The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

“ከክፉ ተወልጂ ስፈጭ አደርኩ” | በኢ/ር ይልቃል ጉዳይ ከይድነቃቸው ከበደ የተሰጠ ምላሽ – “ትናንት የግንቦት 7 ሰው ነው ስትሉኝ እንዳልነበር ዛሬ አትወይኑኝ”

Yidenekachew Kebede

ብዙ ነገር እየተባለ ነው ፤ የተባለው ሁሉ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የእራስ አረዳድ የሚኖረው አሰተዋአዖኦ ቀላል አይደለም። ከዚህ በኃላ የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች ማወቅ የሚገባቸውን እንዲያውቁት መደረግ አለበት።
.

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

በፓርቲያችን ለተፈጠረው ችግር ከመነሻው ጀምሮ እስካሁን ስላለው ሁኔታ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ምስክርነቴን እሰጣለው። ከጀርባ ሆኖ በብዕር ስም እንዲሁም እኔ ካልበላሁት ይደፋ አይነት መሰሪ ተግባር ወደ ጎን ትቶ በምክንያት እና በእውነት ላይ የተመሰረተ የሃሳብ ሙግት ለሚገጥመኝ ዝግጁ ነኝ።
.
በተለይ የጉዳዩ ቀጥተኛ ባለቤት የሆነው ሁላችንም ከፓርቲያችን ሊቀመንበር ጀምሮ የምናቀውን እውነት በአደባባይ የምንገልፅበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው።
.
በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የምትገኙ (ሁሉንም ማለቴ አይደለም) የራሳቸውን ፍላጉት እና ምኞት ከመጻፉ ባለፈ፥በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ሲሆን ሲሆን”የምርመራ ጋዜጠኝነት”መሰረት ያደረገ ፤ ካልሆነ ደግሞ ቀለል ባለ ቃለ መጠይቅ የነገሮችን ሂደት በአግባቡ በማጤን ተገቢውን መረጃ ለህብረተሰቡ ማድረስ የሙያ እንዲሁም የህሊና ግዴታ ጭምር ነው ብዬ አምናለሁ ።
.
የማህበራዊ ሚዲያ ወዳጆቼ፤ የነገሩን ሥረ መሠረት በአግባቡ በማጤን፣ ገንቢ አሰተያየት በመስጠት፣ ለምንፈልግው የለውጥ ሂደት እና ለፓርቲያችን ግባት አጋዥ የሚሆን ትችትና ማበረታቻ በመስጠት የተለመደው ድጋፋችሁ ሊለየን አይገባም።
.
በዚህም መሠረተ ለዛሬው የምለው ነገር ቢኖር የሥነ-ሥርዓት ኮሜቴ በፓርቲያችን ውስጥ የተፈጠሩ ችግሮች በአግባቡ መርምሮ ውሳኔ የመስጠት አቅም እንደሌለው አረጋግጫለው።የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ በተሰጣቸው የኃላፊነት ቦታ የግል ፍላጎታቸውን እየፈጸሙበት ይገኛሉ።
.
ለዚህ እንደ ማስረጃ የማቀርበው ከ1 ወር 14 ቀን በፊት እኔ ከሳሽ ባልሆንኩበት በእኔ ስም የሚደረጉ የደብዳቤ ልውውጦች ተገቢ እንዳልሆነ በጻፍኩት ግልጽ ዳብዳቤ ገልጬላቸዋለው፤ይሁን እንጂ በትላንትናው እለት ባስተላለፉት ውሳኔ የከሳሽ ተወካይ እኔን በማድረግ ፣ተከሳሾች ባልቀረብበት ሆነ ተብሎ የፓርቲውን ደንብ ያልተከተለ ህግ ወጥ ውሳኔ አስተላልፈዋል።
.
በዚህ ጉዳይ ላይ 21የምክር ቤት አባላት፣የሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ፣ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላት በተገኙበት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ “በእኔ ስም የሚደረጉ ማናቸውም የክስ ሂደቶች እኔን የማይመለከት ነው፣ከዚህ በኃላ ምክር ቤቱ የሚፈልገውን ተወካይ መመደብ ይችላል”በማለት ጥር 29 ቀን 2008 በነበረን ስብሰባ ላይ ተናግሪያለው። ይህን ሁሉ እውነታ ወደ ጎን በማድረግ ለፓርቲያችን የማይጠቅም ሂደቱን በአግባቡ ያልጠበቀ ተደጋጋሚ ውሳኔዎች፤ በሥነ-ሥርዓት ኮሜቴ እየተላለፈ ይገኛል።
.
በተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም ለብሔራዊ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን በጻፉት ደብዳቤ ፤በሥነ-ሥርዓት ኮሜቴ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከገለጽበት መካከል ” ከሳሽ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት መሆኑ በማስርጃዎች መረጋገጡ እየታወቀ፤በምክር ቤት ሰብሳቢ ስም አቶ ይድነቃቸው ከበደ ነው የከሰሳችሁ መባሉ “ተገቢነት የሌው እንደሆነና የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ከወቀሱበት መካከል አንዱ ጉዳይ ነው።
.
በመሆኑም ይህን ኮሜቴ ያቋቋመው የሰማያዊ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ነው፤ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ጉዳዩ በአግባቡ መርምሮ ተገቢ ውሳኔ ማሳለፍ ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ ።
.
የዛሬውን ለማጠቃለል ፤ትላንትና የግንቦት 7 ትልቅ ተልእኮ የተሰጠው ፣ዋንኛ የግንቦት 7 ሰዉ ነው ሲሉኝ የነበሩ ፤አሁን ደግሞ እነሱ ወይነው እኔን ሲወይኑኝ ስመልከት፤በልጆቹ የሃሳብ ልጅነት እንደትላንትናው ዛሬም መታዘቤ እንደቀጠለ ነው።
.
በነገራችን ላይ “ከክፉ ተወልጂ ስፈጭ አደሩኩ ” ብዬ ለዚህ ጽሁፍ አርእስት የተጠቀሙት ለምን እንደሆነ በቃጣይ እመለስበታለው።ባለፈውም “እውነቱን ማወቅ ለሚፈልግ”በሚል የጀመርኩት ክፍል አንድ ፤ለንባብ ከበቃ በኃላ ክፍል ሁለት ያልቀጠልኩት የሚቀጠለ ሳይኖር ቀርቶ አይደለም ፣ለውስጥ ጉዳይ ቅድሚያ ልስጥ ብዬ ነው።አሁም እንደ-አመጣጡ ቅድሚያ እሰጣለሁ ።

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: