The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ከቤት አልባው ኢትዮጵያዊ

የጎንደር ህዝብ በኦሮሚያ ጎዳናዎች የሚፈሰው ደም የእኛ ደም ነው ብሎ በወያኔ ተቃዋሚዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረን አጥር እንዲደረመስ አድርጎ ነበር። ብዙም አልቆየም ጀዋር መሃመድ ይህን አጥር አፈረሰው። እንዴት ካላችሁኝ እንዲህ ነበር የሆነው።

ወያኔ ደብረዘይት ላይ የእሬቻን በኣል ለማክበር የወጡ ወገኖቻችንን መሄጃ አሳጥቶ ወደገደል እንዲገቡ ያደረገውን በአገራችን ታሪክ ከአዲስ አበባው የግራዚያኒ ፍጅት ቀጥሎ በአንድ ቀን እጅግ ብዙ ወገኖቻችን ለሞት የተዳረጉበት ቀን ተፈጥሮ አልፏል። ምናልባትም የታሪክ እውቀቴ አንስተኛ በመሆኑ ሳላውቀው የቀረሁት እንዲህ አይነት በአንድ ቀን ብዙ ወገኖቻችን የታረዱበት አሰቃቂ ሌላ ቀን ካለ የሚገልጥልኝ ካለ እፈልጋለሁ።

ወደተነሳሁበት ልመለስና የእሬቻው እሰቃቂ ፍጅት በተከናወነ ማግስት ሃዘናቸውን ለመግለጽ ለተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ምናልባትም በብዛት የኦሮሞ ተወላጆች ጀዋር መሃመድ በኦሮምኛ ንግግር ሲያደርግ ስለኦሮሚያ የነጻነት ቻርተርና ስለኦሮሚያ አገራዊ መከላከያ ሰራዊት ተናግሮ በተቃዋሚዎች መካከለ ተፈጥሮ የነበረውንና የጎንደር ህዝብ ያፈረሰውን አጥር ዳግመኛ መልሶ ገነባው።

ለንደን ላይ የኦሮሚያን ቻርተር ለማጽደቅ የተጠራው ስብሰባ “ኢትዮጵያን ካላፈረስን ቤት አንገባም” ባለ አገር አልባ ስደተኛ ተነግሮ እነጀዋርን ከማስጨብጨብና በተቃዋሚው መካከል የበለጠ ጥርጣሬ ከማንገሱ በቀር ምንም እንዳልፈየደ የምናውቀው ነው። የአትላንታውም የነጻነት ጉባኤ ቢያንስ በኦሮሞ ተቃዋሚዎች መካከል አንድነት እንዲፈጠር መልካም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል ብለው ብዙዎች ተስፋ ቢያደርጉም ጀዋር በፈጠረው ትርምስ ምክንያት ኦሮሞ ወንድሞቻችን ያሉበትን ሁኔታና በኦሮምኛ እንዴት እየተፏከቱ እንዳለ ኦሮምኛ የሚችሉ ጓደኞቻችን እያወጉን ነው።

ይህ አልበቃ ብሎት ዛሬ ደግሞ ጀዋር ሜንጫውን ወደ አንድነት ጎራው አዙሯል። ዛሬ ጀዋርና ዶ/ር እዬዬ ያደረጉትን ውይይት ያላዳመጣችሁ ካላችሁ ስለምን እያወራሁ እንደሆነ ላይገባችሁ ስለሚችል በቅድሚያ ውይይቱን አዳምጡት። ጃዋር በራሱ ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ እንደነገረን ከሆነ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑት ሃይሎች እርስ በእርስ እንዲፋጁ እቅድ ይዟል። ከዚህ በኋላ የአማራ ብሄርተኞች በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ኢትዮጵያውያንን ለመሳደብ ከፌስቡክ በተጨማሪ የጀዋሪ ቴሌቪዥን አለላቸው። እንዲህ ነው እንጂ አጋርነት!

ጀዋር በዚህ አያቆምም ትንሽ ቆይቶ በሙስሊም ኦሮሞዎችና በክርስቲያን ኦሮሞዎች መካከል ሜንጫ ወደማማዘዝ ይሸጋገር ይሆናል። ጥያቄው ⶏርነቱ በክርስቲያን ኦሮሞዎችና በሙስሊም ኦሮሞዎች መካከል ሲሆን የዶ/ር እዬዬ ሚና ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ነው? የአራጋቢነት?

እድሜ ይስጠን እንጂ ገና ብዙ እናያለን። በምርጫ 97 በወያኔ ላይ ትግሉ ሲፋፋም ልደቱም እንዲህ ነበር ያደረገው። ዘንድሮ ደግሞ ይህን ገጸባህርይ የሚጫወተው ጀዋር ሆኗል። ልብ አድርጉ ለወያኔ የሚጠቅም ስራ ውስጥ ለምን ተሰማራ ብዬ እዬጠዬኩ እንጂ ጀዋር ወያኔ ሆኗል እያልኩ አይደለም። መቼም ከዚይ አትራፊው ወያኔ እንደሚሆን ጀዋር ጠፍቶት አይደለም።

ግን ጀዋር ይህን የሚያደርገው ለምንድነው? የራሱ ቴሌቪዥን ዜና አንባቢ የሆነው አብዲ ፊጤ ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ጥያቄ በኦሮምኛ ጠይቆ ነበር። እንዲህ ሲል፦ “የኦህዴድና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ግንኙነት እስከምንድነው?” ትርጉምን ያቀረበው ሲቲዩብ እንደገለጸው አብዲ ይህን ጥያቄ እንዲጠይቅ ያደረገው በኦህዴድና በጀዋር መካከል ያለው ግንኙነት ስላላስደሰተው ነበር። አብዲ ይህን ጥያቄ የጠየቀው ጀዋር ትግሉ በተቃዋሚዎች መካከል እንዲሆን እያደረገ በመሆኑ ወያኔ እፎይታን እንዲያገኝ እያደረገ ነው በሚል ስጋት አድሮበት ይሆን? ወያኔ ግን እድለኛ ነው። ሁሌም ሰው አያጣም!

“ቤት አልባው ኢትዮጵያዊ”

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: