The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ዜና ፍኖተ ዴሞክራሲ (መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓም.)

መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø በሱሉልታ ከተማ በወያኔ ወታደሮችና በከተማዋ ወጣቶች መካከል ፍጥጫና ውጥረት መፈጠሩ ታወቀ። ፍትጫው የተነሳው በሱልልታ ከተማ የሚገኝ አንድ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር መፈንዳቱን ተከትሎ የወያኔ ፖሊሶችና ጦር የከተማዋን ጥበቃ በማጠናከራቸው ሲሆን ወጣቶቹ ተቃውሞ በማሰማታቸው የወያኔ ፖሊስና ጦር ስትተኩስ ለመበተን የሞከሩ ሲሆን ከፍተኛ የዱላ ድብደባም መፈጸማቸው ታውቋል። የወጣቶቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሚደግበት ወቅት የወያኔ የንግድ ሸሪክ የሆነው የመሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆኑ 3 መኪኖች ሲያልፉ በድንጋይ ተደብድበዋል።

Ø በሐረር ዓለማያ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች መኝታ ቤት ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ስለደረሰበት ተማሪዎች ትምሀርት አቋርጠው ወደ ቤተ ሰቦቻቸው ለመሄድ የተገደዱ መሆናቸው ከዓለማያ የመጣው መረጃ ያመለክታል። የእሳቱ አደጋ እንዴት እንደተቀሰቀሰና ለምን ሳይጠፋ ረጅም ሰዓት እንደቆየ የታወቀ ነገር ባይኖርም የዓለማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ግን የወያኔ ደህንነት ኃይሎች የተማሪዎቹን መኝታ ክፍሎች ሆን ብለው በማቃጠል ያነጣጠሩባቸው ተማሪዎችንን መምህራንን በሽብረተኛነት ለመክሰስ በማሰብ ነው በማለት ይናገራሉ። 

Ø ከ10 አመት በፊት በጋምቤላ ከ400 በላይ አኙዋኮች ግድያን ተከትሎ ከወያኔ ጋር ሆድና ጀርባ በመሆን ከሀገር ወጥቶ በኖርዌይ በጥገኝነት ይኖር የነበረው ኦኬሎ አኳይ በወያኔው ፖለቲካ ፍርድ ቤት በሽብረተኛነት ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት ሲሆን ከሶስት ሳምንት በኋላ የቅጣቱ ብይን እንደሚሰጠው ተገልጿል። ኦኬሎ አኳይ በአኝዋኮች ፍጅት ወቅት የጋምቤላ ፕሬዚዳንት የነበረ ሲሆን በጋምቤላ የአኙዋኮችንና የኑዌር ግጭትን ወያኔዎች እንደቀሰቀሱት እና የአኙዋኮቹ ፍጅት በወቅቱ የወያኔ መሪ በነበረው በመለሰ ዜናዊ ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ቀደም ሲል አስታውቆ የነበረ ሲሆን አሁንም በወያኔው የፖሊቲካ ፍርድ ቤት ደግሞታል። የወያኔ ወታደሮች 400 አኙዋኮችን ገድለው 60 ብቻ ነው የሞቱት የሚል ማስተባበያ ኦኬሎ እንዲሰጥ አስገድደውት እንደነበርና አዲሱ ለገሰ በረከት ስምኦንና ገብረአብ ባርናባስ የወያኔው ትዕዛዝ በማስፈጸም እጃቸው እንዳለበት ገልጿል። አኮሌ አኳይ ከዓመታት በፊት ወደ ደቡብ ሱዳን በሄደበት ወቅት የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣኖች ከወያኔ ደህንነት ጋር በመሳጠር ከጁባ ጠልፈውት ወደ አዲስ አበባ እንደመለሱትና በሽብረተኛነት ክስ እንደመሰረቱበት ይታወሳል።

Ø በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነትና ስልጣን ተቀምጠው እጅግ አስነዋሪ ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ የወያኔ ካባ ለባሽ ካድሬዎች ከስልጣናቸው መባረር መጀመራቸውና ዋና ጠባቂው አቡነ ማትያስም ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው ለማባረር መገደዳቸው ታውቋል። የአቡነ ማትያስ ቀኝ እጅ የነበረውና የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ስራ አሲያጅ የነበረው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከየቤተክርስቲያኑና ገዳማቱ ያለውን ንብረት መዝረፉ ብቻ ሳይሆን ለልጁ መታከሚያ በሚል ሰበብ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከቤተ ክርስቲያኗ ካዝና በመሰብሰቡ ከስልጣኑ የተባረረ ሲሆን በእርሱ ምትክ ሌላው ካባ ለባሽ ካድሬ ጎይቶም ያይኔ ተተክቷል። ከየማነ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ኃላፊዎችም ተባረዋል። የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ያሉ ማንኛውም ከፍተኛ ኃላፊነትና ስልጣን በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዲያዝ ባወጣው መመሪያ መሠርት በመንፈሳዊና ሐዋርያዊ ስራ በምትሰራው ቤት ክርስቲያን ውስጥ የዘር መድልዎን በማምጣት ቤተ ክርስትያኗን እያመሳት መሆኑ ምዕመናኑን ካህናቱ በጀመሩት ግፊት ካባ ለባሽ ካድሬዎች ቢነሱም ሌላ ዘረኛ ካባ ለባሽ መተካት ውጤት ስለሌለው ቤተ ክርስቲያኗን ከዘረኛ ካድሬ ቄስና መነኩሴ ማጽዳት የዛሬ ሰራ ነው የሚሉ ምዕመናን ብዙ ናቸው።   

Ø በአስመራ ከተማ በግድ ታፍሰው በካሚዮን ተጭነው ወደ ጦር ማሰልጠኛ ሲወሰዱ የነበሩ ወጣቶች ከተሳፈሩባቸው መኪናዎች ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ በሻዕቢያ ወታደሮች በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። የተገደሉትና እና ምን ያህል እንደሆኑ ለጊዜው ባይታወቅም ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም  ካሚዮኖቹ የሚሄዱበትን መንገዶ በአውቶቡስ አማካይነት  ለመዝጋት ሙከራ ያደረጉ የወጣቶቹ ዘመዶችና ጓደኞች በሙሉ በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ተነግሯል። የሻዕቢያ መንግስት እስካሁን በጉዳዩ የሰጠው መግለጫ የለም። በሻዕቢያ ውስጥ የወታደራዊ አገልግሎት የጊዜ ወሰን የሌለው መሆኑ ሲታወቅ አብዛኛዎቹ እድሜ ልካቸውን ሲያገለግሉ የሚቆዩ መሆናቸውና  የኑሮው ሁኔታቸውም በጣም አሰቃቂ እንደሆነ ይነገራል። ይህ አሰቃቂ የኑሮ ሁኔታና የሻዕቢያን አፈና ለማምለጥ በርካታ ወጣቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገሮች እና ወደ አውሮፓ መሰደዳቸው በየጊዜው የተገለጸ መሆኑ ሲታወቅ የሻዕቢያ አገዛዝ ከፍተኛ አፈናና ጭፍጨፋ ከሚያካሄዱ የአለም አገሮች ውስጥ ዋነኛው ነው በማለት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ድምጻቸው በተደጋጋሚ ሲያሰሙ ቆይተዋል።

Ø በሊቢያ በፌስ ቡክ እና በሌሎች የማህበረሰባዊ መገናናዎች አማካይነት በድብቅ የሚካሄድ የመሳሪያ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ እየደራ መምጣቱን ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን ይሰራጫል የተባለ አንድ ጥናታዊ ዘገባ አመለከተ። ለአርባ ዓመት ሊቢያን ሲገዛ የቆየው የኮሎኔል ጋዳፊ አገዛዝ በየጊዜው ያከማቸው መሳሪያ አገዛዙ ሲወድቅ በተለያዩ አማጽያን እጅ የገባው መሳሪያ ዛሬ በጥቁር ገበያ በሰፊው እየተሸጠ መሆኑን ጥናቱ ይዘረዝራል። በፌስ ቡክ፣ በኢንስታግራም፣ በዋትስ አፕ፣ እና በቴሌግራም አማካይነት በብዛት እየተሸጡ ያሉት መሳሪያዎች እንደሽጉጥና ካላሽንኮቭ የመሳሰሉት የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ሲሆኑ ለሽብርተኞች መገልገያ የሆኑ በትከሻ ላይ ሆነው የሚተኩሱ ጸረ አውሮፕላንና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችም የሚሸጡ መሆናቸውም ተጠቁሟል። አንድ ካላሽንኮፍ መሳሪያ እስከ 1800 ዶላር ሲያወጣ በተለይ የመጓጓዣ አውሮፕላንን ሊመታ የሚችል ጸረ አውሮፕላን መሳሪያ ደግሞ እስከ 62 ሺ የአሜሪካን ዶላር እንደሚሸጥ ዘገባው ይገልጻል። የመሳሪያ ሽያጮቹ የሚከናውኑት በአብዛኛው እንደ ትሪፖሊ፣ ቤንጋዚ እና ሳብራታ በመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች ሲሆን ንግዱ የሚካሄደው ወጣቶች በሆኑ የተለያዩ የሚሊሺያ አባላት መካከል መሆኑም ተድርሶበታል።  የፌስ ቡክ ቃል አቀባይ በሰጠው መግለጫ ይህን የመሰለ ንግድ በፌስ ቡክ አማካይነት መካሄዱ ወንጀል ገልጾ መረጃውን እየፌስ ቡክ አገግሎቱን እንዘጋዋለን ብሏል። የአውሮፓ ባለስልጣናትም ጉዳዩ ያሳሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፤

    በተያያዘ ዜና ትሪፖሊን መሰረት አድርጎ ሲንቀሳቀስ  የነበረው የመንግስት አካል በትናንተናው ዕለት ደም መፋሰስን ለማስወገድ ከስልጣን ወርጃለሁ የሚል መግለጫ በፍርድ ሚኒስቴሩ አማካይነት መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን የዚሁ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሚስተር ካሊፋ ገውሊ  ደግሞ በድረ ገጻቸው ላይ ባወጡት መግለጫ ቀደም ብሎ የወጣውን መግለጫ መቃወማችውን ገልጸዋል። መግለጫ  ማንም ሚኒስቴር ሆነ ሌላ ኃላፊነት የተሰጠው ግለስብ በተመድ ከተሰየመው የአንድነት መንግስት ጋር እንዳይተባበር የሚያሳስብ ሲሆን ተባባሪ ሆኖ ከተገኘ ከፍተኛ እርምጃ እንደሚወሰድበት ይገልጻል። ሚስተር ካሊፋ ገውሊ በተመድ የተቋቋመውን የአንድነት መንግስት በጽኑ ከሚቃወሙ ግለሰቦች መካከል አንዱ መሆናችው የሚታወቅ ሲሆን መግለጫቸው በሌሎች ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው ለጊዜው ለማወቅ አልተቻለም። በአሁኑ ወቅት ሚስተር ካሊፋ ይህንን እርምጃ እንዲወስዱ የገፋፋቸው ምክንያቶች ለጊዜው ግልጽ ባይሆኑም በቡድኑ ውስጥ ከፍተኛ ክፍፍል መኖሩን ያሳያል በማለት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ።

Ø የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሽር ለቢቢሲ ጋዘጠኛ በሰጡት ቃለ ምልልስ የአሁኑ የስልጣን ዘመናቸው በ2013 ዓም ሲያልቅ ስልጣናቸውን የሚያስረክቡ መሆናቸውን ገልጸዋል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ስልጣን የሚለቁ መሆናቸውን በመግለጽ የገቡትን ቃል በተደጋጋሚ ሲያጥፉ የነበሩ በመሆናቸው እለቃለሁ ብለው መናገራቸው የተለመደው ማጭበርበር ነው  የሚሉ በርካታ ናቸው። ፕሬዚዳንቱ በቃለ ምልልስ ወቅት በዳርፉር ከ10 ሺ በላይ ዜጎች ቤታቸው ጥለው ተሰደዋል፤ 2.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በካምፕ ውስጥ ይኖራሉ  በሚል ተመድ ያሰራጨው መረጃ የተጋነነ ነው ከማለታቸውም በላይ የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች በዳርፉር የሚቆዩበት ምንም ምክንያት ስለሌለ ባስቸኳይ መውጣት አለባቸው ብለዋል። የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለፖሊቲካ ማራመጃ ተብሎ የተቋቋመ መሆኑን በመግለጽ በአገራቸው ሕዝብ ተወዳጅነት ስላላቸው የተመሰረተባችውን ክስ እንደማይቀበሉት በቃለ ምልልሱ ገልጸዋል።

 

  • በተያያዘ ዜና ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ከሳልቫ ኪር ጋር ከጥቂት ወራት በፊት እርቅ የተፈራረሙት ሪክ ማቻር በሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም ጁባ የሚገቡ መሆናቸውንና በዚያም ከሳልቫ ኬር ጋር በመሆን የአንድነነቱን የሽግግር መንግስት እንደሚያቋቁሙ ገልጸዋል። ባሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ቦታዎች የሚደረጉት ጦርነቶች ሙሉ በሙሉ ያልቆሙ በመሆናቸው ስምምነት የተደረገበት የአንድነት መንግስት ስራ አለመጀመሩ ብዙዎችን ሲያሳስብ ቆይቷል። በሌላ በኩል በደቡብ ሱዳን  መድኃኒት እና ሌሎች የህክምና አገልግሎት መሳሪያዎች ከፍተኛ እጥረት በመፈጠሩ ርዳታ ፈላጊዎችን ለመርዳት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን ድንበር የለሽ ሃኪሞች የተባለው ድርጅት ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ ገልጿል። መግለጫው የእርዳታ ድርጅቶችና ሌሎች የአለም አቀፍ ተቋሞች ይህን ከፍተኛ የሆነ እጥረት ለማሟላት ባለመቻላቸው የብዙ ሰዎች ህይወት አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊወድቅ ችሏል ብሏል። የአለም የምግብ ፕሮግራም እና የዓለም አቀፉ የእርሻ እና የምግብ ድርጅት ማክሰኞ መጋቢት 27 በሰጡት መግለጫ በደቡብ ሱዳን የእርዳታ እህል እጥረት በመኖሩ ከፍተኛ ረሃብ እየተከሰተ መሆኑን የገለጹ መሆናቸው ይታወሳል።

To Listen PART 1: http://www.finote.org/April07EVE_Hr1.mp3
To Listen PART 2: http://www.finote.org/April07EVE_Hr2.mp3

 

መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø በሊቢያ የትሪፖሊ ከተማን ማዕከል አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ራሱን መንግስት ነኝ ብሎ ሲጠራ የቆየው አካል ስልጣን የለቀቀ መሆኑን የፍርድ ሚኒስትሩ ባሰራጨው መግለጫ አሳታውቋል። መንግስቱ በመግለጫው ላይ ይህንን እርምጃ የወሰደው በአገሪቱ ውስጥ ተጨማሪ ደም መፋሰስን ለማስቀረት ነው ብሏል። የመንግስት ማህተም ያለበትና በማን እንደተፈረመ የስም ዝርዝር የማያሳየው በይፋ የተሰራጨው መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ ፕሬዚዳንቱም ሆኑ ሚኒስትሮቹ ስራ መስራት ያቆሙ መሆናቸውን ገልጿል። ባለፈው ረቡዕ ትሪፖሊ ወደብ የገባው በተመድ አስተባባሪነት የተቋቋመው የሊቢያ የአንድነት መንግስት ተወካዮች ቡድን ከባህር ኃይል ቅጥር ግቢ ውስጥ ስራውን እያካሄደ መሆኑና ከአንዳንድ ክፍሎች ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ የተነገረ ቢሆንም  በርከት ያሉ የመንግስት መዋቅር አባላትና የሚሊሺያ መሪዎች አሁን ድረስ ተቃውሞ እያሰሙ በመሆናቸው በምን ያህል ጊዜና በምን ዓይነት ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቶ አገሪቱ ሊያረጋጋ እንደሚችል እስካሁን ግልጽ አይደለም።

 

Ø የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሚስተር ዙማ በወንጀል ተከሰው ከስልጣን እንዲወገዱ የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ተወያቶ እንዲወስንበት በተቃዋሚ ክፍሎች የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንደተጠበቀው ውድቅ መደረጉ ታውቋል። የፕሬዚዳንቱ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ አብላጫውን መቀመጫ የያዘበት የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ 233 የምክር ቤት አባላት ድምጽ በመስጠት የውሳኔ ሀሳቡን ውድቅ አድርገውታል። የውሳኔ ሀሳቡን የደገፉት የተቀዋሚ ድርጅቶች አባላት ቁጥር 143 ብቻ ነበር። የውሳኔ ሀሳቡ ሊያልፍ የሚችለው ከምክር ቤቱ መቀመጫዎች ሁለት ሶስተኛው ከደገፈው ብቻ ነው የሚል ሕግ በመኖሩ የውሳኔ ሃሳቡ ውድቅ ሆኗል። ፕሬዚዳንቱ በሙሥና በመዘፈቃቸውና የዝምድና ስራ በማስፋፋታቸው ምክንያት የደቡብ አፍሪካ ሕዝብ ከፍተኛ ጥላቻና ጥርጣሬ እያሳየ ባለበት ሁኔታ የአፍሪካ ብሔራዊ  ኮንግሬስ እሳቸውን ለመደገፍ ሙሉ ድምጽ መስጠቱ ፓርቲው በሚቀጥለው ምርጫ ጠንካራ ተወዳዳሪ እንዳይሆን ሊያግደው ይችላል የሚሉ ታዛቢዎች አልጠፉም። ፕሬዚዳንቱን የሚቃወሙ ድምጾችም እየበረከቱ መጥተዋል። ትሬቨር ማኑዔል የተባሉት የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር እና አህመድ ካትራዳ የተባሉት የኔልሰን ማንዴላ የእስር ጓደኛ ፕሬዚዳንቱ በግላቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጠይቀዋል። የሃይማኖት፤ የምሁራንና የሌሎች የብዙኅን ማህበራት ድርጅቶች አባላት ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ለመግፋት ተከታታይ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድርግ ዝግጅት እያደረጉ ነው።

Ø የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ባካሄደው ተከታታይ ወታደራዊ እርምጃ 11 ሺ 595 ሰዎችን ከቡድኑ ጥቃትና ቁጥጥር ነጻ ያወጣ መሆኑን ገልጾ የተያዙትንም ሆነ በነጻ እጃቸውን የሚሰጡትን የቦኮሃራም ታጣቂዎች ወደሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ የማስተማሪያና የማሰልጠኛ ካምፖች ያቋቋመ መሆኑን ገልጿል። ግለሰቦች ራሳቸውን ችለው በህብረተስብ ውስጥ ድርሻቸውን እንዲወጡ በካምፑ ውስጥ ልዩ ልዩ የሞያ ትምህርቶች የሚሰጡ መሆናቸውም ተገልጿል። እስካሁን ድረስ እጃውን ሰጥተው ወደ ካምፑ የገቡ የቦኮሃራም ታጣቂዎች ምን ያህል እንደሆኑ ባይታወቅም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቡድኑ ወደተሸሸገባቸው ቦታዎች ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች እንዳይደርሱ መንግዶች በመዘጋታቸው በረሃብ የተጠቁ በርካታ የቦኮሃራም አባላት እጃቸውን የሰጡ መሆናችው ተዘግቧል። የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ቦኮ ሃራምን ለመደምሰስ ጫካውን ሁሉ ለማጠርና ለመቆጣጠር አቅም ባይኖረውም የምግብና መሰል ቁሳቁሶች የሚጓጓዙበትን መስመር መዝጋቱ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል ተብሏል።

 

Ø የፓናማ ሰነድ የሚል መጠሪያ ያገኘው በድብቅ የተለቀቀው መረጃ ከሚያጋልጣቸው ከፍተኛ ባለስልጣኖችና ታቃቂ ግለሰቦች መካከል የአፍሪካ ባለስልጣናት እንደሚገኙበት ታወቀ። ሞሳክ ፎንሴካ የተባለው የፓናማ የሕግ ኩባንያ የንግድ ግንኙነት ከመሰረታቸው ታዋቂ የአፍሪካ ግለሰቦች መካከል ክላይቭ ኩሉቡሴ ዙማ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት  የወንድም ልጅ፤ ካልፓና ራዋል የኬኒያ ምክትል የፍርድ ሚኒስትር፤ ጆን አድዶ ኩፎር የቀድም የጋና ፕሬዚዳንት ልጅ፤ ማማዲ ቱሬ የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ባለቤት፣ ሙኒር ማጃዲ የሞሮኮ ንጉስ የግል ጸሐፊ፣ ጆዜ ቫስኮንሴሎስ የአንጎላ የነዳጅ ሚኒስትር፤ ኢያን ከርቡ የቦትስዋና የይግባኝ ፍርድ ቤት ኃላፊ፤ ጃኔት ካቢላ የኮንጎው ፕሬዚዳንት ካቢላ እህት፤  ኮጆ አናን የቀደሞ የተመድ ዋና ጸሐፊ የኮፊ አናን ልጅ ይገኙባቸዋል። እስካሁን የተጋለጡት እነዚህ ሲሆኑ ስም አይዘርዘር እንጅ ከኢትዮጵያውም ሰዎች እንዳሉበት ተጠቁሟል። ብዛታቸው 1.5 ሚሊዮን የሆነው እነዚህ ልዩ ልዩ ሰነዶች ምርመራቸው ሲያበቃ በርካታ ሰዎች ይጋለጣሉ የሚል ግምት ተወስዷል።

http://www.finote.org/news.html

posted by Geremew Aragaw

 

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: