The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ዐማራው ከወልቃይት፣ጠገዴ እና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ ጎን ሊቆም ይገባዋል! – ሞረሽ

Protesters demand reforms and the release of political prisoners vow to press the Ethiopian government with more demonstrations, a day after thousands took part in a rare display of public protest

ቡዕ መጋቢት 29 ቀን 2ሺህ8 ዓ.ም     

ቅጽ 4 ቁጥር  12
የማንኛውም አመፅ መነሻ መሠረቱ፣ ገዥዎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ፣ የመብት ረገጣ፣ የማንነት ነጠቃ እና የሥነ-ልቦና ሰለባ ልኩን አልፎ ገደብ ሲጥስ የሚፈጥረው ምሬት እንደሆነ ይታወቃል። የትግሬ ወያኔ ዘረኛ እና ከፋፋይ የፋሽስት ሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ ቡድን፣ በወልቃት ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ እንዲሁም  በዐማራው ነገድ ላይ በወል፣ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ከ1972ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት በተከታታይ ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው። በዚህ ረገድ የወረዳ ግዛቶቹም ሆኑ ነዋሪው ሕዝብ በየትኛውም ጊዜ፣ የትግራይ የግዛት አካል ሆነው አያውቁም። የትግሬ ግዛት ደንበርም ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም። ሕዝቡም ጥንትም ሆነ ዛሬ፣ በጉርብትና ከሚናገረው ትግርኛ፣ ዐረብኛ እና መሰል ቋንቋዎች በቀር፣ የትግሬነት ባህል፣ ታሪክ፣ ወግ፤ ሥነልቦና እና መሰል የማንነት ማረጋገጫ ዕሴቶች ኖሮት አያውቅም፤ እንዲኖረውም አይሻም።

የትግራይ ሕዝብ በተከታታይ በድርቅ እና በርሃብ ሲጠቃ እየፈለሰ የተጠጋው በእነዚህ የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች ነው። ስለዚህ በድርቅ እና በርሃብ ምክንያት ከትግራይ የሚሰደዱት ሰዎች ኑሯቸውን ሲደጉሙ የኖሩት በቀን ሠራተኝነት እየተቀጠሩ የወልቃይቶችን የሠሊጥ እና የማሽላ አዝመራ በማረስ፣ በማረም እና በመሰብሰብ እንደነበረ የቅርብ ዘመን ትውስታችን ነው። ሆኖም፣ «እንግዳ ሲሰነብት፣ ባለቤት የሆነ ይመስለዋል» የሚሉት አባባል ዕውነት ሆኖ፣ የዐማራው ነገድ ባለው የእንግዳ ተቀባይነት የዳበረ ባህሉ ተቀብሎ ባስተናገዳቸው ሰዎች የውስጥ አርበኝነት፣ ወያኔ ዐማራን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት ላደረገው ዝግጅት፣ የጥቃቱ የቅድሚያ ሰላባ የሆነው በነዚህ ወረዳዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ እንደነበር በተደጋጋሚ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።  በዚህም መሠረት በወልቃይት ፣ በጠገዴ ፣ በጠለምት ፣ በሠቲት እና በአርማጭ ሕዝብ ላይ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ከፈጸማቸው እጅግ የበዙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መካከል የሚከተሉት ለናሙና ያህል የቀረቡ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

ሀ)         በ1972 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ የትግራይ እና የጎንደር ክፍለ ሀገሮች የተፈጥሮ ወሰን የሆነውን የተከዜን ወንዝ ተሻግረው የሚከተሉትን ያገርዘቦች በግፍ ገደሉ። እነዚህም፦

 1. አቶ ማሞ ዘውዴ፣
 2. አቶ እንደሻው ታፈረ፣
 3. አቶ አያሌው ሰሙ፣
 4. አቶ በርሄ ጎይቶም፣
 5. አቶ ሐጎስ ኃይሉ፣
 6. አቶ  ልጃለም ታዬ፣
 7. ግራዝማች ወልዴ የኔሁን፣
 8. ቄስ በለጠው ተስፋይ፣
 9. ቄስ ትዕዛዙ ቀለመወርቅ፣
 10. ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣
 11. ወጣት ግዛቸው ዳኜው፣
 12. ወጣት አዲስይ ልጃለም፣
 13. ወጣት ደረጀ አንጋው፣
 14. ወጣት ዋኘው መንበሩ፣
 15. ወጣት ሕይዎት አብርሃ፣
 16. ወጣት ታደለ አዛናው፣
 17. ወጣት ማሞ አጀበ ናቸው።

ለ)         በ1986 ዓ.ም. «ርዋሳ» የተባለውን ከ500 በላይ ቤቶች የነበሩበትን የገበሬ መንደር አቃጥለው ትግሬ አሰፈሩበት። በዚህ ቀበሌ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎለከፍተኛ ችግር ከተጋለጡት መካከል አቶ ጫቅሉ አብርሃ፣ አቶ አብርሃ ሣህሉ፣ ወይዘሮ ስንዱ ተስፋይ፣ አቶ ዋኜው ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ሐ)        ከ1988 እስከ 1989 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ከ3,000 (ሦስት ሺህ) በላይ ጥማድ በሬዎች ባለቤቶች የነበሩ ገበሬዎችን ገድለውና አሰድደው ትግሬአስፍረውበታል። ሠፈራ የተካሄደባቸው ቦታዎችም ማይደሌ፣ አንድ አይቀዳሽ፣ እምባ ጋላይ እና ትርካን ናቸው።

መ)        ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ማይ ኽርገጽ፣ ቤት ሞሎ፣ ማይ ጋባ፣ ቃሌማ፣ እጣኖ፣ መጉዕ ወዘተ ይኖሩ የነበሩ ነባር የዐማራ ነገድ ተወላጆችን አባረው ትግሬንአስፍረዋል። በአጠቃላይ በጎንደር ለም መሬቶች ከ500,000 (አምስት መቶ ሺ) በላይ ትግሬ እንዲሰፍር ተደርጓል።

ሠ)        የትግሬ-ወያኔዎች ዐማራዎችን የጎንደር ክፍለሀገር ተወላጆችን አደህይተው እና አዋርደው፣ ከሰው በታች አድርገው ይገዛሉ። በአካባቢው የትግሬን የበላይነትአስፍነው ቀጥቅጠው እና አዋርደው ለመግዛት እንዲያመቻቸው የአካባቢውን ታዋቂ እና ባለሀብት ሰዎች አስረዋል፣ ገድለዋል፣ ሀብት ንብረታቸውን ዘርፈዋል። በዚህረገድ ለአብነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚከተሉት አዛውንቶችን የቁም ከብቶቻቸውን መዘረፋቸውን የወልቃይት ጠደገዴ ተወላጆች ያስረዳሉ።

 1. ከአቶ ዘነበ ሐጎስ ከ450 ባላይ የቀንድ ከብቶች ዘርፈዋል፤
 2. ከአቶ ባየው ቢያድግልኝ ከ600 በላይ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈው በመጨረሻም ባለሀብቱን ገድለዋቸዋል፤
 3. ከአቶ ገብረሕዎት ኃይሌ ከ80 በላይ የቀንድ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈዋል፤
 4. በ1981 ዓ.ም. ከአቶ አለባው ሕደጎ ከ500 በላይ የቀንድ ከብቶች እና በርካታ ኩንታል እህል ተዘርፏል።
 5. የቀኛዝማች ገብሩ ገብረመስቀል 24 በሬዎቹ ታርደው ከ900 መቶ ባላይ ማድጋ እህል ተወርሷል።

ረ)         የካቲት 21 ቀን 1972 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ የቃብትያ አዲህርድ ከተማን ለመቆጣጠር በነዋሪው ላይ በከፈተው ጦርነት 9(ዘጠኝ) ሰዎችን ገድሎ 18(አሥራስምንት) ማቁሰሉን የዓይን እማኝ የሆኑት ተሰደው በብሪዝበን ከተማ፣ አውስትራሊያ፣ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፈረደ ያስረዳሉ። በዚያ በትግሬ-ወያኔ እና በነዋሪው መካከልበተደረገው ጦርነት ከሞቱት እና ከቆሰሉት መካከል ስማቸውን ማስታወስ የተቻለው የሚከተሉት ይገኙበታል።

 1. አቶ የልፋዓለም ተኮላ፣ ዕድሜ 65፣
 2. አቶ ጎኦይ መብራቱ፣ ዕድሜ 30፣
 3. አቶ አለነ ክንድሽ፣ ዕድሜ 60፣
 4. አቶ አታላይ አበራ፣ ዕድሜ 64፣
 5. አቶ ባሕታይ ወንድምአገኘሁ፤
 6. አቶ በለጠ ወንድምአገኘሁ፤
 7. አቶ በየነ ያዕብዮ፣ ዕድሜ 70፣
 8. አባ ኃይሌ፣
 9. አቶ ገብሩ ጋሼ፣ ሲሆኑ

ከቆሰሉት መካከል ደግሞ፦

 1. አቶ አሰፋ ገብረመድኅን፣
 2. ሙላው ኃይሌ (አለቃቸው ኃይሌ)፣
 3. አቶ መብራቱ ዋሴ፣
 4. አባ ጎላ ዘለለው፣
 5. አቶ አነጋው ገብረእግዚአብሔር፣
 6. አቶ አበራ አጀቢ፣
 7. አቶ ጥሩነህ ከሰተ፣ እና
 8. አቶ ፈቃዱ ይገኙበታል።

ሰ)         ነሐሴ 10 ቀን 1972 ዓ.ም. ወያኔ ከወልቃይት እና ከጠገዴ ወረዳዎች አስሮ የወሰዳቸው እና እስካሁን የደረሱበት ያልታወቁ የአገር አዛውንቶች የሚከተሉትናቸው።

 1. አቶ ሞላ ዘውዴ፣
 2. አቶ ተበጄ በቀለ፣
 3. አቶ አያሌው ሰሙ፣
 4. አቶ እንደሻው ታፈረ፣
 5. አቶ እሸቴ አያልነህ፣
 6. አቶ ጎኢቶም ሐጎስ፣
 7. አቶ በርሄ ሐጎስ ታፈረ፣
 8. አቶ በየነ አየልኝ፣
 9. አቶ ኃይሉ ልዩነህ፣
 10. አቶ አብርሃ ነጋ፣
 11. አቶ አለባቸው መብራት፣
 12. አቶ ድራር ገሠሠው፣
 13. አቶ ገብረሥላሴ ረዳ፣
 14. አቶ ገብረሕይዎት ባሕታ፣
 15. አቶ ኃየሎም ይርጋ፣
 16. አቶ አለባቸው ደፈርሻ፣
 17. አቶ ሊላይ ሐድጎ፣
 18. አቶ ጎኢቶም ምህረት፣
 19. አቶ ታገለ ወርቄ፣
 20. አቶ መሓሪ አዱኛ፣
 21. አቶ ባየው ቢያድግልኝ፣
 22. አቶ ሢሣይ ዘነበ፣
 23. አቶ አታላይ ዘነበ፣
 24. አቶ ተፈራ ሊላይ፣
 25. አቶ ገብረመድኅን የኋላ፣
 26. አቶ ነጋሺ ተበጄ (አራት አንበሣ ገዳይ የነበረ ጀግና፣ ሆኖም በመኮንን ዘለለው የታፈነ)
 27. ወጣት ግፋባቸው ዳኛቸው፣
 28. አቶ ጌትየው ታምሬ፣
 29. አቶ ርስቀይ ኃይሌ፣
 30. አቶ ተድላ ርስቀይ፣
 31. ቄስ ትዛዙ ቀለመወርቅ፣
 32. ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣

በአጠቃላይ ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሬ-ወያኔ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በሠቲት ወረዳዎች ዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግድያ፣ አፈና እና ደብዛ ማጥፋት እጅግ ብዙ ትላልቅ ጥራዞች እንደሚሆን ይታመናል። ሆኖም ሞረሽ-ወገኔ ካሰባሰባቸው መረጃዎች መካከል ለአብነት የሚከተለው ሠንጠረዥ በዝርዝር ቀርቧል።

 ሠንጠረዥ፦ በወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች ላይ ወያኔ ግፍ የፈጸመባቸው ሰዎች በከፊል፣

EMF

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: