The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ሀይሌ ገ/ሥላሴን ለመስደብም ሆነ ለመተቸት በመጀመሪያ እኔ ለሀገሪ ምን አድርጊያለሁ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል –

ከአቅም ማነስ ይሁን በቸልተኝነት ምንም ያለደረገ ሰው ትንሽም ቢሆን ለሀገሩ መልካም ስራ የሰራን ሰው በዚህ ደረጃ ለማዋረድ መሞከር ትዝብት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ይህ ማለት ሀይሌ የሰራው ስራ እና የሚሰራ ያለው ትንሽ ነው ለማለት አይደለም፡፡ መተቸትም የለበትም የሚል እምነት የለኝም፡፡ ከዚህ በተረፈ የሰጠውን አስተያየት በፈለጉት መንገድ ቆርጦ ቀጥሎ ለመተቸት መሮጥ ግን ድንቁርና ነው፡፡ ለምሳሌ ሀይሌ ለቢቢሲ የሰጠው አሰተያየት በግርድፉ “እንደ አፍሪካዊ ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው፤ በጣም አስፈላጊው ነገር መልካም አስተዳደር ነው፡፡ መልካም አስተዳደር ካለ አፍሪካ ለመለወጥ አቅም አላት” የሚል ነው፡፡ (`As an African Citizen democracy is luxury … the most important thing is a good governance` he says `if we have that, African has the potential to change`). ለንፅፅር አንድ የቀበሌ ነዋሪ “የመኪና መንገድ አያስፈልገንም አሁን የምንፈልገው ለእግረኛ መግቢያ መውጫ ነው” የሚል አስተያየት ቢሰጥ፣ የመኪና መንገድ ከነጭርሱ አያስፈልገንም ማለት አይደለም፡፡

12734029_10208778392800611_4213266837931328021_nእኔ በግሌ ሀይሌ ዲሞክራሲ አያስፈልገንም የሚል አስተያየት የሚሰጥ ደንቆሮ ነው ብዬ አላስብም፣ ምን አልባትም ከብዙዎች በተሻላ ማመዛዘን የሚችል እና ተገቢ ነው ብሎ ባመነበት መስመር ከግፊት ነፃ ሆኖ የሚወስን ሰው ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙዎች ለታይታ የእርዳታ ሰራ ሲራወጡ ሀይሌ ግን ለዜጎች ስራ ፈጠራ ላይ ሀብትና ንብረቱን ያውላል፡፡ ብዙዎች ገንዘባቸውን በውጭ ሀገር ሲያስቀምጡ እርሱ ግን በሀገሩ ኢንቨሰት ያደርጋል፡፡ የመንግሰት ሹሞችን ያለምንም ይሉኝታ ለመተቸት አቅም ያለው እንደሆነ በብዙ የነጋዴዎች ስብሰባ ላይ ለመታዘብ የቻልን ሰዎች አለን፡፡ ይህን ላለመቀበል ወይም ሆን ብሎ በግል ጥላቻ “ሀይሌ በእግሩ ነው የሚስበው፣ ዲሞክራሲ ቅንጦት ስለሆነ ጦጣ ነኝ ሙዝ ስጡኝ፣ ወዘተ” የመሳሰሉት አስተያየቶች አስተያየት ሰጭዎችን ከጦጣ በታች ያደርግ ከሆነ እንጂ የሀይሌን ስብዕና የሚገልፅ አይሆንም፡፡ ሀይሌ በወርቅ የሚፃፍ ታሪክ የሰራ ጀግና ነው፡፡ ሀይሌን በማዋረድ ከፍ ማለት አይቻልም፡፡ አንዳንዶች እንርሱ መስማት የሚፈልጉትን ስለማይናገር ቢጠምዱት ውሎ አድሮ ሁሉንም ታሪክ በየፈርጁ እንደሚያስቀምጥ መዘንጋት የለብንም፡፡ ሀይሌ ደግሞ ሰው ነው ይሳሳታል፣ ሀይሌ ቢሳሳት ስለሚሰራ ነው፡፡ ሀይሌ ጠንካራ ባይሆን እና እነዚያን ሁሉ ወርቆች እና ክብረ ወሰኖች በትኖ ድሃ፣ መንገድ ለማኝ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን ለማድነቅ ቃላት ያጥረን ነበር፡፡ በየሚዲያውና ሾው ላይ አቅርበነው ይህን ባለውለታ ዝም ማለት የለብንም ብለን ለማላዘን የሚቀድመን አልነበረም፡፡

ሀይሌ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ሀብቴ ከሚል የፉገራ ብሂል ተላቆ ሀብት ፈጥሮ የሚኖር ጀግና ነው፡፡ ሀይሌ ግን ጀግና የሆነው በመሮጥ ብቻ ሳይሆን ሮጦ ያገኘውን ክብር በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ሰርተው የሚጠቀሙበት ኢንቨስትመንት ውስጥ በማዋል ነው፡፡ በሀይሌ ኢንቨስትመንት ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያዊያን የተደላደለ ኑሮዋቸውን መስረተዋል …. ይህ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡ ለማነኛውም ለመሳደብ ከመነሳታችን በፊት የምንሰድበው ሰው ለሀገር ያበረከተውን ያህል ምን አበርክተናል? ብለን እራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ከዚያ ማመስገን ቢያቅተን መሳደብ እናቁም፡፡

satenaw

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: