The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ባህሩ ደጉ ‹‹ሽንቴን እንድጠጣ ተደርጌያለሁ…››

bahru degu

(ሳተናው) የኢትዮጵያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለት ተከሳሾችን ዮናታን ወልዴና ባህሩ ደጉን ከቀረበባቸው ክስ በነጻ እንዲሰናበቱ ወስኗል፡፡ሁለቱ ወጣቶች በነጻ የተለቀቁት ለ600 ቀናት በወህኒ ቤት ሲሰቃዩና መንግስትን በመተቸታቸው በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በፍርድ ቤቶች ሲመላለሱ ቆይተው ነው፡፡ከሁለቱ ወጣቶች ጋር በአንድ መዝገብ የቀረበው ዘላለም ወርቃገኘሁ ግን በዚያ ዕለት ዕድለኛ አልነበረም፡፡

ፍርድ ቤቱ ዘላለምን ጥፋተኛ ሆኜ አግኝቸዋለሁ በማለቱ የቅጣት ውሳኔውን ለማስተላለፍ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ዘላለም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ወጣት ምሁርና ደብርሃን በተባለው ድረ ገጽ የኢትዮጵያ መንግስት ይፈጽማቸው የነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማጋለጥ ትችቶችን ያዘሉ ጽሁፎችን ያቀርብ ነበር፡፡ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ እንዲያቀርብ ጠይቆ አቃቤ ህጉም ይህንኑ ማድረጉ ታውቋል፡፡

የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርብ የተጠየቀው ዘላለም በበኩሉ የቀረበበትን ክስ አለመፈጸሙን በመጥቀስ ክሱ ፖለቲካዊ በመሆኑና ፍርድ ቤቱም ይህንኑ ለመተግበር የተዘጋጀ በመሆኑ የሚያቀርበው ማቅለያ እንደሌለው አስታውቋል፡፡

ሶስቱ ተከሳሾች የተከሰሱበት የጸረ ሽብር አዋጁ በኢትዮጵያ ስራ ላይ እንዲውል የተደረገው በ2001 ሲሆን መንግስት አዋጁ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ሳይሆን በሰብዓዊ መብት አከባበር ጥሩ ሪከርድ ካላት እንግሊዝ የኮረጅኩት ነው በማለት ስለአዋጁ ይከራከራል፡፡

ዮናታንና ባህሩ 647 ቀናትን ማለትም ሁለት ዓመታትን በወህኒ ቤት ካሳለፉ በኋላ ፍርድ ቤቱ ነጻ ናችሁ በማለት አሰናብቷቸዋል፡፡የወጣቶቹ የረዥም ጊዜያት የወህኒ ቤት ቆይታም በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ያልተፋጠነ የፍርድ ቤት ወይም የምርመራ ጊዜን እንደሚያሳልፉ ማሳያ ይናል፡፡

በአገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤቱ አፋኝነት የከፋ መሆኑን የበለጠ የሚያጋልጠው ደግሞ ዮናታንና ባህሩ በፍርድ ቤት ከእስር ከተለቀቁ በኋላ የደህንነት ሰዎች ሁለቱን ሰዎች በድጋሚ በመያዝ ወደ ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ በመውሰድ ለአንድ ሌሊት ካሰሯቸው በኋላ ‹‹አሁንም ቢሆን እየተከታተልናችሁ እንገኛለን፡፡የሆነ እንቅስቃሴ ብታደርጉም እንገድላችኋለን››በማለት ሊያስፈራሯቸው መሞከራቸውን ወጣቶቹን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ፡፡

ዘላለም የተያዘውና የተከሰሰው በጥቅምት ወር 2006 ነበር ፡፡በወቅቱ ከእርሱ ጋር ሌሎች ዘጠኝ ሰዎችም ለእስር ተዳርገው ነበር፡፡ሰዎቹ ጦማሪያን፣ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ነበሩ፡፡በምርመራ ላይ እያሉ መርማሪዎቻቸው የሚፈጽሙባቸውን ቶርቸር ለማስቆም ሲሉ ያልፈጸሟቸውን ወንጀሎች እንደፈጸሙ በማድረግ መፈረማቸውን ይናገራሉ፡፡

በዘላለም ላይ የቀረበው ክስ የግንቦት ሰባት አባልነት፣መንግስትን ለመገልበጥ ማሴርና የሐሰት ውንጀላዎችን በድረ ገጾች አማካኝነት ማሰራጨት የሚሉ ናቸው፡፡ከዘላለም ጋር በደብርሃን ድረ ገጽ ይሰራ የነበረ ሰውም በክሱ መካተቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የዘላለም ክስ ወደ ሁለት ዝቅ እንዲል የተደረገ ሲሆን በኢትዮጵያ የአረቡ ዓለም አብዩት እንዲፈጠር መስራና ለዚህ ይረዳው ዘንድ ስልጠናዎችን መውሰድ የሚሉት በክሱ እንዲቀጥሉ ተደርገዋል፡፡ዘላለም ስልጠና ወሰደ የተባለበት ጉዳይም ስልጠናው የዲጂታል ቴክኖሎጂን አጠቃቀም የተመለከተ እንደነበር ተናግሯል፡፡

ዮናታንና ባህሩ ተከሰው የነበሩትም ይህንኑ ስልጠና ለመካፈል በማመልከታቸውና በግንቦት ሰባት አባልነት በመጠርጠራቸው ነበር፡፡

የእነ ባህሩን ጉዳይ ይመለከቱ የነበሩት ዳኛ በእንዲህ አይነት ስልጠናዎች መካፈልም ሆነ ስልጠናዎቹን ለማግኘት ማመልከት ወንጀል አለመሆኑን በመግለጽ ክሳቸው አንዲቋረጥ አድርገዋል፡፡ለሁለት ዓመታት በወህኒ ቤት የቆዩት እነ ባህሩ ከመንግስት ያገኙት ምንም አይነት ካሳ አልነበረም፡፡

ባህሩ ደጉ ባሳለፍነው ሳምንት ለዘላለም ምስክር በመሆን ፍርድ ቤት ተገኝቶ ነበር፡፡ለፍርድ ቤቱም በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ የሶስት ወራት ቆይታው ከፍተኛ የሆነ ቶርቸር እንደተፈጸመበት አስረድቷል፡፡

‹‹ልብሴን እንዳወልቅ ተገድጄ በየጊዜው ድብደባ ተፈጽሞብኛል፤ድብደባውን መቆጣጠር ባለመቻሌም ሽንቴን መቆጣጠር አልቻልኩም የራሴን ሽንትም እንድጠጣ ተገድጃለሁ››ብሏል፡፡

ልክ እንደ ብርሃኑ ዘላለምና ዮናታን በወህኒ ቤት የደረሰባቸውን ቶርቸር ተናግረዋል፡፡ጠባቂዎቻቸው ያልፈጸሟቸውን ወንጀሎች እንደፈጸሙ በማድረግ ቃላቸውን እንዲሰጡ እንዳስገደዷቸው ተናግረዋል፡፡በቅርቡ ሂዮማን ራይትስ ዋች ባወጣው ሪፖርት መርማሪዎች ጋዜጠኞችን፣ፖለቲከኞችንና አክቲቪስቶችን በመጫን ያልፈጸሟቸውን ወንጀሎች እንዲናዘዙ እንደሚያደርጉ ማጋለጡ አይዘነጋም፡፡

ምንጭ ግሎባል ቮይስ

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: