The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ትንሳኤ ለፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ – አንተነህ ገብርየ

የተወሰኑ ፊዲዮዎች ለግንዛቤ እንዲረዱ ቀርበዋል ይመልከቷቸው

23 (1)

ትንሳኤ የሚለውን የግእዝ ቃል ትርጉም ተነሳ ማለት ሲሆን ተንስአ ለጸሎት፤ ተንስአ ለሥራ፤ተንስአ ለምሥጋና እየተባለ ይነገራል የሁሉም መልእክት ቀጥታ አባባል ልዩ ልዩ ተግባር ለመፈጸም መነሳት ማለት ነው በሁሉም መልኩ የቃሉ ትርጉም መጠን መገኘትን ጠቋሚ ነው። ከዚሁ ጥሬ ቃል የሚወጣው ስም ትንሳኤ ሲሆን ያለ የተገኘ ያልሞተ ማለት ነው ይህ እንግዲህ ከዚህች ዓለም እኛን ለማዳን ከመጣውና በሰው ልጅ ሕይወቱ ያለፈው ጌታችን ከመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ይጀምራል።ክርስቶስ በአይሁዶች ተወግሮ ከተገደለ በኋላም በሦስተኛው ቀን ተነሳ በዚህ ምክንያት ትንሳኤ እንጀምራለን ትርጉሙም ሞቶ ያልቀረ በሌላ መልክ የተነሳ መሆኑን በማሳየት ነው።ተግባራቸው ከመቃብራቸው በላይ ሕያው ሆኖ ያሉ ግለሰቦችም ምንም እንኳን በአካል ባይኖሩም ከትውልድ ትውልድ እየተዘከረ በመሆኑ ትንሳኤ ግብራቸው ይነገራል።

አነሳሴ ትንሳኤ የሚለውን ቃል በዚህ ጹሑፍ ለመተንተን ወይም ለመዘርዘር ሳይሆን ቃሉ የማይሞት ግብርን ለማሳየት ፈረንጆች እንደሚሉት (Immortal)የሚለውን ቃል ጽንሰ ሀሳብ ለማሳየት ነው።ይህን ጉዳይ ይበልጥ ለማሳየት የተነሳሁት በርዕሱ የተገለጸውን የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አይበገሬነትና ትንሳኤ ምንድን ነው የሚለውን ለማብራራት ነው።እኔ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን በአካል አላውቃቸውም በሕይወት እያሉ በተግባራቸው የፈጸሙትን ግን በተለያዩ ሁኔታውች ለማወቅ ችያለሁ።በተለይ በእርሳቸው እጅ ታክመው የዳኑ፤አብረዋቸው ያደጉ፤ አብረዋቸው የሰሩ ስለፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሲናገሩ ሁሉን አይነት ስሜት የሚነካ ተፈጥሮ እንደነበራቸው ለመግለጽ አያዳግትም።(ደግነት፤ትሕትና፤ወንድነት፤አትንኩን ባይነት፤ብልሃት፤ጥበብ፤ፈገግታ፤አርቆ አስተዋይነት፤ለጋሽነት፤ፈዋሽነት…ወዘተ.)ነበሩ ዛሬ በሕይወት እኛ ጋር ባይሆኑም ጀምረውት ያለፉት ራእያቸውን ትተውልን አልፈዋልና ሁልጊዜ አብረውን እንዳሉ ልንወስደው ይገባል።የተቀደሰ ዓላማቸው ግቡን እንዲመታ ማድረግን የሚያክል ኃላፊነት ተጥሎብናል።

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሕዝብን በእኩል አይን የሚመለከቱ ለሁሉም እጃቸውን የሚዘረጉ በልብ ቀዶ ጥገና በዓለም የታወቁ ሊቅ ነው የነበሩት።እንደሚታወቀው ህወሃት ከበርሃ ጀምሮ የሚቀናቀኑትን በተለይም ደግሞ አማራን ነገር በማፈላለግ እያጠፋ የመጣ ስለነበር ወደ መሐል አገርና ከተማ ሲገባም ያን አውሬያዊ ባህርዩን ይዞ ነው የገባው።ሻእብያ አስመራ ህወሃት አዲስ አበባ መንግሥት መሆናቸውን በግንቦት 16/83 እና በግንቦት 20/83 ካወጁ በኋላ በሰኔ ወር 1983ዓ/ም ህወሃት ልማዳዊ ባህርዩን ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጃው የሚካሄድ ስብሰባ በማዘጋጀት የኤርትራን የአገርነት ጉዳይ የመወያያ አጀንዳ በማድረግ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ምሁራንን አወያየ በዚህ አጋጣሚ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በአንዱ ስብሰባ በመገኘት ሁኔታውን ካዳመጡ በኋላ 1/ኤርትራ አገር እንዳለመሆኗ 2/ኢትዮጵያ ወድብ አልባ መቅረት እንደሌለባት 3/የጎሳ ግዛት አስፈላጊ አለመሆኑንና በሕዝብ መሐከል አላስፈላጊ ቅራኔ ስጋትና አለመተማመን ያስከትላል በሚል ብዙው ተስብሳቢ አድፍጦ ዝም ሲል ፕሮፌሰር አስራት ተቃውሟቸውን በምሬት የገለጹ ሰው ነው የነበሩ።ክዚህች ቀን ጀምሮ ፕሮፌሰር አስራት ከህወሃትና ሻእብያ አይን ውስጥ ገቡ።

ከዚህ በኋላ የቀጠለው የበርሃው መፈክር በከተሞች እንዲሉ አማራና አማራነትን ማጥፋት የሚል መርሃ ግብር ወጥቶ በሐረር የተለያዩ ቦታዎች፤በአርሲ፤ወተር፤አርባጉጉ፤ቤንችማጅ፤ በደኖ ፤ጉራፈርዳ፤ጋቤላ፤ቤንሻንጉልና በመላው ኢትዮጵያ አማራን አሰቃቂና በጣም ጨካኝ በሆነ ዘግናኝ ሁኔታ መግደል፤በሳት ማቃጠል በገደል መስደድ፤ሳይሞቱ በሕይወት እያሉ ቆዳቸውን መግፈፍ በአጠቃላይ ይህ ቀረሽ በማይባል ሁኔታ የአማራው ነገድ ሕዝብ እንዲያልቅ ተደረገ።እንግዲህ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ወደ ፖለቲካው ዓለም ብቅ ያደረጋቸው ይኸው ድርጊት ነው።በመሆኑም ወቅቱ አንድ ለአምስት የምትለዋ የህወሃት መዋቅር ገና ስለነበረች የሚተዋወቁ አብረው ያደጉና የሚተማመኑ በጋራ መክረው የመላው ዐማራ ድርጅት በሚል መዐድን መሠረቱ ፕሮፌሰር መስራች ነበሩ በኋላም ድርጅቱን በሊቀመንበርነት መርተዋል።ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ህወሃት፤ሻእብያና ኦነግ አማራነትን አማራን ማጥፋት በሚለው መርህ አንድ በመሆን ዘመቻው በአማራው ላይ ሲነጣጠር ቀዳሚው ተግባር በስብሰባ ላይ የሞገቷቸውን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ሥነ-አእምሯዊና ሥነ-ልቦናዊ ተጽዕኖ ከማድረግ የዘለለ ጥቃት በመሠንሰር ታዋቂው ኃኪም ኃኪም አጥተው ከዚህ ዓለም በሕይወት ተለዩን።

መዐድ ፕሮፌሰር ከሞቱ በኋላ በድሮው ጥንካሬው ሊዘልቅ አልቻለም አሁን እየተባለ እንዳለው አማራ የሚባል የለም የሚሉ ከሃዲ ትውልዶች በአንድ በኩል በሌላ ወገን ደግሞ አማራው በጎሳ ከተደራጀ የህወሃትን ፈለግ መከተል ማለት ነው ስለዚህ አማራው በጎሳ መደራጀት የለበትም ብለው ሞገቱ መዐድ በመኢዐድ ሆነ በመኢዐድ ላይ ያረፈውን ዱላና ድርጅቱ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለም እያየነው ያለ ጉዳይ ነው።የህወሃትን መንገድ የማይከተሉ በርካታ ድርጅቶች መመስረታቸው ይታወቃል ቁጥራቸው ብዙ ለጥቃት የተጋለጡ ሲሆን ህወሃት በሚጭረው ተንኳሽ ሁኔታ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ከተገኙ በቅድሚያ የሚለቀሙት የዚሁ ሞት የተፈረደበት የአማራው ነገድ ተወላጆች ናቸው።አብነት እንውሰድ ከተባለ በአንድነት ፓርቲ፤መኢዐድ፤ሰማያዊ ፓርቲ የተገደሉ የታሰሩ እነማን እንደሆኑ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው።እነ አንዷአለም፤የሽዋስ፤ሀብታሙ…….ወዘተ አማራ ሆነው ስለተገኙ ብቻ ነው ይህን የመሰለ መራራ ጽዋ እየተጋቱ የሚገኙት።

ህወሃት የሰላማዊ ትግሉን በር ዘግቶ አላፈናፍን ሲል የግፍ ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ ብዙ መንገዶችን መከተል የግድ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ትግሉን በተለያየ ስልት ጀምረዋል።የፊት ለፊት ሰላማዊ ትግል፤ዲፕሎማሲያዊ ትግል በውጭ አገር፤የትጥቅ ትግል…ወዘተ ይሁን እንጅ ሁላቸውም ሊሄዱበት የፈለጉትን መንገድ ፈትሾ ይህ ነው ማለት ይቻላል ይህን ለማለት የአዋቂነት መሥፈርት ማሟላት የግድ አይልም በዙ ጊዜ በትግሉ ዓለም የቆየ ሰው በቀላሉ ሊረዳው የሚችለው ጥሬ ሐቅ ነው።አንድ አጠር ያለች ምሳሌ ጠቅሼ ላሳያችሁ፦ፋሽስት የህወሃት መሪዎች አዘውትረው የሚናገሩት ስለ እድገት ነው።ሞጋቾች ደግሞ እድገት የሚለካው ከታች ያለውን የሕብረተሰብ ክፍል ሕይወት በመቀየሩና ባለመቀየሩ፤ሁሉም ዜጎች አገር ባፈራው ሀብት እኩል ተጠቃሚ በመሆንና ባለመሆን፤በመልካም አስተዳደርና የፍትሕ መረጋገጥ በማስፈንና ባአለመስፈን..ወዘተ አባባሉ ትክክል ነው ይህን የሚሰማው ሲኖር ነው።መጀመርያ እየተገዛን ያለው ህወሃትና ሻእብያን ኦነግ በለስ ባይቀናውም እነኝህን ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ድርጅቶችን አደቁነው ባቀሰሱ(ቄስ)ባደረጉ የምእራብና የዐረብ አገሮች ሲሆን እኛው ራሳችን በምንከፍለው ታክስ የአፋኙ ሥርዓት የበለጠ እንዲደራጅ በማድረግ በቀጥታ እየገዙን ያለ ሲሆን እኛው ተባብረን ሥርአቱን ካልገፋነው እነኝህ ጠላቶቻችን ወደሰውነታቸው ይመለሳሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ኃይለማርያም ደሳለኝ ድርቁና ርሃቡ አሣሥቦኛል ሲል ይህን በል ያለው ይኖራል ወይም ኃላፊነት ተሰምቶት ሊሆን ይችላል ግምገማ እስከሚገባ ድረስ ።በሌላ በኩል አርከበ በምግብ ራሳችን ችለናል ርሃቡ ወይም ድርቁ አያሰጋንም በቁጥጥር ሥር እናውለዋለን ወይም አባይ ጸሐየ የኦሮሞን ሕዝብ ልክ እናስገባዋለን፤አባይ ወልዱ ወልቃይቶች የማንነት መብታችን ይከበር እኛ አማራ እንጅ ትግሬዎች አይደለንም ሆነንም አናውቅም ሲሉ የማዳግም እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱ የሚያመላክተው እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ከሕግ በላይ ርቀው መሄዳቸውን እንገነዘባለን።

ጠባቦች ናቸው ጎጠኞች ናቸው ካልን እንዲህ አስተሳሰቡ ስንኩል የሆነ በሌሎች ጥላቻ በተለይም በአማራው ነገድ ህዝብ ላይ በመከፋት ካደገ አመለካከተ ኩድኩድ ቡድን የምንጠብቀው ነገር ከዚህ በፊት የፈፀሙትን አሁን እየፈፀሙት ያለውን ወደ ፊት ሊፈጽሙ ያሰቡትን ብቻ ነው የሚሆነው።ልብስ ስንገዛ ወይም ምግብ ለመጉረስ ስንፈልግ ልቡሱን እንለካዋለን የምንጎርሰውን መጠንም በእጃችን ለክተን እንጎርሳለን የአጭር ወይም የረጅም ጊዜ ታክቲክና ስትራቴጅ ስንነድፍ የስተሳሰብ አድማሳችን ስፋትና ጥልቀቱን ማየት እንችላለን ህወሃቶች ሊያስቡ የሚችሉት ወርድና ቁመቱም እየተናገሩ ያሉትን ነው።አርከበ ወይም አባዮቹ የሚያስቡት የዘረፉትን የሀብት ክምችት ፤የገነቡትን ፎቅ ውጭ አገር ሰደው የሚያስተምሯቸውን ልጆቻቸውን በውጭ ያስቀመጡትን የገንዘብ መጠን ከሞት የሚታደጋቸውን የአጋዚ ሠራዊት መከላከያ ሠራዊት ፖሊስና ደህንነቱ የሚያቃሳዩትን ኃይል የተሞላበት ርምጃ ነው፤አቃቢ ሕግ የህወሃት ጠበቆች የሚፈጽሙትን የሀሰት ውንጀላ መሠረት ያደረገ ሥልጣን ከአንዱ ወደ ሌላው እየተላለፈ እስከ ዘልዓለሙ ሊገዙን የሚችሉበትን ነው የሚያስቡት የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያስቡበት አዕምሮ በፍጹም አልፈጠረላቸውም የአዲስ አበባው መስፋፋት ፤በጎንደር ቅማንቶችን አደራጅቶ ከአማራው ጋር እንዲጋጩ ማድረግና ቅማንቶች ግዛታቸውን እስከ መተማና ቋራ እንዲያሰፉት ማድረግ ከዚያም የአንበሳውን ድርሻም እንዲያስረክቡ የማድረግ፤የወልቃይቱ ያልጠበቁት የማንነት ጥያቄና ሕወሃትን ከተከዜ ማዶ የማድረግ ከለሙ ሰሊጥ ጥጥና ማሽላ ሌላም የሚያመርተውን መሬት የሚያሳጣ ትግል ሲጀምር  ለህወሃት አደገኛ ምጻት ነው።ስለዚህ ሕገ አራዊትን ከሚከተል ሾተላይ ጋር እሰጥ አገባ ከማለት እስከ ወዲያኛው ድረስ እንዳያንሠራሩ አድርጎ የሚያሽልቡበትን መላ በጋራ ከመፍጠር ውጭ ሌላ ምርጫ የለም።

የህወሃት ዱላ እንዳያርፍባቸው የፈሩ ወይም ህወሃት የሚጥልላቸውን ፍርፋሪ በልቶ ለማደር ለሆዳቸው ብቻ የሚገዙ አማራዎች አማራ አይደለንም ቢሉ መልካም ሆኖ ሳለ አማራ የሚባል የለም የሚሉ አማራዎች አንዳንድ የቃጁ ምሁር ነኝ ባዮችና ጸሐፊያን ይህን የሚሉት ከጥላቻ በመነጨ መሆኑን ማወቅና ምላሹን መስጠት ሲገባ ከማንም ተጓዥ ጋር አብሮ መንጎድን ስለመረጡ ወዳጅ ዘመድ የሆነ ሊያዝንላቸው ይገባል የቻለም ቢጸልይላቸው የተሻለ ነው በግሌ ግን እንዲህ አይነት አባዜ ያለው ሰው ወይም ቡድን ይህን ፀያፍ አነጋገር ከፊቴ ቢናገር አማራነቴ የማንነቴ መገለጫ በመሆኑ ከምር የምጣላው መሆኔን ሊያውቅ ይገባዋል ለምን እሱን ወይም እሷን በማንነታቸው የሚያሳፍር ነገር አልተናገርኩምና።የአማራ ሥጋ እንደ በግና ፍየል በሚበላበት በዚህ ወቅት አማራ የሚባል የለም ወይም አማራ በጎሳ ከተደራጀ ጠባብነት ነው የሚሉ ከመስተኋላ ደግሞ ለህወሃትም ሆነ ለሌሎች በአማራ ላይ ጥላቻ ላላቸው ዱላ የሚያቀብሉና የአማራውን ዘር ለማጽዳና ለማጥፋት ከተሰለፉ ኃይሎች ጋር መተባበር የሚያስከፍለው እዳ ከበደ ያለ መሆኑን ከወዲሁ ሊያስቡበት ይገባል።

በአማራ ላይ ፎክረው የተነሱ ግልጽና የታወቁ ጠላቶች በመሆናቸው ምንም አይደለም ነገር ግን የነዚህ ጠላቶቻችን የጥቃት ሰለባ እንድንሆን ያዘናጉን ወይም እኛን መስለው እጃችን እየጠመዘዙ ተራ በተራ ታርደን እንድናልቅ ያደረጉ እንዲሁ በዋዛ ሊታለፉ የሚገባቸው አይደሉም።በለሳ ከሪጅን 3 በኢህአፓ ላይ አንጃ ፈጥረው ወደ ትግራይ በመሄድ የህወሃትን ቡራኬ ተቀብለው ኢህዴን የሚባል ስም ወጥቶላቸው ወደ አማራው ክፍለ ግዛት በመዝለቅ አማራ መስለው አማራውን በሁለት ወገን ጥይት እንዲንገበገብ ያደረጉት አማራዎች አይደሉም በርግጥ በውስጣቸው አማራዎች ነበሩ እነዚያ ግን አማራ ስለነበሩ ሁሉም በህወሃት አዛዥነት በኢህዴን ገዳይነት አልቀዋል።በዚህ ድርጊት ፊታውራሪዎች፦ታምራት ላይኔ፤ተፈራ ዋልዋ፤ህላዊ ዮሴፍ፤በረከት ስምኦን፤ታደሰ ካሣ(ጥንቅሹ)፤አዲሱ ለገሰ፤ካሣ ሸሪፎ የሚጠቀሱ ሲሆን ህወሃትን እየጎተቱ ወደ መሀል አገር ያስገቡበት ሂደትም በሌላ ወገን በደንብ አልተፈተሸም አሁን ደግሞ ብአዴን የሚል ስም ለጥፈው የአማራውን ነገድ ሕዝብ በከፋ ሁኔታ ዜግነቱን ገፈው ከአማራ ነገድ ጋር ምንም የማይገናኙ ገዥዎች ከላዩ ላይ ጭነው የቁም ስቅሉን እያሳዩት ይገኛሉ።

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ይህን በአማራ ላይ የሚደርሰውን ክፉ ድግስ አስቀድሞ በመገንዘብ ነበር የመላው ዐማራ ድርጅት መመሥረት አለበት ያሉት የመሠረቱትም ይሁን እንጅ እሳቸው በነበሩበት ወቅት የነበረውን ጥንካሬ እንደያዘ ሊዘልቅ ባለመቻሉ በመሃሉ ብርድ ገባ አማራውን የሚታደገው ጠፋ በየደረሰበት ተዋከበ።ተሰደደ፤በግፍ ተጨፈጨፈ፤ሀብቱ ተዘረፈ፤መሬቱን ተቀማ በጥቅሉ በአማራ ላይ ያልተሞከረ መጥፎ ድርጊት አለማለት አይቻልም።እሳት ከነበረበት ረመጥ አይጠፋም እንደሚባለው ይህ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ግፍና በደል ታግየ አስቆመዋለሁ በትግሌ እበቀለዋለሁ የሚሉ ውድ የአማራ ነገድ ሕዝብ ቆራጥ ልጆች ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅትን በመመሥረት የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ራእይ ከግቡ ለማድረስ አማራውን ከሁለንተናዊ ጥቃት ለመታደግ የዘር ማጽዳቱና ማጥፋቱ አባዜ እዚህ ላይ ማክተም አለበት በሚል እነሆ እንቅስቃሴ ከጀመሩ ሦሥተኛ አመታቸውን ተያይዘውታል።በነዚህ 3ዓመታት ውስጥም ያልተጠበቁና አበረታች ተግባሮችን በመፈፀም የበለጠ ተጠናክሮ ለመራመድ አመች የትግል ስልቱን በመንደፍ እየገሰገሰ ይገኛል።ከዚህ ጎን ለጎን ግን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሥራዎቹ አልጋ በአልጋ ሆነውለት ነው የተጓዘው ማለት አይደለም። የሌሎቹ እንዳለ ሆኖ ራሱ አማራው ሞረሽን ተፈታትኖታል አሁንም እጅ እግራቸውን መስብሰብ ያልቻሉት እያደናቀፉ ይገኛሉ።በማህበር ላይ ማህበር፤በድርጅት ላይ ድርጅት መፍጠር የዘመኑ ፋሽን ቢሆንም ሞረሽ ወገኔ በከፍተኛ ደረጃ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ተጠንቶ ለሕዝብ ይፋ የተደረገው በአማራ ላይ የተፈፀመ ግፍ በፍጹም ሊሰማቸው ያልቻሉ አማራዎችን ማየት እጅግ የሚያሳዝን ሰይጣናዊ ባህርይ ነው።

በመጨረሻም ፁሑፌን ከመቋጨቴ በፊት አማራ የለም ወይም አማራ አይደለሁም ብንልም የዘር ቆጠራ መሀንዲሱ ህወሃት እንደ እህል አበጥሮ ያውቃችኋልና ህወሃት እየደወለ ያለውን የአማራ ሞት ደወል ሰምታችሁ ራሳችሁን ከሞት ለማዳን ተነሱ ታጠቁ ይህ ፋሽስትና ቅጥረኛ ድርጅት በወገናችሁ ላይ ያደረሰውን ግፍ አጸፋው ለመመለስ ጥርስን ነከስ ወገብን ጠብቅ አድርጎ ታጥቆ ልኩን ማሳየት እንዲቻል ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ወግኑ በያላችሁበት ሁለት ሦሥት ብትሆኑም ተሰባሰቡ ተደራጁ ኦሮሞችን እዩዋቸው እየሞቱም ትግላቸውን አላቋረጡም ጠንክሮ የታገለ ደግሞ ማሸነፉ አይቀሬ ነው ስለዚህ ይህን ግማሽ አካሉ መቃብር ላይ የገባ አውሬያዊ ስርአት አንዱ ሲታገል ሌላው እያረፈ በተራ በሚካሄድ ትግል አይደልም ከሥሩ ነቅሎ መጣል የሚቻለው።በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ መዋከብና ሰላም ማጣት አለበት በተለይ ወልቃይት ላይ የተደቀነው አደጋ በቀላሉ የምንመለከተው አይደልም።1/የህወሃት ህልውና የማክተም ወይም የመቀጠል ጉዳይ ስለሆነ 2/ ጦርነት ቢጫር በመላ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም አገር ሌሎች የሚወስዱት ርምጃ አስጊ በመሆኑ በዚህ ወቅት ያልተደራጀ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አማራ ብቻ ስለሆነ አማራ ተጠንቀቅ።

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: