The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የኦሮሚያ ለኦሮሞዎች አስተሳሰብን እንዴት ያዩታል; – ሰርጸ ደስታ

በመጀመሪያ ከይቅርታ ጋር ኦሮምኛ ተናጋሪው እያልኩ እንድጽፍ የሚያስድደኝ የማውቀውን እውነት ላለመካድ ነው፡፡ አማራ ለሚባለውም፣ ትግሬም ለሚባለው ሌላም ይሄንኑ ነው የምጠቀመው፡፡

ethiopian-oromosበትላንትናው ዕለት ያለወትሮዬ ሰይፈ ነበልባል ሬድዮንን ሳደምጥ ነበር፡፡ በእርግጥም የዶ/ር መረራን ቃለመጠይቅ ሊንክ ተከትዬ ነው እዛ የገባሁት፡፡ በአጋጣሚው ግን ከዶ/መረራ ቃለምልልስ በተጨማሪ የሌላ ዶ/ር ጌታቸው እጅጊ(ይቅርታ የአባታቸውን ስም ከተሳሳትሁ)ን ቃለምልልስ ተከታተልሁት፡፡ የሰይፈ ነበልባሉ ጋዜጠኛ ኢዮብ ለሁለቱም አንድ መሠረታዊ ጥያቄ አንስቶ ነበር፡፡ ዶ/ር መረራ ጥያቄውን በግልጽ ይለፈኝ ብለውት አልፈውታል፡፡ ዶ/ር መረራ የራሳቸው ምክነያት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ እንደ እኔ ግን ባያልፉት ጥሩ ነበር ባይ ነኝ፡፡ ዶ/ር ጌታቸው ግን በግርድፍድፍ ሊመልሱት ሞክረዋል፡፡ ጥያቄው ኦሮምያ ለኦሮሞዎች የሚለውን አመለካከት በተመለከተ ነው፡፡ርዕስም ያደረኩት ልክ ኢዮብ እንደጠየቀው ነው፡፡  እርግጥ ጥያቄው ለዶ/ር መረራ በቀጥታ እንደቀረበው አይደለም ለዶ/ር ጌታቸው የቀረበው፡፡ ዶ/ር ጌታቸው ብዙዎችን ጥያቄዎች ሲመልሱ ስሜተኛ ሆነው ስለነበር ነባራዊውን ሁኔታ በትክክል በሚገልፅ አልመሰለኝም፡፡ በስሜተኝነታቸው ግን ልወቅሳቸው አልፈልግም ሁኔታዎች በእርግጥም የሚያሳዝኑና የሚያበሳጩ ናቸውና፡፡ ሆኖም ስሜታቸውን መቆጣጠር ቢችሉ ጥሩ የተሻለ ነበር፡፡ በዚህ ቃለምልልሳቸው ሌላው ሕዝብ የኦሮሞን ትግል ያለመቀላቀሉ የኦሮሞ ሕዝብ ችግር አይደለም ብለዋል፡፡ መሠረታዊ ችግሩ ግን በእርግጥም በዋነኛነት የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ እያነሳቸው ያሉት ጥያቄዎች ሌላውን ለማሳተፍ ዝግ በመሆናቸው አልፎም ለሌላው ስጋት በመሆናቸው ነው፡፡

የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ጥያቄ እንዴት ለሌላው ስጋት ይሆናለ ከተባለ በጥቂቱ እንደምሳሌ እያነሳሁ ልጠቁም፡፡

ምሳሌ 1፡ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ችግር፡- ዛሬ ኦሮምያ የሚባውን ክልል ያጥለቀለቀው የሕዝብ ተቃውሞ መነሻው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንደሆነ ሆላችንም እናስታውሳለን፡፡ የዚህን ማስተር ፕላን የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ በተናጥል መቃወሙ ከዚያም በላይ ተቃውሞው መሠረት ያደረገው ከፍትህና መብት ውጭ በሆነ በዘር በተከለለ ጉዳይ መሆኑ አንድምታውም ሌሎችን አይመለከትም እንደውም ሌሎች አዲስ አበባና አካባቢው ላይ መወሰን አይችሉም ስለነበር ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ስጋት እንደሆነ አንካካድ፡፡ ልብ በሉ የአካባቢው ገበሬዎች መፈናቀልና ቀጥሎ የሚመጣውም የኑሮ መመሳቀል የሁሉም ዜጋ ሊቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነበር እንጂ ለኦሮሞ ሕዝብ የተለየ ጉዳይ ባልሆነም፡፡ ያም ሆኖ ተቃውሞውን እውን ሌሎችን ለጥሪ የጋበዘ ቢሆን ኖሮ ሌሎች ይቀላቀሉት ነበር ወይ የሚለው እኔም አይመስለኝም ከሚሉት ነኝ፡፡ ቢያንስ ግን ሌሎችን በማያገል መልኩ ስልታዊ መሆን ነበረበት ባይ ነኝ፡፡ ማግለሉ ባይኖር ሌሎች ዘግይተውም ቢሆን ተቃውሞውን ይቀላቀሉ ነበር ባይ ነኝ፡፡ የሆነው ግን ተቃራኒው ነው፡፡  ብዙ ጊዜ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ እንቅስቃሴዎች ሌላውን በማግለል ናቸው፡፡  እኔ ትዝ ከሚለኝ አንዱ በአንደ ወቅት በቦረናና ባሌ አካባቢ የሰደድ እሳት ተነስቶ ብዙ ደናችንን ሲያወድም ብዙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እሳቱን ለማጥፋት በአንድነት ጥያቄ እያቀረቡ ሳለ  ጉዳዩን አጥበውት የሀገር መሆኑ ቀርቶ የኦሮሞ ተማሪዎች ብቻን የሚመለከት እንደሆነ በይፋ ሌላው ተነገረው በዚህም ብዙ ተማሪዎች አንዳዘኑ አስታውሳለሁ፡፡ የሚገርመው ግን የተቃጠሉትን ደን ቦታዎች በአካል የሚያቋቸው ተማሪዎች እያሉ በኦሮሞነት ብቻ የማይገባውና የማይመለከተውም ተግበስብሶ እንደሄደም አስታውሳለሁ፡፡ ደኖቹን በአካል የሚያውቁዋቸውና ያደጉባቸው ለእነሱ ምን ማለት እንደሆኑ እናስተውል፡፡ ወለጋ ያደገ ቦረና ወይም ባሌ ከአደገው እኩል ስለ ሐረና ደን ከጫካነት ያለፈ ትርጉም አይሰጠውም፡፡  ያኔስ አልፎ አልፎም ቢሆን በዩኒቨረሲቲዎች አካባቢ የተማሪዎች አንድነት ጭልጭል ይል ነበር፡፡ ዛሬ ያ ከጠፋ ብዙ ዓመታት ቆጠርን፡፡

ምሳሌ 2. ኦሮምያ የኦሮሞዎች የሚለው አስተሳሰብ፡- ይሄ አስተሳሰብ ራስን በራስ ከማጥፋት ያልተሻለ እንደሆነ መረዳት እንኳን የቻልን አልመሰለኝም፡፡ እንዲህ በሚባልበት ተቃውሞ እንዴት ሌሎች የተቃውሞው ተሳታፊ ይሆናሉ; ከጥንትም ጀምሮ ኦሮምኛ መነገርም ከመጀመሩ በፊት ዛሬ ኦሮሚያ የተባለው ክልል ውስጥ እኮ የሚኖሩ ሕዝቦች አሉ፡፡ ሲጀምር አገሩ እኮ ከመሠረቱ  የኦሮምኛ ተናጋሪው አይደለም፡፡ ኦሮምኛ ተናጋረው እንደ አንድ የሕዝብ አካል በአገሩ የመኖር እንጂ ሌላውን የማስወጣት መብትም ማን ሰጠው; ይህን ጉዳይ የሰይፈ ነበልባሉ ኢዮብ ለታዳሚዎቹ ማነሳቱን አደንቃለሁ፡፡ ጥያቄው ግን አልተመለሰም፡፡ ይህ አንኳር ጉዳይ ነው፡፡ የዚህ አስተሳሰብ አቀንቃኞች እነማን ናቸው; ዛሬ ኦሮምያ ውስጥ የሚኖረው ሕዝብ በጣም የተወሳሰበ ማሕበራዊና ባሕላዊ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ብዝሀነት ያለው እንደሆነ ለማያውቁት ቆመው ሊቃዡት ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክነያት ግን ሕዝብ በራሱ ላይ የመጡበትን ጠላቶቹን በጋራ እንዳይዋጋቸው ጎልበቱን በመሸንሸን ያደክሙታል፡፡ ኦሮምያም ሌላውም የኢትዮጵያ አካል በእንደዚህ ያሉ አስተሳሰቦች ሽባ እንደሆነ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ በቅረቡ ባሌ ሮቤ ላይ ሕዝብ የሞቱ ወገኖችን ፍትህ ለመጠየቅ ለወጣብት ሰላማዊ ሰልፍ የተወሰኑ እዛ ደግሞ ሀይማኖትም የታከለበት ማግለል የተነሳ የተባለው ሰልፍ እንደቀረ ሰምቻለሁ፡፡ አጋጣሚውን እንኳን ተፈጥሮላቸው ራሳቸውም ለሚፈጥሩት የሕዝብ ጠላቶች ግን ድል ነው፡፡

ምሳሌ3. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ፡፡ እንደ እኔ እምነት የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ሙሉ የኢትዮጰያዊነት ወኔ እስከሌለው ድረስ ራሱም ነጻ አይወጣም እሱ ካልወጣ ደግሞ ሌሎች ነጻ  መሆን አይችሉም ባይ ነኝ፡፡ ያለ ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ነጻነት የሌላው ሕዝብ ነፃነት ሁሉ አደጋ ላይ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ በመሪነት ሌላውን መጋበዝ ሲገባው ብዙ የሚባለው የዚህ ሕዝብ አካል ኦሮሞ ብቻ ከዚያም በላይ ኢትዮጵያ የሚባል ቃል እያስደነበረው እንዴት ፍትህ የሰፈነባት ኢትዮጵያ የምትባል አገር ማየት ይቻላል፡፡ ዛሬ እኮ ወይኔ በሉት ሌላው እንደልቡ የሆነው ይሄ አስተሳሰብ ጽኑ መከላከያ ግንብ ሆኖት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ አንስቼዋለሁ አሁንም አነሳዋለሁ ግልጽ የሆነው የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ የበላይ የሆነበት የታላቁ ሚንሊክን ታሪክ ይህ ትውልድ እስከሚረዳው ድረስ የሌሎች ተገዥነቱ ይቀጥላል፡፡ ዶ/ር ጌታቸው በንግግራቸው ልጅ ኢያሱን ከእነ ታደሰ ብሩና፣ ሌሎቻ ጋር  እንደ አንድ የኦሮሞ ልጅ ሰለባ አንስተዋል፡፡ እዚህ ጋር እኔና ዶ/ር ጌታቸው እንስማማለን፡፡ ስለምኒሊክ ግን ምን እንደሚያስቡ ስለማላውቅ ምንም ማለት አልችልም፡፡ አንድ ነገር ግን እኔ የማውቀውን እናገራለሁ፡፡ ሁሉም ኢያሱ የምኒሊክ የልጅልጅ እንሆኑና ምኒሊክ ስልጣናቸውን ሰጥተዋቸው እንዳለፉ ያውቃል፡፡ ምን አልባት ብዙው የማያውቀው ምኒሊክ እንዴት ስልጣንን ለልጅ ልጃቸው ሰጡ የሚለውን ነው፡፡ ለዛሬው ኦነግና ወያኔ የፈጠሩት የቁቤ ትውልድም የማይገባው ይሄ ነው ቢገባውም እንዲገባው አይፈልግም፡፡ እውነታው ምኒሊክ ሥልጣን የመንግስታቸው ምሰሶ ለነበረው ለኦሮምኛ ተናጋሪወ ሕዝብ መስጠታቸው ነበር፡፡ አልያማ ኢያሱ እኮ በእድሜም ልጅ፣ በትውልድም የልጅ ልጅ እንጂ ቀጥታ ልጅም አልነበሩም፡፡ ከዚህ በኋላ ስለተደረገውና እስከዛሬም ያ ታሪክ ይፋ እንዳይሆን ሌት ከቀን  ስለሚያሴሩት ለሕዝብ እተዋለሁ፡፡ ይህን ታሪክ በደንብ የተረዳ ሕዝብ ማንም እንደፈለገው እንደማይዘውረውና ለማንም እንደማይበገር ከኃ/ስላሴ ጀምሮ ያሉ ባለስልጣኖች በድንብ ያውቁታል፡፡ የአሁኖቹ ደግሞ እጅግ ያስፈራቸዋል፡፡ ይህን ታሪክ ግን በኢትዮጵያዊነቱ የሚመካ ሁሉ ይፈልገዋል፡፡ ክብርና ኩራቱም ነውና፡፡

ምሳሌ4፡-ጎሰኝነት ብዝሀነትን ያለመውደድ፡- ራሱ የኦሮምኛ ታናጋሪው ሕዝብ በዘርም፣ በባሕልም፣ በእምነትም ብዝሀነት ያለው ሲሆን አሮሞ በምትባል ቃል ብቻ ራሱን አስሮ ሌላውን ያገላል፡፡ ለሌሎችም ከእነሱ ለመለየት ስም ይሰጣል፡፡ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ሐበሽነቱን ክዶ ለሌሎች ሰጥቷል፡፡ ሐበሻ የሚባለው ሕዝብ ግን ሱዳንን፣ ሶማሌን፣ የመንን ጨምሮ የሚኖረው ሕዝብ ባለ የተለያየ ቀለም (ቀይ፣ ጠየም፣ ጥቁር …) በሚል የሚታወቅ ሕዝብ መጠረያ መሆኑን ብዞዎች አንረዳም፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ከዚህ የሚለይብት አንድም እውነት የለም፡፡ ስሜት እንጂ፡፡ ከዛም ባላይ ኦሮምኛ ተናጋሪው ጥንታውያን አባቶቹ ዛሬ ሐበሻ እያለ ባዕድ የሚያደርጋቸው እንጂ ወላቡ አይደለም፡፡ ይህንን እውነት እንድንነጋገር እድል የሚሰጥ መድረክ ቢኖር በስሜትና በቲፎዞ ሳይሆን በግልጽ በሚቀርብ መረጃ ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ አሁን ከአለንበት ሳይንስ እንጻር ከባድ አይደለም፡፡  የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ይህን ያህል ግዙፍ ሆኖ ራሱን ባጣም እያጠበበ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ዘፈኖች ሳይቀሩ አሮሞ በሚል እጂ እንደ ድሮው ብዝሀነቱን በሚገልጽ የሰፈረባቸውን አካባቢዎች በሚወክል መዘፈን አቁመዋል፡፡ ኢጆሌ ሻምቡ፣ ኢጆሌ ሀሮ፣ ኢጆሌ ባሌ፣ በረዱ ሀረር፣ በረዱ ጂማ ወዘተ በሚል የምናውቃቸው ዘፈኖች ሁሉ አሮሞ በሚል ታጥፈዋል፡፡ አንዳንዶችም ከሌሎች የሆኑ ያሳመሩ መስሏቸው ትርጉሙን ሳይረዱ እንድሁ በሬዱ ኦሮሞ በሚል ዘፈናቸው ሲያደነቁሩን እናያለን፡፡ ሕዝብ ማንነቱና አካባቢው ተመሳሳይ ስያሜ ካለው በዛው ቢዘፈንለት ችግር የለውም፡፡ ለምሳሌ ጉራጌ፡፡ ግዙፍና ሰፊ ቦታን ያካለለ፣ የተለያየ በሕልና እምነት ያለው ሕዝብ ግን እራስን እንደማሳነስ ነው የማየው፡፡ አስቡት እስኪ የአማራ ቆንጆ ተብሎ ቢዘፈን፡፡ ዘረኝነት ከመናገር ውጭ ምን ጣዕም ይሰጣል፡፡ አማርኛ ተናጋሪ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነው ብሎ ከማለት በስተቀር፡፡

አንግዲህ እንዲህና አነዚህን በመሳሰሉ ምክነያቶች የኦሮምኛ ተናጋሪው ራሱን ከሌሎች እያራቅ  ሌሎች ከእሱ ጋር ባይተባበሩ ለምን ይደንቃል፡፡ ይልቁንም ሌሎችን እንቅስቃሴዎቹ ስጋት እየሆኑ፡፡ የኦሮሞን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ሁሉ እውን የሕዝቡን ነጻነት የሚፈልጉ ከሆነ እነዚህን አስተሳሰቦች በይፋ እያወገዙ ኢትዮጵያዊነትን ለሕዝቡ ጉልበት ይስጡት፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ በሆኑ አማራጮች ነገሮች እጅግ የከበዱ እንደሆኑ ይረዱ፡፡ ዶ/ር ጌታቸውም ሌሎችን ሊወቅሱ ሞክረዋል፡፡ መወቃቀሱን አልጠላውም፡፡ ግን የምንወቃቀሰው አንድ መሆን ስንችል ነው፡፡ መውቀስ የሚቻለው የራስን ሰው እንጂ ወዳጅ፣ ወጋን ያልሆነን አይደለም፡፡ ወቀሳ እንዴት እኔ እየተጎዳሁ አንተ ዝም ትላለህ የሚል የወንድማዊነት ስሜት እንጂ እኔ እንጂ አነተ ባለመብት አይደለህም በሚባባሉ ወገኖች መካከል የሚሆን አይደለም፡፡ እላለሁ አሁንም የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ እንደአሁኑ ባይሸረሸር ዛሬ 4 ወር ያስቆጠረው ተቃውሞ ባነሰ ጊዜ የምንፈልገው ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ማምጣት በተቻለ ነበር፡፡ እንዲህ ከሕዝብ ጋር አይንና በርበሬ የሆኑ ባለስልጣኖች አገሪቷን እንደልብ የሚጋልቡት በዋነኝነት በኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ የአመለካከት ችግር እንደሆነ ልናገር እወዳለሁ፡፡ ሊያውም መሀል ኢትዮጵያ ውስጥ፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪውን ሕዝብ ጉዳይ እንደተለየ ጉዳይ አድርጎ በማቅረብ ከማንነቱ እንዲመክንና እንዲባዚን ጎልበትም እንዳይኖረው የተደረገውን ያህል ኢትዮጵየውነቱ ላይ ሩቡ ተሰርቶ ቢሆን ሊሆን የሚችለውን እናስብ፡፡ አሁንም ቢሆን የዚህን ሕዝብ ጉዳይ ይዘናል የምትሉ ሁሉ ከኢትዮጵያዊነት ውጭና ሌላው በማግለል የምታደርጉትን እንቅስቃሴ አስቡበት፡፡ ይሄው 70 ዓመት ሆኖናል እያላችሁን ነው፡፡ ሕዝቡ ግን ጭራሽ ስቃዩ እየበዛ ነው፡፡  ዛሬም አልመሸም በይፋ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ ጀምሩት ያኔ ምን ያህል ሕዝብ ደጋፊያችሁ እንደሚሆነ ታዩታላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ሌላ አንድ ሊያደረገውት ጉልበት የሚሰጠው የለም፡፡ ሁሉም ያስተውል ወደ ኢሳያስን የሸወዳቸው ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስታር ማመን ያዳገታው ለኢትዮ-ኤርትራ ጦር ጥሪ ሲደረግለት እንዴት እንደወጣ፡፡ መለስ ግን ከጦርነቱም በኋላ የዚህ ሕዝብ ኢትዮጵያ ለሚለው ቃል ያለው ሕብረት ያስደሰታቸው አልነበረም ነግ በእኔ በሚል አሳሰባቸው እጂ፡፡ እውንም እንደፈሩት በ1997ዓ.ም ምርጫ መጣባቸው፡፡ የአደዋ ድል እኮ የኢትዮጵያዊነት ወኔ ነው፡፡ ዛሬ ያሉት ባለስልጣኖች ከዚህ በላይ የሚፈሩት ነገር እንደሌለ እናውቃለን፡፡ ለምን በዘር ልክፍት እንድንበከል እንዳደረጉን እንንቃ፡፡ የጠላቶቻችን ምኞትና ዕቅድ ፈጻሚ አንሁን! መጀመሪያ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን ያግኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ምሁራንም አበክረው ቢያስቡበትና ቢነጋገሩበት ሕዝቡንም ወደዚሁ መንፈስ አንድ አደርገውት ጉልበት ቢሰጡት መልካም ነው፡፡ እኔም እንዳቅሜ ሌላውም እንደዛው መፍትሄ የሚሆን ነገር አለን፡፡

 

አመሰግናለሁ

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: