The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ጥቂት ታማኝ የህወሃት ካድሬዎች ብቻ የተገኙበት የመቀሌው ስብሰባ – አሞራው ምንአለ ባሻ

mekele

በከፍተኛ የህወሃት ማይከላዊ አመራሮች በሆኑት አቶ ተክለወይኒና አባይ ወልዱ እንዲሁም የትግራይ ክልል የደህንነት ቢሮ ሓላፊ የሆኑ አቶ ዘነበ ሐዱሽ የተመራው ጥቂት ታማኝ ካድሬዎች ብቻ የተገኙበት የትላንት ወዲያ (የሚያዚያ 8/2008 አ/ም) የመቀሌው ስብሰባ ከአንድ በመቀሌ ኗሪ የሆነ የአዲግራት አከባቢ ተወላጅ “ባስቸኳይ ለኢትዮጵያውያንና ለመላው የአለም ህዝብ ይጋለጥ” ብሎ የደረሰኝ መረጃ፣ ልጁ በላከልኝ መረጃ መሰረት እንደወረደ ያለ አንዳች ማሻሸያ እንዲህ ከታች ቀርቧል። ዘጋቢው የህወሀት አባል ሲሆን መረጃው ያገኘው በስብሰባው ከተሳተፈው የልብ ካድሬ ጓደኛው በቀጥታ ከነገረው እንደሆነ ጠቁሞናል።

አመሻሹ ላይ ይህን ዘገባ የላከልኝ ውዱ ዘጋቢ “ህወሃት መሞቱ የሚታወቀው ገና የስብሰባው አዳራሽ ሳይከፈት መረጃው ቀድሞ ህዝቡ ጋር ይደርሳል፤ ከዚህ በላይ ያንድን መንግስት ተሰባብሮ መውደቁንና መበስበሱን አማላካች ሊሆን የሚችል ነገር የለም” ብሎኛል።ምስጋናዬን ለዚህ ውድ ኢትዮጵያዊ ላቅርብና ዘጋቢው “ምንም ይሁን ምንም አገሬ ኢትዮጵያን እወዳለሁ” ያለ ሲሆን “ህዝባችን የወያኔ ተንኮል አውቆ መጠንቀቅ እንዲችል ሆኖ ባጭር ግዜ ውስጥ ማስወገደ አለበት” ብሏል።

“የወያኔ ኢትዮጵያዉያንን በዘርና ሐይማኖት ከፋፍሎ የማጋጨትን ዘመቻ ግምገማ በትላንትናው ቀን 8 ሚያዚያ 2008 አ/ም በመቀሌ ከተማ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ህልውናን ሙሉ ለሙሉ እንዲያከትም ለማድረግ በጣም አስገራሚ የሆነ ስብሰባ ተደርጓል። ስብሰባው አንድን ወሳኝ የተባለን ኦፕሬሽን ግምገማ በማካሔድ ለቀጣይ አፈጻጸሙ እርማት በማድረግ እንዴት በተሳካ ሁኔታ ማስኬድ እንደሚገባ አቅጣጫን ለማስያዝ ነበር። የስብሰባው ትእዛዝ የወረደውም ከአዲስ አበባ ከአቦይ ስብሓት ነጋና አባይ ጸሓየ ሲሆን ወደ ስብሰባው መጨረሻ አካባቢም አቶ አባይ ጸሐየ በስልክ ደዉለው በማያክሮፎን ላውድ ተደርጎ ቀጭን ትእዛዝ ለተሰባሳቢው ተላልፏል። ትእዛዙ ከታች ባጭሩ የጽሑፌ መጨረሻ አከባቢ እገልጸዋለሁ።

የስብሰባው ዋና አላማም የህወሀት ካድሬዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የዘርና የሐይማኖት መከፋፈል ወደ ግጭት እንዴት ስውር በሆነ መንገድ በባለፉት 7 ወራት ሲያካሒዱ እንደቆዩ የሚገመግም ሲሆን በጣም ብዙ የተባሉ ክፍተቶች እንደድክመት ተነስተዋል። ይህም ከግምገማው ብሗላ በተደረገው የችግሩ ምክንያቱ የተባሉት ደግሞ አንደኛው የአንዳንድ ካድሬዎች አለመታመን ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የህዝቡ በነገሮች ላይ መጠነኛ መባነን ሊሆን ይችላል ተብሎ ደምዳሜ ተሰጥቶታል።

ኦፕሬሽኑ ከተግባራዊነቱ አንጻር ከሞላ ጎደል የተሳካ አፈጻጸም ያለበት ነው ቢባልለትም ደካማ ጎኖች ከተባሉ ዋነኛ ነጥቦች መካከል ደግሞ ከያንዳንድዋ ኦፕሬሽን ብሗላ ህዝቡ በቀላሉ ጣቱ እኛ ጋር እየቀሰረ ነው ያለው ይላል። ለምሳሌ የአንዋር መስጊዱ ጥቃት ህዝበ ሙስሊሙ በሚነቃበት ሁኔታ ነው የተከናወነው ከዚህም የተነሳ የታሰበ ግቡ አልመታም፤ በኦሮሚያ አመጽ የተከናወነው የቤተ-ክርስቲያናት ቃጠሎ የአንዱዋ የፕሮቴስታንት ቸርች ብቻ በአካባቢው ባሉ አክራሪ ሙስሊሞች የተፈጸመ ቢሆንም የእኛው ካድሬዎች የሰሩት ተልእኮ ግን በክፊል የተነቃበት ሁኔታ ነው ያለው። ሌላው የአማራውና የቅማንቱ ዘር ግጭት በብዙ ኢትዮጵያውኖች መንግስት እንዳቀነባበረው የተደረሰብት የሚመስል እምነት በህዝቡ ዘንድ እንዳለ ታማኝ ካድሬዎቻችን አድርሰውናል። ይህ ሊሆን የቻለውም ከትግራይ ተወላጆች ውጭ ያሉት ካድሬዎቻችን በብዛት ታማኝ ሆነው ሳይሆኑ ለሆዳቸው ብቻ ብለው ግዳጅ እየፈጸሙ እንደሆነ ነው የሚያሳየው። ከጎንደሩ የአማራና ቅማንት የዘር ግጭት ውጭ በኦሮሚያ በሚገኙ አንዳንድ አከባቢዎች በከፊል አማሮች ከደረሰው ነገር በቀር እንዲያውም ባልጠበቅነው ሁኔታ የኦሮሞ አባቶች ከለላ የሰጡበት ሁኔታ ሁሉ ስለነበር በተግባር እንደ እቅዳችን ተሳክቷል ለማለት አያስደፍርም። እንዲህም ሆኖ ግን ኦፕሬሽኑ ፍርሀትንና ጭንቀትን፤ ውጥረት፣ አለመተባበርንና አለመተማመንን ከመፍጠር አኳያ ግን እጅግ አጥጋቢ የተባለን ውጤት አስገኝቷል። ይህም በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች የተነሱ አመጾችን ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ከማምጣትና መንግስትን ከመዳፈር ውጭ የተበጣጠሱና ለውጥ የማያመጡ አድርጓቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ኦፕሬሽኑ ከፍተኛ በሆነ የመባነን ሰለባ ሆኗል የምንለው ደግሞ በዩኒቨርሲትዎች የደረሱት የቦንብ ፍንዳታዎችና ቃጠሎዎች በብዛት ማለት ይቻላል መንግስት እንዳደረሰው ነው ህዝቡ ካድሬዎቻችንን ሳይፈራ በየሻይ ቤቱና መጠጥ ቤቱ በንቀት የሚያወራው፤ ይህ ለእኛ ውርደት ከመሆን በዘለለ መልኩ ህልውናችንን የሚፈታተን ነገር ነው። እይህ ድፍረትም ካድሬዎቻችን የበለጠ እንዲፈሩና የሚፈጸሙት ተልእኮ ይባስ የተባነነበት እንዲሆን ያደርገዋልና ታማኝና ቆራጥ ካድሬዎችን ለተልእኮው ማሰልፍ የግድ ይላል። ካልሆነ ግን በፍርሃታቸው እንዲህ አይነት የተንዘላዘለ የጅል አሰራር የሚሰሩ ካድሬዎች ባስቸኳይ ሊወገዱ ይገባል።

እንደዛም ሆኖ ግን አመጹ አሁንም ቢሆን ለመንግስት ስጋት ስለሆነ ይህ ኦፕሬሽን ክፍተቶቹን በመዝጋትና ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በተጠናከረ መንገድ መቀጠል አለበት። ቁልፍ መርሗችን እስከሆነ ድረስ በታማኝነትና ቆራጥነት ልንወጣው ግድ ይለናል። ለምሳሌ የወልቃይት ጉዳይ ለእኛ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ጥያቄያቸውም ህገ-መንግስታዊ ሽፋን ያለው በመሆኑና የተለያዩ ሚዲያዎች ሽፋን ስለሰጡት በቀላሉ ለማጥቃት ቢያስቸግረንም የስልክ ኔትዎርክና የመረጃ መረቡን በመዝጋት የሚቻለንን ያህል እይደረግንን ነው። ህዝቡም በጣም እልኸኛና ቆራጥ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ህጋዊ የፌደረሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ በትዕግስት መስማት ስለፈ ለገ ነው እንጂ ውሳኔው አይሆንም ከተባለ በቀላሉ ወደ ጦርነት ገብቶ ከፍተኛ ኪሳራ ሊያደርስብን የሚችል ህዝብ ስለሆነ የፌደርሽኑ ውሳኔ በማዘግየት ወደ ሗላ በሳል ስራዎችን ከመስራት በቀር ምንም ልናደርገው አንችልም። ነገር ግን ይህ ኦፕሬሽን በወልቃይት ተፈጻሚ ሲሆን በዛ አካባቢ ያሉ ሙስሊምና ክርስቲያኖች በመተማመን ስለሚኖር በህዝቡ መከፋፈል ለመፍጠር መሞከር ኪሳራ እንጂ ውጤት አያመጣም፤ ግን ደግሞ የአካባቢው ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ኦፕሬሽን ለየት ባለ መልኩ ነው ባስቸኳይ መፈጸም ያለበት።

ህዝቡ በቀላሉ የመባነን ባህሪ ስላለው በህዝቡ እማኝነት እንዲኖረው ለማድረግ አካባቢው ክርስቲያን የበዛበት እንደመሆኑ መጠን የታጠቁ አክራሪ እስላሞች ከሰሜን ሱዳን እንዲዘልቁ በማድረግ የድንበር ችግር ያለባቸው በማስመሰል እዛ በአከባቢው ያሉ የትግራይ ተወላጆችና ባለ የመከላከያ እዝ ተመጣጣኝ ስትራተጂያዊ ዋጋ በመክፈልና የሚዲያ ሽፋን በማሰጠት ሌላ ቋሚ መፍትሔ እስኪገኝለት ድረስ ጉዳዩ እንዲበርድ ማድረግ ይቻላል። የህወሃት መቃብር የተቆፈረው በመቀሌ ሳይሆን በወልቃይት እንደመሆኑ መጠን ከሁኔታው አንገብጋቢነት አንጻር ይህ የምናወራው ኦፕሬሽን ባስቸኳይ መፈጸም ያለበት በዚህ መልኩ ከሆነ ፍጹም አመርቂ የሆነ ግን ደግሞ ያለተባነነበት ሁኔታውን ያገናዘበ ኦፕሬሽን ተካሔደ ማለት ነው።

አሁንም ቢሆን ግጭቱ በዋነኝነት በሙስሊምና ክርስቲያኖች፣ በክርስቲያኖችና ፕሮቴስታንቶች፣ በሙስሊልምና ፕሮቴስታንቶች እንዲሁም በተለያዩ ብሔረስቦች መካከል ባስቸኳይ እውን መሆን አለበት። ከብሔር አንጻር ሲታይም ግጭቱ በኦሮሞዎችና በአማሮች፤ በኦሮሞዎችና በሶማሊዎች፣ በሶማሊዎችና አፋሮች፣ በአፋሮችና የጁቡቲ ድንበር አፋሮች፣በጋምቤላና በደቡብ ሱዳን ድንበርተኞች፣ በኦሮሞዎችና ደቡቦች እንዲሁም በእነዚህ የተጠቀሱ አካባቢ ህዝቦች በውስጣቸው በተለያየ መንገድ መከፋፈልና ግጭት በሰፊው እንዲከሰት በማድረግ ጣታቸውን ከመንግስት ቅሰራ እንዲቆረጡ በማድረግ መንግስትን ለአስታራቂነት እንዲለምኑ መደረግ አለበት። ስብሰባው ሊያልቅ ወደ 40 ደቂቃ ገደማ ሲቀረው አቶ አባይ ጸሐየ በስልክ ደዉለው በማይክሮፎፎን ላውድ ተደርጎ እጅግ በጣም በተበሳጨ ስሜት ሆኖ በቀጥታ በስልክ በተላለፈው ቀጭን ትእዛዛቸው ‘ስትነጋገሩበት የቆያችሁ አገራዊ አጀንዳ በውስጥ መስመር ሲደርሰኝ ነበር’ ካሉ ብሗላ ‘አንዳንድ ማጉረምረም በሚሰማባቸው የትግራይ አካባቢዎች ቢሆንም እንኳ ኦፕሬሽኑ ካስፈለገ ተግባራዊ ይደረግ’ ከእንግዲህ ወደሗላ ማለት የለም” ካሉ ብሗላ ሁለት ካድሬዎች በፍጥነት ሲያጨበጭቡ ሌላውም በፍርሃት እየተያየ ደማቅ ጭብጨባ አሰምቷል” ተብሏል።

በአሁኑ ስአት ስለብሔርና ስለሐይማኖት ልዩነት የሚያወሩ ሰዎች የወያኔ ካድሬ አለያም ደግሞ ወያኔ ባይሆኑም በስራቸው ተባባሪዎችመሆናቸውን አውቃችሁ እንደትጠነቀቁ በማሳሰብ አስፈላጊውን ኢትዮጵያዊ መልስ እንድተሰጧቸው አሳስባለው። በተባበረው ክንዳችን ወያኔን በፍጥነት እናስወግድ!!! ይህ ሲባል ታድያ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ስለብሔሩ ችግር አያውራ ወይንም ደግሞ አይደራጅ ማለት አይደለም። ነገር ግን ብሔርነታችን ለኢትዮጵያዊነታችን ዋስትና ሊሆነው ይገባል፤ ኢትዮጵያዊነታችንም ለብሔራችን ዋስትና ሊሆነው እስከቻለ ድረስ። ከዚህ ውጭ ግን ኢትዮጵያውያን ሆነን በሃይማኖትና በብሔር ያተኮረ ስድብና የፈጠራ ታሪክ ነገር ሁሉ መጥፊያችን ነው። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

ሞትና ውድቀት ለወያኔ ትንሳኤ ደግሞ በውርደት ላለች አገራችን ይሁን፤እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!

satenaw

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: