The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የኦሮሚያ የግብይት ማቆም አድማና መንገድ መዘጋት አዲስ አበቤውን ለከባድ የዋጋ ንረት በመዳረግ አራቁቶታል። በዓሉን አደብዝዞታል::

ከኦሮሞ ተቃውሞ ኣስተባባሪዎች በተደረገ ጥሪ መሰረት የግብይት ማቆም አድማ ከቤት ያለመውጣት አድማ እና መንገድ መዝጋት በመላው ኦሮሚያ ከጷግሜ 1/2008 መጀመሩና ለመጨረሻ ሰባተኛ ቀን ዛረም ቀጥሎ መዋሉ ይታወቃል::ለአንድ ሳምንት የተጠራው የግብይት ማቆም አድማና መንገድ መዝጋት በተሳካ መልኩ ከመቀጠሉም በላይ በዚህ ኣድማ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ክልሎች ለሽያጭ እቃዎችን ወደ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ማስገባት አልተቻለም ነበር; በጥሪው መሰረት እህልና ሸቀጣ ሸቀጦች ከኦሮሚያ ክልል ወደአዲስ አበባ እንዳይገቡ የተጀመረውን የገበያ ማቆም አድማና ከቤት ባለመውጣት አድማ በማሳካት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች መንገዶችን በመዘጋጋት ኣዲስ ኣበባን ለዋጋ ንረት አቀባብሎ ሰቷታል:: ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ አድማው ግብይቶችን ከጥቅም ውጪ በማድረግ አዲስ አበባን ጭር አድርጓታል::የዋጋ ንረትን አስከትሏል::የሕዝብን ጥንካሬ ለአምባገነኖች ከማሳየቱም በላይ ሕዝቡ የወያኔን አገዛዝ እንደማይፈልግ በተግባር አስመስክሯል::
በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የተለያዩ ግብይቶች ላይ ከጤፍ ጀምሮ የበግና የአውደ አመት ውጤቶች ላይ የአቅርቦት እጥረት የታየ ሲሆን ከ400 እስከ 500 ብር ጭማሪ ሲያሳይ አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አውደ አመቱ ፍሰሃና ደስታ የጎደለው ምንም አይነት የአመት በኣል ድባብ እንዳልታየበት ተናግረዋል::በኦሮሚያና በአማራ ክልል የወያኔ አገዛዝ በወሰደው ጭካነያዊ ግድያ እና የጅምላ እስር ምክንያት ሕዝቡ ልቡ እንደተሰበረ ከአመት በአሉ ድባብ መጥፋት ጋር ተያይዞ የገበያ መገዝቀዝ የዋጋ መናር የአዲስ አመቱ 2009 መፍዘዙን በሰፊው ይታይ ነበር::የሸማቾች ማህበር ዋጋ ለማረጋጋት ቢሞክርም እንዳልተሳካ ታውቋል::
በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ እና መንገድ መዝጋት በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ከተለያዩ አከባቢዎች የተሰበሰቡ መረጃዎች ያሳያሉ ለኣንድ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ በኣዲስ ኣበባ ቡራዩ በኣምቦ በነጆ በነቀምት በደንቢዶሎ በባሌ ጎባ በሃረርጌ ደደር ጋራሙለታ ጅማ አጋሮ ጉደር ሻሸመኔ በኣወዳይ በድሬዳዋ በቢሾፍቱ/ደብረዘይት በናዝሪት/አዳማ እና በመላው የኦሮሚያ ክልሎች እና ክተሞች የመገበያያ መደብሮችን ሆቴሎችን የአገልግሎት መስጫዎችን በመዝጋት ከቤት ባለመውጣት ገበሬው አስፈላጊ ምርቶቹን በመያዝና ባለመላክ ባለመሸጥ እንዲሁም ገንዘብ ከባንክ በማውጣት በተሳካ ሁኔታ ሲካሄድ የምስራቅ ኢትዮጵያዋ ጅጅጋ እና በጫት ተቀባይነቷ የምትታወቀው ጅቡቲ ጫት ሳይላክ መቅረቱ ሲታወቅ ድሬዳዋም ጭር ብላለች::ሕዝቡም በወያኔ አገዛዝ ላይ ያለውን ተቃውሞ በተግባር ያሳየበት መሆኑ ተረጋግጧል::
በመላው ኦሮሚያ ሆቴሎች የአገልግሎት መስጫ ሱቆች ምግብ ቤቶች መጠጥ ቤቶች መደብሮች በስፋት ተዘግተው የታዩ ሲሆን የአገዛዙ አሾክሻኪዎች ቢከፍቱም በሕዝብ ማስጠንቀቂያ ወዲያው መዝጋታቸው ሲታወቅ በተለይ የትራንስፖርት ኣገልግሎት የሚሰጡ ኣውቶብሶች መናሕሪያዎችን ጭር ያደረጉ ሲሆን ትራፊኮች ታርጋ በመፍታት ሲወስዱ ተስተውለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሕወሓት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ጨምሮ የተለያዩ በስራ ላይ ለመሰማራት ሲያሽከረክሩ የተገኙ አውቶብሶች እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን መንገዶች በተለያዩ ኣከባቢዎች ተዘግተው መውጫና መግቢያ ኣልነበረም:: ከዚሁ አድማ ጋር በተያያዘ የወያኔ አገዛዝ ሃይሎች ከፍተኛ የሆነ ግፍ በሕዝብ ላይ ሲፈጽሙ በተለይ በሃረርጌ ውስጥ በግድያ ላይ በመሰማራት ሲገድሉ በርካቶችን ከተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች እያፈሱ ማሰራቸው እውሰምቷል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በበርካታ የደቡብና የኦሮሚያ ክልሎች ወደ ባንክ ሂደው ገንዘብ ለማውጣት ሲፈልጉ ገንዘብ የለም የተባሉ ደምበኞች “ያስቀመጥነውን ገንዘባችንን እንፈልገዋለን፣ ለልጆቻችን ትምህርት ቤት ወጪና ለአዲሱ ዓመት ያስፈልገናል፣ ገንዘባችን ካልተሰጠን አንሄድም” ስላሉ በፖሊስ ድብደባ ደርሶባቸዋል።የባንኮች ቀውስ ወደ አዲስ አበባ ደርሶ በአዲስ አበባ ዋና ባንኮች ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ከወትሮ የበለጠ ገንዘባቸውን በቦርሳና ሻንጣዎች ስያወጡ ተስተውለዋል።ቀድሞ ከብሄራዊ ባንክ መረጃ የሚደርሳቸው የህዋሃት ባለስልጣኖች ገንዘባቸውን በገፍ እያሸሹ ነው። በአዲሱ አመት 2009 መስከረምና ጥቅምት በርካታ ባንኮች ሊጨናነቁ ይችላሉ ሲሉ የባንክ ባለስልጣናት ይናገራሉ::ይህ ሕዝቡ በወያኔ አገዛዝ ላይ እምነት ማጣቱን በተግባር እያሳየ ያለበት አንዱ መንገድ ሲሆን ሀሰተኛ የብር ኖቶች በብዙ ከተማዎች ውስጥ ቢገኙም ብሄራዊ ባንክ ይህንን መረጃ ደርሶት እርምጃ ባለመውሰዱ በሕዝቡ ውስጥ በሰፊው ተሰራጭተው ‘ንደሚገኙና ባንኮችም ውስጥ ሃሰተኛ የብር ኖቶች እንዳሉ የባልክ ባለስልጣናቱ ይናገራሉ::
ባለፉት ሰባት ቀናት የተካሄዱ የግብይት ማቆም አድማ ከቤት ያለመውጣት አድማና የመንገድ መዝጋት የትራንስፖርት መቆም በተሳካ መልኩ ከመሰራቱም በላይ ሕዝቡ አገዛዙን እንደማይፈልግ ለአድማ ጥሪው ትብብር በማድረግ በተግባር አሳይቷል:

Esat Stavanger's photo.

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: