The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ታፍነው የተወሰዱት የጋምቤላ ህጻናት የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እየሆኑ ነው

save

ዳዊት ሰለሞን

መንግስት ጊዜ ወስዶ ባወጣው መግለጫ ‹‹የደቡብ ሱዳን ወንበዴዎች››በማለት የጠቀሳቸው ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረው 208 ንጹሐንን በመግደል 100 ልጆችንና ከ2000 የሚበልጡ የቁም ከብቶችን በመውሰድ መሰወራቸው አይዘነጋም፡፡ጋምቤላን ያስለቀሰው ጥቃት ከተሰነዘረና ህጻናቱ ታፍነው ከተወሰዱም አንድ ወር ሊሞላ የቀረው በጣት የሚቆጠር ቀናት ብቻ ነው፡፡

‹‹ጀግናው ሰራዊታችን ህጻናቱ የሚገኙበትን ቦታ ከብቧል››ከሚለው በሬ ወለደ የምኞት ወሬ ጀምሮ የኢህአዴግ ቱባ ባለስልጣናት ጦሩ ወደ አካባቢው ዘልቆ በመግባት ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር ወንበዴዎቹን አሳድዶ በመምታት ህጻናቱን ለማስመለስ ‹‹ክተት››ማለቱን ነግረውናል፡፡

ልጆቹ ተገኝተው ወደ ቤተሰቦቻቸው (ቤተሰቦቻቸው በጥቃቱ ተገድለውም ሊሆን ይችላል)የሚመለሱበትን ሁኔታ ከፕሮፓጋንዳዎቹ ማግስት ስንጠብቅም ሌሎች አፈናዎች መፈጸማቸውን ከጋምቤላ ክልል ሰምተናል፡፡

በደቡብ ሱዳን ባላንጣ የነበሩ ሁለት ከፍተኛ የቡማ አካባቢ ባለስልጣናትም የጥቃቱን አድራሾች በተመለከተ አንዳቸው ሌላኛቸውን ሲከስሱ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡አሁን ሁለቱ ሰዎች በመካከላቸው የነበረውን ሽኩቻ በማብረድ በአገሪቱ መንግስት ውስጥ ቁልፍ ስልጣን በመጨበጣቸው እርስ በርስ መወነጃጀሉን አቁመዋል፡፡ይህም አስቀድሞ ‹‹በዚህ ጉዳይ ውስጥ የደቡብ ሱዳን መንግስት እጁ የለበትም››በማለት ከአዲስ አበባ መግለጫ ለሰጠው የኢህአዴግ መንግስት ችኩልነት አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ከሁለቱ ሰዎች የአንዱ ወገን በጋምቤላ ወረራ በማካሄድ አለም አቀፍ ወንጀል ፈጽሟል፡፡የዚህ ቡድን መሪ ደግሞ በደቡብ ሱዳን መንግስት ውስጥ ቁልፍ ስልጣን ጨብጧል፡፡

የቀናቱ እየረዘመ መሄድ ህጻናቱን በህይወት የማግኘት ዕድልን የበለጠ የማይደረስበት ያደርገዋል፡፡ልጆቹ በህይወት ቢገኙ እንኳን የሚደርስባቸውን አካላዊ፣አእምሯዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳቶች ማከም የማይቻል ሊያደርገው ይችላል፡፡

ከበባ መፈጸሙ ሲነገርለት የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት ታጣቂ ኃይል ‹‹ህጻናቱን በድርድር ለማስለቀቅ እየሞከረ ስለመሆኑ መረጃዎች ዘግየት ብለው መውጣታቸው አልቀረም፡፡ይህም ለመንግስት ሌላ ሽንፈት በመሆን እንዲመዘገብ በር ከፍቷል፡፡

በአንጻሩ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ለህዝባቸው ሁኔታውን በተመለከተ በየጊዜው ማብራሪያዎችን ይሰጣሉ፡፡በቅርቡ የአገሪቱ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት ከሆነም የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበር ጥሰው ወደ ሱዳን ገብተዋል መባሉን ውሸት ነው፡፡ባለስልጣኑ በምንም መንገድ ድንበር ጥሰው ሉዓላዊነታችንን ደፍረው እንዲገቡ አንፈቅድም ብለዋል፡፡

ይህንን መግለጫም http://www.sudantribune.com/spip.php?article58887 ማንበብ ይቻላል፡፡ድንበር ላይ መስፈር የተለመደ ነገር መሆኑን የሚናገሩት የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጦር ድንበር ላይ መስፈሩን አልተቃወሙም ነገር ግን ወደ እኛ እንዲዘልቁ አንፈቅድም እያሉ ነው፡፡

ከትናንት ጀምሮ ደግሞ የኢህአዴግ መንግስት ልሳኖች 19ኝ የጋምቤላ ህጻናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው ማቀላቀል መቻሉን እየተናገሩ ነው፡፡እርቃናቸውን የሚታዩ ህጻናትን ፎቶ ግራፍ የለጠፈው ኢብኮ ቁጥራቸውን በግልጽ ያስቀመጠ ቢሆንም ሌሎች   http://aa.com.tr/en/world/ethiopia-rescues-dozens-of-children-abducted-last-month-/569357የተመለሱት ህጻናት ቁጥር ብዛት ምን ያህል እንደሆነ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አለመናገራቸውን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ለንባብ የበቃ የደቡብ ሱዳን ብሊንዲንግ ሬዲዩ ዌብ ሳይት ዘገባ ከሆነም የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት እስካሁን ባደረጓቸው ፍለጋዎች 42 ህጻናትን አግኝተዋል፡፡ነገር ግን ህጻናቱን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው አለመስጠታቸው አስፍሯልhttps://radiotamazuj.org/ar/article/

ቀደም ብሎ ከሙርሌ ሶስት መንደሮች መገኘታቸው የተነገረላቸው 32 ህጻናት ወደ ጁባ የሚወስዳቸውን መጓጓ ዣ ማግኘት ባለመቻላቸው ተላልፈው አለመሰጠታቸውን የገለጹት የአገሪቱ ባለስልጣናት በጋምቤለው ጥቃት በጥይት የተመቱ ኢትዮጵያዊያንም የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኘው በደቡብ ሱዳን መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

አሁን መሰረታዊው ጥያቄ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ደቡብ ሱዳን ባልገቡበት ሁኔታና የአገሪቱ ባለስልጣናትም ያገኘናቸውን ህጻናቶች ገና አሳልፈን አልሰጠንም እያሉ ኢትዮጵያ የተወሰኑትን ልጆች አስመለስኩ የምትለን ከየት ፈጥራቸው ነው? የሚለው ነው፡፡

ህዝብ ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት አለው፡፡በዚህ አስጨናቂ ወቅትም በአደጋ ላይ የሚገኙ ህጻናት የፕሮፓጋንዳ ሰለባ መሆን የለባቸውም፡፡‹‹ልጆቻችን መቼ ነው የሚመጡት?››ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ከኢትዮጵያ መንግስት ይልቅ የደቡብ ሱዳን መንግስት የተሻለ አቅም ያለው መስሎ የሚታይ በመሆኑም ጥያቄውን ለደቡብ ሱዳን ማቅረብ አሳማኝ መስሎ ይታያል፡፡የኢህአዴግ መንግስት ‹‹እኔ እንደ ናይጄሪያ መንግስት አይደለሁም ››ለማለትም የጠለፋው አካል ያልነበሩ ህጻናትን ፎቶግራፍ እየለጠፈ ፕሮፓጋንዳውን ከመንዛት ወደኋላ አላለም፡፡

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: