The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ብሄራዊ ውርደት ይብቃን – ግርማ ቢረጋ

Ethiopia 78

እነሆ እንግዲህ ኢትዯጵያዊነት እንዲዋረድ ጥረት ያደርጉ የነበረ የባንዳ ልጆች እየተሳካላቸው ያለ ከመምሰል አልፎ ብሄራዊ ውርደት ለኢትዮጵያ ተተው እነሱ በህልም በፈጠሩዋት ታላቋ ትግራይ ለመዋኘት እኛን ክመላው አለም አጋጭተው ለማለፍ ጥቂት ሆዳሞችን መጠቀሚያ በማድረግ ኢትዮጵያዊነት መቅመቅ እንዲገባ የማይቆፍሩት የማያርሱት ምድር የለም ፣  እውነትም ኢትዯጵያዊነት የክብር መገለጫነቱን ስቶ በኬንያ፣ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ሱዳን፣ኡጋንዳ ፣ደ.አፍሪካ፣የመን፣ዱባይና በመላው አረብ ሃገራት አሁንማ በአውሮፓ፣ አሜሪካ እንዲሁም በመላው አለም ውርደታችን ብሶ ከመገደልም አልፎ በሰለጠነው ሃገር ውስጥ የጎዳና ተዳዳሪነታችንና አስከሬናችን በየመንገዱ ወድቆ በሰፊው እየታየና እንዲሁም የርሃብና የስደት ምሳሌ እየሆንን እንታያለን ። እኮ ለምን ? የቀደሙት አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በመላው አለም የክብር መገለጫ አድርገው ያስረከቡንን ሃገር ቀድሞም ሃገር ለመውረር ከመጣ ወራሪ ጋር በባንዳነት ያገለገሉ ወላጆቻቸውን ውርስ ይዘው ኢትዮጵያችንን ሲያፈርሱዋት ቆመን እያየን ነው። ኣረ መቼ ነው ለሆድ ማደሩን ትተን ስለ ህሊናችን ማስተዋልና ትንንሽ ልዩነቶችን ትተን እንደ አንድ ቆሞ የሚሄድ አእምሮ እንዳለው ሰው ሆነን የምናስበው?መቼ ነው ስለእውነት የትግሬ ወያኔ ጠላታችን ነው ብለን ለመናገር የምንደፍረው መቼ? አንዳንዶቻችንማ ይባስ ብለን ዛሬ በጋምቤላ በወገኖቻችንን ላይ የደረሰውን ግፍ ሊያስቆጨንና  እግዚዮ ከማለት ይልቅ በፌስቡክ ላይ የተለጠፈልንን ምንም ጣዕም የሌለው የፈረንጅ  ፍጡር ሼር በማድረግ የተጠመድን ፣ኣረ ስለ ወደፊትዋ ኢትዮጵያችን ጥቂት እንኳን ማሰብ እንጅምር ።

ወገን በርሃብ እንዲሁም በጥላቻ ብቻ በአንድ ዘር በታለመልን ጥይት የምንሞተው እስከ መቼ ነው ? በይበልጥ በአውሮፓ እና አሜሪካ ተቀምጦ መኪና ተደግፎ ፎቶ መነሳት ፣ በተለያየ ሬስቶራንት ግብስብስ ቁልል ምግብ ከፊት አስቀምጦ ፍቶ መነሳት በየቀኑ የተለያየ ፋሽን እየቀያየሩ ፎቶን ማሳየት ለጊዜው ቆም ብሎ የወገንን ሰቆቃ እና እልቂት ዞር ብሎ አለማየት እርግጠኛ ነኝ ማስተዋል ከሌለበት አንድ ቀን ዋጋ ያስከፍላል።  በእውነት እኮ ቀደም ባለው ግዜ የኢትዮጵያዊነት መነካት ያም ነበረ እኮ ታዲያ ያ ሁሉ የት ገባ ምን ዋጠው ? ህሊናን ሸጦ ለሆድ መገዛት? ወይስ አላየውም የሚለውን ጨዋታ እየተጫወትን? ኢትዮጵያ እኮ ጥቂት አልነበሩም ጀግኖችዋ ፣ ሁሉም ስለ ሃገራቸው ባንድ ድምፅ የሚያወሩ ልጆች ነበሩዋት ።

ታዲያ የነዛ ጀግኖች ልጆች የት ገቡ ኢትዮጵያዊያን ?ከአንድ ብሄር የወጡ ጥቂት የትግራይ አራዊቶች ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ እያሰሩን እየገደሉን በየእስርቤቱ ሲያጭቁን ዝም ብለን የምንሞትና የምንታጨቅ የሆንነው ከኢትዮጵያችንን የወረስነው ነው እንዴ?ክርስቲያንም ሆነ ኢስላም ሃይማኖታችን የማይፈቅደውን እኛ ፈቅደን የርሃብ ምሳሌ ፣ የስደት ምሳሌ፣የፍቅርና አብሮ የመኖር ምሳሌያችን ወያኔ የወረሰብን ወኔ የሚባል ነገር ያልፈጠረብን ከንፈር መጣጭ የሆንን ለመተባበርና በጋራ ለመቆም ማሰብን ያጣን። እኮ እኛ እንዴት የስልጣኔ ምንጭ ነን ብለን እናወራለን የስልጣኔ ምንጭነታችንን ይዘን ወደ መቃብር የምንወርድ አገልግሎት የሌለን በቁማችን የረከስን እንዴት እንሁን ? ሊያውም እኮ አብልቶ አጠጥቶ ለወንበር ያበቃቸውን ገበሬ መልሰው የሚገሉ መሬቱን ተቀራምተው ለስደት የሚዳርጉ በተሰደደብትም ሃገር ለመገደሉ ምክንያት ለሆኑት ጥቂት የትግራይ ቡችሎች እደግመዋለው ጥቂት የትግራይ ቡችሎች እንዴት በቃቹ ልንላቸው ህሊናችን ከዳን ? ቀደም ባለው ግዜ ትግሉን የሚመሩ ብቃት ያላቸው ሰዎች ማግኘት ችግር ብዙም ባይሆን ነበረ ።

አሁን ግን ብዙዎች ምሁራን ህመሙን መታገስ አቅቷቸው በአደባባይ ብቅ እያሉ ሃሳብ ከመግለፅም አልፍው ሙሉ ሃይላቸውን ስለ ሃገራቸው እየሰጡ እያየን ነው እሰየው ነው ታዲያ እኮ እኔስ ምን ላርግ አቅም ባይኖር እንኳን በሃሳብ ደረጃ ትግሉን እንድንሳተፍ ግድ ይላል ። ትግሉ መደራጀትን ይጠይቃል ታዲያ እንደራጃ ጎበዝ ማንም አልያዘንም ሊይዘንም አይችልም በካባቢያችን ያሉ ፀረ ወያኔ ትግሬ ድርጅቶችን እንቀላቀል ያኔ ነው ስድቱ ፣ግድያውና በዓለም ፊት መሸማቀቁ የሚቆመው ደግሞም አይቀርም ጥቂት ሃገራቸውን የሚወዱም ቢሆኑ ወያኔ ትግሬን ከሃገራችን ኢትዮጵያ አስወግደው በዛች የስልጣኔ ቁንጮ የነበረች ሃገራችን ላይ ዲሞክራሲያዊ መንግስት መስርተው ስደትና እንግልቱ በቃ የሚሉበትና ሃገራችን ኢትዮጵያ በጎረቤት ሃገሮች ላይ የነበራትን ክብር የሚያስመልሱበት ቀን ቅርብ ነው።

ሞት ስለ ኢትዮጵያ መፈራረስ ለሚመኙ ወያኔ ትግሬዎች!!!

ድል ስለ ሃገራቸው ለሚደሙ ለሚቆስሉ ጀግኖች!!!!

ስቶክሆልም

አፕሪል 2016.

Ethiofri@gmail.com.

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: