The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የኦሮሞ እንቅስቃሴ ለምን የሌሎች ኢዮጵያውያንን ድጋፍ ሊያገኝ አልቻለም? (መሰረተብርሃን ከቴክሳስ) – See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/12548#sthash.uKIXypFy.dpuf

E1146A7C-D99D-4F41-9E50-E55315A1BC72_w640_r1_s_cx0_cy5_cw0

የኦሮሞዎች የትግል እንቅስቃሴ ከተጀመረ ወደ ሶስተኛ ወር ገደማ እንደሆነው ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ግን  በእርቀት ከምንገኝ ኢትዮጵያውያን በስተቀር በአገር ቤት ከሚገኙ ቤተሰቦቻችን፣ዘመዶቻችንና ወደጆቻችን በኩል ትግሉን የመደገፍ አዝማሚያው የለም ብሎ ሙሉ ለሙሉ መደምደም ባይቻልም፣ አብዛኛው የሌላ ብሄረሰብ አባል ድጋፍ ግን አነስተኛ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ሊባል የሚችል ይመስለኛል፡፡  ይህ ለምን ሊሆን ቻለ? ለሚለው ጥያቄ በቂ ምላሽ ካልሰጠነው ይህን የመሰል የትግል ተነሳሽነት አምልጦን የመከራ ዘመናችንን እናረዝመዋለን የሚል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ስጋት እንደሆነ ሁሉ እኔንም ያስጋኛል፡፡ እንደ እኔ ምልከታ የኦሮም ሽማግሌዎች አማራና ኦሮሞን ለመለያየት የሚደረገውን ሙከራ ገና በጠዋቱ ነጭና ጥቁር ጤፍን ቀላቅሎ የመለየት ያህል ነው ብለው ትንቢት ሳይሆን ከህይወት ተሞክሯቸው ያዩትን ሲናገሩ የኦሮሞ ምሁራን ደግሞ ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መልኩ የተቀላቀለውን ጤፍ ሊለያይ በሚችልበት መልኩ እየሰሩ ጠላቴ ለሚሉት ወያኔ ሳይውቁ ወይም አውቀው በወደፊቷ ኦሮሚያ የሚይዙትን የስልጣን ወንበር እያሰቡ አማራውና ኦሮሞ በጠላት እንዲተያይ ሲያደርጉ ኖረው ዛሬ በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ስቃይ ብቻቸውን በሚያሰኝ መጠን ችግሩን  እንዲጋፈጡ ተገደዋል፡፡

የኦሮሞ አባቶች የአማራና ኦሮሞን የተዛመደና የተጋመደ ግንኙነት በልጅነታቸው እንደልጅ፣ በጉርምስናቸው እንደጎረምሳ፣ በጉልምስናቸው እንደጎ ልማሳ በተግባር ሲሞክሩትና  ሲመረምሩ የኖሩትን በሽምግልና ዘመናቸው የነገሩን የሁለቱን ብሄሮች አብሮነትና  አንድነት፣ አንድ ምሁር ለፕሮፌሰርነት ከሚያበቃው የምርምር ስራ የሚበልጥ መሆኑን አሳይተውናል፡፡ የሁለቱን ወገኖች አብሮነት ጠቀሜት በሌላ ምሳሌ ሲገልጹ፣ የአራት በሬዎች ህብረት ያስፈራው አውሬ ነጩ በሬ በጨለማ ጎልቶ ስለሚታይ ለጥቃት ያጋልጣችኋል ሲል ቀሪዎቹ እራሳቸውን ለማዳን ፈቃዳቸውን ሲጠይቅ ቀሪዎቹ ተስማሙና  ነጩ ተበላ ሌሎቹም ተራ በተራ በልዩ  ልዩ ምክንያት ተበሉና በመጨረሻ አንዱ ብቻውን ሲቀር ፈቃድ መጠየቅ ሳያስፈልግ ተበልቶ በሬ በሬ ሆኖ ቀረ፡፡ እነኚህ አባቶች የሰጡት ምክር ሰሚ ባለማግኘቱ፣ የተንኮል ስብከት ቦታውን ይዞ የዛሬ ቀን ላይ ደረስን። የኦሮሞ ወገኖቻችን በበሬዎቹ ላይ የተተረተው ተረት ዛሬ በእነሱ ላይ ደርሶ ይገኛል።

የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁራን ታሪካቸውን ሳያውቅ የአገር ባለውለታዎችንና ጠላታቸውን  ሳይለዩ ሁሉንም የህዝብ ጠላት አድርጎ የ1966ቱን ለውጥ የመራው ያትውልድ ያኔ የሰራውን አይነት ስህተት በዚህ ዘመን ላይ በእራሳቸው መንገድ ስህተቱን በመድገም የኦሮም ህዝብ አማራ ጠላቴ ነው በሚል ስሜት እንዲነሳሳ ለአለፉት 25 አመታት ተግተው ሲሰሩ በመቆየታቸው ፍሬውን አሁን እየለቀሙ ይገኛል፡፡ ናዝሬት ለ7 አመታት ኖሪያለሁ፣ አሁንም ዘመዶችና ጓደኞች ሰላሉኝ ከኦህዴድ ካድሬ ውጪ የሆነው ብዙዉ ኦሮሞ እራሱ የጥላቻ ስሜቱን በደንብ አውቀዋለሁ፡፡እኔ የማውቀው የአባቴ የአርባ አመት ጓደኛ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በአለ ጓደኝነት አብረው ተርበው፣ማደሪያ አጥተው፣ አብረው ብርድ አንገላቷቸው ሁለቱም በትምህርት እራሳቸውን ለትልቅ ደረጃ ካበቁ በኋላ ኦሮሞው የአባቴ ጓደኛ ስትጨቁነኝ የኖርክ ጠላቴነህ አሁን እገሌ የሚባለው የኦሮሞ ድርጅት አባል ነኝ እገልሃለሁ ብሎ መዛቱን ከ20 በፊት የነበረ ትውስታዬ ነው፡፡

ነጻነት ባለበት አገር ውስጥ ያለን ኢትዮጵያውያን ችግሩን በግልጽ ካልተነጋገርነውና ማረሚያ ካላኪያሄድን፣አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ የሚለውን ተረት እውንነት ማረጋገጥ ካልሆነ ፋይዳ የለውም፡፡ ወያኔ የዛሬው ቀን እንደሚመጣ ቀድሞ ስለተረዳ ጠላታችሁን አማራን አባሩ ሲል ኦሮሞው ተባባሪ ሆኖ ሲደግፍ ቆይቶ ወይም መደገፉን ትተን እባካችሁ ተዉ ብሎ ጩኸቱን ሳያሰማ ዛሬ ላይ በመድረሱ አማራው ምኑን አምኖ የኦሮሞን ጩኸት እንደሚደግፍ ለአንባንቢ እንኳን ግራ ይገባል እንኳን ለነዋሪው፡፡  እኔ በእርግጥ ክፋት በክፋት መመለስ በጎ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ከዚያም ባሻገር ይህን አምባገነን ስርአት ለመጣል የሁሉም ህዝብ ትብብር አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡ ነገር ግን ለአለፉት አመታት በህዝብ መሃል የተፈጠረው የጥላቻን ግድግዳ መፍረሱን በተለይም አማራው እንዴት እንዲያምን ማድረግ ይቻላል?የምንሊክ ጦር ለሆኑት  አማሮች ለገደሏቸው ኦሮሞዎች ተባለ እንጂ  በጊዜው ሌሎች ብሄረሰቦች አልነበሩም ወይ ብዬ ለማነሳው ጥያቄ እስካሁ ጥያቄው ሲጠየቅ ወይም ገላጭ ሃሳብም ሰምቼ ባላውቅም  መታሰቢያ ተብሎ የቆመውን ሃውልት ግን በኦሮሞ የጦር ጀነራል በተመራው የምንሊክ ጦር ለሞቱት ኦሮሞዎች ብቻ መደረጉ ለገዢዎቹ መጠቀሚያ ቢሆንም ነዋሪ ለሆኑት አማሮች ብቻ ሳይሆን ትግሬዎችና ሌሎች ብሄሮች የበቀል ማስታወሻ በመሆኑ፣ ፍርሃት እንዳለባቸው እራሴ ያረጋገጥኩት ነው፡፡ ለአለፉት 25  አመታት ኦሮሞዎች ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ አሰቃቂ ሰቆቃ ደርሶባቸዋል፣ ተሰደዋል፣ ተገለዋል በጥቅሉ ተነግሮ የማያልቅ በደል ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በህውሃት ከጀርባ በሚሸረብ ተንኮልና በኦሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁራን ድግፍ ሰጪነት በኦሮሞዎች ድርጊቱን ፈጻሚነት መሰል ጥቃት በአማራው ላይ ደርሷል፡፡   አማራው  ይህንን የሚመራው ህውሃት ይሁን እንጂ ኦሮሞዎችም ዋንኛ ተሳታፊ መሆናቸው መዘንጋት የለበትም፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁራን ግን እንኳን እነሱ አያቶቻቸው በውል የማያውቋቸው ምኒሊክን እያወገዙ የትውልዱን የትግል የትኩረት አቅጣጫ በማስቀየር ማስተዋል የጎደለው ስህተት ሰርተዋል ፡፡

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዛሬም ድረስ ትግሉን እየመሩ የሚገኙት የያትውልድ ከሃምሳዎቹ እድሜ መጨረሻ እስከ ሰባዎቹ እድሜ ላይ የሚገኙት ዛሬም በዚህ እድሜ ከስህተታቸው በመጸጸት በትግል ላይ እንደሚገኙ አንዳርጋቸው ጽጌና የትግል ጓዶቹ  ጥሩ ምስክሮች ናቸው፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁሩንም እራሳችሁን ከምኒሊክ ዘመን አውጡና  ዛሬ ላይ ወያኔ የፈጸመውን ስህተት እንኩን ትታችሁ የእራሳችሁን ስህተት በጥልቀት ተመልከቱ፡፡ ህዝቡ ቀድሞዋችሁ በግብታዊነት አብዮት እያኪያሄደ ነው፡፡ አማራ ጠላቴ እያላችሁ የምትሉት ስሜት 25 አመት ሙሉ በተለይም በኦሮሚያ ክልል በአማራው ላይ እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ የበቀል ስሜታችሁ መቼ ነው የሚያበቃው በቁጥርስ ከሆነ መቼም የአሁኑ ግድያና ማፈናቀል ቢበልጥ እንጂ የምንሊክ ጊዜ ይበልጣል ብላችሁ የምትከራከሩ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ በኋላ ቢያንስ እንደየእምነታችሁ ንስሃ ገብታችሁ ለእውነትም ይሁን ለይቅርታ እራሳችሁ አስገዝታችሁ የመኖርን ትርጉም ሳያይ ለሚያልፈው ኢትዮጵያዊ ጊዜ ሳታጠፉ በጋራ እንድረስለት፡፡ በእናንተ ላይ የተፈጠረውን ለውጥ ለህዝቡ አድርሱ ህዝብ እንዴት መተማመን ሊፈጠር እንደሚችል እዚያው መሬት ላይ ያለውን እውነታ በመቀየር ተአምር ይሰራል፡፡ ጊዚያዊ ድጋፍ ለማግኘት ሲባል ሌላው ህዝብ ትግሉን እንዲቀላቀል የሚደረገው ጥሪ ለውጥ አያመጣም፡፡ እንዲያውም በዚህ ክፍተት መሃል ወያኔ ቀጣዩን ልዩነት የማስፊያ ስልቱን ተግባራዊ እንዲያደርግ ጊዜ በመስጠት  ሁላችን ኪሳራ ውስጥ እንዳንገባ የእናንተ ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ልብ ካላችሁ ልብ በሉ፡፡ ወደፊት በታሪክም ተወቃሽ በህሊናችሁም ጸጸተኛ ሆናችሁ እንዳትቀሩ በማለት ሃሳቤን አካፍላለሁ፡፡

መሰረተብርሃን ከቴክሳስ

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: