The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የአማራ መደራጀት የጎጥ ድርጅቶችና ኢትዮጵያ

አስካሁን አማራንና አማረኛን በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮች ሁሉ የሁሉንም ትኩረት ይስባሉ። በተለይም አማራዉ ይደራጅ የሚለዉ ለአንዳንዶች ኢትዮጵያን እንደማፍረስ እንደ ክደት ይፈርጁታል። በእራሳቸዉ አማራ ነን በሚሉ ምሁራን ሳይቀር። በአማራዉ ላይ ለዘመናት ጥላቻ ተሰብኮበታል። የአለፉት ሥራቶች ጥፋቶች ሁሉ ለአማራዉ ተሰጥተዋል። ይህ የሆነዉ ደግሞ ሆን ተብሎ ነዉ። በእዉነት ለመናገር አማራዉ ባለፉት ሥራቶች እኩል እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተጨቋኝ እንጅ ተጠቃሚ አልነበረም። ይህንንም የአማራዉ ኑሮ በተጨባጭ የሚመሰክረዉ ነዉ። የነበሩት ሥራቶች በመደብና በዕሪኦት ዓለም የተገነቡ እንጅ በአማራነት ብቻ የተገነቡ አልነበሩም። ይህ መሆኑ በደንብ እየታወቀ መሰሪዎች ግን አማራዉን ለማስጠላት ተጠቅመዉበታል። ስለሆነም ሌሎች ለአማራዉ ቅንና ቀና አመለካከት እንዳይኖራቸዉ አድርጓል። አማራዉ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመበት ይገኛል። ስለሆነም አማራዉ እራስን ከመጥፋት የመከላከል ሃላፊነት አለበት። ይህን በእሱ ላይ እየተፈፀመበት ያለዉን የዘር ማጥፋት፣ የእልቂትና የእስራት፣ ስደትና መፈናቀል ለመቋቋም መደራጀትና ተደራጅቶ እራሱን ከሚደርሱበት ጥቃቶች መታደግ፣ መብቱንና ነፃነቱን ማስከበር አለበት።
ምንም እንኳን እስከ አሁን የአማራዉ መደራጀት አስፈላጊ አይደለም የሚሉ ባይታጡም። በአማራዉ መደራጀት ቀድመዉ ያመኑ እንደ ፕሮፌስት አስራት ያሉት አማራዉን አደራጅተዉ የአማራዉን መብት ለማስከበር ጥረዋል። በትግሉም የህይወት መስአዉትነት ከፍለዉበታል። በመዐድ ተደራጅተዉ ይታገሉ የነበሩ ብዙ አማሮች ብዙ እንግልት ደርሶባቸዋል። ብዙዎችም ታስረዋል፣ ተሰደዋል፣ የደረሱበት ጠፍቷል፣ ተገለዋል።
አሁንም አማራዉ የሚያታግለዉ አንድ ጠንካራ ድርጅት አላገኘም። አማራዉን እንደ አማራ ማደራጀት እንደ ሌሎች ቀላል አይደለም። አማራዉ ሰፊና ከብዙዎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ተቀላቅሎ፣ ተጋብቶ ተዋልዶ መኖር የለመደ ሕዝብ ነዉ። አማራነት ከኢትዮጵያዊነት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ማንነት ነዉ፣ አማራነት አመለካክት ስነልቦና ነዉ። አማራነት አማራነኝ ብሎ ያመነ ሁሉ የሚቀላቀለዉ ነዉ። አማራዉ በመላዉ ኢትዮጵያ ተበታትኖ የሚኖር ሕዝብ ነዉ። ስለሆነም የሚኖርበት ሁሉ ለአማራዉ አገሩ ነዉ። አማራዉ አገሬ የሚለዉ ኢትዮጵያን ነዉ። አሁን በኢትዮጵያ ስም በአማራዉ ላይ እየደረሰበት ያለዉ በደል አማራዉን ኢትዮጵያዊነቱን ለማስጠለት እየተፈፀመበት ያለ ደቫ ነዉ። አማራዉ አገር አላጣም በኢትዮጵያ የሚኖርበት ሁሉ አገሩ ነዉ። አማራዉ ያጣዉ በሚኖርበት አገሩ መብትና ነፃነቱን ነዉ። ለአማራዉ የሚያስፈልገዉ ድርጅትም አማራዉ ያጣዉን መብቱንና ነፃነቱን አታግሎ የሚያስከብርለት ነዉ። አማራዉ እየተበደለና ነፃነቱን ተገፎ በሁለተኛ ዜግነት የሚኖርባትን ኢትዮጵያ ሳይሆን መብቱና ነፃነቱ የተከበሩባት ኢትዮጵያን እንዲመሰርት ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር የሚያስተባብረዉና የሚያታግለዉ ድርጅት ያስፈልገዋል።
አሁን አሁን የአማራ ድርጅቶች ነን የሚሉ ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል። በአንድ በኩል ይበጅ ሚያሰኝ ነዉ። የአማራዉ መደራጀት አምነዉ ብዙ ድርጅቶች ብቅ ማለታቸዉ በሌላ በኩል ደግሞ አንደኛ ጠላት የአማራዉን ትግል ሳቦቴጅ ለማድረግ የሚያደራጃቸዉ እንዳይሆኑ ያሰጋል። ሁለተኛ በመካከላቸዉ በሚከተሏቸዉ የተለያዩ አቋሞች እርስ በእርስ እየተጋጩ የጎንዮሽ ትግል እንዳይገቡና ለጠላት መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
በኢትዮጵያ መሆን ባይችል መልካም ነበር ግን ሁኗል። ከአሁን በሁዋላ በብሔርና በጎሳ አንደራጅ አትደራጁ ማለት አይቻልም። ሆኖም እነዚህን የብሔርና የጎሳ ድርጅቶች በአግባቡ ከተያዙና በጋራ ለጋራ ጥቅም ከሰሩና በጠላትነት መተያየቱን ካቆሙ። የጋራ አገራዊ አጀንዳዎችን ከነደፉ ጥቅም ሊኖራቸዉ ይችላል። ነገር ግን አሁን ከአንዳንዶች ጎጠኛ ድርጅቶች እንደምናየዉ አንዱን ከሌላዉ የሚያጋጩ ካርታዎችን እየሳሉ የነፃ መንግስት ምስረታ ሕልም ነድፈዉ የሚያራምዱትና እራሳቸዉን በዚያ በእነሱ ሕልም በመሰረቱት መንግስት ዉስጥ ዘዉድ ደፍተዉ ያነገሱ በመሆናቸዉ ከዚያ ዉጭ የሆነዉን ሁሉ በጠላትነት ፈርጀዋል። የኢትዮጵያን ችግር በአግባቡ ተረድተዉ መጋፈጥ አይወዱም። መካሪዎቻቸዉንም አይሰሙም። በቅዠት የደፉትን የነፃ መንግስትነት ዘዉድ የሚነጠቁ ነዉ የሚመስላቸዉ። ለእነሱ መብት፣ ነፃነት ዲሞክራሲ ምናቸዉም አይደሉም። ነፃ መንግስት በሚል ቅዠት ዉስጥ ስለሆኑ። በእዉነት ለመናገር ነፃ መንግስት የሕዝብን መብትና ነፃነት ያስጠብቃል ማለት አይደለም። በስንትና ስንት ነፃ መንግስታት ዉስጥ ነዉ የሕዝብ መብቶችና ነፃነቶች እየተረገጡ ያሉት። የእኛዋ ኢርትራ አንዷ የዚህ የቅርብ ምሳሌ ነች። ስለዚህ እንደዚህ አይነት አደረጃጅቶች በአማራዉም መታየታቸዉ አይቀርም። ኢትዮጵያንና ታሪኳን የሕዝቧን ሁኔታ በሚገባ የሚረዳ የነፃ የጎሳ መንግስት ጥያቄ በብዙ መልኩ ጠቀሜታ የለዉም። ይልቁንስ የሕዝብ መብትና ነፃነት የተከበረባት፣ የሰባዊ መብትና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቿ የበለጠ ትጥቅማለች። የሕዝብ ችግር በትክክል የተረዱና በቅንነት የሚሰሩ ድርጅቶች ሁሉ ልዩነታቸዉን አቻችለዉ በጋራ ለሕዝብ መብትና ነፃነት መከበር፣ ለሰባዊ መብት መከበር፣ ለሕግ የበላይነትና ለዲሞክራሲ መስራት አለባቸዉ።

7f984-map2b1-2bethiopia2bduring2bfascist2bitaly

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: