The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

በሙሶኞች እርምጃ ልንወስድ ከሆነ ህዝብ ጥቆሟ ይስጠን – አስገደ ገብረስላሴ

አቶ አስገደ ገብረስላሴ

በሙሶኞችና ኪራይሰብሳቢዏቸ እርምጃ ልንወስድ ከሆነ ከጥልቅ ጥናት የተመሰረተ ወይ ተጨባጭ ማስረጃ ያለው ህዝብ ጥቆሟ ይስጠን ጠ /ም / ሀይለማርያም ደሳለኝ !!!!
—————————————————-

አስገደ ገብረስላሴ

አኛ ከላይ እስከ ቀበሌ ተገማግመን በጥልቀት ታድሰናል ቡዙ ማስተካከያዏችም አድርገናል ። ወደ ህዝብም እንወርዳለን የሚል ሽወዳ ሰምተናል ።

በሌላ በኩል ህዝብ ታድሰናል ሙሶኞች አስወግደናል እያላቹ ነው በሙሶኞችና ኪራይ ሰብሳቢዏች እርምጃ ስትወስዱ አላየንም እያለን ነው ።

እኛ እርምጃ ልንወስድ ከሆን በጥልቀት መጠናት አለበት ፣ ስለሆነ በሙሶኞች ላይ ጠንካራ እርምጃ ልንወስድ ከሆነ ህዝብ ይጠቁመን ካለበለዚያ ዝም ብለን እርምጃ አንወስድም ብለውን ቁጭ አሉ ።
ምነው ጠ / ምንስቴር ባለፈው ጊዜ ለማስመሰል ሀገራችን ከቤተመንግስት እስከ ቀበሌ ያሉ የኢህአደግ ባለስልጣናትና እነሱ የሚመሩት መንግስታዊ መዋቅር ባለስልጣናት በሙሱና እና ኪራይ ሰብሳቢነት በስብሰዋል ፣በተለይ ደግሞ የመንግስት ባለስልጣናት የመንግስት ስልጣንን ተጠቅሞው ህዝብን ማሳቃዬት የህዝብ ሀብት በመመዝበር ከደላዮችና ከመዝባሪ ባለሀብቶች በመሻረክ በአካባቢና በዘመድ አዝማድ ፣ በቡዱን ተደራጅተው ለፈጸሙት ወንጀል ጠንካራ እርምጃ እንወስዳለን ብለው እርግጠኛ ሆነው ተናግረዋል ።
በተጨማሪ በሀገራችን የተፈጸመው ወንጀል ግድያ ብጥብጥ የህዝብ መሬት ወረራ ለወደመው ሀብት ለጠፋው ጀምላ ግድያ ሁሉ ተጠያቂ የኢአደግ አባል ፓርቲና አጋር ፓርቲዏች እንዲሁ እነሱ የሚመሩት መንግስታዊ መዋቅር ናቸው ብለው ነበር ።
በዛን ጊዜ የሚንስቴሩ ዲስኩር የሰሙ ቡዙ የዋህ ወገኖች የህወሐት ኢህአደግ ሴራና የኃላ ጉዞው የማያውቁ እንዴ እነዚህ ሰዎች ልብ ገዝተዋል እንዴ ብለው ነበር ። የኢህአደግ ባህሪ የሚያውቁ ወገኖች ግን የኢህአደግ አማራር ጸረሙሱናና ኪራይ ሰብሳቢነት ክንዳችን እናነሳለን አካኪ ዘራፍ ማለት በሀገር ደረጃ ተቀስቅሶ ለነበረው ተቃውሞና አመጽ ለስልጣኑ አስጊ ስለሆነበት አመጹ ለማብረድ( አቅጣጫውን ለመቀልበስ) ነው እንጅ ይህ ፓርቲ ከመሰረቱ ፍትሀዊ ሊሆን አይችልም እያሉ ከርመዋል ።

የነዚህ ወገኖች አባባል ትክክል ነበር ለዚሁ መረጋገጫ ጠ/ ም / ሀይለማርያም ሰሙኑን ደግሞ መንግስታችን ከቤተ መንግስት እስከ ቀበሌ ያለው ሁሉም የመንግስት መዋቅር በስብሰዋል መቆረጥ አለበት እያሉ ከርሞው ፣ አሁን ተመልሰው ደግሞ መንግስት የአቅሙ ታድሳል በተሀድሶው እርምጃ አልወሰዳችሁም የሚሉ ወገኖች ካሉ ማስረጃ ያቅሩቡልን እርምጃ ልንወስድ በማለት ሀላፍነቱ ለጭቁን ህዝብ ጣሉበት ። ይህ የጠቅላይ ምንስቴር የማጭበርበር ወይ ሽወዳ በኢህአደግ መንደር አሁን የተጀመረ ሽወዳ አይደለም ። ኢህአደግ ወታደራዊ ስርአት ደርግ በጦርነት አስወግዶ ወታደራዊ ስርአት ከመመስረቱ በፊት የ17 አመት በፊት የነበረው ባህሪ ለታሪክ ልተዏውና ፣ ከዛ በኃላ የነበረው ባህሪው ስንመለከት በ1993 ዓ ም ፣በ2002 ዓ ም ፣ አሁን በ2009 ዓ ም በስብሰናል ፣ በኪራይ ሰብሳቢነት ተወረናል እርምጃ እንወስዳለን በማለት ባላቸው የውሼት የሚዲያ ነጎድጓድ ህዝብ አደንቁረዋል ።
ውጤቱ ግን ውሀ ቢወግጡት እንቡጭ ሆነ ። እንዳውም በሁሉም ተሀድሶዏች ተባላሽተዋል በስብሰዋል ተብለው በህዝብ የተጠሉ ባለስልጣናት ለፈጸሙት ወንጀል የሚመጥን ቅጣት እንደመስጠት ፈንታ የፈጸመው ወንጀል እንዳለ ሳይነካ ፣ በሙሱና የመዘበረው ገንዘብ ቁሳቁስ ፣ የገነባው ህንጻና ቢለዏች ሳይጠዬቅ ፣ ወረዳ የነበረ ወደዞን ፣ዞን የነበረው ወደ ክልል ፣ በክልል የነበረ ወደ ፈደራል የተለያዩ ቢሮዏች ፣ ወደ አንባሳደርነት የስልጣን እርከን ተሽሞዋል ።
የዘንድሮ የኢህአደግ የውሼት በጥልቀት መታደስም ልክ እንዳለፉት ተሀድሶዏች ኢህአደግ ሳይነካካ በስመተሀድሶው የበሰበሰ ስርአቱ አጠናክሮ የወጣበት ሁኔታ ነው ያለው ።

ጠ / ምኒስቴሩ ግን ለ100ሚሊዮን የኢትዮጱያ ህዝቦች በግልጽ ሲሸውዱዋቸው ያሉ መሆናቸው ይታየኛል ። ለዚሁ ሽወዳቸው ግን ለእሳቸውና ለኢትየጱያ ህዝብ በጥያቄ እና አጫጭር አስታያዮቶች ፣
ጠቁሜያቸው ልለፍ ።

1ኛ ምኒስቴሩ ሊሸውዱ ባይፈልጉ ንሮ ሁሉም የኢህአደግ ባለስልጣናት ደሞዛቸው ለወርሀዊ ምግብ ለልጆች ትምህርት ክፍያ ለልብስ በየሳምንት ሶደሬና ሻራቶን ሌሎቸ መናፈሻና መዝናኛ የሚጠፋ ወጭ በሞቶ ሽ የሚገመት ወጭ ነው የሚፈጁት ። ደሞዛቸው ግን የምኒስቴሮች እንካን ብንወስድከ6000ብር ወይ ከ10 000 አይበልጥም ፣ መልከም ይህ ሁሉ እንተዏው ፣ የኢህአደግ ምኒስቴሮች አንባሳደሮች ዯክልል ፣የዞን ፣የወረዳ ፣የቀበሌ ባለስልጣናት በአዲስ አበባና ክልሎች ዞኖች ከሁለት በላይ ህንጻዏች ፣ቪሏዏች ሰርተዏ በሞቶዏች ሽ ብር ወይ በአስርሺ የሚቆጠር ዶሏር አካራይተው በየአመቱ በቡዙ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ይዝቃሉ ። በተለይ በአዲስ አበባ ፣በጎንደር ፣መቀሌ ፣ ናዝሬት ፣ አዋሳ ፣ባህርዳር ፣ አክሱም ፣ ጅጅጋ ፣አዳማ ፣ ድኮም ፣ ሽሬ እንዳስላሴ ፣ ደብረ ማርቆስ ፣ለቀምት ፣ ጅማ ፣ ጋንቤላ ፣ወዘተ ያሉ በምዝበራ የተሰሩ የባለስልጣናት ምንጩ የማይታወቅ ሀብቶች አሉ ።

2ኛ ልጆቻቸው ምንጩ በማይታወቅ መነሻ ገንዘብ ይዘው በቢሊዮን የሚገመት ብር ፣ዶሏር ይዘው አስመጭና ላኪ ናቸው ። የትላልቅ ኮባንያዏች በባለቤትነት ይዘዋል የባንክ ፣እንሽራንስ ሸሮች ናቸው።
በየቀኑ ለመዝናኛ የሚያወጡት ገንዘብ በአስርሽ የሚቆጠር ነው ።

3 የነዚህ ገዥዏች ልጆች በአመሪካ ታላላቅ ስቴቶች ከተሞች ፣በበልጅም ፣ጀርመን ፣በቻይና ፣ ያለአንዳች ወድድር ለትምህርት ተልከው በከፍተኛ ክፍያ በተለዬ ሙቾት ይማራሉ ፣ ስለነዚህ የተቀማጠለ ንሮ ፈረንጆችም ይገረማሉ ።

በተለይ በአመሪካ በተለያዩ ከተሞት አማሪካውያን የሌላቸው ምርጥ በውድ ቤት ክራይ ይኖራሉ ፣በአመሪካ ከ20 አመት በላይ ተቀምጠው ያልገዙዋቸው ገዝተው ይዝናናሉ ። ይዶሏር የሀገራችን ገንዘብ ነው ።

4ኛ የኛ ገዥዏች በስርአታቸው ንቀጥላለን አንቀጥልም የሚል በራሳቸው መተማመን ስለሌላቸው ልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው ዜግነት አግኝተው በኩፉ ጊዜ መጠግያ እንዲሆኑባቸው አስቀድመው ለ25 አመታት እየሰሩበት የቆዩ ሚስቶቻቸው ሲያረግዙ አመሪካ ይላካሉ በውድ ዶሏር ይዋለዳሉ ፣ የተወለደው ህጻን አመሪካዊ ዜግነት ይይዛል ። ይህ ራሱ ሙሱና ነው ። በእንደዚህ አይነት የባለስልጣናት ሚስቶች ሊወልዱ አመሪካ ሄደው በዛው የቀሩ እጅግ ቡዙ ናቸው ። በተጨማሪ ባለስልጣኖቹ ያላቸው የስልጣን ቦታና ከውጭ ዲፕሎማሲ ግንኝነት በመጠቀም ዘርዘራቸው እንዲሁም ጓደኞቻቸው አመሪካ ፣ ከናዳ ፣አውስትራሊያ ፣አውሮፓ አስፈረዋል ። ዜጎች ወደ ውጭ ፍልሰትም በር ከፋች ናቸው ።

5ኛባለስልጣናት በልጆቻቸው ፣በራሳቸው በቤተሰቦቻቸው በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ ሙንጩ ያልታወቀ ሀብት የከንስትራክሽ ማሽነሪ በሞቶየሚቆጠሩ የደረቅና የፈሳሽ ጭነት መኪኖች በባለቤትነት የያዙ ትጃሮች ተፈጥረዋል ። እነዚ የያዙት የምዝበራ ሀብት በየት ገባ ፣በምን ተገዛ ፣ተቀርጿል ወይ ? የሚል ቁቁጥር የለውም ። ለምሳሌ አንድ ጡሮቶኛ ጡሮታ ሲወጣ ከ40 በላይ ቡልደዞሮች ካተር ፒላር ኤክሰካባታር ሲገዛ ፣ዝቅተኛ የስልጣን እርከን ያላቸው ። እንኳን ከ5 እስከ 15 ገልባጭ ቡልዶዞሮች ፣ግሪደር ፣ሎዶር ፣ የመሳሰሉት ሀብት አካብተዋል ።

6ኛ እነዚህ ገዥዏች የሰሩት ህንጻዏች የገዙዋቸው የጭነት መኪናዏች የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እንተዏውና በቤታቸው ያለው ፈርንቸር የቤት ጌጣጌጥ በ100 ሚሊዮን የሚገመት ብር ሸ ዋጋ ከጀርመን ፣ከኢታሊ ፣ ከድባይ ፣ከቻይና ፣ከቱርክ ወዘተ ገዝተው ያስገባሉ ። ወደቤታቸው መሰሎቻቸው ካልሆኑ ማንም ሰው ወይ እንግዳ አያስገቡም ሚስጢር እንዳይ ጋለጥ ነው ።በተጨማሪም እነዚህ ፍጡራን ከስስትነታቸው የተነሳ በሁሉም ክልሎች ፣ አዲስ አበባ የሚኖሩ ገዥዏች ህዝብ በመኖርያ ቤት እጦት እየተሰቃዬ እያለ በምዝበራ የሰሩት ህንጻዏችና ቪሏዏች በወድ ዋጋ እያካራዩ ለራሳቸው በምርጥ የመንግስት ቤት ይኖሯሉ ። በሌላ በኩል በዬክልሉ የሚገኙ የኢህአደግ ባለስልጣናት አዲስ አበባም የሚኖሩ ጭምርር የማይኖሩበት በስማቸው በዘመድ አዝማድ ፣ በጓዶኞቻቸው ስም የቀበሌ ቤት በባለቤትነት በመያዝ በውድ ዋጋ እያካረዩ የህዝብ ገንዘብ ይዝቃሉ ።

ሌላ ጠ/ ምኔስቴር ያላዩት በባለስልጣናት ሚስቶች ፣ወንድም ህት ፣ እየተባሉ ኤፈርትና ጥረት የመያክል ምንጩ የማይታወቅ በቢሊዬን ብር የሚገመት ሀብት ያፈሩ ለማየት ተስናቸው ምሶኞች ጠቁሙን ሲሉ ምን ያህል የዋህ መሆናቸው ገርሞኛል ። በመሆኑም በተናገሩት አነጋገር ህዝብ ከማፈሩም በዘለለ አመኔታም አጥቷል ።
የተከበሩ ጠ / ምንስቴር በሙሶኞች እርምጃ ለመውሰድ ህዝብ ይጠቁመን ያሉትን ዳግም ቢፈቱሹት ያሻል ።
ጠ/ ምንስቴር እኔ የጀንሆይ ፣የደርግ ፣ በህወሀት ኢህአደግ ጋርም 19 አመት ታግዬ ከዚሁ ፓርቲ ውጭም 24 አመት ኑሬ አለሁ የኢህአደግ ምዝበራ ካለፉት ስርአታት ሳወዳድር ምንም እንካን ሁለቱ ሰርአቶች የተባላሹ ቢኖሩም ጥቂቶች ተራ መኖሩያ ቤት ቢኖራቸውም ። የዘመናችን ባለስልጣናት ግን ከላይ የዘረዘር ኩት ፣ ሀብት እጅጉን የላቀና ሀላፍነት የጎደለው ወረራን ይታያል ። ይህ ሁኔታ ጠ / ምኒስቴሩ ደፍረው ለመናገር አልደፈሩም ። ምክንያቱም ደፍረው እርምጃ ከወሰዱ ሁሉም የስርአቱ ባለሰልጣናት በሙሉ ወደ ጭቃ ስለተነከሩ ኢህአደግ ከግንዱ እንዳይገረሰስ ስለሰጉ ነው መሰለኝ ። ግን ደግሞ የመንግስትዎ ቁስሉን ቢደብቁት ቢደብቁት ፣ቢያክሙት ቢያክሙት ፣በምንም አይድንም ይልቁንስ ከህዝብ ጋር በግልጽ በመወያዬት ለሀገራችን መፍትሄ ያፋላልጉ ።በአሁኑ ጊዜ ለህዝብ መሸወድ አይቻልም ።ህዝቡ ከኢህአደግ ስርአት በንቃተ ህሊና ወደ ፊት መጥቋል ።
ከአስገደ ገብረስላሴ ከመቀሌ ፣
11 / 5 / 2009 ፣

EMF

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: