The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ሀገር ማለት ምን ማለት ነው? ገረመው አራጋው ክፍሌ

በ ገረመው አራጋው ክፍሌ

እውን ሀገር ማለት ምን ማለት ነው?
ለእኔ ሀገር ማለት ህዝብ ማለት ነው፡፡
ለእኔ ሀገር ማለት ወንዝ ተራራ መሬት ማለት አይደለም አለን መለስ ዜናዊ፡፡
ከዚያም ጉደኛው መለስና ወያኔ ኢትዮጵያውያንን ሀገር አልባ አድርገው መሬቱን የባህር በሩን ታሪኩን ባህሉን ወዘተ ለባእድ ቸበቸቡት፡፡ምን ይህ ብቻ መለስ ከኢሳያስ ጋር ተመሳጥረው ለባድሜ መሬት ሲሉ ሊበቀሉት የፈለጉትን አማራ ከፊት አሰልፈው ከ70 ሺህ በላይ አስጨረሱት፡፡መለስና ወያኔ በሰው ፍቅር እንጂ በመሬት ፍቅር መቼ ይታሙና ነው፡፡አንድ ዌብ-ሳይት ላይ ታላቂቷ ኢትዮጵያ ቀስ በቀስ ወደ ታላቂቷ አዲስ አበባ እየተቀየረች ነው የሚል አነበብኩኝ፡፡እውነት ይመስላል፡፡ከእያንዳንዱ ሀብት ጀርባ ወንጀል አለ የሚባለው ለካ እውነት ነው፡፡ይህ አባባል ከምንጊዜም በላይ በዘመነ ወያኔ ግልፅ የሆነ አባባል ነው፡፡ዛሬ ግን ከእያንዳንዱ ወንጅል ጀርባም ሀብት አለ ለማለት ያስደፍራል፡፡

ወያኔ በ17 ዓመት የነፃ-አውጪ ጦርነት ዘመኑ የሰው ህይወት ቸበቸበ ኤርትራን ቸበቸበ የባህር በራችንን ቸበቸበ መሬታችንን ቸበቸበ ታሪካችንን ቸበቸበ ቅርሳችንን ቸበቸበ ሃይማኖታችንን ቸበቸበ ኢትዮጵያውያን ሴቶቻችንን ለዘመናዊ ባርነት(ግርድና) አረብ ሀገር ቸበቸበ በጉዲፈቻ ሽፋን ህፃናትን ለውጪ ሀገራት ካኒባሊስቶችና ለፔዶፊሊያ ሳታኒስቶች ቸበቸበ በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን እንደ ጉድ ቸበቸበ፡፡በዘመነ ወያኔ ምን ያልተቸበቸበ ነገር አለ፡፡ከዚያም ኢትዮጵያዊ ሀገር አልባ እንዲሆን ተደርጎ በስደት በድህነት በርሃብ በበሽታ በድንቁርና በአደንዛዥ-ዕፅ በጫት በግብረሰዶም በዝሙትና በአጠቃላይ በሞራል ውድቀት ትውልዱ ተኮላሽቶ ተስፋ ቢስ ሆኖ እንዲሰቃይ ተደረገ፡፡ሀገር የውክልና ቅኝ ግዛት ውስጥ ወደቀች፡፡ከዚያም የሀገርና የህዝብ ችብቸባው የውጪ እርዳታና ብድር ተጨምሮበት አዲስ አበባ ላይ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ መቀሌ ውስጥ ደግሞ ፎቅና ፋብሪካ ተገነባ፡፡ወያኔም ታላቂቷን ኢትዮጵያን በዘር ክልል ከፋፍሎና እርስ በርስ አናክሶ ሲያበቃና ወደ ታላቂቷ አዲስ አበባ ቀይሮ እንካችሁ አዲስቷን ኢትዮጵያን እዩልኝ አለን፡፡ገበያ ሲደራ የሚባለው ለካ እንደዚህ ነው፡፡ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ የቃብድ ብር እየተቀበሉ የሚጠፉ ነጋዴዎች በርክተዋል አሉ፡፡ወያኔም ኢትዮጵያን ቃብድ ተቀብሎባት ሸጧት እንዳይሄድ ቦሌ ላይ ጥበቃው ቢጠናከር ጥሩ ነው፡፡እንግዲህ የ11 በመቶው የኢኮኖሚ እድገት ውጤት ይህ ነው፡፡ከ20 ሚሊዬን ህዝብ በላይ በርሃብ እየተሰቃየ እንደ ቅጠል የሚረግፍባት የጉድ ሀገር፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም አዲስ አበባ ውስጥ ቤትና ቦታ ከመግዛት ይልቅ ገነት ወይንም መንግስተ-ሰማያት ውስጥ ቦታ መግዛት ይቀላል ነው የሚባለው፡፡ሀገርና ሰው እረከሰ መሬት ተወደደ፡፡ለካ ሀገር ሲረክስ ሰውም ይረክሳል ማለት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ አያት ቅድማያቶቹ መስዋእትነት የከፈሉበትን መሬትና ሀገር ተቀምቷል፡፡እድሜ ለወያኔዎች ሀገር የሚባለውን ትልቅ ፅንሰ-ሃሳብ አጥፍተውታል፡፡ዛሬ ሀገር ማለት መንገድ ፎቅ ባቡር መኪና ሸቀጣ-ሸቀጥ አርሰናል ማንቸስተር ወዘተ ሻል ካለ ደግሞ ሀገር ማለት ብሄር-ብሄረሰብ ወይንም ዲሞክራሲ ማለት ነው፡፡በዘመነ ወያኔ ለብዙሃኑ ሀገር ማለት ትርጉሙና ፋይዳው ከዚህ የዘለለ አይደለም፡፡ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን የሀገርንና የነፃነትን ትርጉምና ፋይዳ ላለፉት 25 ዓመታት ያክል ብዙም አያውቁትም ነበር፡፡ብኩርናውን ለምስር ወጥ እንደሸጠው ኤሳው እኛ ኢትዮጵያውያን ሀገርንና ነፃነትን ለሸቀጥና ለሌላም ሌላም የማይረባ ነገር ለውጠነዋል፡፡የሀገርና የነፃነት ትርጉምና ፋይዳው የሚገባን ስናጣው ብቻ ነው፡፡ምክንያቱም ጦርነትን ያላየ የሰላምን ዋጋ አያውቃትምና፡፡ስለዚህም ሀገራችንን እና ነፃነታችንን መልሰን ለማግኘት ውድ ዋጋ መክፈል አለብን፡፡በቀላሉ ሊገኝ አይችልም፡፡አያት ቅድመ-አያቶቻችን ለሀገርና ለነፃነት ሲሉ የከፈሉትን ውድ የህይወትና ሌላም መስዋእትነት ዋጋ አቃለነዋል፡፡ዛሬ ለእኛ ሀገር ማለት ከምንዝናናበት ሆቴልና ካፍቴርያ ወይንም ከምንነዳው አውቶሞቢል የተለየ ነገር አይደለም፡፡አሳፋሪ ዘመን ነው፡፡

ይህ ትውልድ ሀገርና ነፃነት አይገባውም፡፡ደግሞም ሀገርና ነፃነትን ይገባኛል ካለ በውድ ዋጋ ይግዛት፡፡ዝም ብሎ በነፃ የሚሰጥ ነገር የለም፡፡ከውጪ የፈረንጅ እርዳታ ማግኘት እንደ መብት የሚቆጠርበት ዘመን፡፡ለምንድን ነው ከውጪ እርዳታ ማግኘትን እንደ መብት የቆጠርነው?ፈረንጆቹ የሚረዱንስ እውን ለምንድን ነው? እውን ለእኛ ብለው ነው? ነው ወይንስ የዘመኑ ኢትዮጵያዊ በርካሽና በነፃ የሚሰጥ ነገር ይወዳል ማለት ነው?ወያኔዎች ከውጪ ባገኙት እርዳታና ብድር አዲስ አበባ ላይ ፎቅ ገነቡበት መቀሌ ላይ ፋብሪካ ገነቡበት የቢሊዬን ዶላር ካምፓኒ ኢፈርትን ገነቡበት ሌላም-ሌላም ነገር አደረጉበት የተቀረው ኢትዮጵያዊ ግን ማንነቱን ክብሩን ሀገሩንና ነፃነቱን ተቀማ፡፡በዘመነ ወያኔ ያለው እድገት ከወጪ ቀሪ ሂሳቡ ሲወራረድ ይህንን ይመስላል፡፡ወያኔ የኢትዮጵያን ገበሬ በሴፍቲ ኔት እንደ ራሱ የውጪ እርዳታ ጥገኛና ለማኝ አደረገው፡፡ዛሬ የኢትዮጵያ ገበሬ በርሃብ እንዲያልቅ የተደረገው ሆነኝ ተብሎ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ገበሬ ሀገሩን የሚመግብ የሰብል እህል ሳይሆን ለወያኔዎች በሚመች መንገድ ጫት ቡና ወዘተ ብቻ የንግድ ምርት እንዲያመርት ተደረገ፡፡ግብርናው የተዋቀረው ለወያኔ ዝርፊያና አፈና በሚመች መንገድ ሆነ፡፡በአጠቃላይ ሀገርና ነፃነት የሚባለው ትልቅ ቁም-ነገር ቢዝነስ በሚባል ነገር እየተተካ የመጣ ይመስላል፡፡በእርግጥ ለተራ ቢዝነስ የሸጥነውን ሀገርና ነፃነት ምን ያህል ቢዝነስ ሰርተን መልሰን እንደምናገኘው አላውቅም፡፡እውን ሀገር ማለት ሰው ነው?ብሄር በሄረሰብ ማለት ነው? ዲሞክራሲ ማለት ነው?የፖለቲካ ፓርቲ ማለት ነው? ሃይማኖት ታሪክና ባህል ነው?እቁብ እድር ሰርግ ማህበር ሰንበቴ ተዝካር ለቅሶ?እናት አባት እህት ወንድም ባል ሚስት ልጅ ነው?አርሰናል ማንቸስተር ጊዮርጊስ ቡና ማለት ነው ?ወይንስ ግኡዝ የሆነ መሬት ወንዝ ተራራ ሸለቆ ፎቅ መንገድ መኪና ባቡር? ነው ወይንስ ነፍስ ወይንም መንፈስ ያለው ነገር ነው?በእውነት ሀገር ማለት ምን ማለት ነው?ምናልባት ሀገር የሚባለው ትርጉሙ በደንብ የሚገባን ስናጣው ይመስለኛል፡፡ስለዚህም ትርጉሙ እንዲገባን ከእጃችን ወጥቶ እንጣውና ትርጉሙ ሲገባን መልሰን ውድ ዋጋ ከፍለን እናግኘው፡፡

 

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: