ዳንኤል ፈይሳ

አባ ገዳዎች ዛሬም ዳግም ወደ ሞራል ማማ ተምዘገዘጉ!!!

” የኦሮሞ ህዝብ እንኳን የሚወደው ልጁን ገድለውበት ይቅር እና የሚወደውን ከብቱን ሥነኩበት አይወድም።በገዳ ሥርዓት አንድን የኦሮሞ ልጅ መግደል ሚልዮኖችን ማሥቀየም ነው”አንደኛው አባ ገዳ በኦሮሚያ አባ ገዳዎች ምክር ቤት ላይ የተናገረው።

“የኦሮሞን ህዝብ ችግር መንግሥት አያውቀውም ።እኛ ግን እናውቀዋለን ።ህዝቡ በየቀኑ ይነግረናል።”ሌላኛው አባ ገዳ የተናገረው።
በነገራችሁ ላይ አሁን ያሉት አባ ገዳዎች ብዙዎቹ ከመንግሥት ጋር ፀብ ላይ አይደሉም።ምክርቤቱም በመንግሥት እውቅና ያለው ነው።

ለማሥታወሥ ያክል ላለፉት ብዙ መቶ ዓመታት በአንፃራዊነት ያለምንም ጣልቃ ገብነት እምነት ሥመሩ እና ጠንካራ ተቋም ገንብተዋል እንድሁም ብዙ ሚሊዮን ተከታይ ያላቸውን ቤተ እምነቶች የሚመሩት የእምነት አባቶች ከአንዱ በሥተቀር ሁሉም ግድያን ሳያውግዙ መንግሥት ተጨማሪ ግድያ እንድፈፅም እንዳበረታቱ እናሥታውሳለን።በተቃራንው ለላፉት ከመቶ በላይ ዓመት እንዳይተገበር የተከለከለው ፤ ተቋማቱ የተዳከሙበት እና እራሱን እንደገና ለማቋቋም እየተፍጨረጨረ ያለው የገዳ ሥርዓት መሪዎች በምንም ዓይነት መልኩ በመንግሥት ታጣቅዎች እየተወሰደ ያለውን ግድያ እናወግዛለን በማለት ለሰበሰባቸው መንግሥት በፍትለፍት ነግረውታል።

ይህንን ነው አባ ገዳዎች ዛሬም በሞራል ማማ ወደ ላይ ተምዘገዘጉ ያልኩት።

 

10406827_775582875875503_9172276004030874316_n (1)

 posted by Geremew Aragaw