The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ደቡብ ሱዳን – የህወሀት ከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካ ኪሳራ ማሳያ

(ዘ አዲስ Ze Addis)
54ኛ ሀገር ሆና አፍሪካን በቅርቡ የተቀላቀለችው ደቡብ ሱዳን – እጅግ በሚገርም ሁኔታ ከህወሀት መንግስት ጋር እሰጥ እገባ ገብታለች:: አልፎ ተርፎም መንግስተ ህወሀትን እስከ ማስጠንቀቅ ደርሳለች:  ህወሀት መራሹ መንግስትም የሱዳንን ዲፕሎማት ከአዲስ አበባ በማባረር የተበቀለ ቢመስለውም -ሱዳን ግን “ዲፕሎማቴ ያፍሪካ ህብረት ተወካይ ናቸውና ልታስወጡ አትችሉም” ብላ ሞግታ ይዛለች:: ታላቅ እድሜ ያላት ኢትዮጵያና በቅርብ የተፈጠረችው ደቡብ ሱዳን ይሄን ያህል ስታሾራት ማየት ያስደንቃል:: ሲጀመር ደቡብ ሱዳንን እዚህ ያደረሰቻት ኢትዮጵያ ናት:: ሲቀጥል እነ ግብጽና ሰሜን ሱዳን ደቡብ ሱዳንን ለማጥፋት ብዙ የደከሙ ሀገሮች ናቸው:: እንዴት ደቡብ ሱዳን ከነሱ ልታብር ቻለች?

የደቡብ ሱዳን እንቅስቃሴ እንዴት ተጀመረ
*****************************
ሱዳን ትልቅ ሀገር ናት:: ቀድሞ የአፍሪካውያን መኖርያ ነበረች:: በኋላ ግን ግብጻውያን : አረቦችና ቱርኮች በተደጋጋሚ ባደረሱት ወረራ በነዚሁ አካላት እጅ ወደቀች:: ቀስ በቀስም አረቦቹና ቱርኮቹ ነዋሪውን አፍሪካዊ ( ነገደ ኩሽ)ነገድ እያጠፉ እየተዋለዱ – ሰሜን ሱዳንን ወረሷት:: ደቡቡ ግን እስከ እንግሊዝ ቅኝ ግዛት መነሳት ድረስ የኩሽ ዝርያ ባለቸው ነባር ነገዶች የተያዘ ነበር:: የ እንግሊዝ ቅኝ ግዛት አልቆ ሰሜኖቹ ሙሉ ሱዳንን ማስተዳደር ሲጀምሩ ግን ደቡብ ሱዳን ሲኦል ሆነች:: ሰሜኑ ባብዛኛው የእስልምና እምነት ያለውና የአረብ ድቅል ሲሆን ደቡቡ ደግሞ ባብዛኛው ክርስትያን ና ኩሻዊ ነው:: ሰሜነኞቹ ደቡብ ሱዳንን ለማስለምና ለማስገበር በይፋ ዘመቻ ጀመሩ:: ይህንንም ዓላማአቸውን ዳር ለማድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያንን አጥፍተዋል( ጳውሎስ ኞኞ ታሪካዊ ዝርዝሩን እንዲህ ከትቦታል “የደቡብ ሱዳን ብጥብጥ” ብሎ የጻፈውን መጽሓፍ እዚህ ሊንክ ላይ ያገኙታል)

ይህ ግፍ ያንገሸገሻቸው ደቡብ ሱዳናውያን እምቢታ ጀመሩ:: እያደገም ሄዶ አጥቂውን የሰሜን ሱዳንን ጦር በሃይል መመክት ጀመሩ:: በዚያን ወቅት ሱዳን : ግብጽና ቱርክ ቀጥተኛ የእኮኖሚ : የሚሊታሪና የዲፕሎማሲ ድጋፋቸው ለሰሜን ሱዳን ነበር:: አፍሪካዊና እና ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ እንደ አውሬ ታድነው ከመጥፋት የታደጋቸው የወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ነበር:: ሰሜን ሱዳን የመንግስቱን ተቃዋሚዎች ታስታጥቅና ትረዳም ስለነበር አጸፋ ለመመለስም ጭምር ደቡብ ሱዳንን ኢትዮጵያ መርዳት ጀመረች::ይህንን ጉዳይ አሌክስ በመጽሓፉ እንዲህ ይገልጸዋል

” The SPLA turned to the Ethiopian government as a natural ally in its struggle, and Colonel mengistu on his part saw Colonel Garanags movement as a useful counterweight to Khartum continuing support to EPLF, TPLF and other smaller fronts. Close links were quickly established between the SPLA and the Ethiopian government at the highest level.The Ethiopian government provided the SPLA with Military equipment, base and radio station. … there was a close Military and security coordination between the SPLA and the Ethiopian army. The Ethiopian army assisted the SPLA in attacks on Kurmuck..”

እ.ኤ.አ ከ1986-1990 የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጭ ግንባር ኢትዮጵያ ውስጥ ዱል ተብላ በምትታወቀው ቦታ ልዩ ካምፕና ማሰልጠኛ ነበረው:: የእንቅስቃሴው መሪዎችም እነ ጆን ጋራንግና ሳልቫኪርን ጨምሮ ደብረ ዘይት ቀበሌ ሶስት አርመን ሰፈር የሚባለው አካባቢ ልዩ መኖርያ ነበራቸው:: ኢትዮጵያም የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን : ተዋጊዎችን ዲፕሎማቶችን በሙሉ ኃይል ስትቀበልና ስትረዳ ነበር:: ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በአንድ ሬድዮ ኢንተርቪዋቸው እንደገለጹት

” ኢትዮጵያ 80 ሺህ የሚደርሱ የደቡብ ሱዳን ወታደሮችን አሰልጥና አስታጥቃ እና የማያቋርጥ የመሳርያና የሎጂስቲክ ድጋፍ እየሰጠች ደቡብ ሱዳንን ነጻ ሀገር እንድትሆን አድርጋለች”
ሙሉ ቃለ መጠይቁን እዚህ ያድምጡ http://ecadforum.com
https://zelalemkibret.files.wordpress.com/…/mengistu_book.p…

የደቡብ ሱዳን ውለታ የመመለስ አዝማምያ
******************************
ደቡብ ሱዳኖችም ነጻ እንደወጡ በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ምስጋናና አድናቆታቸውን ገልጸዋል:: አልፎ ተርፎም ” ለኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በብዙ ገንዘብ ልዩ ቤት አሰርተው” እንደነበረ ተገልጻል:: ይህ ግን በህወሀት መራሹ መንግስት ትልቅ ተቃውሞን ስላመጣ ደቡብ ሱዳኖች ይህን ዜና አስተባብለው እንዲህ ሲሉ ግን ለኢትዮጵያ ያላቸውን ከበሬታ ገልጸዋል
https://www.tesfanews.net/mengistu-hailemariam-reportedly-…/

“የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ከፍተኛ ድጋፍ ሲደረግለት የነበረው በኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን ያስታወሱት ምክትል አምባሳደሩ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ያደረጉት ውለታ ለኮሎኔል መንግሥቱ ተደርጐ ሊወሰድ እንደማይገባ አመልክተዋል፡፡ ”
ከዚህም አልፈው ደቡብ ሱዳኖች በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀል ያለውን ውዝግብ ለመፍታት በአስታራቂነት የተቻላቸውን ደክመዋል:: የደቡብ ሱዳኑ ዲፕሎማትም ምክንያታቸውን ሲገልጹ እትዮጵያም ኤርትራም ለደቡብ ሱዳን ነጻነት ደማቸውን አፍሠዋል መቼም አንረሳውም በማለት እንዲህ ነበር የገለጹትhttp://www.sudantribune.com/spip.php?article44341

“I personally take this as a moral duty because it is disturbing to us seeing both countries bleeding again while both of them also paid the ultimate sacrifice in order for the people of South Sudan to be free today,” Kiir then added.

እንዲህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አክብሮታቸውን ሲገልጹ የነበሩት ደቡብ ሱዳናውያን ለምን ህወሀት ላይ ተነሱ?
**************************
ዋናው ምክንያት የህወሀት መንስግት ከሰሜን ሱዳን ጋር በማበር ደቡብ ሱዳንን የሚጎዳ ድርጊቶች ማድረጉና ኢትዮጵያ ውስት እንደለመደው ደቡብ ሱዳንም የዘር መከፋፈል ልክፍት ውስት መግባቱ ነው::

የሱዳን ዋንኛው ሀብት ያለው ደቡብ ሱዳን ነው:: ሰሜኑ ባብዛኛው በረሃ ነው:: የሱዳን የነዳጅ ሀብት ከ80% በላይ ያለው ደቡብ ሱዳን ውስጥ ነው:: ሰሜን ሱዳን ና ደቡብ ሱዳን ሲለያዩ ስምምነታቸው የነዳጁን ገቢ ለመካፈል ነው:: ደቡብ ሱዳን ብትጠበክር ግን ሰሜን ሱዳንን ከዚህ ውች ልታደርጋት ትችላለች:: ከዚህም ባሻገር የነጭ አባይ ትልቅ የውሃ ሀብት ሃይቅ ያለው ደቡብ ሱዳን የሃይቆች ግዛት ውስት ነው:: ትልቁና አስተማማኙ የርሻ ቦታም ደቡብ ሱዳን ነው:: የደቡብ ሱዳን መጠናከርና እነዚህ ሀብቶች በሙሉ መቆጣጠር ስለሚያስችላት ለሱዳን ትልቅ ስጋት ነው:: ስለዚህ ሰሜኗ ጠንካራ ደቡብ ሱዳንን አትፈልግም:: ለዚህም ብዙ ትንኮዎሳች ታደርጋለች::

የሚደንቀውና የሚገርመው የህወሀት መንግስት የዚህ የሰሜን ሱዳን ሴራ ተባባሪ ሆኖ መገኘት ነው::

የደቡብ ሱዳን ያሁኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኬር የዲንቃ ጎሳ አባል ናቸው:: ምክትላቸው ሪክ ማቻር ደግሞ የኑዌር ጎሳ አባል ናቸው:: ኑዌሮች ኢትዮጵያም ደቡብ ሱዳንም ይኖራሉ:: ዲንካዎች ግን በቁጥር አብላጫዎች ሲሆኑ ኑዌሮች ደግሞ ከዲንካ ያንሳሉ:: የህወሀት ዲፕሎማሲ አንዱን ዘር ከአንዱ ዘር ጋር በማጋጨት : ከግጭቱ ትርፍ ማግኘት ነው:: በዚህም ዓላማ እጅግ አደገኛ የሆነ የዘር ድጋፍ ውስጥ እጁን ነክሯል:: ይህንን ግን ደቡብ ሱዳኖች አይተው ሊያልፉት አልቻሉም:: እነሱም አጸፋዊ እርምጃ ጀመሩ::

የህወሀት የደነዘዘ ፖለቲካ ደቡብ ሱዳንን እንኳን ማትረፍ አልቻለም:: እኛው ተዋግተን: እኛው አስታትቀን ነጻ ያወታናትን ሀገር እንኳን ከራሱ ጋር ማሰለፍ አቅቶት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዙርያ መለስ ጠላት እያፈራለት ይገኛል::

አስጊው ሁኔታ
***********************
ህወሀት “ሕዝብ ሲጣላ እርስ በርሱ ስለሚያያዝ እኔ ተዝናንቼ እገዛለሁ” በሚለው ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲዋ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተቻላት ለመከፋፈል ሞክራለች:: አማራውንና ኦሮምውን ለማጋጨት ብዙ ርቀት ሄዳለች:: በራሷ ሎሌዎች ወገኖችን አስጨፍጭፋ አማራው ጋ ሄዳ ” ኦሮሞ ጨረሰህ” ኦሮሞው ጋ ሄዳ ደግሞ ” አማራው ተነሳብህ” በሚል ርኩስ ስብከት ብዙ ሰርታለች:: ደቡብ ላይ ወጋዳጎ በሚል ሙት ፍልስፍና ብዙ የደቡብ ሰዎችን አባልታለች:: አሁን ደግሞ ሱማሌና ኦሮሞን እያጫረሰች ነው:: አሁን ደግሞ በቅርቡ ” ቤተ አጋ ዕዝያን” በሚል ክርስትያኑንና እስላሙን ለማጫረስ አዲስ ዘመቻ ጀምራለች:: ህወሀት ከሱማሌ ጋር ጸብ ናት:: ከደቡብ ሱዳን ጋ ጸብ ናት:: ከኤርትራ ጋር ጸብ ናት:: ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጸብ ናት:: ወትሮም ነገር ነገር የሚላት ኳታርና ሳውዲም የሚፈልጉት ምክንያት ነው::

መጨረሻችን ምን ይሆን?

EMF

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: