The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

በአርባምንጭ ከ20 በላይ የመንግስት ወታደሮች ተገደሉ | መንግስት ከኤርትራ የተላኩብኝን “አሸባሪዎች” አሰርኩ ይላል | ግንቦት 7 ጥቃት ፈጸመ???

File Photo

(ዘ-ሐበሻ) በአርባ ምንጭ ከተማ ድንገት ታጣቂዎች በሰነዘሩት ጥቃት ከ20 በላይ የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውን መዘገቡን ተከትሎ መንግስት ማምሻውን በኢቢሲ በኩል ባስተላለፈው መረጃ ከኤርትራ መንግስት በኩል የተላኩብኝን አሸባሪዎች ደቡብ ክልል ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት ያዝኩ አለ::

የኤርትራ መንግስት በኡጋንዳ በኩል በአየር አሳፍሮ እንዲሁም በኬንያ በኩል እንዲያልፉ በማድረግ በደቡብ ክልል ጥቃት ለማድረስ ሲሉ በቁጥጥር ስር አይውያለሁ ቢልም ኢሳት በሰበር ዜናው በአርባ ምንጭ ከተማ ከ20 በላይ የመንግስት ወታደሮች ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል ሲል ዘግቧል::

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በሶሻል ሚድያ በኩል “ወያኔ በአርባ ምንጭ የተሰነዘረበትን ድንገተኛ ጥቃት በተዘዋዋሪ ለማማን ተገዷል።” በሚል መንግስት በኢቢሲ በኩል የሰጠውን መግለጫ በመንተራስ አስተያየታቸውን እየሰጡ ባለበት በዚህ ወቅት ያዝኳቸው ያላቸውንና ከኤርትራ በኩል ተላኩብኝ ያላቸውን ታጣቂዎች ምንም ጉዳት ሳያደርሱ ያዝኩ ማለቱም እያነጋገረ ነው::

ኢሳት በዘገባው

“የአካባቢው ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ታጣቂዎቹ ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት 20 የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል የአካባቢው ወታደራዊ አዛዥም ይገኝበታል። የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ሰአታት የቀዬ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ህክምና ተወስደዋል። የመንግስት የጸረ ሽብር ግብረሃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ የተንቀሳቀሱ ሃይሎች በሞያሌ በኩል ወደ አርባምንጭ ጫካ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ገልጿል። መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉና የተገደሉ ታጣቂዎች መኖራቸውን ቢገልጽም ፣ በአሃዝ ከመግለጽ ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ድንገተኛ ጥቃቱን የፈጸሙት የታጠቁ ሃይሎች፣ ጥቃቱን ካደረሱ በሁዋላ ከአካባቢው ተሰውራል። ይህን ተከትሎም ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የከተማው ሰዎች እየታፈሱ ተወስደዋል። ”

ያለ ሲሆን ኢቢሲ በበኩሉ የሚከተለውን ዜና አስተላልፏል:-

“ኤርትራ ውስጥ በሻዕቢያ የተለያየ የሽብር ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆዩት መካከል ከመነሻ እስከ መድረሻቸው ድረስ የብሄራዊ የመረጃና ድህንነት አገልግሎት ክትትል ሲያደርግ እንደነበርም ገልጿል።
“የኤርትራ መንግስት ተላላኪዎቹን ስማቸውን በመቀየር የኤርትራ የጉዞ ሰነድ ካዘጋጀላቸው በኃላ ከአስመራ ተነስተው ወደ ዩጋንዳ በአውሮፕላን ማረፊያ ቀጥሎም ወደ ኬንያ በተሽከርካሪ ተጉዘው በሞያሌ በኩል ድንበር ተሻግረው ነው ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ የሽብር ድርጊታቸውን ለመፈፀም ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ የገቡት። የገበደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ደቡባዊ ጫፍ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ያልታወቁ መስሏቸው ራሳቸውን በመደበቅ ለተለያዩ የሽብር ተግባር ሲዘጋጁ እያለ ክስትትል ሲያደርግ የነበረው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ፌድራል ፖሊስ የፀረ ሽብር የጋራ ግብር ኃይል ሚያዚያ 28፣ 2008 ባካሄደው ዘመቻ አብዛኞቹ ካሰባሰቡት የጦር መሳሪያና ቁሳቁስ ጋር በቁጥጥር ስር ሲውሉ ለማምለጥ የሞከሩ ጥቂት አሸባሪዎች ተገድለዋል። ግብረ ኃይሉ የሽር ደርጊቱን ለማድረስ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የኤርትራ ተላላላኪዎች ብዛት ምን ያህል እንደሆነ ግን የገለፀው ነገር የለም። ግብረ ኃይሉ እንደገለፀው የኤርትራ መንግስት ተላላኪዎቹን በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ያድረገው ተደጋጋሚ ሙከራ በኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል፣ በአማራና ትግራይ ብሄራዊ ክልሎች ፈጥኖ ደርሽ የፖሊስ ሀይሎች በወሰዱት ተከታታይ እርምጃ ሲከሽፍበት ነው በደቡብ ኢትዮጵያ በኩል ዳግም ሙከራ ሲያደርግ የሽብር ቡድኑ አባላትበቁጥጥርስር የዋሉት። በቁጥጥ ስር በዋሉት የሻዕቢያ ተላላኪዎች የተጀመረው ምርመራ ተጠናክሮ የቀጠል መሆኑን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌድራል ፖሊስ የፀረ ሽብር የጋራ ግብር ኃይል ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አመልክቷል።”

በሌላ በኩል ኢሳት በዜና እወጃው በአርባምንጭ ሕዝቡ ጥቃት የፈጸመው ግንቦት 7 ነው እያለ በማውራት ላይ ነው ካለ በኋላ ግንቦት 7 ግን ምንም መግለጫ በዚህ ጉዳይ እንዳልሰጠ ዘግቧል::

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: