The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ከጠቀመ ትንሽ ሀሳብ – ዳዊት ዳባ

130153

መንግስት ዋና ሀላፊነቱ የዜጎቹን ደህንንት መጠበቅ ነበር። ጋንቤላ ውስጥ እየተፈፀመ ባለው ዘር ማጥፋት የተነሳ አልቻላችሁምና ስልጣን ልቀቁ ትክክለኛ ነው። መንግስት ቢሆኑ ሳይባሉም ስልጣን በለቀቁ ነበር። ያሉት አንድና አንድ ወያኔዎች ናቸው።  ያገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የደህንነት አባላት እራሳችሁን ነፃ ሳታወጡ ህዝባዊም አገራዊም መሆን አትችሉም። ትክክል።   ይህ ፅሁፍ በወገኖቼ እልቂት  የተሰማኝን መራራ ሀዘን የገለጥኩበት መንገድ ነው።

 

ስርአቱ እጅግ አስከፊ ከመሆኑ የተነሳ  እስካሁን በአንድ ቃል ለመግለፅ የቻለ የለም። አንባገነን፤ አገር ሻጭ። ጨፍጫፊ፤ ዘረኛ። አድሏዊ ባለጌዎች።  ደናቁርት፤ ጠይዎች። ትግሬዎች ዘራፊዎች። …..  ሁሉም ስሞች ግን ይገልፁታል። ለማንኛውም  “ሰዎች ናቸው”። ጀሌውንም ጨምርን ያን ያህል ጉልበት ሆኗቸዋል ሊባል በሚችል ደረጃ ቁጥራቸው ብዙ አይደለም። “ ጉድ” ሊሰኝ በሚችል ለረጅም ጊዜ መግዛት ግን ችለዋል።  ታዲያ የመግዛት ጉልበቱን ከምን አገኙት?። ለሚለው ከባድ ጥያቄ የምናገኘው መልስ  በጣም ቀላል ነው። ሁላችንም የምንስማማበት መልስም ነው ያለው። ብዙ አባሪ ሊሆኑ የሚችሉ መልሶች ቢኖሩም በዋናነት የመግዘት ጉልበቱ የሚመነጨው መከላካያ ፖሊስና በደህንነት ስራ ላይ ከተሰማሩ ዜጎች ነው።  ለመግበያ ያህል ነው እንጂ ዋናው አሳቤ ላይ እንዳያጠላ ትንታኔ ውስጥ አልግባ። ስልጣን ላይ በቆዩበት ጊዜ ሁሉ እነዚህን ሰዎች እየተቃወምን እየታገልናቸው አለን።  ለማሸነፍ  ቁልፍ የሆነው  ያላስፈላጊ ጉልበት የሆናቸው አካል ላይ የተሰራ ስራን በተመለከተ ጥረቶች አሉ ማለት ይቻል እንደው አላውቅም። በበቂ አልተሰራበትም ብሎ መናገር ግን ይቻላል። ለማንኛውም ይህ ጉዳይ ሌላም አስገራሚ ጎን ስላለው እሱን ብዬ ወደዋና አሳቤ ልግባ። አገዛዙ ውስጥ ያሉትን ሰዎች በሶስት መክፈል ይቻላል። ሙሉ ነፃነት ያላቸው እንዳሻቸው ተጠቃሚ ፈላጭ ቆራጮች ስብስብ። በገደብ ተጠቃሚ ግን ነፃነቱ እንደኛው የሌላቸው ይባስ ብሎ የተዋረዱ ስብስቦች።  ተከፋይ ግን እንደኛው ተጨቋኝ ብቻ ሳይሆኑ የተናቁ ግልጋሎት ሰጪዎች።  ከጥቂት አለቆች በቀር በሙሉ የመከላካያና የፖሊስ ሰራዊቱ አባላት ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ሶስተኛው ክፍል ውስጥ ነው የሚመደቡት። ይህ ክፍል ነው እንግዲ ላገዛዙ እስትንፋስ የሆነው።

 

 

ሀሳቡ ሚዛን ከደፋና ሊተገብረው ፍቃደኛ ከተገኘ እንድ ወር የመዘጋጃ ጊዜ ሰጥተን ለአንድ ወር የሚቆይ ሁሉ ድርሻ የሚያደርግበት ዘመቻ እናድርግ። በፈረንጅ አቆጣጠር ዛሬ ቀኑ መያዚያ 18 ነው። እስከ ሚቀጥለው ወር መጀመርያ ሀሳቡ ተቀባይ ሊሆን ይችላል እንበልና። ሙሉ ግንቦትን መዘጋጃ እናድርገው። ከዛም ሙሉ የሰኔ ወር ቀጥቅጠን የማሳወቅና የመማማር ዘመቻ የምናደርግበት ወር ይሆናል ማለት ነው። ይህ ታላቅ አገራዊ ቁም ነገር የሁለት ወር ካስራ አምስት ቀን ትኩረታችንን ያገኛል።

 

ይህን አይነት ዘመቻ በሌሎች አገራዊ ጉዳዬች ላይ መለስተኛ በሆነ ደረጃ ሲደረግ ነበር። መሳርያ በጁ ያለው ላይ የሚሰራውን ያህል ግን ሌሎች ጉዳዬች ላይ ጉልበት የለውም። አገዛዙን ገሸሽና ቀርቅበን  የምንሰራው ስለሆነም ነው። ጠቅለል አድርገን ስናየው የምናደርጋቸው ነገሮች በጣም ቀላል ናቸው። የምንናገር፤ የምንወያይ፤ የምንሰበሰብ፤ የምንፅፍ ላንድ ወር ፍፁም በሆነ ሁኔታ አንድና አንድ ይህንን አገራዊ ቁም ነገር የሰኔ ወር አርእስታችን እናደርገዋለን። ጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ካሉ ግኝታችውን በዚሁ ወር ያቀርባሉ። መናገርያ መሰብሰቢያ መወያያ መድረኮችን እናዘጋጃለን። በዚሁ ወር ውስጥ ቤተሰብ፤ ቤተዘመድ፤ ጓደኛ ሚሰት  በቁም ነገር ቁጭ አድርገውም ሆነ ደውለው መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት ውስጥ ያሉ ልጆቻቸው ጋር አገራዊ ውይይት የሚከፍቱበት ወር ይሆናል። ዘመቻው በሙሉ አወንታዊ መንፈስ ያያዘ ስለምናደርገው ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ለፖሊስ ሰራዊቱና ለፖሊስ አባላት ወገኖቻችን ቅናሽ እንዲያደርጉ ትብብር ይጠየቃሉ። ሰልፎች፤ የሚበተኑ ወረቀቶች መልእክቶች ላገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊቱን የሚመለከቱ ይሆናል። ሜዲያዎቻችን የየለት ፕሮግራም ይኖራቸዋል። ከሞቀ ሰላምታና ፈገግታ ጀምሮ ህዘብ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በዚህ ግዚያት መልክም መቀራረብን ያደርጋል። ጠንካራ መልእክት ያላቸው አጫጫር ማስታወቂያዎች በብዛት ይተላለፋሉ። የኪነ ጥበብ ስራዎች ይጨመሩበታል። ብቻ የዚህ አይነት ቀላል ልናደርጋቸው የምንችላቸውን ነገሮች የምናስብበትና የምንፈጥርበት ወር ይሆናል። እውነት ለመናገር ጭንቅላታችንን ከሰጠነው በዙ መፈጥር እንችላለን። ለምሳሌ የእርስ በርስ ሰላምታችንን ላንድ ወር ወታደራዊ ማድረግ እንችላለን።  አሁን ማድረጉ ብዙ ተሳታፊን አገር ውስጥ ከማስገኘት አኳያ ጥቅሙ ያየለ ነው። አመት መጠበቁ የኦሮሞ ህዘብና የስልምና እምነት ተከታዬች እንዲሁም ሌሎችም በቀላሉ የትግላቸው አካል ሊያደርጉት የሚችሉበትን መልካም አጋጣሚ ሊያሳጣን ይችላል።  ጉጀሌው የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት ወር ብሎ በሰየመው በየአመቱ የካቲት ላይ የሚደረገው ጊዜም ተስማሚነት አለው የሚለው ስለታሰበኝም ነው። ይህን ሀሳቡ ተመችቷቸው ተፈፃሚ ለማድረግ ለደፈሩ የዘመቻወን ጊዜ በተመለከተ ውሳኔውን እንተወው። ከአረቡ አቢዬት ጀምሮ በሌላ መስመር ሀሳቡን ተፈፃሚ ለማድረግ ተሞክሮ ስላልተሳካ ወደ ህዝብ የመጣ መሆኑ ግን ይታወቅ።

 

ፋይዳው ምንድን ነው?። ምንም ካለማድረግ የሆነ ነገር መሞከር ይሻላል ከሚለው ጀምረን– ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለሁሌም የአገር መከላከያ፤ የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት አባላት ከመንግስት ጋር ያላቸው የተበላሸ የግንኙነትና ያሰራር ባህል በመጪው ማስተካካያ ሊበጅበት በሚቻልበት ቁም ነገር ላይ የምንመክርበት ይሆናል የሚል ድረስ የሚሄድ ነው። መሀል ላይ ያለው ተገልፆ የማያልቅ ጥቅም የተተወው ለማሳጠር ሲባል ነው። በጭራሽ ግን ከማሸነፍ አኳያ ብቻ  ፋይዳው የተሰላ አድርገን እንዳንወሰደው።

 

የዘመቻው ግብ ምንድን ነው?። የምንሰራውን ስራ ስኬታማነት የምንለካበት መስፈርት ማበጀት ሁሌም ያስፈልጋል።  የመጨረሻ ግቡ ወገንታዊነቱ ለዜጎችና ለአገር የሆነ የመከላከያ የፖሊስና የድህንነት አባላት እንዲኖሩን ማድረግ ነው። ያ ትልቁ ግብ ሆኖ በዚህ ዘመቻ ልንደርሳቸው እየጣርን እንደሆነ እንዲያውቁት ማድረግ ከቻልን ከበቂ በላይ ነው። ይህን ማድረግ ከቻልን ዘመቻውን በተሳካ ሁናቴ በበቂ ፈፅመንዋል ብለን እንወስደዋለን።

 

ልንሰራው የሚቻለን ነው ወይ?። በደንብ። ለለውጥ በሚታገለው ክፈል አቅም በቀላሉ ሊሰራ የሚችል ነው። ድርጅቶችን የሚያስተባብር  ከመሆኑም በላይ ዜጎች ሁሉ ድርሻ ሊያደርጉበት የሚችሉበትም ስራ ነው። ባሉን የመገናኛ አገልግሎቶች ለስራው በቂ ናቸው። ይህም ብቻ ሳይሆን መገናኛዎቻችን አንድ አገራዊ ቁም ነገር ላይ አነድ አይነት ስራ የመስራትን ልምድን እንዲዳብር የሚያደርግ ነው።

 

ሊኖሩ የሚችሉ ተግዳድራቶች ምንድን ናቸው?። የዚህ አይነት ስራ ውጤቱ ያኔውኑ የሚታይ ስላልሆነና ተሰልፎ እንደመቃወም የተለመደ ስላልሆነ መሳነፍ ሊኖር ይችላል። የነገሱብን ፈላጭ ቆራጮች ስለሆኑ ለምን ሰላም አላችሗቸው ማለታቸው ስለማይቀር አገር ውስጥ ያሉ ዜጎች በተሳትፏቸው በድርጊታቸውም ሆነ ቃላቶቻቸው ላይ ጥንቃቄን ማድርግ ሊኖርባቸው መቻላቸው ነው። ሲጀመር ሀሳቡን በመነሻነት ወስዶ አዳብሮ ሊተገብረው የሚችል መኖሩም ትልቁ ችግር ነው።

 

የተረገዘው አገራቀፋዊ እንቢተኝነት ከመወለድ በፊት በሗላ ችግር ከመዘርዘርና አጨናጋፊ እንዳይሆን ደግሞ መሰራት ያለበት ስራ አሁኑኑ ይሰራ። ኢሳትና ቪዥን ኢትዬጵያ ያዘጋጁት የውይይት መደርክ አገራዊ ፋይዳው የበለጠ የሚታወቀንና የምናደንቀው ዛሬ አይደለም። መቀጠል ያለበት ታላቅ  ስራ ብዬዋለው። በግሌ ሙዚቃም እንደዚህ መስጦኝ አላዳምጥም። እንደዚህ ዝግጅት የተማርኩበትም ተስፋም የሰጠኝ ነገር የለም። ምስጋና ለተሳታፊዎችም ላዘጋጆችም በሙሉ።

 

ብሄራዊ ጭቆና ይብቃ።

 

ዳዊት ዳባ dawitdaba@yahoo.com Monday, April 18,

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: