The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

በ‹ተሃድሶ ስልጠና መስጫ ካምፖች› የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በጨረፍታ

ኑርሃሰን ሁሴን ከሁለት ወራት ቆይታ በኋላ ከ‹ተሃድሶ ስልጠና› ሲመለስ ቤቱ ድረስ በመኪና አድርሰውታል፡፡ ሌሎቹ የስልጠናው ተመላሾች ግን በጋራ በአውቶብስ ተጭነው ከተማ ከደረሱ በኋላ በግላቸው ነው ወደ ቤታቸው ያመሩት፡፡ ኑርሃሰን ወደቤቱ ሲመለስ በተመቸው ጊዜ ስልክ መደወል እንደሚችል፣ በዚህም ሊያሳክሙት እንደሚችሉ ተነግሮት የስልክ ቁጥር ሰጥተውት ነበር፡፡ በተባለው መሰረት ኑርሃሰን የተሰጠውን የስልክ ቁጥር ቤቱ በገባ ማግስት ጀምሮ ባሉት ቀናት ሊደውልበት ሞከረ፡፡ ሆኖም ግን ስልኩ ሊሰራለት አልቻለም፡፡ ይህኔ ነው ኑርሃሰን የተሰጠው ስልክ ቁጥር ትክክል አለመሆኑን የተገነዘበው፡፡

ኑርሀሰን በኦሮሚያ ክልል አለምገና ወለቴ አካባቢ ተቀስቅሶ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በመንግስት ኃይሎች ታፍሰው ከታሰሩትና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በታወጀበት ዕለት (መስከረም 29/2009 ዓ.ም) ወደ አዋሽ ሰባት የፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ካምፕ ከገቡት ሺዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ኑርሃሰን ለእስር በተዳረገበት ወቅት ባለቤቱ ገና የሁለት ወር አራስ ነበረች፡፡ እሱም በጎሚስታ ስራ በሚያገኛት ገንዘብ ባለቤቱንና ህጻን ልጁን የሚያርስበት ጊዜ ነበር፡፡

 

በ‹ተሃድሶ› ካምፖች በተለየ መልኩ እጅግ አስከፊ ጊዜ ካሳለፉት መካከል ኑርሃሰን አንዱ ነው፡፡ ኑርሃሰን አዋሽ 7 በገባበት ወቅት ምርመራ ስም ብዙ የመብት ጥሰቶች ደርሶበታል፡፡ ኑርሃሰን አንድ ቀን ለምርመራ በተጠራበት ጊዜ የሆነው ግን እጅግ የከፋ ነበር፡፡ መርማሪዎቹ ቀጫጭን ብረቶችን በእጁ ጣቶች መካከል በማስገባትና አጣብቆ በመያዝ፣ ጣቶቹን ወደኋላ አጥፈው አሰቃይተውታል፡፡ ከስቃዩ አልፎ ጣቶቹን ወደኋላ ሲያጥፏቸው ‹‹ቃ..ቃ..ቃ›› የሚል የስብራት ድምጽ ይሰማው ነበር፡፡ ኑርሃሰንን ምርመራ ያደርጉበት የነበሩ ሦስት ፖሊሶች/ደህንነቶች በወቅቱ ኑርሃሰን የሚጠይቁት ጥያቄ ‹‹እመን! የሰራኸውን እናውቃለን! ሌሎችንም ጠቁም!›› የሚሉ ድፍን ያሉ ጉዳዮችን ነበር፡፡ መርማሪዎቹ በኑርሃሰን የእጅ ጣቶች በብረት በማጣበቅ ሲያሰቃዩት፣ ኑርሃሰን ከስቃዩ ብዛት የተነሳ እግሮቹን ሲያወራጭ ፊት ለፊት የነበረውን መርማሪ በእግሮቹ ይገፈትረዋል፡፡ የዚህን ጊዜ ነው የከፋው በደል በኑርሃሰን ላይ የተከተለው፡፡

 

ከመርማሪዎቹ አንዱ በኑርሃሰን እግሮች መገፍተሩን ተከትሎ ሁሉም መርማሪዎች ባገኙት ዱላ ሁሉ ኑርሃሰን ላይ ይረባረቡበት ጀመር፡፡ ኑርሃሰን ራሱን ሳተ፡፡ ራሱን ስቶም ግን መርማሪዎቹ የያዙት ዱላ ተሰባብሮ እስኪያልቅ ድብደባው አላባራም ነበር፡፡ በመጨረሻም መርማሪዎቹ ኑርሃሰን ሞቷል ብለው ጥለውት ሄዱ፡፡ ይህ በሆነ በሚቀጥለው ቀን በአዋሽ ሰባት የነበረ የፌደራል ፖሊስ ባልደረባ ኑርሃሰንን ወድቆ ይመለከታል፡፡ ኑርሃሰን በወደቀበት ቦታም ብዙ የዱላ ስብርባሪ ያያል፡፡ ይህኔ ‹‹እነዚህ መርማሪዎች ሰው ገድለው ሄደዋል›› ይልና ሌሎች ባልደረቦቹን ጠርቶ ሁኔታውን ያሳያቸዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ አባላቱም ‹‹እነሱ ገድለው እኛን ገዳይ ሊያስብሉን ነው›› በሚል እየተነጋገሩ ኑርሃሰን በወደቀበት የኑርሀሰንን እስትንፋስ ለማረጋገጥ ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ኑርሃሰን በህይወት አለ፡፡ ፖሊሶቹ ኑርሃሰንን ክሊኒክ ይወስዱታል፤ ህይወቱም በዚህ መልኩ ትተርፋለች፡፡ ኑርሃሰን ወደራሱ ሲመለስ ብዙ የሰውነት አካሉ መጎዳቱን ተገንዝቧል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን እግሩ ላይ ቁርጭምጭሚቱ ተሰብሮ፣ አጥንቱም የፊተኛው ወደኋላ መዞሩንና ከፍተኛ ስቃይ እንደተፈጸመበት ሊያውቅ ቻለ፡፡

 

ኑርሃሰን ይህን ሁሉ ስቃይ ተሸክሞ ያለምንም የተሻለ ህክምና የ‹ተሃድሶ ስልጠና›ውን እንዲከታተል ተገዷል፡፡ ኑርሃሰን በቆይታው ሁሉ የሌሎች ሰልጣኞችን ትከሻ ተደግፎ ነበር ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሰው፡፡ የተፈጸመበትን በደል ገልጾ ህክምና ሲጠይቅ ስልጠናው አልቆ ወደቤትህ ስትገባ እናሳክምሃለን የሚል መልስ ነበር የሚያገኘው፡፡ ወደቤቱ ተመልሶ ህክምና ለማግኘት ‹በዚህ ስልክ ደውልልን› ባሉት መሰረት ስልኩን ሲሞክር ግን ስልኩ አልሰራም፡፡

 

የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃንን ከመግደል በተጨማሪ በየማጎሪያ ቦታዎች ኑርሃሰን ላይ የደረሰውን አይነት አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ ስለመገኘቱ፣ ከተጎጂዎቹ ምስክርነት መረዳት ይቻላል፡፡ በተለይ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ መንግስት ተቃውሞው ላይ እጃቸው አለበት በሚል ሰበብ ዜጎችን በዘመቻ ለእስር ዳርጓል፣ እያሰረም ይገኛል፡፡ መንግስት 18 አመት ያልሞላቸው ታዳጊ ህጻናትንና አዛውንትን ሳይቀር በግፍ ለእስር ዳርጎ ‹ለተሃድሶ ስልጠና› በወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች አግዟል፡፡ በአዋሽ ሰባት ካምፕ ከርመው ከተመለሱት መካከል ከአንድ ቤተሰብ ስድስት ሰዎችን አስሮ አቆይቷል፡፡ ከእነዚህ ስድስት የቤተሰብ አባላት መካከል ገመዱ በሪሶ የተባለችው ታሳሪ የ17 አመት ልጅ ትገኝበታለች፡፡ እነዚህ የቡልቡላ ነዋሪዎች ለእስር የተዳረጉት በአንድ ላይ በትራንስፖርት ወደቤታቸው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ሲሆን፣ ስለመታሰራቸው የሚያውቅ አንድም ሌላ የቤተሰባቸው አባል አልነበረም፡፡ መስከረም አበራ እና ትዕግስት አበራ የተባሉ እህትማማቾችም እንዲሁ በጋራ ተግዘው የከረሙ ናቸው፡፡

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: