The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ሀዝብን ማዳናገር ውድቀት እንጅ እድገትን ኣያመለክትም – አስገደ ገ/ ስላሴ

Haile Mariam

ጠ/ ም/ሃይለማርያም ደሣለኝ የሚናገሩት ያሉ ወደ ሠላም ወይሥ ወደጦርነት?
ጠ/ምኒሥትሩ  በሃገራችን ሥላለ የህዝቦች ዲሞከራሢያዊ ጥያቄ  በተለይ ደግሞ በኦሮሞ በጎንደር በወልቃይት በኣፋር በጋንቤላ  ሥላለው የሀዝብ የመብት ጥያቄ  ሠላማዊ የሆነ  የመፍትሄ ኣቅጣጫ  ያሥቀምጡ ይሆን ?  የሚል ጥርጣሬ ነበረኝ ሁለተኛው ከህሞራ ኣከባቢ  እድሪሥ ቀበሌ የሻብያ ሠራዊት ያፈናቸው 85 ወጣቶችም ኣንሥተው ዘራፍ ዩሉ ይሆናል?  የሚል ግምት ነበረኝ ::
ሁለቱ ጥርጣሬዎች ግን ትክክል ኣለነበሩም ትምኒት ሆነው ቀሩ ሥህተት ግምትም ነበር: :
ሃይለማርያም ደሣለኝ ግን በመግለጫቸው ለሁሉም የህዝቦች ጥያቄ በሙሉ በቅንነት ተመልክተው ዲሞክራሢያ ዊ  በሆነ መንፈስ ለመፍታት እንደሞሞከር የመንግሥቱ ሃይለማርያም የሚመሥል  ነው የተናገሩ::ያኣንባ ገነን ኣነጋገር: ግን  በፊታቸው ይነበብ የነበረው  የጭንቀትና ነጻነት የሌለው ሠው  ፊት ነበራቸው::
በመጨረሻ ግን  በሃገራችን ያለው የሚሊዮኖች ዜጎች ጠያቄ በተለይ ደግሞ በኦሮሞ በጎንደር በትግራይ ወልቃይት ያለው የኣሥር ሚሊዮኖች   የመብት ጥያቄ  በሥተጀርባ ሆኖ የሚያንቃሣቅሠው ሸኣብያ ነው ብለው ቁጭ ኣሉ::
እኔ የሚገርመኝ   የለፉትን 25   ኣመታት በመላው የሃገራችን ክልሎች ተፈጥረው የነበሩ  ከሁሉም ተቃዋሚ ፖርቲዎች ለማለት ይቻላል በስተጀርባቸው ሸኣቢያ  ኣለ እያሉ እጅግ ብዙ ተቃዋሚ  ፓርቲዎች በመወንጀል እና በመፈረጅ     ቡዙ ፓርቲዎች አጥፍተዋል ::     በአሁኑ ጊዜ ያሉ ተቃዋሚ  ፓርቲዎችም   ለሠላማዊ ጥያቂያቸው በማፈን ምርጫ በማጭበርበር  በማሠር በመግደል በአሱረቤት ማጎር በሽብርተኝነት በመፈረጅ  እሱር ቤት ያለፍርድ በወህን ቤት እንዲበሠቡሱ  እንዲበሠቡሱ      ማድረግ: በማእከላዊ እና በድብቅ እሱር ቤቶች በማፈን የፓርት መሪዎች እና ኣባሎቻቸው ደጋፊዎቻቸው በመሰወር   በውሥጣቸው ሠርጎ  ገብ ሠላዮች   በማሠረግ መበታተን  ሥራችን  ብለው ተያይዘውታል:: የሃገራችን  ከፍተኛ  ባጀት የሚረጨው ሰላማዊ   ተቃዋሚ  ፓርቲዎች ለማጥፋት ነው :: በሥተጀርባቸው ሸኣብያ ኣለባቸው የሚባሉ ፓርቲዎች  እነማን ናቸው  ?  በሽኣብያ ሥር ተጠግተው የሚገኙ ጉንበት ሠባት ኣርቦኞች ድሚሒት የኦነግ የጋንቤላ  ጥቂት ሠዎች ናቸው እነዚህ ሃይሎች ተጠቅልለወ  ለኢትዮጱያ ሃይሊ ለመዛባትሥ ይቅር  ለኣንድ ሻንበል ወታደር ተዋግተው ሊያሽንፉ እንደማይችሉ ጠ/ምሥቴርና ጓዶቻቸውም ያውቁዋቸዋል
ሸኣብያም  በሥሩ ላሉት የኢትዮጱያ ተቃዋሚ ሃይሎች እንደማያምናቸው ያውቃሉ:: ታድያ ሸኣብያ ለራሱ በሞት ኣፍ ኣፍ እያለ እንዴት ብሎ ነው የኦሮሞ የጋንቤላ የኣማራ እና ቅማንት  የወልቃይት  የህዝብ ሠላማዊ ጥያቄ እማራር  ነው ትላላችሁ?በእኔ እምነት ይህ ማጭበርበር ነው:: ሊቦሏት የፈለጉ ኣሞራ ቆቅ ብለው ይቦሏቷል እንደሚባለው ይህ ተንኮል ሆን ተብሎ ባገር ውስጥ ላሉ ራሣቸው ያዳከሙዋቸው ጨርሠው ለመብላት ሥለኣሠባችሁ ነው::ይህ ኣባባል  90 ሚሊዮን የኢትዮጱያ ህዝብ ያውቀዋል  ለኢህኣደግ ቡዱን ኣማራሮች  ኣበጥሮ ያውቃቸዋልና::
በመሆኑ ሃይለማርያም ደሣለኝና ጓደኞችዎ በሠላማዊ ዜጎች  መብ ታቸው    ሥለ    ጠየቁ  ወጣት ኣርሶ ኣደሮች ሙሁራኖች ተማሪዎች ጾታ ሣይለይ ሽማግሌዎችና ሀጻናት የመንግሥት ሠራተኞች ማሠር  መግደል ካገር ውጭ ፈርተው እና ተሸብረው ከሚሠደዱ ኣሁንም እርምጃ እወስዳለን በማለት በሠላማዊ ሀዝበ ጦርነት ማወጁ ኣቁማችሁ በትክክል ኢትዮጲያዊ ዜጎች ከሆናችሁ የዜጎች ጥያቄ ኣዳምጣችሁ  ለህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ የፖለቲካ ኣይዶሎጃችሁ ፓሊሣችሁ በመፈተሽ ለፈጸማችሁት ወንጀል ማነው ተጠያቂ

ብላችሁ   መልሥ  በመሥጠት  መታረቁ ያሻችኋል  : ሸኣብያ እንደሽፋን መጠቀሙም ኣያዋጣም:
ይቀጥላል

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: