የሚባል ጤናማ የአገር መሪ አለመኖሩ ግልጽ ነው። በመልካቸው እኛን የሚመስሉት ከአንድ ጎሳ የበቀሉ ጠባቦችና ዘረኞች ከሁሉም በላይ ሥልጡንና እንደፍልፈል የሀገር ሀብት ዘርፈው ወደ ትግራይ ወይም ሰርአቱ አገግሞ መሰንበት ከቻለ እስከ እለተ ሞታቸው በዝርፊያ ለመኖር የተሰማሩ ናቸው። እንደምናውቀው በየመን ፤ደቡብ ሱዳን ፤በሱዳን በኬኒያ ፤ እንዲሁም በመላው የአፍሪቃ አገሮች ማለት ይቻላል የህወሃትን ስርዓት ተቃውመው ወደ ጎረቤት አገር የሚሸሹ የፖለቲካ መሪዎችና አባላት፤ጋዜጠኞች፤የኢኮኖሚ ስደተኞች ሁሉም እየተለቀሙ ተመልሰው ለህወሃት ይሰጣሉ ከህወሃት ምን እንደሚጠብቃቸው ይታወቃል። እዚህ ላይ አንድ ነገር አስታውሻችሁ ልለፍ አዲሱ አበበ ከአሜሪካ ራዲዮ ጣቢያ የአማርኛው ክፍል ዝግጅት አንድን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኃላፊ ሲያነጋግር በግባባት ሳይችሉ ቀሩና ፖሊሱ አምጥቸ እዘጋሃለሁ አይነት ነገር ተናገረ አዲሱ እኔ እኮ ያለሁት አሜሪካ ነው ሲለው ከሰማይ ብትወጣም አምጥቸ እዘጋሃለሁ ብሎት አረፈ።እንደዚህ አይነቱ ነው እንግዲህ የሕዝብን ደህንነት ይጠብቃል ተብሎ በኃላፊነት ተቀምጦ የምናገኘው።

 ለምንድን ነው ይህ የሚሆነው ሲባል የህወሃት ደህንነት መምሪያ በሚስጢር የያዘው ጉዳይ ነው የሚባለው። የአፍሪካ መሪዎች ወደ አዲስ አበባ ሲባል ለአፍሪቃ ሕበረት ስብሰባም ሆነ ለተየያዩ ጉዳዮች የሚያስኬድ ምክንያት ሲገኝ በጣም ደስተኛ ሆነው ለመዝናናት እንደሚመጡ አንድ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ በቅርቡ ከኢትዮጵያ የመጣ ሰው አጫውቶኛል።ይህ  ቸርነት ወይም ድግስ ለአፍሪቃ መሪዎች ብቻ አይደለም ለምእራባውያንና ለዐረቦችም የሚደረግ ነገር ነው።ለሁሉም መሪዎች በሚኖሩበት ቆይታ አስፈላጊው ነገር ሁሉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ይሟላላቸዋል።ከስብሰባ በኋላ በአፍሪቃ ሕብረት አዳራሽ ከቆንጆም ቆንጆዎቹ ሴቶች ተመርጠው በጋድም ይቀመጣሉ እያንዳንዱ የአፍሪቃ መሪ የፈለጋትን ሴት እንደ ዕቃ አንስቶ ይወስዳታል ያማግጣታል።የገንዘብ ችግር የለም ያች ስጋዋን የሸጠች ሴት ከመኪና የተለየውን ከቤትም ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለውን ይገዛላታል።ገንዘቡ የተገኘው ከአፍሪቃ ምስኪን ሕዝብ እንደሆነ አይዘነጋም።ለዚህ አይነቱ መስተንግዶ ምላሹ ደግሞ የህወሃት አረመኔያዊና አምባገነናዊ ስርአት እንዲቆይ የአፍሪቃ መሪዎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እያነቁ ለዚህ ሰው በላ ቡድን ማስረከብ ነው አበቃ ተከተተ።

ወደ ርእሴ ስመለስ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ1997 ምርጫ ህወሃትን ሲያሰናብት የተወሰደው ርምጃ ሁላችንም የምናውቀው ነው ከዚያም ተከትሎ ህወሃት ኮሮጆ በመዝረፍ በጉልበት ተመርጫለሁ አለ። ሕዝቡ ድምጻችን ተሰርቋል ይመለስ ብሎ ጠየቀ መልሱ ግድያ እስራት ስደት ሆነ ይህን ለማዘናጋት ሲባል አቅምን ያልመጠነ ሙያዊ ጥናት ያልተደረገበት ከአጎራባች አገሮች ጋር ጦርነትን የሚያጭር እቅዶች ወጥተው በአዋጅ ተነገሩ የሕዳሴው ግድብ፤የስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን ኧረ ምኑን ብየ ልጥቀሰው?ያ! የሕዝብን ሀብት ጨርሶ ለማሟጠጥ የሕዝቡ አመለካከት በዚህ ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ ነበር።ሊሆን አልቻለም።የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም እንዲሉ ሕዝቡ ሳንፋረድ እንዴት ብሎ አላቸው።ያ እያደገ ስር እየሰደደ በልብ የታመቀው እምቢኝተኝነት እግር አውጥቶ መንቀሳቀስ በጀመረበት ዓመት ዘንድሮም እንደዚሁ አስደንጋጭ ድርቅና ርሃብ በመላ አገሪቱ ሲያንዣብብ የሚያስከትለውን መዘዝ የተገነዘቡት ገዥዎቻችን የኢትዮጵያን ለም መሬት ለሱዳን አሳልፈን መስጠት አለብን ብለው አገር ይያዝልን ዑዑታቸውን ለቀቁት፤አዲስ አበባን ማስፋት አለብን ብለው ሕዝቡን ማፈናቀል ጀመሩ።ያለ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ፍላጎትና ውሳኔ የወልቃይት የጠገዴ የጠለምት መሬት ወደ ትግራይ እንዲካለል ያደረገው ኢፍትሃዊና አፋኝ በዘር ማጥፋት ጉዳዩን አዳፍኘ አስቀረዋለሁ ያለው ህወሃት እሣት ከነበረበት ረመጥ አይጠፋውም እንዲሉ የቀደሞቹም ሆነ የአሁኖቹ የአካባቢው ተወላጆች ፋና ወጊ መፈክራቸውን ከፍ አድርገው ይዘው እኛ ጎንደሬዎች ነን ፤እኛ አማራ እንጅ ትግሬዎች አይደለንም ብለው ሞገቱ ።ለሱዳን ይሰጣል የተባለው ለም መሬትም ወልቃይትን ጨምሮ በመሆኑ ሁሉም ነገሮች ተያይዘው ሕዝቡን ማሰባሰብ ማስተሳሰር ጀመሩ ገዥዎች ተራወጡ አስፈራሩ ሕዝብ ጥያቄውን እስካልተመለሰ ድረስ እረፍት የለም መብታቸን ለማስከበር የሚከፈለውን ዋጋ እንከፍላለን በለው እንቅጩን ተናገሩ። ሕዝብ አምኖባቸውና ጥያቄየን አቅርበው መፍትሔ ያመጡልኛል ያላቸውን ኮሚቴዎች መርጦ ከላይ እስከ ታች ላለው ይህወሃት ቡድን አቀረበ ኮሚቴዎቻችንን አስረው ለማስፈራራት ሞከሩ፤ይቅርታ ጠይቁን አሉ ማን ነበርይቅርታ መጠየቅ የነበረበት?? ግድ የለም የሚሆነውን እናያለን ትግሉ ግን አይቆምም። የቅማንት ሆዳሞችን በማሰለፍ ከአማራው ጋር ለማጋጨትና ትኩረት ለሱዳን በሚሰጠው መሬት ጉዳይ ላይ እንዳይሆን አላስፈላጊ ደም አፋሰሰ ዘመዶቼ ብልጦች ናቸው እኛ በደምና በሥጋ የተዋህድን ስለሆንን ጣልቃ አትግቡብን ብለው ሞገቱ አገር ቤት ያሉትን ሆዳሞችን ሆነ በውጭ የተደራጁ የህወሃት አጫፋሪ የቅማንት ተወላጆችን አፋቸውን አስያዙዋቸው።

እያንዳንዳቸውን ለይተን ስንመለከት፦አዲስ አበባን ለማስፋት የተዘጋጀው እቅድ(master plan) ብዙ ሲመከርበት ቆይቶ ከአመት በፊት በዚህ እቅድ ምክንያት በርካታ የአምቦ ወጣቶችና ተማሪዎች ተቃውሞ አድርገው በርካታ ለጋ የሆኑ ወጣቶች ተገደሉ በአመቱ ደግሞ ዘንድሮ ይህን ጉዳይ ይዘው ብቅ አሉ በመላው ኦሮሞ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን አስነሳ በአንድ ጊዜ እንደ ሰደድ እሣት ተቀጣጥሎ መላ ኢትዮጵያውያንን አስቆጣ የበርካታ ወጣቶችን ሴቶችና ሕጻናት ሕይወት ቀጠፈ ማስተር ፕላኑ ቆሟል ተባለ እስከመቼ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወይስ ለተወሰነ ጊዜ ጥርት ያለ መልስ ሳይሰጡ እያድበሰበሱ ለማቆየትና በሌላ ስልት ገብቶ የተፈለገውን ጥቅም ለማሟላትና አዲስ አበባ የጥቂት የህወሃት ባለሥልጣናት መናኸርያ እንድትሆን ለማድረግ ወይም በሌላ መንገድ ብጥብጡ ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆንና ሥርአት አልበኝነት እንዲሰፍን በዚህም ምክንያት አንዳንድ የመገንጠል አባዜ ላለባቸው በሩን ለመክፈት ያለመ ይመስላል።ለዚህ ይመስለኛል ሌንጮ ለታ ከየትም ከርሞ ወጣቶች ባስመዘገቡት ድል ባለቤት ለመሆንና አመራር እየሰጠ ያለ ለመምሰል ብቅ ማለት የጀመረው። አያ ጅዋርም በካድሬው በሠራዊቱ በደህንነቱ ትግሉ እንዲደገፍ ተገቢውን ሥራ ሠርተናል ብሎናል ያም ሆነ ይህ ሌንጮ ለታ ያሰበው ኦሮሞን የመገንጠሉ ቅዥት ይሁን አባይ ጸሐየ የኦሮሞ ተወላጆችን በማፈናቀል ከሕዝብ በዘረፈው ገንዘብ ዘመናዊ ፎቆችን እያሰራ የማከራየቱ ሥስታም አስተሳሰብ ነቄዎቹ የኦሮሞ ወጣቶች ቀልድህን ወደዚያ በል አገራችን ጥለን የት እንድንሄድ ትፈልጋለህ? በማለት ሞትን ተጋፈጡት አሁንም እየሞቱ ነው ሞታቸው ግን የውሻ ሞት አይደለም።ነጻነትን ሊያስጨብጥ የሚችል ትግል ነው እየተካሄደ ያለው።ይህ ትግል የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው እሱም ትግሉ አገር አቀፋዊ እንዲሆን በሳል በሆኑ የፖለቲካ መሪዎች አቅጣጫ እየተሰጠው እንዲጓዝ ማድረግ ነው።

ህወሃት ጠዋት ከመነሻው ጀምሮ የራሱ ከሆነው የኢኮኖሚ ችግርና የትግራይ ምድር ለምርት የታደለ ባለመሆኑ ምክንያት ለም የሆኑትን የኢትዮጵያ ክፍሎች በቅድሚያ በቅርብ ያሉትን ከዚያም የሩቆቹን ለመያዝና የኢኮኖሚ ችግራቸውን ለማራገፍ ከማሰብ በዘለለ ሌላ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ የደረሰ ጭቆና አለመኖሩና ለትግል የሚያበቃ ምክኒያታዊ አጀንዳ ሳይኖረው በቅጥረኝነት የተነሳና የባእዳንን ፍላጎት ስኬታማ ለማድረግ ስለሆነ ለኢትዮጵያ የሚበጅ ነገር ይኖረዋል ተብሎ የሚታሰብ አልነበረም ልክ እንደ አዲስ አበባው የመሬት ወረራ በሰ/ውሎና ጎንደር ትግራይን የማስፋፋትና የእዚህ አካባቢ ነዋሪዎችን በማፈናቀል ትግሬዎችን በማስፈር ትልቋን ትግራይ የመገንባት ጉዳይ ጋር በተያያዘ መተከልን ከጎጃም ራያ አዘቦ ከወሎ ጠለምት ጠገዴ ወልቃይት እንዲሁም የምእራብ አርማጭሆ በከፊል ከጎንደር ወደ ትግራይ አስገብቶ ትግሬዎች ሆናችኋል በማለት የተስፋፊነት ተግባሩን መፈጸም ነበር። የሕዝብ ይሁንታ ባያገኝም በቁርቁስ ተፋጠን ያለንበት ሰአት ነው። ይባስ ብሎ ሰፊና ውሃ ገብ የሆነውን ለም መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ከመቸውም ጊዜ በላይ ህወሃት ፍጥነት የጨመረበት ወቅት አሁን ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው ለምንድን ነው ሲባል የሁላችንም የተለያየ ምክንያት ሊኖረን ይችላል ህወሃት እውን ይህን መሬት ለሱዳን አሳልፎ የመስጠቱ ጉዳይ በጊዜያዊነት ወይስ በቋሚነት? የሚለውን ጥያቄ ትተን በድርቁና ድርቁ ባስከተለው ርሃብ ምክንያት አንዳንድ ያልተጠበቁ ድንገተኛ የሕዝብ ቁጣዎች መሪዎቻቸውን ለማስወገድ የተነሱበት ሁኔታዎች ስለነበሩ የሕዝብን አስተሳሰብ አቅጣጫ ለማስቀየስ ጉዳዩ አሁን ቢነሳ ብዙ ጨዋታ ልንጫወት እንችላለን ከሚል ስልት ነው ብየ አምናለሁ።1966እና 1977 እንመልከት።የመስጠቱ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው።

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ የጎንደር ሕዝብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ በመሆኑ ሱዳን እኛ የምንጠይቃት  እንጅ ከኢትዮጵያ የምትወስደው ኢትዮጵያን የምትጠይቅበት ምንም አይነት መሬት የላትም እኔ ከዚህ አካባቢ ከበቀሉት ተወላጆች አንዱ ነኝ አካባቢውን አበጥሬ አውቀዋለሁ የእኛና የሱዳኑ ድንበር የት እንደሆነ በሚገባ የማውቀው መሆኔን ህወሃቶች ጠንቅቀው ያውቁታል በዚህም ምክንያት ለመጀመርያ ጊዜ ከሱዳኑ ልኡክ ጋር የጋራ ድንበር የሚባለውን ለማየት በ1977 ዓ/ም ምህረቴ መለሰ ከሰሜን(ደባርቅ) የዞኑ ክንስትራክሽን ዘርፍ ኃላፊ ፤ታረቀኝ እማኙ ከአለፋ ጣቁሳ የዙኑ የብአዴን የጋራ ኮሚቴ አባል ፤ደሳለኝ አሰሜ እስቴ  የታች አርማጭሆ ወረዳ ም/ ሊቀመንበር ፤ሌላው ደሳለኝ ደብረታቦር የመተማ ወረዳ ሊቀመንበር ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ሱዳን መሶሎኒ የሚባል ትግሬ በመስፍን አማረ እንዲመራ ሲዋቀር የመሬቱ ባለቤት ይህን ጉዳይ የሰማሁት ቡድኑ ሲመለስ ከአዘዞ አየር ማረፊያ ስልክ ተደውሎ ለቡድኑ አልጋ እንዲያዝላቸው እንዳደርግ ካደረጉ በኋላ ነው ጉዴን የሰማሁት እዚህ ላይ ጠቁሜ ማለፍ የምወደው ቢኖር መስፍን አማራ የሰሜን ምእራብ የኮር አዛዥ እኔ ለምን በኮሚቴው ውስጥ እንዳልገባሁ ሲጠይቅ አንዱ የአዲሱ ለገሰ ግብር ሰብሳቢ ፈጠን ብሎ እሱን በዚህ ኮሚቴ ውስጥ ማስገባት ማለት ሄደህ ጦርነት ግጠም ማለት ነው ብሎ ለመስፍን መለሰለት።ዛሬ እንዲህ ሊርቀኝ ያኔ ግን ይጀምሩትና እንተያያለን ድንበሩ ሲካለል የሚፈላውን ጉድም ራሳቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ ለጊዜው በመከላከያ ኃይል ተመክተው ድንበሩን ሊከልሉት ይችሉ ይሆናል በሚል ነበር የምመለከተው ። ይህ ጉዳይ ወደ ተግባር አፈጻጸሙ ከተገባ መጀመርያ ሱዳንን በጣም ይጎዳታል ቃታ ከተከፈተ ማቆሚያው የት እንደሆነ ያውቃሉ።የእኛ ሕዝብ በህወሃትየመከላከያ ሠራዊትና በሱዳን ጦር በሚጠመድ ሴራ ጉዳት ይደርስበታል ድንበሩን ግን በኃይል ይከብራል ። ህወሃት ያኔ የሜዳ ጦጣ ነው የሚሆነው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ይነጠላል፤ከሱዳን ጋር ያለው ወዳጅነትም ያከትማል የወልቃይቱ ጉዳይ ትልቅ የትግል መድረክ ከፍቷል ከሁኔታው እንደሚታየው የወልቃይት ሕዝብ በድል አድራጊነት እንደሚዘልቅ ደፍሮ መናገር ይቻላል።

አማራውን ለዘመናት አብረውት ከኖሩት ቅማንቶች ጋር ለማጋጨት የህወሃት ቡድን የሄደበት መንገድ ከሁለቱም ወገን ደፍሮ የሚገባበት ባለመኖሩ እንጅ ያ ሕዝብ ለህወሃት ጀሮ የሚሰጥ አልነበረም ጥቂት እበላ ባዮች ደግሞ ያሰቡት ሳይሳካ እኛ ሳንደርስባቸው ራሱ ህወሃት እንደሚውጣቸው ግልጽ ነገር ነው።በተመሳሳይ ሁኔታ በኑዌሮችና በአኝዋኮች ላይ ሰሞኑን የተጫረው የህወሃት እሳትም እንዲሁ የአቅጣጫ ማሳሳቻ ዘዴዎች ድጋፍ ሰጭ እንዲሆን የታሰበ ቢሆንም ሁለቱ ክፍሎች ሊነቁና በፍጥነት ችግሩን ሊያበርዱት ይገባል ምክንያቱም ህወሃት አሁን ያለበት ደረጃ አንድ እግር ከውጭ አንድ እግር ጉድጓድ ውስጥ ስለሆነ በዚህ በሞተ ሰአት የታሪክ ጠባሳ ጥሎ ማለፍ ከኢትዮጵያውያን የሚጠበቅ ተግባር አይደለምና።ሀሳቤን ለማጠቃለል አንኳር አንኳር የሆኑትን ላስቀምጥ።

*ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር በወሰደችው ርምጃ ተዋርዳ ተመልሳለች፤እንግሊዝም በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ጥሩ ሆነው ተኮርኩመዋል፤ሱዳኖች በመሃዲስት ወረራ ተሸንፈው ተመልሰዋል፤ቱርኮችና ግብጻውያን በተደጋጋሚ ያደረጉት ሙከራ ከሽፏል የሌሎችም እንዲሁ ከዚህ አንጻር ለዚህ የበቀል ፍላጎት አገር በቀሉና ለም ሆኖ የተገኘው ቡድን በጣሊያንና በእንግሊዝ ፕሮግራም የሚመራው ህወሃት የተሰለፈበትን የቅኝረኝነት ግዳጅ ለመወጣት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረግ ነበር ተሳክቶላቸዋል።አሁን ደግሞ በክብር ተጠብቆና ታፍሮ የኖረውን የሀገራችን ድንበር ለማስደፈርና ለም መሬታችን ለጠላት(ሱዳን)አሳልፎ በመስጠት ዳሩ መሐል መሃሉ ዳር እንዲሆን ዝግጅቱ የተጠናቀቀ በመሆኑ የድንበር ማካለሉ ከመጀመሩ በፊት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሬቱ የጎንደር ብቻ ስላልሆነ ለጠላት ይሰጣል ወደ ተባለው አካባቢ ለመሄድ ስንቁን መሰነቅ ዝግጅቱን ማጠናቀቅና የማካለሉ ሥራ ሲጀመር ኢትዮጵያዊነቱን በማሳየት የአያት ቅድመ አያቶቹን ታሪክ መድገም አለበት።

*ድርቁና ድርቁ ያስከተለው ርሃብ ፋታ የሚሰጥ ባለመሆኑ በችግር ላይ የሚገኘውን ወገናችን ለመታደግ በስቪክ ማህበራት ሆነ በፖለቲካ ድርጅት ዙርያ የተደራጀን ሕዝባችንና ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የተፈጠረውን አደገኛ ሁኔታ በማስረዳት ድጋፍ መስጠት ወገነን መታደግ ይገባናል፡፤ራሳቸውን እንደ መንግሥት ቢቆጥሩም በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ሳይሆን በውጭ ኃይሎች ትዕዛዝ የሚንቀሳቀስ ቅጥረኛና ዘራፊ ቡድን ርሃቡን እንደ አንድ የሕዝብ ክንድ የሚዝልበት እየተራበ እንዲገዛ የማጥቂያ መሣርያ አድርጎ ስለሚጠቀምበት በዚህ ቡድን ላይ ዘመቻ መክፈት ካስፈለገም ሕዝብ ሲርበው መሪውን ይበላል እንደሚባለው በሀገር ስምና ከሕዝብ የዘረፉትን ገንዘብ እስከ ማውጣት እንዲሄዱ ማስገደድ ድረስ መሄድ አለብን።

*የኦሮሞ ወጣቶች ያቀጣጠሉት ትግል በኦሮሞ ክልል ብቻ ተወስኖ መቅረት የለበትም ቢቻል በተመሳሳይ ጊዜና ሰአት በሁሉም ክልሎች የሚቀሰቀስ አመጽ እንዲካሄድ ማድረግ፤መሪ መፈክሮችም አገር አቀፋዊ እንዲሆኑ ማድረግ ድርቁና ርሃቡን ህወሃት መጠቀሚያ እያደረገው እንደሆነ፤የኢትዮጵያ ድንበር ለጠላት ተላልፎ መሰጠት እንደሌለበት፤ህወሃት ራሱን ከሕግ በላይ አድርጎ ንጹሐን ዜጎችን መብታቸውን አፍኖ ዜግነታቸውን ገፎ የመሬት ቅርምት ማድረጉን አቁሞ ሥልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክብ፤መሬት የሕዝብ ነው ወዘተ.መፈክሮችን መጠቀም ፤የተቃዋሚ ኃይሎች ተገደው ወደ ሕብረት እንዲመጡ ማድረግ ያስፈልጋል።

*እነዚህን ሁሉ ስናደርግ አንዱ ሌላውን እንዲያጠናክር ተያያዥነትና ትሥስር እንዲኖራቸው ለማድረግ መሪ ሚናውን የሚጫወቱት ሚሥጥራዊና ሕቡአዊ መስመር ዘርግተው ግንኙነታቸው ሳይቋረጥ አመጹን እንዲመሩት ማድረግ ጠቃሚ ነው።አሁን ባለው ሁኔታ እንዲጓዝ ከፈቀድን ግን መጥፎ አደጋ ላይ ሊጥለን እንደሚችል ልንገነዘብ ይገባል።የእያንዳንዱን የተቃዋሚ ኃይል የፖለቲካ ፕሮግራም በደንብ ከተመለከትን አንዱ በሌላው ላይ አሽከላ ለመጣልና ጥሎ ለማለፍ ያነጣጠረ እንጅ መላ ኢትዮጵያውያን በእኩልነትና በጋራ የሚኖሩባትን አገር ለመገንባት ያለመ አይደለም።ይህን ደግሞ እኛው ፈቅደን አሻግረን በመመልከታችን ድርጅቶችን ደፍረን ቁሻሻ ተሸክማችኋል እኛን ከመምራታችሁ በፊት ቁሻሻችሁን አራግፉ ለማለት መድፈር አለብን።ምክንያቱም እኛ በውጭም ይሁን በአገር ውስጥ ያለነውን ድጋፍ ካላገኙ አንድ ርምጃ መሄድ አይችሉም።

*የአማራው ነገድ ሕዝብ በማንኛውም አካባቢ ሠርቶ  መብላትና መኖር እንዳይችል ድብቅ አጀንዳ ይዞ የተደራጀው  የአማራውን ዘር እያጠፋ ያለው አገር መራሹ ህወሃት 80% የትግራይ ሕዝብ በመላው ኢትዮጵያ ሀብት ለማካበት የህወሃትን ኮቴ እየተከተለ በሚያፈራው ሀብት ትግራይ ስንትና ስንት ግንባታ እየተካሄደ ሌሎች አካባቢዎችን ግን ድሮ በጫካ እያለ ይዞት በነበረው የአፍራሽና የማውደም አመለካከት ተመርኩዞ ሁሉም ተቋዋማት መደበኛ ተግባራቸውን መፈጸም ከማይችሉበት ደረጃ ለማድረ ተግባራዊ  እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።አሁን ትግራይ ውስጥ የሚገኘው ሕዝብ የሚበዛው ሕፃናትና ሴቶች ሲሆኑ ሌላው የመንግሥት ሥራ የሌለው በሱዳን ፤በሶማሌ፤በደቡብ ሱዳን እንዲሁም የህወሃት ስርአት በየትኛውም የአለም አገር ዳቦ ፍለጋ እንዲሰደዱ ያደረጋቸውን እንዲሰልሉ አብሮ በማሰደድ በእናትና ልጅ፤በወንድማማች፤በእህትማማች፤በእድር፤በመረዳጃ ማህበራት፤በኮሚቲዎች፤በሲቪክ ማህበራት፤በእምነት ማእከሎች በሥራ ቦታዎች ሁሉ በማሰማራት ከፈተኛ የሀገሪቱ ሀብት ተመድቦ ለብጥብጥና የሕዝብን ሰላም እንዲነሱ የተሰማሩበት ይገኙበታል።ሌሎች 80% ያልኳቸው ዳቦ ያቀብሉናል ማለት አይደለም እነሱ ቀድመው ተደራጅተው በመጠበቅ አስተናጋጆች ናቸው።ከዚህ ላይ በዚህ ሀሳብ መሠረት የትግራይ ሕዝብ በህወሃት ሥርዓት ተጠቃሚ አይደለም እል የነበርኩት ሀሳቤን ሙሉ በሙሉ አንስቻለሁ።

*ሕዝቡን ተወልዶ ካደገበት ርስትና ጉልቱ በማፈናቀል ለድህነት መዳረግ፤አገር ጥሎ እንዲሰደድ ማድረግ ሠርቶ የመብላት እድሉን በመንፈግ ኢ-ሰብአዊ የሆኑ ድርጌቶችን በመፈጸም በማናለብኝነት ሕዝብን በመገናኛ ብዙሃን የስድብ ናዳ ማውረድ ሠርተው የሚበሉ ንጹሕ አርሶ አደሮችን ሽፍታ፤ጥጋበኛ እያሉ መዘለፍና በጭፍን የሱዳንን መሬት ተሻግረው እንደሚያርሱ አስመስሎ ማቅረብ ጠቅላይ ሚንስትሩን ተጠያቂ የሚያደርግ ሲሆን ከኋላ ይህን አድርግ ይህን ተናገር እያሉ የሚገፉት (አዲሱ ለገሰ፤ታደሰ ካሣ፤በረከት፤ካሣ ተክለብርሃን፤ሕላዊ ዮሴፍ፤ ደመቀ መኮንን ከብአዴን)፤ (ስብሃት ነጋ፤ስዩም መስፍን፤አርከበ እቁባይ፤ፀጋየ በርሄ፤አባይ ጸሐየ፤ቴዎድሮስ አድኅኖም፤ደብረጽዮን ሳሞራ የኑስ፤ጌታቸው አሰፋ ከህወሃት) ፤ኩማ ደመቅሳ አባዱላና ሙክታር እንዲሁም ሽፈራው ሽጉጤና የመሳሰሉት ስለሆኑ ሕዝቡ በዋዛ እንዳይመለከታቸውና አገሪቱን እያጠፉ ያሉት የመጀመርያዎቹ ተጠያቂዎች መሆናቸው እንዲታወቅ በነዚህ ሰዎች ማንኛውም ተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ እርምጃ እንዲወሰድና የማእቀብ ማለትም ማንናውንም አገልግሎት አለመጠቀም ምሳሌ፦ምግብ፤መጠጥ፤ትራንስፖርት፤ባንክ ሌሎችንም በነዚህ ግለሰቦች የሚቀርቡ ምርቶችን አለመግዛት በመጠኑም ቢሆን ከጥጋባቸው ሊያበርዳቸው ይችላል”።

ወገኖቼ! ቢቻል ዋናውን ሁላችንም ሊጠቅም የሚችለው አንድነት ለማምጣት እንግባባ ይህ ጊዜ የሚወስድ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ሕብረት በመፍጠር በሕዝባችን ላይ የተቃጣውን ማንኛውም አይነት ጥቃት ለመመከት ሕዝቡን በየደረጃው ራሱን ሊከላከል እንዲችል የማደራጀት ሥራ እንሥራ።ህወሃት እንዳለ ሆኖ ከየካቲት 1966 አብዮት ጀምሮ ከህወሃት ባልተናነሰ መልኩ የአገርን ሉዓላዊነት፤የሕግ የበላይነት የሚረግጡ፤የዜግነት መብትን የሚያፍኑ በጥቅሉም አንድ ነፃ ሕዝብ ሊያገኝ የሚችለውን መሠራታዊ መብት እንዲያጣ ጠንክረው እየሰሩ እስከ አሁን የዘለቁ ድርጅቶች ጣልቃ እየገቡ እንዳያምሱን ለይተን ልናውቃቸውና ልናጋልጣቸው ከዚህ የጥፋት ተግባራቸው እንዲታቀቡ ልናደርግ ይገባናል።

                    ድል ለኢትዮጵያ ግፉአን ሕዝብ!!

                     ሞት ለህወሃትና ግብረ-በላዎቹ!!

                                        ከአንተነህ ገብርየ

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: