The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የብአዴን አመራር ጎንደር ውስጥ የማንነት ጥያቄ ያነሱት ዜጎች ለማጥቃት ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ ሆነ – (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

#ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ወደ ጀርመን ሄደ ተባለ
#በመተከል አካባቢ ኦሜድላ ላይ የሱዳን ታጣቂዎች ንብረት ዘርፈው ዜጎችን አፍነው ወሰዱ
#የብአዴን አመራር ጎንደር ውስጥ የማንነጥ ጥያቄ ያነሱት ዜጎች ለማጥቃት ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ ሆነ።
#የግብጽ የጋዜጠኞች ማህበር አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማ ጠራ
#በሱዳን ግብጽ የወሰደቻቸውን ቦታዎች ለማስመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው
#የአለም የገንዘብ ድርጅት በዚህ አመት የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ይቀንሳል አለ
#በናይጄሪያ 15 ሚሊዮን ዶላር በሙስና ተሰረቀ ተባለ

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ሚያዚያ 25 ቀን 2008 ዓ ም
ርዕሰ ዜና
 ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ወደ ጀርመን ሄደ ተባለ
 በመተከል አካባቢ ኦሜድላ ላይ የሱዳን ታጣቂዎች ንብረት ዘርፈው ዜጎችን አፍነው ወሰዱ
 የብአዴን አመራር ጎንደር ውስጥ የማንነጥ ጥያቄ ያነሱት ዜጎች ለማጥቃት ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ ሆነ።
 የግብጽ የጋዜጠኞች ማህበር አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማ ጠራ
 በሱዳን ግብጽ የወሰደቻቸውን ቦታዎች ለማስመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው
 የአለም የገንዘብ ድርጅት በዚህ አመት የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ይቀንሳል አለ
 በናይጄሪያ 15 ሚሊዮን ዶላር በሙስና ተሰረቀ ተባለ
ዝርዝር ዜና
 የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለቅንጦት ህክምና ወደ ጀርመን
ማምራቱን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የፊት ገጹን ለማስተካከል
እና ለማስዋብ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና እንደሚያደርግ ታውቋል። ኃይለማርያም ደሳለኝ
ወደ ጀርመን የተጓዘው በግል አውሮፕላን መሆኑ ሲታወቅ በባደን ከተማ በገዛው ቤት
ውስጥ እንደሚያርፍ ተገልጿል። ሁለት ሚሊዮን ነዋሪ ያለው የባደን ከተማ የጀርመን
ሃብታሞች የሚኖሩበት ውድ ከተማ መሆኑ ይታወቃል። የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር
ለህክምና በማለት ወደ ጀርመን ማቅናቱ ሲነገር በኢትዮጵያ በመሰረታዊ የጤና እጦት
የተነሳ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በሚሰቃይበት በድርቅና በረሃብ አንድ አምስተኛው
የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የዓለም አቀፉን ሕብረተሰብ እጅ በሚያይበት ሰዓት መሪ
የተባለው ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለቅንጦት ህክምና ወደ አውሮፓ መጓዙ ግብዝነነትና
ለሕዝብ ደንታ ቢስነትን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

 የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እየተደፈረ፣ ዜጎችም በወራሪ ኃይሎች እየተወረሩና እየታፈኑ
መመጣቱን መቀጠሉን የሚገልጹ መረጃዎች ከመተከል አካባቢ ከኦሜድላ እየመጡ
መሆናቸው ይነገራል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በመተከል ኦሜድላ አካባቢ
አድፍጠው የነበሩ የሱዳን ወታድሮች በኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው በመግባት ወረራ
መፈጸማቸውና ንብረት በማውደም ሰባ ዜጎችን አፍነው የመውሰድ ወንጀል
መፈጸማቸው ታውቋል። ይህ ካለፈው አርብ ጀምሮ በቀጠለው ወረራ በአቅራቢያ
የነበረው የወያኔ የምዕራብ ጦር አባላትም የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ በማለት ነዋሪው በባዕድ
ኃይል እንዲወረር አድርጓል።

 የወያኔ የበኩር ጥፍጥፍ የሆነው ብአዴን ጎንደር ውስጥ የማንነት ጥያቄ ያነሱ ዜጎችን
ስልታዊ በሆነ መንገድ ለማጥቃት ላማስር ያወጡትን እቅድ የጎንደር አስተዳድሪዎችና
ሹማምንት አንቀበልም ማለተታቸው ተሰምቷል። በማንነት ጥያቄ ዙሪያ ሕዝብን
ያስተባበሩ ናቸው የተባሉትን ሰዎች የማዳበሪያ ዕዳ ወይም ጥቃቅን አበዳሪ ተቋማት
እዳ ካለባቸው እንዲከፍሉ ማስገደድና ካልከፈሉ እንዲታሰሩ የሚጠይቀውን ትእዛዝና
መመሪያ የጎንደር ባለስልጣናትና ሹማምንት አሻፈረኝ ማለታቸው ታውቋል። ብአዴን
ከወያኔ የሚሰጠው ትእዛዝ ሕዝብን ለማሸበር የሚያደርገው ጥረት ከፍተኛ ካድሬዎችና
መካከለኛ አባላት ተግባራዊ አናድርግም ማለታቸው በበአዴን አመራር መካከል ክፍተት
ሳይፈጥር እንዳልቀረ ተገምቷል።

 የዓለም አቀፍ የፕሬስ ቀን ሊከበር አንድ ቀን ሲቀረው እሁድ ሚያዚያ 23 ቀን ለሰኞ
አጥቢያ ሁለት የግብጽ ጋዜጠኞች በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው በመወሰዳቸውና ጽህፈት
ቤቱ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በጸጥታ ኃይሎች በመወረሩ ምክንያት የግብጽ የጋዜጠኞች
ማህበር አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማ የጠራ ከመሆኑ ባሻገር የየግብጽ የአገር ውስጥ
ጉዳይ ሚኒስትር ከስራቸው እንዲነሱ ጠይቋል። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር
የማህበሩን ጽሕፈት ቤት መውረሩን ቢክድም ሁለቱ ጋዜጠኞች አመጽ የሚያነሳሳ
ጽሑፍ በመጻፋቸው መታሰራቸውን አምኗል። ሁለቱ ጋዜጠኞች የፕሬዚዳንት ሲሲ
አስተዳድርን በመንቀፍ ለሚታወቀው ባዋቤት ያነያር (የጥር በር) ለሚባለው ድረ ገጽ
የሚሰሩ ነበሩ። የጋዜጠኞቹ ማህበር ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 2008 ዓም. ባወጣው
መግለጫ የጸጥታ ኃይሎች የማህበሩን ጽቤት ወረረው የጋዜጠኞችን ክብር በሚያጎድፍ
ሁኔታና መብታቸውን በሚጻረር መንገድ አሰቃይተው ያሰሯቸው መሆኑን ገልጾ
ድርጊቱን በጽኑ አውግዟል። የማሕበሩ ጠቃላላ ስብሰባ ረቡዕ ሚያዚያ 26 ቀን
እስከሚካሄድ ድረስም ጋዜጠኞች በማህበሩ ጽ/ቤት ዙሪያ በመሰብሰብ ላይ የቁጭ በሉ
አዳማ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፏል። ከአስራ አምስት ቀን በፊት የሲሲ አገዛዝ ለሳኡዲ
አረቢያ የግብጽን ደሴቶች ማስረከቡን በማውገዝ 2000 የሚደርሱ ጋዜጠኞች
በማሕበሩ ጽ/ቤት ዙሪያ የተቃውሞ አንቅስቃሴ ማድረጋቸው ይታወሳል።

 የግብጽ መንግስት ሁለት ደሴቶችን ለሳኡዲ አረቢያ ካስረከበ ወዲህ ግብጽ ከሱዳን
የወሰደቻቸውን ሁለት ቦታዎች ለማስመለስ እንቅስቃሴ የተጀመረ መሆኑ ታውቋል።
ሱዳን በ 1948 ዓም ነጻነቷን ስታገኝ አለአግባባ ለግብጽ ተሰጥተዋል የሚባሉቱን
ሃይላቢን እና ሸላቲን በሚል ስም የሚጠሩ በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያሉ ቦታዎች ለሱዳን
መመለስ አለባብቸው በማለት በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርባ ከግብጽ አዎችንታዊ መልስ
ሳታገኝ መቆየቷ ይታወቃል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ጥያቄው እንደገና ተነስቶ መወያያ
የሆነ ሲሆን በቅርቡ በይፋ ጥያቄ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን ለሱዳን ምክር ቤት አባላት ባሰሙት ንግግር ሱዳን
ግዛቶቿ እንዲሰጧት መጠየቋን የማታቋርጥ መሆኑን ገልጸው ይህንንም ተግባራዊ
ለማድረግ የተለያዩ ህጋዊና ፖሊቲካዊ መንገዶችን እየተወሰዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

 በዚህ ዓመት አፍሪካ የምታሳየው የኢኮኖሚ አድገት ባለፉት አስራ አምስታት ከነበሩት
ዝቀተኛ ሊሆን እንደሚችል የአለም የገንዘብ ድርጅት ገለጸ። ባለፈው ዓመት አፍሪካ
በአማካይ ያሳየችው የኢኮኖሚ እድገት 3.5 ከመቶ ሲሆን በዚህ ዓመት 3 ከመቶ ብቻ
ይሆናል የሚል ግምት ተሰጥቷል። የአፍሪካ የህዝብ ቁጥር እድገትም ሶስት ከመቶ
አካባቢ በመሆኑ እድገቱ የዜጎችን ህይወት በመለወጥ ረገድ ለውጥ ሊያመያ
እንደማይችል ተገምቷል። የሸቀጦች ዋጋ መቀነስና የመዋእለ ንዋይ መጠን መዳከም
ለእድገቱ ዝቀተኛ መሆን ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል። ናይጄሪያና አንጎላ
በከፍተኛ ደረጃ የእድገት መቀነስ የታየባቸው ሲሆን ዛምቢያ እና ደቡብ አፍሪካም
መጎዳታቸው ተነግሯል።

 የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 2008 በሰጡት መግለጫ ባለፈው
አስተዳድር ወቅት ናይጄሪያ 15 ቢሊዮን ዶላር በሙስና ተስርቃለች ብለዋል። ገንዘቡ
የተሰረቀው በተለያዩ ምክንያቶች ቢሆንም አብዛኛው ገንዘብ በሙስና መልክ የጠፋው
ወታደራዊ መሳሪያዎችን ለመግዛት ከተመደበው ወጭ ነው ብለዋል። ምክትል
ፕሬዚዳንቱ የተበዘበዘው የገንዘብ መጠን በጣም የሚያስደነግጥ መሆኑን ገልጸው
ምርመራው እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።

finote.org

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: