The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የወያኔ እና ሻእቢያ ቁማር ፦ ወያኔና ካድሬዎቹ አሰብን ሳያስመልሱ ውጊያውን አቆሙ

የወያኔ እና ሻእቢያ ቁማር ፦ ወያኔና ካድሬዎቹ አሰብን ሳያስመልሱ ውጊያውን አቆሙ ? ( በሳቅ )
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Eritrea‬ ‪#‎Tsoronafront‬ ‪#‎Zalambesa‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ተመጣጣኝ ዕርምጃ ፣ የአጸፋ እርምጃ ፣ ቀጣይ እርምጃ ፣ ተመጣጣኝና አስተማሪ ቅጣት…….ኣቤት ወያኔ…….የግንቦት 20 ቀን ጀግኖች ኣቅራሪዎች…….ሻዕቢያ ሲመጣ ለፍላፊ ሞጥሟጦች……ይህ ውሸታም ኣገዛዝ እንዳለን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በወሰደው ጠንካራ የአጸፋ ምት ለጥቃት የተንቀሳቀሰው ኃይል ሙሉ ለሙሉ መመታቱን የጠቀሰው መግለጫው፥ የመከላከያ ሰራዊት ቀጣይ እርምጃ በኤርትራ መንግስት እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን ጽህፈት ቤቱ በአጽንኦት ገልጿል። የወያኔው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኣጽንኦት ሰጠሁት የሚለው የወያኔ እና ሻእቢያ ቁማር ሕዝብን ለማታለል ኣቅጣጫ ለማስቀየር የተጫወቱት ሴራ ነው፥የሕዝብን ደም ለስልጣን መቆመሪያ ኣድርገውታል።

ሕዝብን አስከመቼ እያጭበረበሩ እንደሚኖሩ ባይገባንም ሕዝቡ ግን ከድጋፍ እጁን መሰብሰብ ኣለበት። እነዚህ አምባገነን ኣገዛዞች ሕዝብን በመጨፍለቅ ለመግዛት በሃገሮቻቸው ውስጥ ለውጥ አንዳይመጣ የሚጫወቱት እኩይ ሚና የጀመረው በረሃ በነበሩበት ጊዜ ነው።አጅግ በጣም ጥንቃቄ የሞላበት ፖለቲካ ማራመድ ያስፈልጋል በተገኘበት እየተለጠፉ ድጋፍ ማድረግ ኣያዋጣም፥ የሚገርመው የወያኔ ካድሬዎች ብዙ የለፈለፉበት ውጊያ በኣጭሩ መቀጨቱ አንዲሁም አሰብ አሰብ ብለው የለፈለፉት ሰሚ ማጣቱ ኣገዛዞቹ ምን ያህል የስልጣን ገብጋቦች ቁማርተኞች አንደሆኑ ያመለክታል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

posted by Geremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a comment