The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ኦዴፎች ምን ነካቸው? ግርማ ካሳ

Oromo-joint-press

Joint Statement by Four Oromo Liberation Organizations: ODF/ADO, OLF-U/ABO-T, OLF/ABO and FIO/KWO

አንዳንድ በተለይም በዉጭ ያሉ የኦሮሞ ብሄረተኞች ፣ የአክራሪዉን እና የብዙ ወገኖች ደም በእጁ ያለበትን የኦነግን ባንዲራ እያዉለበለቡ፣ የጭቁን ኦሮሞ ወገኖቻችንን ተቃዉሞ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እና እንቅስቃሴው፣ ሃይጃክ በማድረግ፣ የኦሮሚያ ሪፑብሊክን ለመመስረት ያላቸዉን ሕልም ለመተግበር ደፋ ቀና እያሉ ነው።

አራት ለኦሮሞ ማህበረሰብ ቆመናል የሚሉ ድርጅቶች በሜኔሶታ ያወጡት አንድ መግለጫ አነበብኩ። አዘንኩ። እነዚህ ደርጅቶች የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (የተባበሩት) ፣ የኦሮሚያ ነጻነት ግንባር (Front for Independence of Oromia) እና በነ አቶ ዮሐነስ (ሌንጮ) ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ናቸው።

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር አመራሮች ያለኝህ አክብሮት በመግለጽ እነርሱንም በመደገፍ ብዙ ጽፊያለሁ። “የመገንጠንል ጥያቄ አይሰራም ፣ የኦሮሞ ጥያቄ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ የመብትና የዲሞክራሲ ጥያቄ ነው” በሚል ሁሉም ዜጎች እኩል የሆኑባት አንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በጋራ ለመገንባት ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ብዙ ጊዜ ሲናገሩ ይሰማሉ። አንድ ወቅት እንደዉም ዶር በያን አሴቦ፣ አሁን ያለው የፌዴራል አወቃቀር ሳይቀር ጠረቤዛ ላይ ተቀምጦ፣ ውይይቶች ተደርገው ፣ ሁሉንም በሚያስማማ መልኩ መዋቀር እንዳለበት ሲናገሩ አስታወሳለሁ። አቶ ሌንጮ ባቲ ደግሞ “ኦዴፍ ለኦሮሞዎች ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ኢትዮጵያውያንም መብት ይታገላል። ከሌሎች ሃይሎች ጋር በመነጋገርም አገር አቀፍ የሆነ ደርጅት እናቋቁማለን” ብለው ነበር። በብዙዎች ዘንድ ፣ ኦዴፍ በርግጥም፣ ያሉ ልዩነቶችንን በማጥበብ አንጻር ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል የሚል ትልቅ ግምትና ተስፋ ነበር።

ሆኖም ኦዴፍ ወደፊት መሄድ እየፈለገ ወደኋላ መጎተትን የመረጠ ይመስላል። የኦዴፍ አመራሮች የኦነግ አመራሮች የነበሩ ጊዜ የነበራቸውን እና “አይሰራም ፤አያዋጣም” ብለው የተዉትን አቋም መልሰው የያዙ ይመስላል።

ኦዴፍ ከሌሎች አክራሪዎች ጋር ሆኖ ያወጣው መግለጫ “እኛ ፣ ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነትና ለኦሮሚያ ነጻነት (መገንጠል) ቆርጠን የተነሳን የአራት ደርጅቶች ተወካዮች (We, the representatives of four organizations which are committed to the liberation of the Oromo people and the independence of Oromia”) “ ብሎ ነው የሚጀመረው። የኦሮምሚያን ነጻነት(መገንጠል) የሚለው ቃል አስምሩበት።

ሌሎቹ አቋማቸው የታወቀ ነው። ከነ ዳዎድ ኢብሳ አይነቶቹ ዘረኞችና ጠባቦች ብዙም የሚጠበቅ ነገር የለም። “ኦሮሞ ፣ ኦሮሞ” ይላሉ እንጂ፣ ቅንጣት ያህል የኦሮሞ ማህብረሰብን የማይወክሉ፣ ፖለቲካቸው የተሸነፈና የከሰረ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ሆኖም ኦዴፍ የዚህ መግለጫ ፈራሚና አካል መሆኑ ግን አስደንጋጭና በጣም አሳዛኝ ነው። ምን ነካቸው የሚያስብል ነው። ታጥቦ ጭቃ መሆን ነው።

በኦሮሚያ በተነሳው ሰላማዊና ሕዝባዊ ተቃዉሞ ፣ ሕዝቡ የግፍ አገዛዝን በመቃወም ተቃዉሞዉን አሰምቷል። ፕሮፌሰር ህዝቄል ጋዲሳ እንዳሉት የሕዝቡ ጥያቄ የመብት፣ የዲሞክራሲና የልማት ጥያቄ ነው። የኦሮሞዎች ጥያቄና የሌላው ኢትዮጵያዊ ጥያቄ አንድ እንደሆነ ነው በግልጽ በኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ እኝህ ምሁር ለማስረዳት የሞከሩት። ሆኖም በዚህ መግለጫ፣ እነ ኦዴፍ የኦሮሞዎች ተቃዉሞ ለኦሮሚያ መገንጠል መሰረት ይሆናል ሲሉ ያናገራሉ። “ We believe that your blood that was shed and the bodily harm you sustained because of EPRDF/TPLF action will become the building blocks for constructing a free and democratic Oromia. “ ይላል መግለጫው። ክቡር እና ታሪካዊ የሆነዉን የኦሮሞዎችን ትግል እንዲሁም በኦሮሚያ የተከፈለዉ መስዋእትነን አሳንሶና አራክሶ፣ በድሃውና የተገፋው የኦሮሞ ወጣት ጀርባ ላይ በመጠንጠል፣ የራሳቸዉን አጀንዳ ለማራገብ መሞከራቸው ግን ተገቢ አይደለም።

አቶ ሌንጮ ባቲ፣ በቅርብ እንደተናገሩት፣ በኦሮሚያ ዉስጥ አሥራ አንድ ሚሊዮን ኦሮሞ ያልሆነ ህዝብ እንደሚኖር ገልጸዋል። ከኦሮሚያ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው በሸዋ ነው። አዲስ አበባን ጨምሮ በሸዋ 44% የሚሆነው ህዝብ ኦሮምኛ ተናጋሪ አይደለም። በኦሮሚያ ባሉ ትላልቅ ከተሞች አብዛኛው ነዋሪ multi-ethnic ነው። በኦሮሚያ ባሉ አምስት ትላልቅ ከተሞች አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂማ፣ ሻሸመኔና ቢሾፍቱ የሚኖረው ሕዝብ አብዛኛው የተዋለደ multi-ethnic ነው።

ታዲያ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክ እምብርት የሆኑት እንደ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ቦታዎች፣ እንዲሁም አዲስ አበባ ጨምሮ በክልሉ ትላልቅ ከተሞች የሚኖረዉ ሕዝብ የማይደግፈዉና አጥብቆ የሚቃወመውን፣ የሚጸየፈውን፣ በታሪክ ያልነበረና ትላንት በሕወሃትና ኦነግ ተፍጥሮ በሕዝቡ ላይ በሃይል የተጫነውን ኦሮሚያ የሚባል አርቴፊሻል ክልል ስለመገንጠል ወይንም ነጻ ስለማውጣት ማውራት ምን ይባላል? እነርሱ ኦሮሚያን እንገጥል ሲሉ የአዲስ አበባ፣ የአዳማና የአካባቢ የሸዋ ህዝብ ከኦሮሚያ እንገነጠላለን እንደሚል ረሱትን ? ነው ወይስ ጦርነት ገጥመው ሸዋን በሙሉ አዲስ አበባ ጨመሮ፣ በሞጋሳ ከአራት መቶ አመታት በፊት እንዳደረጉት፣ ሙሉ ለሙሉ ኦሮሞና ከአማረኛ የጸዳ ለማድረግ ነው የሚያስቡት ? ሸዋ ለብቻ ሆኖ፣ ምእራብ ያለው እና ምስራቅ ያለው የኦሮሚያ ክፍል እንዴት ነው የሚገናኘው ? እንደ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሻሸመኔ የመሳሰሉት ሳይኖሩ ምን ተይዞ ነው ነጻ አገር የሚመሰረተው ? ምን አለ ከጠባብነት ወጣ ብለው በሜዳ ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ቢረዱ ?

የነ ኦዴፍ መግለጫ የኦሮሞ ማህበረሰብን ጥቅም ያስጠበቃል ብዬ አላምንም። የኦሮሞ እጣ ፋንታ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር የተቆራኘ ነው። ኦሮሞው ከሌላው ጋር ተዋልዷል;። ተጋብቷል። ገዢዎች ኦሮሞዉን ከሌላ ነጥለው ለመምታት እየሞከሩ ነው። ሌላው ኦሮሞዉን፣ ኦሮሞው ሌላውን እንዳያመን በማድረግ፣ በከፋፍለህ ግዛ የስልጣን ዘመናቸው እያራዘሙ ነው። ይህ የነ ኦዴፍ መግለጫ፣ ሕዝብ ከሕዝብ የሚያቀራረብ ሳይሆን ህዝብ ከሕዝብ የሚያራራቅ ነው። የተሽነፈ አስተሳሰብ ያንጸባረቀ መግለጫ ነው።

ያለ ኢትዮጵያ ኦሮሞ የለም። ያለ ኦሮሞ ኢትዮጵያ የለም፡፡ኦሮሞነት ኢትዮጵያዊነት ነው።የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄና የሌላው ማህበረሰብ ጥያቄ ተመሳሳይ እንደመሆኑ፣ የመብትና የፍትህ እንደመሆኑ፣ ከጎጥና ከዘዉግ በዘለለ መልኩ ለጋራ ጥቅም ሁሉም ዜጎች መሰባሰብ አለባቸው። በዚህ መግለጫ እንዳየነው አይነት ወደ ኋላ የሚጎትት፣ ዘረኛ የኋላቅ ቀር አመለካከቶች ማባባልና መታገሥ የሚያስፈለግ አይመስለኝም።

የኦሮሞ ማህበረሰብ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ በደልና ግፍ እየተፈጸመበት ያለ ማህበረሰብ ነው። ኦነግ እየተባሉ ኦሮሞዎች እንደሚታሰሩትም፣ ሌሎችም ደሚት፣ ግንቦት ሰባት እየተባሉ እየታሰሩም ነው። በአምቦ፣ በሃረርጌ ደም እንደፈሰሰም፣ በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በጎንደር ፣ በቴፒ ደም ፈሷል። ከአዲስ አበባ አካባቢ የኦሮሞ ገበሬዎች እንደተፈናቀሉትም ከኦሮሚያ “አማራ” ናችሁ ተብለው፣ ከአዲስ አበባ ከጋማቤላ …ለልማት ይፈለጋል ተብለው ሌሎችም በኃይል ተፈናቅለዋል። ሁላችንንም ነው ይህ አሁን ያለው አገዛዝ እያሰቃየ ያለው። በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ ከሌላው የተለየ ደረሰ የሚባል ጉዳት የለም። ከአንድ ነገር በስተቀር። እርሱም ኦሮምኛ ብቻ በሚለው የቋንቋ ፖሊሲ ምክንያት፣ ብዙ ኦሮሞዎች አማርኛ ማንበብና መጻፍ አለመቻላቸው ነው። ከዚህም የተነሳ የኢኮኖሚክ ማእከል በሆኑ፣ ብዙ ሥራ በሚገኝባቸው እንደ አዲስ አበባ፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ባህር ዳር ባሉ ቦታዎች የመስራት ፣ በፌዴራል መንግስት የመቀጠር እድላቸው በጣም የመነመነ ነው። አዳማ እንኳን ቢሄዱ በአዳማ ባሉ የግል መስሪያ ቤቶች የሥራ ቋንቋ አማርኛ ስለሆነ መቀጠር አይችሉም። ውጤቱ ምንድን ነው ? እጅግ በጣም ትልቅ የሥራ አጥነት። ኮሌጅ ተመርቀው ሥራ የለም። ለሌላዉም ሥራ የለም፤ ግን የኦሮሞዎች በጣም ይበሳል። ይሄም በተለየ ሁኔታ በኦሮሞው ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለ፣ ትልቅ የኢኮኖሚክ በደልና ግፍ ነው።

ኦሮሞው መሻሻል ነው የሚፈልገው። የኦሮሞው ጥያቄ የመብትና የኢኮኖሚ ጥያቄ ነው። ከሌላው እኩል ሆኖ ማንም የደረሰበት ደረጃ መድረስ ነው የሚፈልገው። ለዚህ ደግሞ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራ ማለት ሳይሆን፣ ለሁሉም እድሎች እኩል የሚከፈትበት፣.ሁሉም፣ ሃይማኖት ፣ ዘር ሳይባል በእኩልነት የሚኖርባት አንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገናባት በጋራ መነሳት ነው። በተናጥል የትም አይደረሰም።

ላለፉት አምስት ወራት ብዙ ዋጋ ተከፍሏል። ያ ሁሉ እንቅስቃሴ ታይቶ ለዉጥ ካልመጣ መቼ ነው ታዲያ ሊመጣ የሚችለው? በዘዉግ ፖለቲካ ረገድ መጫወት ያለብንን ካርዶች በሙሉ አውጥተን ተጫወተናል። ከዚህ በኋላ በእጃችን የቀረ ምንም ነገር የለም። አሁን እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ከዘር አስተሳሰብ እልፍ ብለን፣ በአንድነት፣ ለጋራ ጥቅማችን በጋራ መታገል ነው የሚያስፈልገን።

ይሄንን ጽሁፍ የምታነቡ የኦሮሞ ወገኖቼ ከስሜት በጸዳ መልኩ በሜዳ ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በማሳብ ለነዚህ ሜኔሶታና አስመራ ለተቀመጡ፣ የሕዝቡ የኢኮኖሚ ችግር ለማይሰማቸው፣ ኦሮሞን እንወክላለን ለሚሉና በኦሮሞዉን በሌላ መካከል ህወሃት የገነባዉን አጥር የበለጠ ለሚያጠናክሩ ደካማ መሪዎች ጆሮ ሳትሰጡ እንታነቡ በአክብሮት እጠይቃለሁ። የኦሮሞ ደም የሌለበት ኢትዮጵያ የለም። ኢትዮጵያ ማለት ኦሮሞ ነው። ሌላውን ኢትዮጵያዊ እየገፉ፣ ሌላውን ኢትዮጵያዊ እንደ ጠላት እያዩ፣ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ለመለየት መሞከር ጸረ-ኦሮሞነት ነው።

http://www.zehabesha.com/ethiopia-joint-statement-by-four-oromo-liberation-organazations-must-read-2/

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: