The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የጅቦችና የአህዮች ድርድር | ቬሮኒካ መላኩ

በአለፉት 25 አመታት የህውሃት የአገዛዝ ዘመን ውስጥ ድርጅቱ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ የሚመዛት ካርድ አለች ። ይች ካርድ ” ድርድር “ትባላለች ።
የወያኔን የድርድር የተለመደች ድራማ ስሰማ ሁሌ ትዝ የሚለኝ ቁም ነገር አዘል “የጅቦችና የአህዮች ” የድርድር ተረት ነው ።

_______________

 አስተያየት በቴዲ አፍሮ አዲሱ ‘ኢትዮጵያ’ ዜማ ላይ … ለማየት እዚህ ይጫኑ

_______________
በአንድ አገር የሚኖሩ ጅቦችና አህዮች ሰላም ለመመስረት ተስማምተው በየጊዜው በችግርም በደስታም ወቅት ሊጠያየቁ ተግባብተው በጉርብትና መንፈስ አብረው ሊኖሩ ተነጋገሩ። ብዙም ውሎ ሳያድር ከጅቦቹ ዋሻ አንድ አሮጌ ጅብ የመሞቱን መርዶ አህዮቹ ይሰሙና ለቅሶ ለመድረስ ይሄዳሉ።
አረፍ እንዲሉ ከተጋበዙት እነዚህ ቂል እንስሳት ዘንድ አንደኛው ጅብ ይጠጋና በመሰረቱ የእዝን መስጠት እንደሚገበ ዳሩ ግን ይህ ደሞ ስለሚበዛ አህዮች የላይኛውን ከንፈራቸውን ብቻ እንድሰጡ ይጠይቃቸዋል።
መቸስ ምን ይደረግ አስተዛዛኞቹ አህዮች የላይኛው ለንጨጫቸውን ተገሽልጠው ተቀመጡ ።ሌላው ጅብ ደግሞ መጣና ያላችሁት ሀዘን ቤት ውስጥ ነው ። ኀዘን ቤት ውስጥ ደግሞ መገልፈጥ ትክክል አይሆንምና ዘመድ ሲሞት ስላፌዛችሁብን ትበላላችሁ ተባለና ሁሉም አህዮች የጅቦች ሲሳይ ሆኑ።

በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔና በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚደረግ ድርድር የጅብና የአህያ ፣የተኩላና የፍየል ድርድር ነው ። ከዚያ አያልፍም ። ጅብና ተኩላ ያሸንፋሉ ፣ አህያና ፍየል ይሸነፋሉ ።
በቅርቡ የኢትዮጵያ ታሪክ የሃይለስላሴ እና ደርግ መንግስት ብንመለከት ተለጣፊ አልነበራቸውም። ወያኔ ራሱን የቻለ ህይወት የሌላቸው ተለጣፊ ድርጅቶች አሉት። እነዚህ ድርጅቶች የሚስቡት ኦክስጅንና የሚያስወጡት ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ህውሃት የሚባል ነው ። የተለጣፊ አውራዎቹ በየነ ጴጥሮስ እና ልደቱ አያሌው ናቸው ።

__________________

አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ ለማየት እዚህ ይጫኑ 

__________________
ወያኔ ድርድርና ምርጫ ሲያደርግ ድርድሩ እና የምርጫው ውጤት የተፈለገው ሣይሆን የታወቀው ነው ።

የህውሃትን የድርድር ታሪክ መለስ ብሎ ለገመገመ ማንኛውም ሰው በፖለቲካዊ የድርድር ቲያትር ውስጥ ገብቶ መተወን እጅግ አደገኛ መሆኑን በቀላሉ መረዳት አያቅተውም። በአለም አቀፍም ህገ ሆነ በባህላዊ ህግ ድርድር ላይ የሚከበሩ ስርአቶች አሉ ። እነዚህን ስርአቶች የጫካ ሽፍታ እንኳን ያከብሯቸዋል ። ለምሳሌ ለድርድር የመጣን የተቃዋሚ ወይም የጠላት ተደራዳሪ አክብሮ በክብር መሸኘት እንደ ህግ የሚቆጠር ባህል ነው።
ይሁን እንጂ በዚህ ዘመን ህውሃት በሚባል የሽፍታ ቡድን ይህ ለዘመናት የቆየ ክቡር የድርድር ሥርዓት ተናጋ። እስኪ ከዚህ በታች ለምሳሌ ይሆኑ ዘንድ ከወያኔን ያለፈ የድርድር ታሪክ ውስጥ ሁለቱን እንመልከት

1~ የህውሃት የትግል ታሪክ እንደሚነግረን ከሆነ
ህውሃት የመጀመሪያውን ድርድር ያደረገው በ1968 ነበር ። ህውሃት ይሄን ድርድር አድርጎት የነበረው “ግንባር ገድሊ ሐርነት ትግራይ ” ከሚባለው ድርጅት ጋር ነበር ።
በዚህ ድርድር ሁለቱ ድርጅቶች ማለትም ህውሃት በአንድ በኩል ግንባር ገድሊ ሃርነት ትግራይ በሌላ በኩል ለመዋሃድ ከተስማሙ በኋላ ውህደቱን ለመፈፀም የሚያስችላቸውን ፊርማ ለማስቀመጥ የሁለቱ ፓርቲ አመራሮች በተገኙበት ቦታ ላይ ቀድመው ሴራ ጠንስሰው እና ተነጋግረው የገቡት የወያኔ ተደራዳሪዎች በእንቅልፍ ላይ የነበሩትን የግንባር ገድሊ ሃርነት ትግራይ አመራሮች በጥይት ደብድበው ገደሏቸው። ድርድሩም በዚሁ ተፈፀመ ።

2~ ሌላው የሚጠቀሰው የህውሃት የድርድር ታሪክ ከኦነግ ጋር የተደረገው ድርድር ነው።
በዚህ ድርድር ሁለቱም ድርጅቶች ጦራቸውን ወደ ካምፕ ለማስገባት ተስማሙ ። በስምምነቱም መሰረት ኦነግ ጦሩን ወደ ካምፕ እንድገባ ካደረገ በኋላ ህውሃት የኦነግን 20 ሺህ ሰራዊት የታጠቀውን ትጥቅ አስፈትቶ በቁጥጥር ስር ካደረገ በኋላ ድርድሩን አፈረሰው። ለስልጣን ቋምጦ የነበረው ኦነግ የተጠመደለትን ፈንጅ ረገጠው ።

የማይቀየረው የወያኔ ባህሪ ሁልጊዜ ተለጣፊ ተቃዋሚን እየፈለፈለች መጠቀምና ዋናዎቹን የተቃዋሚ ድርጅቶች ማፍረስ ነው። ተቃዋሚዎች ደግሞ ምን እያደረገች መሆኑን እንኳን አይረዱም፡፡ ወያኔ ከ 130 በሰላማዊ መልኩ ከሚታገላት ተቃዋሚ ይልቅ ጠመንጃ ያነሳ 2 ሰው ያስፈራታል፡፡

በአሁኑ ሰአት ያለው እውነታ ደግሞ ወያኔ በአማራና በኦሮሞ ህዝብ አመፅ ቅርቃር ውስጥ ገብተዋል፡፡ ወያኔ ይህንን የተቃውሞ አንጃ ለመስበር ወደእሷ ሊወረወር የነበረውን ቀስት አቅጣጫ ማስቀየር ነው፡፡ በዚህ አካሔድ የተቃዋሚ ጎራ ስኬት ያጠራጥራል፡፡ ተቃዋሚዎች እንደ ህወሀት ትግሉን ሊመሩ የሚችሉ በቂ ሰዎች የሏቸውም፡፡ ተቃዋሚ ተብለው የሚቀርቡት የሰው ዝቃጭ የክህዴት ምሳሌ የሆኑት እነ አየለ ጫሚሶ ፣ትግስቱ አዎሉ እና ልደቱ አያሌው ናቸው። ወያኔ እነዚህን ይሁዳዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ” ከእኔ ጋር የሚደራደሩ ወኪልህ ናቸው ” ብሎ ሲያቀርብለት ከጭቆናው የበለጠ ቅስም የሚሰብር ጉዳይ ነው ።

ወያኔ ከትግራይ ውጭ ያለውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ህዝብ ቆጥሮት አያውቅም። ለወያኔ ይሄ ህዝብ ዜጋ ሳይሆነ በዚህች ሀገር ላይ የሚርመሰመስ ጉንዳኖች ናቸው። ወያኔ ህዝቡን የሚፈለገው ግብር ለመክፈል፣ ጦርነት ሲመጣ ለመማገድ እንዲሁም ደግሞ መዋጮ ለሚሉት በልማት ስም ለሚካሄድ ዘረፋ ነው። ለዚህ ዘመናዊ ባሪያ ህዝብ የፖለቲካ ድርድር ምን ይጠቅመዋል ተብሎ ነው የሚያምኑት ።

ይሄ ህዝብ ጠግባሃል ሲባል የጠገበ፣ በባልስልጣኖች ወዝ የፈካ ፣ በሳቃቸው ገነት ላይ የበቀልን የሚመስለን በአጠቃላይ እነሱ ናቹሁ ያሉንን የሆን ነን።

__________________

የአዲስ አበባ ስታዲየም የአርሰናል ደጋፊዎች በቃላት ግድፈት የዓለም መሳቂያ አደረጉን… ለማየት እዚህ ይጫኑ

__________________

እንደ ወፍ ጫጩት አፋችንን ከፍተን ጠብታ መና ከነሱ እንጠብቃለን ፣ ደሞክረሲ ከወያኔ እንደ ዳረጎት እንድሰጠን እንፈልጋለን ፣ ድርድር ሲባል ደግሞ መኣት ምስጋና እናዥጎደጉዳለን።

የኢትዮጵያ ህዝብ ለወያኔ በገንዘብ የሚተመን ቁሶች ነን ።፡ እዚህ የባለስልጣኑን ቀፈት የሚሞላ ካለ እዚያ ቤታቸው ፈርሶ ቤተሰቡ ወደ ጎዳና ቢበተን መንግስት ለምንለው ወንበዴ ምኑም አይደለም፡፡ አማራጭ በማጣት ተገፍቶ ለተሰደደው ወጣት በሰው ሀገር ላይ ደመ ከልብ ሆኖ መቅረት እዚህ በምቾት ለሚንከባለለው ባለስልጣን ምኑም አይደለም።

እኛ ለእነዚህ ማፊያዎች ራሳችንን ችለን ለድርድር የሚቀርቡ ተወካዮችን የመምረጥ አቅም የለንም ። ስለዚህ ለዚህ ህዝብ አየለ ጫሚሶዎች ፣ልደቱ አያሌዎች ፣ ትእግስቱ አዎሎች ይወክሉት ዘንድ ይመረጥለታል ። ድራማው በዚሁ ይቀጥላል ። የጅብና የአህያ ድርድር።

zehabesha

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: