The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ትግራይ ውስጥ ሕዝቡ በእርዳታ የመጣ እህል እንዳይወሰድ ተከለከለ| የፍኖተ ዴሞ.ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

ሰኔ1 ቀን2009 ዓም
ርዕሰ ዜና
 የዓለም ባንክ ለወያኔ ተጨማሪ ብድር ሰጠ
 ትግራይ ውስጥ ሕዝቡ በእርዳታ የመጣ እህል እንዳይወሰድ ተከላከለ
 ግብጽ ውስጥ ሙስናን ያጋለጡ የሂሳብ መርማሪ ተከሰሱ
 በተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ስር የተመደቡ የኮንጎ ዴሞክ. ሪ. ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸውን የተመድ ዘገባ አጋለጠ
 በኬኒያ የጸጥታ ኃይሎች ሁለት ሰልፈኞችን ገደሉ
 የናይጄሪያ መንግሥት ከደቡብ አማጽያን ጋር ያለውን ችግር
በውይይት ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
 ሙሰቨኒ ባለቤታቸውን የትምህርትና የስፖርት ሚኒስቴር አድርገው ሾሙ

ዝርዝር ዜናዎች
 የዓለም ባንክ ለወያኔ አገዛዝ ተጨማሪ የ300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት መስማማቱን አስታውቋል። ባንኩ ለወያኔ አገዛዝና ለዘረኛ መሪዎቹ በልማት ስም ጠርቀም ያለ ገንዘብ በማበደር መጭውን ትውልድ በዕዳ ሰንሰለት ይዞ እያሰራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ባሁኑ ወቅት ለመስጠት የተስማማው ብድር የትራንስፖርት ውጤታማነትን ለማጎልበትና የመንገድ ድህነነትን ለመጨመር ነው ተብሏል። ይሁን እንጅ የብድሩ ገንዘብ በአብዛኛው በወያኔ መሪዎች የውጭ ባንክ ሂሳብ ውስጥ እንደሚጨመር አጠያያቂ አልሆነም። የዓለም ባንክ ፀረ ኢትዮጵያ ለሆነው ለአምባገነኑና ዘረኛው የወያኔ ቡድን ለአንድ ዓመት የሚሰጠው የብድር መጠን ለቀድሞ መንግሥታት በ40 ዓመት ያላደረገው እንደነበር የሚገልጹ ወገኖች የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ልማትና ዕደገት ሳይሆን የወያኔን ዕድሜ ዘላለማዊ ለማድረግ ከገባበት የውጭ ምንዛሪ ዕጥረትም ለማውጣት የቆመ ድርጅት መሆኑን በመግለፅ፤ የዓለም ባንክ ለወያኔ መሪዎች በኢትዮጵያ ስም ብድር የሚሰጠውን መጠየቅ ይገባል ይላሉ።

File Photo

File Photo

 ሰሞኑን ትግራይ ውስጥ የወያኔ መሪዎች በድርቅና በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች እንዲከፋፈል የተቀመጠውን የእርዳታ እህል የማዳበሪያ ዕዳ ካልከፈላችሁ አናከፋፍልም በማለት የዕርዳታ አህሉን በመኪና በመጫን ወደ መቀሌ ለመውሰድ ሲሞክሩ በሕዝብ ትብብርና ቁጣ የተዘረፈውእህል ሊያዝ መቻሉ ውቋል። የወያኔ መሪዎች በድርቅና በረሃብ በመነገድ ገንዘብ መሰብሰቡ በረሃ እያሉ የተካኑበት ሰይጣናዊ ተግባራቸው መሆኑ ይታወቃል።

 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ከሳምንታት በኋላ ለሚጀመረው የብራዚል አትሌክቲክስ ውድድር በልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች የሚሳተፉትን አትሌቶች ይፋ ማድረጉንና ይህን ተከትሎም የአመራረጡ ሂደት ላይ ውዝግብ መነሳቱ ይታወቃል። ይህን በሚመለከት ማክሰኞ ዕለት የአትሌቶች ማህበር አስቸኳይ የምክክር ስብሰባ ካደረገ ወዲህ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለብራዚሉ ኦሎምፒክ ባካሄደው የአትሌቶች ምርጫ ላይ ግልጽ ተቃውሞንና ቅሬታውን አቅርቧል። የአትሌቶቹ ማህበር አሁን ባለው አመራር ላይ ቅሬታ ማቅረቡ ተዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪ የአትሌክስ ፌዴሬሽን በባለሙያ የማይመራና ሃገርን ከመጥቀም ይልቅ ግለሰቦችን እየጠቀመ መሆኑንም አትሌቶቹ አውስተው፤ የአትሌቲክስ ማህበር በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ውስጥ ተወካይ ቢያስቀምጥም ለይስሙላ ብቻ በመሆኑ አትሌቶች ፌዴሬሽኑን በአጋርነት እንዲመሩ ጠይቋል። አትሌቶቹ ጥያቄያቸውንና ቅሬታቸውን የሚከታተል አንጋፋ አትሌቶቹ ያሉበት አንድ ኮሚቴም ማቋቋሙ ታውቋል።

 በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከግብጽ የአስተዳደር ተቋሞች 67.6 ቢሊዮን ዶላር ተሰርቋል በማለት አጋልጠው የነበሩት የቀድሞ ከፍተኛ የሂሳብ መርማሪ ሚስተር ሂሻም ገኒና ሀሰት ዜና አሰራጭተዋል በሚል ክስ የፕሬዚዳንት ሲሲ አገዛዝ ፍርድ ቤት ያቀረባችው መሆኑ ታውቋል። ባለፈው መጋቢት ወር በዚሁ ምክንያት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገው የነበሩት የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) ሂሳቡን መርመረው መደምደሚያ ላይ የደረሱት በተጨባጭ ማስረጃዎች ተመስርተው መሆኑ ጠቅሰው የተሰነዘረባቸውን ክስ የፖለቲካ ምክንያት ያለው መሆኑን መግለጻቸው ይታወቃል። የፕሬዚዳንት አል ሲሲ መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነን እየሆነ መምጣቱ በአገሪቱ ውስጥ ሆን ብሎ ሙስናን እያስፋፋ መሆኑን በመጥቀስ በርካታ ዜጎች እየወነጀሉት ይገኛሉ።

 ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2008 ዓም ይፋ ባደረገው ዘገባ ከታህሣስ 2006 እስከ ሰኔ 2007 ዓም ባለው የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በአፍሪካ ኅብረት እና በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ስር በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ተሰማርተው የነበሩ የኮንጎ ዴ. ሪፐብሊክ ወታደሮች 18 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለው የነበሩ መሆናቸውን አጋልጧል። ባለፈው የካቲት ወር በነዚህ ወታደሮች የተገደለኡ የ12 ሰዎች አስከሬን በጅምላ ከተቀበረበት ጉድጓድ የወጣ ሲሆን በሌላ ወቅትና ቦታ የተገደሉ አራት የክርስቲያን ሚሊሺያ መሪዎች እና አባላት እንዲሁም ሌሎች ሁለት የሰላማዊ ሰዎች አስከሬኖች መገኘታቸው ታውቋል። በተገኘው የጅምላ መቃብር ውስጥ አንዲት እርጉዝ ሴትን ጨምሮ በጠቅላላው የአምስት ሴቶችና የሁለት ህጻናት አስከሬኖች እንደሚገኝበት ታውቋል። ሁኔታው ተጣርቶ በወንጀለኞቹ ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ድርጅቱ ለኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪ ደብዳቤ የጻፈ መሆኑም ተነግሯል።

 ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓም በኬኒያ ምዕራባዊ ከተማ በኪስማዩ ሁለት ሰልፈኞች መገደላቸውን ተከትሎ በተቃዋሚዎች የተደራጁ ማንኛውም ዓይነት ሰልፎች የተከለከሉ መሆናቸው የኬኒያ መንግስት በይፋ አውጇል። የኬኒያ የምርጫ ቦርድ አባላት ሙስና ውስጥ የተዘፈቁ በመሆናቸውና ቦርዱም አድሏዊ በመሆኑ መፍረስ አለበት በሚል መፈክር በተቃዋሚ ኃይሎች የተደራጁ ስልፎች ላለፉት ጥቂት ወራት በየሳምንቱ ሰኞ ሲካሄዱ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን አንዳንዶቹ ሰልፈኞች ከፖሊሶች ጋር ግጭት መፍጠራቸው ይታወቃል። ኳሊሽን ፎር ሪፎርምስ ኤንድ ዴሞክራሲ (Coalition for reforms and Democracy) የተባለው የተቃዋሚዎች ትብብር መሪ ሰላማዊ የተቃውሞ ስልፍ ማካሄድ በመንግስት የተቸረ ስጦታ ሳይሆን ሕገ መንግስቱ ለዜጎቹ ያጎናጸፈው መብት ነው በማለት በሚቀጥለው ሳምንት ሰኞና ሐሙስ ሰልፉ የሚቀጥል መሆኑን ተናገረዋል። ህገ መንግስቱን የሚጥስ አፋኝ አካል በተገቢው መንገድ መልስ ይሰጠዋል ብለዋል።

 የናይጄሪያ መንግስት በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ከሚንቀሳቀሱት አማጽያን ጋር እርቅ ለመፍጠር ፍላጎት ያለው መሆኑን ገለጸ። በሎንደን ህክምና እያደረጉ ያሉትን የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትን በመተካት አገሪቱን እያስተዳድሩ ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ የነዳጅ ሚኒስትሩ እና የወታደራዊ ተቋም ኃላፊዎች ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2008 ዓም. የነዳጅ አምራች ከሆኑ ጠቅላይ ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጋር ተገናኝተው እርቅ ስለሚደረግበት ጉዳይ መወያየታቸው ታውቋል። በውይይቱ በጠቅላላው እርቅ ስለሚደረግበት ሁኔታና እስከዚያው ድረስ በአካባቢው የሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ስለሚቀንስበት ሁኔታ ስምምነት የተደረሰ መሆኑ ተገልጿል። ከአማጽያኑ ጋር ቀጥተኛ ንግግር ለማድረግ በናይጀሪያ መንግስት የጸጥታ አማካሪ ቡድን የሚመራ አንድ ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑም ተነግሯል።፡ ከጥቂት ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የአማጽያን እንቅስቃሴ በመስፋፋቱ በቀን 2.2 ሚሊዮን በርሚል ነዳጅ ሲመረት የነበረው በቀን ወደ 1.6 ሚሊዮን በርሚል ዝቅ ማለቱ አገሪቱን በኢኮኖሚ ክፉኛ እየጎዳት ነው ተብሏል። የናይጀር ዴልታ ተበቃዮች የሚባለው ቡድን ረቡዕ ሰኔ 1 ቀን 2008ዓም በቲውተር ባሰራጨው መግለጫ በቀጥታ ከመንግስት ጋር በስተቀር ከሌላ አካል ወይም ከተቋቋመ ኮሚቴ ጋር ድርድር ለማድረግ ዝግጁ ያልሆነ መሆኑን ገልጿል። በዚህ ቡድን ስር የሚንቀሳቀሱት ግለሰቦች አብዛኞቹ ከሰባት ዓመት በፊት በአካባቢው ሲንቀሳቀስ የነበረ የአማጽያን ቡድን መሪ የነበረውና አሁን በሙስና እየተፈለገ ያለው ግለሰብ አድናቂዎችና ተከታዮች መሆናቸው ይነገራል።

 ባለፈው የካቲት ወር ብሔራዊ ምርጫ በድጋሚ አሸንፈዋል ተብለው ለአምስተኛ ጊዜ በስልጣኑ የቀጠሉት የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ሙሰቨኒ የ67 ዓመት ሚስታቸውን የትምህርትና የስፖርት ሚኒስቴር በማድረግ የሾሟቸው መሆኑ ተገልጿል። የሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ጠርቀም ያለ በጀት የሚመደብለትና የሙስና ምንጭ ሲሆን በርካታ ሰዎች ቦታውን ለመያዝ ሲመኙና ከፍተኛ ጥረት ሲያድርጉ እንደነበር ይታወቃል። ሙሰቨኒ ለሚስታቸው ይህንን ሹመት የሰጡት በወታደራዊ ተቋም ውስጥ፡ላለው ልጃቸው ከብርጋዴር ጄኔራልነት ወደ ሜጀር ጄኔራልነት የማዕረግ እድገት በሰጡ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ነው። ሙሰቨኒ ዘመዶቻቸውን ሁሉ በመሾም የኦጋንዳን ፖለቲካ በቁጥጥር ስር ያደረጉ ሲሆን የማዕረግ እድገት በመስጠት ልጃቸው እሳቸውን እንዲተካ ሁኔታውን እያመቻቹ ነው የሚል ውንጀላ እየተካሄድባቸው መሆኑ ይታወቃል። ሙሰቨኒ ተቃዋሚዎቻቸውን በኃይል ሲያፍኑ የቆዩ መሆናቸው ሲታወቅ ባለፈው ምርጫ ተወዳድረው አሸንፈዋል የተባሉት ሚስተር ቢሲግየ በቁጥጥር ስር ውለው በሀገር ክህደት ወንጀል የተከሰሱ መሆናቸው ይታወሳል።

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: